Lucrative Business Ideas

Description
YOU CAN'T GO BACK AND CHANGE THE BEGINNING, BUT YOU CAN START WHERE ARE NOW AND CHANGE THE ENDING"!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 2 days ago

Last updated 2 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

2 years, 4 months ago

*ድካም አልባ ውጤት የለም!

መስዋዕትነት የሌለው ግኚት ጠዓም የለውም ፤ በልፋት ያልታገዘ ከፍታ አያስደስትም ፤ ትጋት አልባ ስኬት የለም ። እያንዳንዱ ለውጥና እድገት ውስጥ ልፋት፣ ትጋት ፣ ጥረት አለ ። በዚም በዛም ፣ በላይም በታችም ያለድካም የመጣ ነገር ለመጥፋትና ለመበተን እጅጉን የቀለለ ነው ። የጉጉት ብዛት (temptation) ያለድካም አንዳች ነገር አያስገኝም ። የማትፈልገው ልማድ ቢኖርብህ ከማቆም ጉጉት በላይ ልትሰራበት ይገባል ፤ የምታልመው ስፍራ ቢኖር ያለምንም ጥረት ከምትመኘው ይልቅ መጣር ይኖርብሃል ። ጥረት ሲባል ግን ትንሿና ማንም የሚያደርጋትን ጥረት አይደለም ። በሃሳብህ ልክ የገዘፈ ፣ በህልም ልክ የረቀቀ ፣ ስኬትህን ከፍታህን የሚመጥን የማይገታ ብርቱ ጥረት ።

አዎ! ጀግናዬ..! ድካም አልባ ውጤት የለም ፤ ካልለፋህ ፣ ካልሰራህ ፣ እራሰህን ካላሻሻልክ ስኬት አይኖርም ። በስኬት አለም አንድና አንድ ህግ አለ "እያንዳንዱ ግኚት የልፋትህ ውጤት ነው ፤ እድል የሚባል ነገር የለም"። እድልን ጠብቆ ከስኬት የደረሰ የለም ፤ ለስኬቱ ግን ለፍቶ ተግቶ እድልን ለእራሱ የፈጠረ አለ ። ባዶ አጋጣሚ ፣ ባዶ እድል የሚባል ነገር የለም ። ባልተገነባ ማንነት ውስጥ እድል ኬትም አይመጣም ። ምንም አድርግ ምን ለተለወጠ ህይወት ፣ ለተቃና ኑሮ ፣ ለተስተካካለ ማንነት ፣ ከፍ ላለ አስተሳሰብ ፣ ለላቀ ለውጥ እራሱን የቻለ መሱዓትነት ያስፈልገዋል ። መሱዓትንተ ሲባል የአንድ ቀን አይደለም ፤ ዛሬ ወጥቶ ነገ እንደሚደርቀው ጤዛም አይደለም ፤ ፍላጎቱን የሚመጥን ፣ ከመሻቱ ደረጃ ጋር የሚሄድ ከፍ ያለ መሱዓትነት ።

አዎ! ያለውበት ስፍራ አይመጥነኝም ስላልክ ፣ ስለተማረርክበት ፣ አብዝተህ ስለጠላሀው ብቻ አንዳች የሚቀየር ነገር የለም ። ጥረት አልባ ምሬት ሁሌም ምሬት ነው ፤ አዲስ ነገር የማያስሞክር ሰቆቃና ችግር ሁሌም ችግር ነው ። ችግር ችግርነቱ የሚያበቃው የመፍትሔ አካል ስትሆን ብቻ ነው ። ስራህን የመቀየር ፍላጎት ካለህ አማራጮችን መመልከት ይኖርብሃል ፤ ባልለመድከው መንገድ መጓዝ አለብህ ፤ የማታውቀውን ማወቅ ፣ ያልተማርከውን መማር ይጠበቅብሃል ። ከማትፈልገው ህይወት ለመውጣት የማትፈልገውን ነገር ማድረግ ሊኖርብህ ይችላል ፤ ከሞቀው ጎጆህ ውጪ ለዝናብ ፣ ለብርድና ለውርጭ ልትጋለጥ ትችላለህ ። እርሱ ለፍላጎትህ የምትከፍለው ትንሽ መሶዓትነት ነው ። መቀየር ስለምትፈልገው ሁኔታ የመቀየር አቅሙና ብርታቱ ይኑርህ ፤ እያንዳንዱ ድካምህ ፣ ጥረትህ ዋጋ እንዳለው ተረዳ ፣ አሻጋሪ መሰላልህ ፣ ህይወት ቀያሪ ምዕራፎችህ የምኞትና የጉጉት ጊዜያቶችህ ሳይሆኑ የጥረትና የትጋት ጊዜያቶችህ እንደሆኑ ተረዳ ።
═════════❁✿❁ ═════════*

2 years, 8 months ago

ምን ዓይነት መርዛማ ልማዶች ስኬትን ያጠፋሉ?/ What toxic habits
destroy success?
1. ፍርሃት/ Fear
2. የዓላማ እጦት/ Lack of purpose
3. ነገሮችን አለማመጣጠን/Inconsistency
4. የዲሲፕሊን እጦት /Indiscipline
5. ነገሮችን በይደር ማቆየትና ማመቻመች/ Procrastination
6.በራስ መተማመን ማጣት/ Lack of confidence
7.ተነሳሽነት ማጣት/Lack of motivation
8.ደካማ የአመራር ችሎታ/Poor leadership skills
9.ደካማ የግንኙነት ችሎታዎች/Poor communication skills
10. የእርስ በርስ ግንኙነት ችሎታዎች ደካማነት /Poor relationship skills
11. ቅናት/ Jealousy
12. ስግብግብነት/Covetousness
13.ቅሬታዎችና አጉረምራሚነት/Complaints
14. ታማኝነት ማጣት/Dishonesty
15. ማስፈራራት/Intimidation
ከላይ የተዘረዘሩ መርዛማ የሕይወት ልምዶችን ራሶ ላይ ከታዘቡ ለእርሶ
ሁለንተናዊ እድገትና ስኬት እንቅፋት ነዉና ራሶንና መጥፎ ልምዶቾዎን አሁኑኑ
ማሻሻል ይጀምሩ።
ማደግዎን ይቀጥሉ!
መልካም ቀን

2 years, 8 months ago
ልጆች በተፈጥሮ ፍርሀትን አያውቁም። ስለነገ ወይም …

ልጆች በተፈጥሮ ፍርሀትን አያውቁም። ስለነገ ወይም ስላለፈ ትላንትም አይጨነቁም። ፣አቅማቸውን ሁሉ ተጠቅመው ዛሬን የመኖር ዛሬን የማጣጣም ትልቅ የህይወት ክህሎት አላቸው። ሰው ምን አለኝ አያስጨንቃቸውም። እድሉን እና ነፃነቱን ሲያገኙ እጅግ የሚገርም የፈጠራ ክህሎታቸውን እና ነገሮችን በፍጥነት የመማር እና የማወቅ ብቃታቸውን በየቀኑ ያንፀባርቃሉ። እኛ ደግሞ በተቃራኒው ስላለፈው ትላንት እና ስለማናውቀው ነገ እጅግ ከማሰባችን የተነሳ ዛሬን አጣጥሞ፣ መደረግ ያለበትን ሁሉ አድርጎ መኖርን ረስተናል። በእኛ እና በልጆቻችን መሀል ያለው ዋንኛ ልዩነት እና ግጭት መንስኤ ይሄ ነው:: በራሳችን ፍርሀት ተከበን ልጆቻችንንም እናስጨንቃለን። ወደ ፊት ስራ ባያገኝስ፣ ካልተማረ ምን ሊሆን ነው? ካልፃፈ፣ ካላወራ፣ካላነበበ እንዴት ስኬታማ ይሆናል.... የመሳሰሉ ጭንቀቶችን ይዘን ልጆቻችን ዛሬን የማጣጣም ክህሎታቸው ላይ ጫና እንፈጥራለን። እኛ እነሱን መሆን ሲያቅተን እነሱን ጎትተን ወደ እኛ እንስባቸዋለን። 🙏

2 years, 9 months ago

ለአዕምሮአችን⌛️ መቀላጠፍ ና ጤንነት የሚረዱ 10ነጥቦች !!!!

  1. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው ። በቫይረስ መጠቃት የለበትም ። ሁልጊዜ ሊጸዳ ይገባዋል፡፡ አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ - በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡

  2. አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል ። ያስወግዷቸው፡፡

  3. አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡

  4. አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡

  5. ጥሩ ምግቦች አእምሮ ስል እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ የአሳ ዘይትና ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በቀን በቀን ካገኘ ሥራ ማቀላጠፍ ያውቅበታል፡፡ በቂ ውኃ መጠጣት ለአእምሮ እንደ ግሪስ
    ያገለግላል፡፡

  6. አእምሮ በቫይረስ ይጠቃል፡፡ የአእምሮ ቫይረስ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? አሉታዊ አስተሳሰቦች፡፡ ምቀኝነት፣ ክፋት ማሰብ፣ በማይረቡ ነገሮች መጨነቅ አእምሮን ያውካሉ፡፡ ይህን ቫይረስ ለማጽዳት መልካም መልካሙን ማሰብ ብቻ ይበቃል፡፡

  7. ቁርስ አይዝለሉ፡፡ መኪናዎ ማለዳ ተነስተው እንደሚያሞቋት ሁሉ አእምሮዎንም በአሪፍ ቁርስ ያነቃቁት፡፡ ቀኑን ሙሉ በንቃት እንዲሰራ ጥሩ ቁርስ ያስፈልገዋል፡፡

  8. ተሸፋፍነው አይተኙ፡፡ አእምሮ እጅግ ብዙ መጠን ያለው ኦክሲጂን የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ሲታፈን ግራ ይገባዋል፡፡ መኪና የሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ ኢንደስተሪዎች፣ ብዙ ሲጋራ የሚጨስባቸው አካባቢዎችን ያስወግዱ፡፡ በተቃራኒው መናፈሻ፣ አረንጓዴ ተክሎች የሚበዙባቸው ሜዳማ ስፍራዎች የእግር ጉዞ ቢያደርጉ አእምሮ በጣም ያመሰግንዎታል፡፡

  9. የከሰል ጭስ ለአእምሮ መርዝ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ቤታቸውን በእጣንና በከሰል ጭስ ያፍናሉ፡፡ በነጋታው ኃይለኛ ራስ ምታት ያማቸዋል፡፡የከሰል ጭስ አእምሮን ሊገድለው ይችላልና ይጠንቀቁ፡፡

  10. ለእርስዎ የማያስደስትዎትን ነገር ለሰው ሲሉ ብቻ አያድርጉ፡፡ የማያምኑበትን ነገር በፍጹም አይተግብሩ፡፡ ወደፊት ለጸጸት የሚዳርግዎትን መልካም ያልሆነ ተግባር በድብቅም ቢሆን አይስሩ፡፡ ፀፀትና የሕሊና ወቀሳ ለአእምሮ መርዛማ ነገሮች ናቸው፡፡ ሙሰና፣ ከትዳርዎ ውጭ መማገጥ፣ በሰው ላይ ተንኮልና ሴራ መፈፀም አእምሮን እስር ቤት ውስጥ ማጎር ማለት ነው፡፡ አእምሮ ሰላሙን አጥቶ ሰላምዎን እንዳይነሳዎ መልካም መልካሙን ብቻ ያድርጉ፡፡

  11. መልካም ምክር ለክፉ ጊዜ ስንቅ ነው፡፡ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉት የበለጠ ሰዎች እንዲወድዎት ያደርጋል፡፡

ለስነልቦና ህክምና ቀጠሮ ለመያዝ
+251915955656

#አድራሻ ቤቴል
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!

#ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን !

@BiniGirmachew @BiniGirmachew

2 years, 11 months ago

Morning Questions to Ask Yourself:

  1. What good will I do today?
  2. What bad habit can I avoid doing?
  3. What am I grateful for in my life?
  4. How can I improve today?
  5. What challenge might I face today and how can I overcome it?
    GOOD MORNING ☀️
2 years, 11 months ago

ማንኛውንም
አላማ እንዴት
ማሳካት
ይቻላል?

___

1:-ስለምትፈልገው በትክክል መወሰን

2:-እቅዶችህን በወረቀት ላይ አስፍር

3፦ዋጋ ለመክፈል አታመንታ

4፦ግልጽ እቅድ ንደፍ

5፦ በእቅድህ መሠረት ወደ ተግባር ግባ

6፦ በየቀኑ የሆነ ነገር ስራ

7:- እጅ አትስጥ

2 years, 11 months ago

ማንኛውንም
አላማ እንዴት
ማሳካት
ይቻላል?

_______

1:-ስለምትፈገው በትክክልመወሰን

2:-እቅዶችህን በወረቀት ላይ አስፍር

3፦ዋጋ ለመክፈል አታመንታ

4፦ግልጽ እቅድ ንደፍ

5፦ በእቅድህ መሠረት ወደ ተግባር ግባ

6፦ በየቀኑ የሆነ ነገር ስራ

7:- እጅ አትስጥ

2 years, 11 months ago
*አዲስ ነገር ስንማር የምናልፍባቸው አራቱ ደረጃዎች

*አዲስ ነገር ስንማር የምናልፍባቸው አራቱ ደረጃዎች

መኪና መንዳት ስንለማመድ ይሁን አዲስ ቋንቋ ስንማር አዲስ አፕሊኬሽን ስንጠቀም ይሁን አዲስ ስራ ስንጀመር በተመሳሳይ የምናልፍባቸው አራት ደረጃዎች አሉ ፡፡

1⃣ #አለማወቅን_አለማወቅ በዚህ ደረጃ ላይ ስንሆን ስለነገሩ ግንዛቤ ስለሌለን አለማወቃችንን እንኳ ልናውቅ አንችልም ፡፡ ብስክሌት አይቶ የማያውቅ ልጅ ብስክሌት መንዳት እንደማይችል እንደማያውቀው ማለት ነው ፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ የሚኖረው ስሜት የአላዋቂ ደስታ ነው ፡፡

2⃣ #አለማወቅን_ማወቅ በፊት ከማናቀው ነገር ጋር ከተዋወቅን በኃላ የመጀመሪያዎቹ ሙከራዎች ስኬታማ አይሆኑም ፡፡ (በምሳሌ እንደምትጠቀሰው ከበሮ) አለመቻልን መገንዘብ የሚፈጥረው ጭንቀት አለ ፡፡ ይህንን ጭንቀት መቋቋም የማይችሉ አዲስነገር መማር ፣ መልመድ ወይም ማወቅ እዚህ ጋር ያቆማሉ ፡፡

3⃣ #ማወቅን_ማወቅ ልክ ብስክሌት መንዳት ስንለምድ ስለፔዳል እያሰብን እንደምንነዳው ወይም አዲስ ሀላፊ ስንሆን መመሪያ አገላብጠን እንደምንወስነው ማለት ነው ፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ አዲስ ነገር በመቻል ምክኒያት የሚመጣ ደስታ 'ምናልባት' ከሚል ፍርሀት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ይመጣል ፡፡

4⃣ #ማወቅን_አለማወቅ በዚህ ደረጃ ላይ ሲደረስ አዲሱ ነገር ከተፈጥሮአችን ጋር ስለሚዋሀድ እናደረገዋለን እንጂ አናስበው ፡፡ ልክ አንድን ቋንቋ በደንብ ስንችል ቃላት ሳንመርጥ ስለ ሰዋሰው ሳንጨነቅ እንደምንናገው ማለት ነው ፡፡ በዚህ ደረጃ ብስክሌት የሚነዳ ለምሳሌ የሚሄድበት ቦታ ሲደርስ ምን እንደሚያደርግ እንጂ ስለመሪና ፔዳል አያስብም ፡፡#አምስተኛው_ደረጃ የሚሆነው ሌላ አዲስ ነገር ለመማር ፣ ለመልመድና ለማወቅ ከላይ የተጠቀሱትን እንደገና መጀመር ነው ፡፡*

3 years ago

ስኬትን ምን ያህል እንፈልገው ይሆን ?

አንድ ሰው ከመጠን በላይ ስኬታማ መሆን ይመኝ ነበርና ወደ አንድ አዋቂ ዘንድ ይሄዳል። ለአዋቂውም ታላቅ ሰው መሆን እንደሚፈልግ እና እርዳታውን እንደሚሻ ይነግረዋል። አዋቂውም መልሶ “ እሺ ስኬታማ ሰው መሆን ከፈለግክ ነገ ባህር ዳርቻ እጠብቅሃለው በጠዋቱ ና” ሲል መለሰለት። ሰውየው ግራ ተጋብቶ “እኔ ስኬታማ ሰው አድርገኝ አልኩኝ እንጂ ዋና አስተምረኝ አላልኩሁም እኮ” ይለዋል።

አዋቂውም “ወንድሜ ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ነው ያልከው... ነገ ጠዋት ከባህር ዳርቻው ጋር እንገናኝ” ብሎት መልሱን ሳይጠብቅ ጥሎት ሄደ። በበነጋታው ሰውየው ከባህሩ ዳርቻ ተገኘ ፤ሙሉ ልብሱን ሽክ ብሎ ነበር የመጣው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ሰውየው መጀመሪያ የጠየቀውን ጥያቄ አንደገና ጠየቀ “ስኬታማ ሰው ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው።

አዋቂው በዝምታ ተመለከተው እና… “ና ተከተለኝ” ብሎ ወደ ባሕሩ ተጓዙ… ሰውየው ግራ ገባው... ነገር ግን አዋቂ የተባለው ሰው እጅግ የተከበረ ነበረና የሚሰራውን ያውቃል በማለት ዝም ብሎ ተከተለው... ወደ ባሕሩ ዘለቁ… መጀመሪያ ውሃው እስከ ጉልበታቸው ደረሰ… ቀጥሎ እስከ ወገባቸው…. ቀጥሎ እስከዳረታቸው... የሰውየው ልብ ተረበሸ... ስኬታማ መሆን ከዚህ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ግራ ቢገባው “ይህ ነገር ስኬታማ ከመሆን ጋራ ምን አገናኘው?” ሲል ጠየቀ...
አዋቂውም “ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ነው ያልከኝ ወዳጄ?” አለው... ሰውየው “አዎ” ሲል መለሰ... አዋቂው የሰውየውን መልስ እንደሰማ የሰውየውን ጭንቅላት ይዞ ወደባሕሩ ደፈቀው። ሰውየው እራሱን ለማዳን ቢንፈራገጥም አልቻለም... አዋቂው የሰውየውን ጭንቅላት ለሴኮንዶች ውሃ ውስጥ ካቆየው በኋላ ቀና አደረገው... ይሄኔ ሰውየው በሃይል እየተነፈሰ “እኔ….ስኬታማ አድርገኝ ባልኩኝ ለምን ልትገለኝ ፈለግክ?” ሲል ጠየቀ “ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ?” አለው አንገቱን እንደያዘ... “አዎ”... ብሎ ሲመልስ ደግሞ ከባሕሩ ነከረው፤ እንደቅድሙ ትንሽ አየር እስኪያጥረው ካቆየው በኋላ ቀና አድርገው እና እንዲህ ሲል ጠየቀው “አሁን በዚህች ቅፅበት በጣም የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?” ሰውየው... ቁና ቁና እየተነፈ... “አየር” አለ... “አየህ አሁን አየር እንደፈለግከው ያህል... ስኬትን ክፉኛ ካልፈለግካት መቼም አታገኛትም... ይህ ነው የስኬት ሚስጥር” አለና አሰናበተው ይባላል። አንዳንዶች የፈለጉትን ሲያገኙ እናያለን አንዳንዶች ደግሞ እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ይቀራል።

የሁለቱን ሰዎች ልዩነት እድል በሚባለው ነገር ልናስታርቀው ብዙ ጊዜ ብንጥርም እውነታ ግን ሌላ ነው... ስኬት ጥቂቶች ብቻ የሚታደሏት አይደለችም... ሁላችንም እንድንደርስባት በእኩል ቦታ የተንጠለጠለች ፍሬ እንጂ... እጅግ የተራባት ሰው ማድረግ ያለበትን ሁሉ አድርጎ ያገኛታል…. ብዙዎቻችን ስኬታም መሆን ብንፈልግም እጅግ ከስኬት በላይ አብዝተን የምንወዳቸው ሌሎች ጥቃቅን ነገሮች ህይወታችንን ሞልተውታል።

ሁሉም ስኬታማ ሰዎች ወደ ስኬት የመጡበት መንገድ ይለያያል፤ አንድ ፍጹም የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ግን ሁሉም ይቻላል ብለው ማመናቸውና ላመኑት ነገር ያላቸውን ሁሉ ሳይሰስቱ መስዋት ማደረጋቸው ነው። አሁን በሌሎች ሰዎች አይን “ስኬታማ” ተብለው የሚጠሩ ሰዎች በአንድ ወቅት እንደማንኛችንም አይነት አቅም እና ችሎታ ነበራቸው… የአስተሳሰብ ሁኔታ ግን አንዳንዶቻችንን ወደ ኋላ አንዳንዶቻችንን ደግሞ ወደፊት እንድንራመድ አደረገን።

አይምሮዋችን እንደ እርሻ ነው... የዘራንበትን ያሳጭደናል... አይምሮ እኛ ምን እንዝራ ምን እንትከል ግድ የለውም። መሬት በቆሎ ተዘራ ጤፍ ተዘራ ግድ አለው እንዴ?... እናም አይምሮዋችን ላይ መልካሙን ሰብል መርጠን እንዝራ…

3 years ago

የሰሞኑ ጉንፋን!

የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡

• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ህመም
• የጀርባ ህመም
• የጡንቻ ህመም
• ምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ኃይለኛ ራስ ምታት
• ፍዝዝ ማለት

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?

ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው። ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ?

• የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
• ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ
• የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
• ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
• ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
• መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ

ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

• ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልየአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
• ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
• ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
• ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
• የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
• ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
• ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል።

ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው ?

• ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
• ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
• ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
• በቂ እረፍት ማድረግ
• የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ
• እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም

Credit : ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

@tikvahethiopia

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 2 days ago

Last updated 2 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago