ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 3 days ago
Last updated 1 week, 5 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
የዛሬ ዕለተ ሰኞ ታኀሳስ 7/2017 ዓ.ም.
የዕለቱን የጣና ዜናዎቻችን በተለመደው ሰዓት ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
በዕለቱ ዜናዎቻችን፦
……የብልጽግና ወታደራዊ አዛዥ ከእነ ምክትሉ በተደመሰሱበት ግንባር የብልጽግና ሠራዊትን ብቻ ነው ማከም ያለባችሁ ተብሎ አንድ ጤና ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ዝግ ተደርጓል፡፡ ይህ ታላቅ ድል የተመዘገበበትን የወሎ ግንባር መረጃ በዜናች አካተናል ትሰሙታላችሁ፡፡
……ከመናገሻ ጎንደር ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የዐማራ ፋኖ በብልጽግናው ሠራዊት ላይ ድል ተጎናጽፏል፡፡ የዐማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ያስመዘገበውን ታላቅ ድል ለዕለቱ በቀዳሚነት የምናቀርበው ዜናችን ነው እናስደምጣችኋለን፡፡
…..ብልጽግና ከጦር ወንጀል እስከ ማኀበራዊ ነውር ተዘፍቋል፡፡ አዛውንት ወላጆቹ የታፈኑበት ዐርበኛ ማስረሻ ሰጤ ለጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን የሰጠውን ምላሽ በዜናችን ትሰሙታላችሁ፡፡
…..ዘመቻ አንድነት ዛሬም በታላቅ ድል ታጅቦ ቀጥሏል፡፡ ከመና መቀጠዋ እስከ ጉና በጌምድር በተዘረጋው የፋኖ ተጋድሎ ዙሪያ የፋኖ መሪው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በዜናችን እናስደምጣችኋለን፡፡
….ከአዲስ አበባ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ፋኖ ታላቅ ድል ተጎናጽፏል፡፡ ይህን ታላቅ የፋኖ ድል በዝርዝር አሰናድተነዋል ትሰሙታላችሁ፡፡
…..የአፍሪቃ ቀንድ አሁንም በውጥረት ላይ ነው፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ ወደ አፍሪቃ ቀንድ እጁን በረጅሙ ዘርግቷል፡፡ ኮንግረሱ ስለ ሶማሊላንድ ምን አለ? በትንታኔ ዜናችን ተመልክተነዋል።
……….እነዚህንና ሌሎች ዝርዝር የግንባር ውሎ ዜናዎችን ይዘናል፡፡
የዜና ጥቆማ መቀበያችን
Email 📧:
📲 +256 767 972513
Via WhatsApp & Telegram
ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን
ከሀቅ ጋር…!
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውና ገነት አስማማውን ጨምሮ በነዶክተር ወንድወሰን መዝገብ የተከሰሱ የአማራ ግፉአን ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ገነት አስማማው፣ ጎበዜ ሲሳይ እና መስከረም አበራ የአገዛዙ ዓቃቤ ህግ የከሰሳቸው ሲሆን፤ በምሁራኑ ዘርፍ ደግሞ፤ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ፣
ረ/ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይን፣
ዶክተር መሰረት ቀለምወርቅ፣
መንበር አለሙ፣ ሲሳይ መልካሙ እና
ዶክተር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ የአማራ የህሊና እስረኞች ከነገ ታህሳስ 7 እስከ 18 ለምስክር ተቀጥረዋል።
እነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሚከፍሉልንን ዋጋ ማየት አለብን ብላችሁ የምታምኑ ሁሉ፤ ልደታ በሚገኘው የካንካሮው ፍርድ ቤት እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።
የፋኖ መሪው ማብራሪያ ስለ ፋኖ አንድነት።
የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው ፋኖ እያሱ አበራ ከጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርጓል። በቆይታው ከተናገራቸው ሃሳቦች መካከል። "የአማራ ህዝብ ትግል፤ ጠላት ብልጽግና በሚያደርስበት ልክ እንጂ፤ በግለሰቦች የስልጣን ፍላጎትና ለጠባብ ቡድኖች የጥቅም ፍላጎት የሚወሰን አይደለም። የአማራ ፋንዶ አንድነት እንዲፈጠር የምንፈልገውም የህዝባችንን መከራ ለማስቀረት እንጂ፤ ግለሰቦችን ለማንገስ አይደለም" ብሏል።
የዛሬ ዕለተ ሰኞ ሕዳር 30/2017 ዓ.ም.
