Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ዞዓር መንፈሳዊ ሚድያ

Description
ዞዓር መንፈሳዊ ሚድያ በ @dn_abeselom የሚቀርብ ልብን ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማሉ ተብለው በአዘጋጁ የሚታመንባቸው ሃይማኖታዊ፣ሃገራዊና ታሪካዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሃሳቦች *በጽሑፍ፣በድምፅ፣በተንቀሳቃሽ ምስል፣ በምስል፣በግጥም፣መጣጥፍ..መልክ የሚተላለፍበት ንዑስ ሚድያ ነው። ለአስተያየቶ @Son_of_Meharit ።
"አንተ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው ጸጋ በርታ"፪ ጢሞ ፪÷፩
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 16 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 day, 5 hours ago

Last updated 1 day, 18 hours ago

1 week, 4 days ago
ዞዓር መንፈሳዊ ሚድያ
1 week, 6 days ago

፮. እስከ አሁን የተመለከትናቸው ማስረጃዎች መልአክ እንደነበር የሚያስረዱ ብቻ ናቸው። ቁጥር  21 ላይ፦ "....በዚህ ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚያጸናኝ የለም" ተብሎ የተቀመጠው ዓ.ነገር ግን መልአክ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ያ መልአክ "ቅዱስ ገብርኤል" መሆኑን ያመለክተናል።

☀️ በዚሁም ❝ እንዴት አንድ መልአክ ሌላውን መልአክ ሊረዳኝ መጣ ሊል ይችላል ወይ?❞ የሚለውን እንፈትሸው።

....... ትንቢተ ዳንኤል በተደጋጋሚ እንደሚያስረዳን ለነቢዩ ዳንኤል ራዕያትን ይገልጥለትና ምሥጢራዊ ጥያቄዎችንም ይመልስለት የነበረው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነበር። የዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ የተጻፈው እስራኤላውያን ፋርስ ባቢሎን በግዞት በሄዱበት ዓመታት ነው። ነቢዩ ዳንኤል ለተከከታታይ 3 ሳምንታት (ማለትም ለ21 ቀናት) ሱባኤ ገብቶ ሲጾም እና ሲጸልይ እግዚአብሔር አምላክ ገብርኤልን የዳንኤልን ጸሎት እንዲያሳርግ ልኮታል።

☀️ ገብርኤልም  የተላከበትን ጊዜ  ሲያሰረዳው ጸሎትህን ለማሳረግ ወደዚህ ፋርስ ባቢሎን የመጣሁት በመጀመሪያው ቀን ከ21ቀን በፊት ነበር ። ገብርኤል እንዲህ እያለው ነበር፦ " ዳንኤል.... "በአሐቲ ስእለቶሙ" (በአንዲት ልመናቸው) የሚሹትን ሁሉ ከሚያገኙት፤ እውነተኛ የአምላክ ልጆች መካከል አንዱ አንተ ስለሆንክ እኔ ወደአንተ የተላክሁት ገና ጸሎት የጀመርክበት የመጀመሪያው ቀን ላይ ነበር፤ የፋርስ መንግስት አለቃ ግን ተቋቋመኝ፣ አዘገየኝ እያለው ነው። ( ት ዳን ፲÷፲፪)።

.... የአሕዛብ መምህር ቅዱስ ጳውሎስ "ሰይጣን አዘገየኝ" እንዳለ (፩ ተሰሎንቄ ፪:፲፰)።

☀️ ጌታ በወንጌል ዲያብሎስን "የዓለም ገዥ" እያለ መጥራቱ የዓለም ፈጣሪዋ፣ የዓለም መጋቢዋ እርሱ ነው ለማለት ሳይሆን፤ በዓለም የሚሰራውን ኃጢአትና ክፉ ሥራ የሚያሠራ እርሱ ነው ለማለት እንደሆነ ሁሉ (ዮሐ ፲፪÷፴፩ ፤፲፬÷፴)።

..... "በስመ ሓዳሪ ይጼዋእ ማሕደር፤ ወበስመ ማሕደር ይጼዋእ ማሕደር" በሚለው የቤተ ክርስቲያን ብሂል መሠረት የራማው ልዑል ገብርኤልም ልክ እንደ ጌታው ዲያብሎስን "የፋርስ መንግስት አለቃ" ብሎ ጠራው።

☀️ የቅዱስ ገብርኤል ንግግር ሲብራራ፦ " ወዳንተ በምመጣበት ጊዜ የፋርስ መንግሥት አለቃ ዲያብሎስ ባቢሎን ውስጥ ኃጢአት ሲያሰራ፣ አምልኮተ እግዚአብሔርን ሲያሽር ስመለከት በመንፈሳዊ ቅንዓት የእርሱን ሥራ በማጥፋት ዘገየው።"

👇👇👇👇 ይቀጥላል።

2 weeks ago

የመጨረሻው እና እጅግ አሳማኙን የሆነውን ማስረጃ የምናገኘው ት. ዳን 10:21 ላይ ባለው ኃይለ ቃል ነውና፤ ይነበብ።

2 weeks, 3 days ago
ዞዓር መንፈሳዊ ሚድያ
2 weeks, 3 days ago
፬. ❝..እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን …

፬. ❝..እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ። አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ ምስያ ነበር፤ ዓይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፥ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፥የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ።❞ ት.ዳን 10÷ 5-6

🌕* በቅዱሱ መጽሐፍ ከላይ በተጻፈው መልኩ የግርማቸው ከፍታ እና ልዕልና፣ ክብራቸው የሚገለጸው ቅዱሳን መላእክት እንጂ ሰዎች አይደሉም።

ለምሳሌ፦ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሕዝቅኤል በትንቢቱ መጽሐፍ 28፥12 ጀምሮ የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ሳጥናኤልን የአሁኑን ዲያብሎስን አወዳደቁን በአንክሮ ሲጠይቅ፦  ❝..ጥበብን የተሞላህ ውበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነህ። በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ:የከበረ ዕንቁስ ሁሉ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ፥ ሰንፔር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ወርቅ ልብስህ ነበር። አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ፤በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ❞ ይላል። 

🌕* ልዑለ ቃል ኢሳይያስ፣ ዕዝራ ሱቱኤል፣ አቡቀለምሲስ ዮሐንስን ጨምሮ  መላእክትን የንጋት ኮከብ፣ አብረቅራቂ፣ ፍጹማን እያሉ ገልጸዋቸዋል።

🌕*...መጻሕፍት እንደሚስረዱን ፈጣሪ ቃሉን ያስተምሩና ይሰብኩ ዘንድ ኃያላኑን መላእክትን ሳይሆን ደካማ ውሉደ ሰብእን ከመረጠባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱና ቀዳሚው፦  የሰው ልጆች ቃሉን ሰምተው ሲያምኑ ያለፍርሃት ያለመደንገጥ መሆን ስላለበት ነው። ቅዱሳን መላእክት ደግሞ እንደምንመለከተው እንኳንስ እኛን ጀማሪዎቹን ይቅርና ነቢያቱን (ዳንኤልን፣ ዕዝራን፣ በለዓምን) የሚያስደነግጥ ግርማ አላቸው።

❇️ ሐሳቡ ሲጠቀለል፦ ነቢዩ ዳንኤል ያየው ባለ ግርማ "ሰው" መልአክ እንደነበር እንረዳለን።

3 weeks ago

❇️ታሪክ፤ አንድ ምዕመን አለቃ ገብረ ሃና ዘንድ ሄዶ።

እርሱ፦ መምህር መንገድ ልወጣ ነውና ጥብቅ ጸሎት ያድርጉልኝ ይላቸዋል።

እርሳቸው፦ወዴት ልትሄድ ነው ?

፦ ወደ ኢየሩሳሌም።

፦ ምን ልታደርግ?

፦ ጌታዬ የተወለደበትን ቤተ ልሔምን ልመለከት፣ በተጠመቀበት ዮርዳኖስ ልጠመቅ፣ ከምን በላይ ደግሞ ጌታዬ የተቀበረበትን ጎልጎታ መቃብሩን ልስም ነው የምሄደው።

፦ ቆርበህ ታውቃለህ እንዴ?

፦ አው መምህር ሥጋውና ደሙን ተቀብያለሁ።

፦ (ጠጋ በል ብለው) ሆዱን ገልጸው ሳሙት

፦ ምን እያደረጉ ነው መምህር? ጸሎት አድርጉልኝ ብል እርሶ ሆዴን ይስማሉ ምነው መምህር? (በቀልዳቸው ስለሚታወቁ እየቀለዱ መስሎት)

፦ አይ አንተ ገና ሩቅ ሄደህ መቃብሩን ልትስም ነው። እኔ ግን ይኸው እዚሁ ጌታዬ የተቀበረበትን መቃብር (ሆድህን) ተሳለምኩ አሉት ይባላል።
(ጌታ ማንም ባልተቀበረባት አዲስ መቃብር እንደ ተቀበረ፣ ከ18 ሰዓታት ጾም በኋላ ባዶ በሚሆነው ሆዳችን ሥጋውና ደሙን ስለምቀበል ስንቆርብ ሆዳችን የጌታ መቃብር ይሆናል ዮሐ ፲፱÷፳፭)።

ላይፈቱ አይተርቱ ይባላል፦
[አለቃ]፦ ቦታውን ከመሳም በላይ ራሱ ቦታውን መሆን እንደሚበልጥ ገብቷቸዋል።
[እኛስ ተወዳጆች]፦ ቅዱሳን ተአምራት ወዳደረጉበት በጸሎት ወደባረኩት ቦታ ከመሄድ በላይ ራሳቸውን ቅዱሳንን መሆን አይበልጥም ትላላችሁ?

☀️ (ምሑር የነበራችሁ ከመምህሩ አንደበት ሰምታችኋል) አሁን አሁን ባሉ ጉዞዎች ላይ ሰዉና መኪናው እኩል ሆኗል። እኛ ሰዎች ከመኪናው የምንለየው ቦታውን ከመርገጥ በተጨማሪ ቦታውን የቀደሱት ቅዱሳን ሰዎች ያደረጉትን (ሥጋውን ደሙን ስንቀበል፣ ትምህርተ ወንጌል ስንማር፣ ምስጋናውን ስናመሰግን....) ስናደርግ ነው።

☀️ ስለዚህ ቅዱሳን መካናትን የምንሳለም ብቻ ሳይሆን እኛ ራሳችን ቅዱስ መካን(አካል) እንሁን (፩ ጴጥ ፪÷፭)። 

☀️ ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ እንደ ናርዶስ ሽቱ በውስጣቸው ለታቆረው ፍቅርህ ሙቀት ቅዝቃዜ ሳይሉ በየበረሃ/ጫካ ውስጥ የተንከራተቱ ቅዱሳንህ የድካም ዋጋ ለእኛ ለምንፍጨረጨር ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ትድረሰን። (ለመከየድከ መልክዓ ኢየሱስ)

☀️ ❝ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ መካን ወኩሎን መካናት.....❞
☀️ ❝ (ከአንድ ሚሊንየም በላይ ዕድሜ ስላላት) ስለዚህች ቦታ (ገዳመ ኢየሱስ) መጽናትና በሃገራችን ኢትዮጵያ ስለሚገኙ ቅዱሳት መካናት መጽናት ጸልዩ❞ ግብረ ሕማማት።

☀️ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አገላለጽ ድርብ ድርብርብ በዓላት ለተከበሩበት መጋቢት 29፤ ዕለተ ሰንበት እንኳን አደረሳችሁ።

https://t.me/dn_abeselom
መጋቢት ፴/፳፻፲፮ ዓ.ም
#Wolkite_university.
#ነፍሳችን_እስከዳነችባት_ታናሽ_ያልሆነችው_ዞዓር

Telegram

ዞዓር መንፈሳዊ ሚድያ

ዞዓር መንፈሳዊ ሚድያ በ @dn\_abeselom የሚቀርብ ልብን ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማሉ ተብለው በአዘጋጁ የሚታመንባቸው ሃይማኖታዊ፣ሃገራዊና ታሪካዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሃሳቦች *በጽሑፍ፣በድምፅ፣በተንቀሳቃሽ ምስል፣ በምስል፣በግጥም፣መጣጥፍ..መልክ የሚተላለፍበት ንዑስ ሚድያ ነው። ለአስተያየቶ @Son\_of\_Meharit ። "አንተ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው ጸጋ በርታ"፪ ጢሞ ፪÷፩

***❇️*****ታሪክ**፤ አንድ ምዕመን አለቃ ገብረ ሃና ዘንድ ሄዶ።
3 weeks, 3 days ago

፤÷፤ ቀናተኛው ሌሊት ፤÷፤ ... ኢየሱስ ክርሰቶስ በተሰቀለባት በዕለተ አርብ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ በምድር ላይ ጨለማ እንደነበር በቅዱሱ መጽሐፍ ተጽፏል(ማቴ ፳፯÷፵፭)። ስለዚያ የቀን መጨለም:- ነቢያት በራዕይ ተመልክተዋል፣ ብዙ ጸሐፍት በመገረም አብራርተዋል፣ ዲዮናስዮስ የመሰሉ በዘመኑ የነበሩ የታሪክ ሊቃውንት በክታባቸው መዝግበዋል፣ የሳይንስ ሰዎችም ግምታቸውን አስቀምጠዋል፣ ቅዱስ ያሬድና…

3 weeks, 5 days ago

፪. ያም "ሰው" የተባለው አካል መልአኩ ገብርኤል መሆኑን እንመልከት፦

☀️ ባለ ራዕዩ ዳንኤል በምዕራፍ ፱÷፳፩ ላይ "አስቀድሜ በራዕይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል ወደ እኔ እየበረረ መጣ" ማለቱ ደስተኛው መልዓክ ገብርኤል በአርዓያ ብእሲ ወይም በሰው አምሳል ስለተገለፀለት ነው።

☀️ መላእክት ለሰው ልጆች በተለያየ አምሳል ይገለጻሉ፦

፨ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በጦር አበጋዝ አምሳል (ኢያሱ 5:13)፣
፨ ሎጥን ከመከራ ለማውጣት ሁለት መላእክት በሰው መልክ(ኦሪት ዘፍ19:1)፣
፨ መልአኩ ሩፋኤል ለጦቢት በዘመድ ምሳሌ (ጦቢት 3)፣
፨ 66 ዓመታት አንቀላፍቶ ከግዞት ለዳነው ለኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ መልአኩ በሽማግሌ መልኩ እንደታየው ማለት ነው።

☀️ ቅዱሳን መላእክት ሰው መስለው ስለተገለፁ ግን የሚናገሩት ቃልም ሆነ የሚሠሩት ሥራ የግድ የሰው ነው ማለት አይቻልም። አገላለጣቸውም አምላክ እንደወደደ እና እንደ ሚገለጹለት አካል አቅም ይወሰናል። ይህንን ይዞ የድርሳነ ገብርኤል ጸሐፊም ደጋግሞ ገብርኤልን ሰው ፣ ወጣት እያለ ይጠቅሳል። (ድርሳነ ገብርኤል ዘየካቲት)

ሌሎቹ ማስረጃዎች ይቀጥላሉ👇👇👇👇

3 weeks, 5 days ago

መላሾች ለተሳትፏችሁ እናመሰግናለን። ብዙዎቻችን ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓ.ነገር (ኃይለ ቃል)   በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ተጽፎ፣ በመጓጓዣ መገልገያዎች ላይ ተለጥፎ፤ አልያም መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ  ተመልክተነዋል። ቅዱስ ሚካኤልንም ለማመስገን እንደ ምስጋናም የተጠቀምንበትም እንኖራለን። መልካም ነው! ቃሉን የተናገረው ማን እንደሆነ ግን አስተውለናል? ምን ያው ዳንኤል ነዋ ወይም ሌላ ሚካኤል የደረሰለት…

1 month ago

"ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ"
ትንቢተ ዳንኤል ፲÷፲፫(10:13)

ይህን ቃል ማን የተናገረው ይመስላችኋል? ምክንያቱንም በአጭር አመክንዮ አብራሩ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 16 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 day, 5 hours ago

Last updated 1 day, 18 hours ago