የዕለቱን የጣና ዜናዎቻችን ከደቂቃዎች በኋላ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
በዕለቱ ዜናዎቻችን፦
….. የትግሉ ማርሽ ቀያሪ የተባለለት ሁነት ከጎንደር ግንባር ተሰምቷል፡፡
አሁናዊ የትግሉ ዘመቻ ፍጹማዊ የአንድነት ዘመቻ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው›› የሚለው የዐማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዘመቻ መምሪያ፤ ለሁሉም የጎንደር ቀጠና ፋኖዎች ያስተላለፈው የዘመቻ መመሪያ ወታደራዊ አንድምታ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡
….በጎንደር ግንባር የብልጽግና ሰራዊት መስመራዊ መኮንኖች የተሰውበትን አዛዦች ለማንሳት ሄሊኮፕተሮችን እስከመላክ ያስገደደውንና አምስት የፋኖ ክፍለ ጦሮች ተናበው ያደረጉትን ተጋድሎ በዜናችን አሰናድተነዋል ትሰሙታላችሁ፡፡
…… ሸዋ ላይ ታላቅ ተጋድሎ ያደረገው ፋኖ የግንባር ውጤቱ ምን ይመስላል? ዜናው ሰዓቱን ጠብቆ ወደናንተ ይደርሳል፡፡
….. በጎጃም ግንባር ደብረ ኤሊያስ፣ ጮቄ ተራራና በዙሪያው የሚገኙ አካባቢዎች የውጊያ ቀጠናዎች ሆነው ቀጥለዋል፡፡
ለመሆኑ ጎጃም እንዴት ሰነበተ? አጠናቅረናል፡፡
….የዐማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የምዕራብ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር በወሰደው የደፈጣ ጥቃት ታላቅ ድል ተጎናጽፏል፡፡ የግንባር ውሎ መረጃውን እናስደምጣችኋለን፡፡
….. በጋይንት አውራጃ ሦስት የፋኖ ክፍለጦሮች ውጊያ ላይ ናቸው፡፡ ደምቢያ መስኩ ላይ የበጌምድር ክፍለጦር ሁለት ብርጌዶች የድል ብስራት አሰምተዋል፡፡
………. እነዚህንና ሌሎች ዝርዝር የግንባር ውሎ ዜናዎችን ይዘናል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ እንቀርባለን፡፡
የዜና ጥቆማ መቀበያችን
Email 📧:
📲 +256 767 972513
Via WhatsApp & Telegram
ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን
ከሀቅ ጋር…!
አርባ ነጋሪት በትግራይ ቀጥሏል!!
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቀሌ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ። ከተማዋ በቅርቡ በእነ ደብረጺዮን ቡድን በከሉል ሌላ ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር ይታወቃል፡፡
በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው። በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት ፤ " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም ፤ አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያውም መንግስት የመደበው ብቻ ነው። በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም ፤ ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል። ይህም በትግራይ ክልል አርባ ነጋሪት እየተፈጠረ መሆኑን አመላካች መሆኑን ድርጊቶቹ ያመለክታሉ፡፡
"ይህንን ጉዳይ ያነሳሁት አስተያየት እንድትሰጡበት ሳይሆን ለአለቆቻችሁ እንድትነግሩ ነው" ክርስቲያን ታደለ
"በችሎቱ ግድግዳ በተገጠመው ካሜራ ያለፍቃዳችን እየቀረጻችሁን ነው፤ ይህ ትክክል አይደለም፤ ለግልጽ ችሎት አስፈላጊነቱ ከታመነበት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቀጥታ (live) ለኢትዮጵያ ህዝብ የችሎት ሂደቱ ሊተላለፍ ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል።
"ለተወሰኑ ባለስልጣናት በቀጥታ እየቀረጹ ለመስጠት ስለሚሆን ይህ አካሄድ በተከሳሾች ላይ ጫና ይፈጥራል" በማለት ከፍቃድ ውጪ የሚደረግ ቀረጻን ተቃውመዋል፤ ይህ እስካልተስተካከለ ድረስም ከቀጣይ ቀጠሮ ጀምሮ ፊታቸውን ከችሎቱ በተቃራኒው አዙረው ለመቀመጥ እንደሚገደዱ አሳውቀዋል።
በተጨማሪም ከሳሽ ከእኛ በኋላ ለመጡ በርካታ መዝገቦች ክሱን እያሻሻለ የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ እያደረገ መሆኑ እየታወቀ ይህን መዝገብ በተለየ መንገድ ለማራዘም ስለምን አስፈለገው? ሲሉ ጠይቀዋል።
"መንግስታዊ ባህሪን ባልተላበሰ መልኩ ታግተን ከርመናል፤ አሁን ደግሞ በህግ ስም ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ፍ/ቤቱን ተጠቅሞ አገዛዙ ተደራራቢ የሆነ ግፍና በደል እያደረሰብን ይገኛል። እኔ እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የወከልኩት ህዝብ ያለኝ እንደራሴ ነኝ፤ የመረጠኝ ህዝብ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፤ እኔም እንደ ዜጋ ፈጣን ፍትህ እፈልጋለሁ" ሲሉም ተደምጠዋል።
"ይህንን ጉዳይ ያነሳሁት አስተያየት እንድትሰጡበት ሳይሆን ለአለቆቻችሁ እንድትነግሩ ነው" ብለዋል።
"አካሄዳችሁ የሚያስተምር ሳይሆን ትውልድ ቂም እንዲይዝ የሚያደርግ በመሆኑ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ፣ ስለትውልዱ ብላችሁ ህሊና ካላችሁ ስለህሊናችሁ ብላችሁ ግፍ መስራት ይብቃ፤ ፈጣን ፍትህ ይሰጠን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የተከበሩ ክርስቲያን አያይዘውም በማንነታችን እየተፈጸመብን ያለው ስልታዊ በደል ይቁም፤ በፓርላማም ሆነ በዐቃቤ ህግ ተስፋ ቆርጫለሁ፤ ቢያንስ የምታስተሳስረን ክር እንዳትበጠስ ፍ/ቤቱ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እጠይቃለሁ ብለዋል።
ይቀጥላል!!
‹‹አማራን ሲያይ የሚፈራ መንግሥት ነው›› አቶ ዮሃንስ ቧያሌው
የኣማራ ህዝብ ጠላት የሆነው ብልጽግና በእነ አቶ ዮሀንስ ቧያሌው መዝገብ የከሰሳቸውን የአማራ ልጆች ትናንት ፍርድ ቤት አቅርቦ ነበር፡፡ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ተቃውሟቸውን ያሰሙት፤ አቶ ዮሀንስ ቧያሌው፣ ዶክተር ካሳ ተሻገር፣ ክርስቲያን ታደለ፣ ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ፣ ዶክተር ጫኔ ከበደን ጨምሮ የሁሉንም ሃሳቦች በዚህ ገጽ እናጋራችኋለን፡፡ በቅድሚያ የአቶ ዮሀንስ ተቃውሞ እነሆ፡፡
"በፍትህ ሂደቱ ላይ አንድ የተለመደ አሻጥር አለ፤ ይኸውም ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ በጋራ መድረክ እየተገናኙ የእነገሌን መዝገብ እናራዝም እያሉ ነውና በደሉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን፤ በውሸት፣ በእገታ፣ በፖለቲካ እና አማራነትን በመወንጀል ጭምር ግፍን አሳልፈናል" ያሉት ዮሃንስ አማራን ሲያይ የሚፈራ መንግሥት ነው የገጠመን ሲሉ ተናግረዋል።
"ገና ወደ ፍ/ቤት ሳንቀርብ እንደፈረደብን እናውቃለን፤ ለወራት በእገታ ላይ የከረምን በመሆናችን ጭምር ፈጣን ፍትህ ያስፈልገናል" ብለዋል።
አያይዘውም በችሎቱ ውስጥ በስለላ ካሜራ ያለፈቃዳችን እየተቀረጽን ስለሆነ ሊቆም ይገባዋል ሲሉም ተደምጠዋል።
ከአሁን ቀደም ከፍ/ቤቱ ትዕዛዝ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በቃሊቲ ማ/ቤት በኩል እያጋጠሙን ያሉ ችግሮች እንዲስተካከሉ እየተደረገ ነው ላሉት ጥረት ችሎቱን ያመሰገኑት ዮሃንስ አሁንም ግን የሚቀሩ ጉዳዮች እንዳሉ አመላክተዋል።
በእስር ቤቱ ውስጥ ከመኖሪያ ክፍላቸው ተነቅሎ የተወሰደው ቴሌቪዥን እንዳልተመለሰላቸው እንዲሁም የስልክ አገልግሎትም በአንድ ክፍል ካሉ 23 ታሳሪዎች መካከል 21 የሚሆኑት በአማራነታቸው ተለይተው የተከለከሉ ስለመሆኑ ጠቅሰው የዘረኝነት አሰራሩ "የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ አገዛዝን ያስናቀ ነው" ብለውታል።
የቃሊቲ ማ/ቤት ከአገዛዙ የፖለቲካ አስፈጻሚነት በመውጣት ተቋማዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንዳልሆነ በመግለጽ ይህ አካሄዱ እንዲስተካከል፣ በቤተሰብ ላይም የበቀል በትር ማሳረፉን እንዲያቆም ነው የጠየቁት።
ይቀጥላል!!
ነፍጠኛ እየመጣብህ ነው ተነስ ዝመት በሚል በምስራቅ ሐረርጌ በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያ መወሰዳቸው ተሰማ!
የአማራ ሕዝብ ወንድማችን እንጂ ጠላታችን አይደለም፡ ልጆቻችን ለማነው የሚዘምቱት የሚል ጥያቄ ያነሱ ወላጆች ድብደባ እና እስር እንደተፈፀመባቸውም ታውቋል።
ገዢው የብልፅግና ቡድን "ነፍጠኛ እየመጣብህ ነው ተነስ ዝመት፡ አባይን ሳይሻገር እዛው ባለበት እናስቀረው" በሚል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች በርካታ ወጣቶችን አፍሶ ወደ ሁርሶ እና ጦላይ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች መውሰዱን የመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ወጣቶቹ ታፍሰው የተወሰዱት በዞኑ ስር ባቢሌ፣ ጃርሶ፣ ጪናቅሰን፣ ኮምቦልቻ እና ኤረር በተባሉ ወረዳዎች ሲሆን የወጣቶቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስመለስ እስከ 100 ሺ ብር ተጠይቀዋል ነው የተባለው።
በጅምላ ታፍሰው ከሚወሰዱት ወጣቶች መካከል ዕድሜያቸው 13 እና 14 ዓመት የሆነ ታዳጊዎችም ይገኙበታል ሲሉ ከመረብ ሚዲያ ኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በባቢሌ ወረዳ ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ወደ ጦላይ እና ሁርሶ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።
ወጣቶቹ በጅምላ ከታፈሱ በኋላ በባቢሌ ወረዳ ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለቀናት እንዲቆዩ የሚደረጉት ምን አልባት ልጆቻቸው ወደ ውትድርና እንዳይሄዱ የሚፈልጉ እስከ 100 ሺ ብር ከፍለው ማስለቀቅ የሚችሉ ወላጆች ካሉ እስኪመጡ ድረስ ለመጠበቅ ሲሆን፡ ወላጆቻቸው የተጠየቀውን የገንዘብ መጠን መክፈል ያልቻሉ ወጣቶች ከቀናት በኋላ ወደ ማሰልጠኛ ይወሰዳሉ ነው የተባለው።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 3 days ago
Last updated 1 week, 5 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago