የግጥም ቤት✍

Description
ግጥም የምትጥም ፤ እንደ ዶሮ ቅልጥም.....
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 week, 1 day ago

*በእንስሶቹ በረት....

በቆሸሸ ገላ ፥ በበከነ ነፍስ ሞት ተቀልሶ
ለፍዳ ሲታዘዝ ፥ ክፋት የወረረው ዛሬም ተመልሶ
ሀጥያት አንከባሎ ፥ ቁልቁል እየገፋ
ነበልባል እሳት ስር ፥ በደል እያካፋ
ዘመን እስኪቆጠር ፥ ፅልመት እያገሳ
ኩነኔን ሲያሰፋ ፥ ፅድቅ እያረሳሳ

ጭንጋፍ በሆነ ፥ ስንኩል አለም ስር
በባርነት ቀንበር ፥ ተደርገን እስር ስር
የዘመን ሸክም ፥ የሰው ልጅ ፍዳ
ደሙን አንጠባጥቦ ፥ ለነፍሱ ጓዳ
ያለም ጥበብ ንቆ
ከራሱ ሊያስታርቅ
ፀሀይ ተወለደ ፥ ሞትን ከኛ ሊያርቅ።

በቤተልሄም ከበረቱ ግርግም
ተጠቅልሎ በጨርቅ ፥ አዳማችን ዳግም
ዘላለም ሊያኖረን ከእቅፉ ጉያ
ሰው ሆነ አምላክ በከብቶች ማደሪያ።

🎄🎄🎄እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም🎄🎄🎄
                  አደረሳችሁ💐💐💐

ገጣሚ ፦ keyso*@getembate@getembate

1 week, 1 day ago
***🎄***እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ልደት በሰላም አደረሳችሁ***🎄***

🎄እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ልደት በሰላም አደረሳችሁ🎄

💥 መልካም ገና💥

💐💐💐💐💐🌼🌼🌼🌼💐💐💐💐💐💐💐

@getembate
@getembate

1 week, 2 days ago

**አፈቀረኝ/2/,ከሰማይ እስከ በረት
ግርማውን እስከማደንገዝ ያለቅንጣት ወረት
ከትዕቢቴ በላይ ከክህደቴ ልቆ
ከብቶች ስር ተገኘ ሞገሱን ደብቆ

ምን ?ትዝታ ከአዳም ምን ናፍቆት ቢኖርበት
እረኛ ስር አደረ.......   ንቆ ንጉስነት
አፈቀረኝ ሳላፈቅረው
ቤቱ አስጠጋኝ ሳላስጠጋው

አፈቀረኝ
✍️አቤል(ያኖስ)
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳቹ.።**@getembate@getembate

1 week, 4 days ago
*ጭላንጭል ተስፋዎች~ ውስጤን አቁመውት፣

*ጭላንጭል ተስፋዎች~ ውስጤን አቁመውት፣
ያስታምሙት ጀመር ~ ምክንያቶች ሰተውት።
ልፋት ያጀዘበው፥ የተናጋ መንፈስ፣
ውድቀት ቁርጡን አውቆ ፥ እንደወንዙ ሲፈስ።
ብርሀን ተስፈንጥሮ ፥ ያኖረው ነፍሴ ላይ
ምን አይነት ፀጋ ነው ፥ የሰጠኝ ያ ሰማይ

ዳሩን ባልደርስበት ፥ ባይፈታም ቅኔው
ሞት ባይሸረሽረው ፥ ጥላዬንም ከኔው
ከቶ አልነጠቀኝ ፥ የሺ ሺ ብምፏቀቅ
ያቆመኝ ስባሪ ፥ ልቤን ከኔ አይነጥቅ።

ልክ እንደንፋሱ ፥ ሽው ሲል በውስጤ
ሲንጎራደድ ለጉድ ፥ እንደእንግዳ መጤ
ይታወቀኛል ሽር ጉዱ ሲከር፣
ዛሬዬ ላይ ቆሞ ትላንቴን ሲምር።

ገጣሚ፦ keyso*@getembate@getembate

1 week, 4 days ago
፦...... . . . . በመጨረሻም …

፦...... . . . . በመጨረሻም የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ታገኛለህ.... . . . .💙💙💙

@getembate
@getembate

1 week, 5 days ago

አስተማሪ ታሪክ

......ጠላ እየጠጣን ከጓደኞቼ ጋ ተሰባስበን እየቀደድን ሳለ ፦

ምድር ላይ የትኛውን ገጠመኝህን በይበልጥ ትወዳዋለህ የሚል ቀደዳ ጀመርን

ፍሬንድ ቀጠለ

"አንድ እለት እሁድ ጠዋት እናቴ ቡና እየጠጣች ፣ እየመከረችኝ ፣ እየመረቀችኝ ፣ እየሰደበችኝ ሳለ

በጣምምም ደስስ የሚልሽ ምን ብታገኝ ነው  አልኳት  አጠያየቄ ድንገት ነበር

ላሊበላ ፣  አክሱም ጽዮን ፣ ውቅሮ ማርያም ካዲ ብሄድ ደስ ይለኛል አለቺኝ

ፊቷ ላይ ያለው ምኞት የደስታ ዳር ይመስል ነበር።  ። በነጋታው ስጣደፍ ሄጄ ቢሮ አንድ መቶ ሺ ብር  ተበደርኩ ፍቃድ ወሰድኩ

ሎተሪ ደረሰኝ ብያት  ላሊበላ ፣  አክሱም ጽዮን ፣ ውቅሮ ማርያም ካዲ ወሰድኳት   ደስስ አላት ፀለየች  ፣ ለነዲያን መፀወተች ፣ እጄን ይዛ መረቀቺኝ ። 

ከዛ ከተመለስን በኋላ ሶስት ወርም አልቆየች ትንሽ አሞት ሞተችብኝ። ሳለቅስ ፣ ሳዝን ያፅናናኝ እና ያበረታኝ ህልሟን ማሳከቴ ነበር

ቀጠለ ሌላ ፍሬንድ ፦

"አንድ ቀን ክላስ ቀጥቼ ዩኒፎርሜን እንደለበስኩ  ጠላ ቤት ደቅ ብዬ አባቴ ከጓደኞቹ ጋር  ከች አለ ሳየው ስካሬ ጠፋ ።

ልጄ ነው ብሎ ለፍሬንዶቹ  አስዋወቀኝ ። ሃይለኛ ስለነበር እዛው ካልገደልኩ ይላል ብዬ ነበር። ምንም አላለኝም ። እንደውም የጠጣሁበትን ከነ ፍሬንዶቼ ከፈለልኝ ። ቀድሜው ወጣሁ ፦

አላመንኩትም የሚገድለኝን አገዳደል እያሰብኩ  ስፈራ ስቸር እቤት አምሽቼ ገባሁ ። እሱ ምንም አላለኝም ።

በሳምንቱ "ጋሻው ዛሬ ትምህርት የለህም አይደል "

"አዎ"
"በቃ ዛሬ አብረን እንዋል አለኝ" እሺ ብዬው የሚሰራበት
አብረን ሄድን

ውሎውን አዋለኝ ። የሆነ ህንፃ ይጠብቃል ፣ ህንፃው ጋ የሚቆም መኪና ይጠብቃል ፣ መኪና ያጥባል ።

የጠበቀበትን እና ያጠበበትን  ብር እንዲሰጡት ደጅ ይጠናል ፤ ትንሹም ትልቁም ይጠራዋል ፣ ያዙታል ያን ቀን አባቴ በጣም አሳዘነኝ

ከፊቱ ገሸሽ ብዬ አለቀስኩ

እንዴት እንደሚያሳድገኝ ያኔ ነው የገባኝ ። ምን እያለ እንደመከረኝ ፣ በእኔ ጉዳይ ለምን እንደሚናደድ ገባኝ

የዛ ቀን ህይወቴ ተቀየረ ።

ሌላ ፍሬንድ ቀጠለ ፦

"አንድ ቀን  እቃ ጠፍቶኝ ቤታችንን ሳምሰው
የታናሽ እህቴ ዲያሪ አገኘሁት በማላውቀው ምክንያት የማስሰውን ነገር ትቼ ደቅ ብዬ ማንበብ ስጀምር ።

ጥጋቤ ፣ ድፍረቴ እልሄ ተነፈሰ ። የግሩፕ ጠብ አጓጉል ውሎዬ ጣጣ  ለመጀመሪያ ጊዜ ገባኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ መፍራት ጀመርኩ ፤ ለቤተሰባችን ምን ያህል እንደማስፈልግ ማስታወሻዋ ነገረኝ" 

ለካ አንዳንድ ቀን ብቻውን ዘመን  ያህላል !!

@getembate
@getembate

1 week, 5 days ago

ያሬዳዊ ግጥም)  
።።።።።።።።                ገጣሚ ያሬድ ከበደ

     ፣፣፣፣፣፣ስጦታዬ፣፣፣፣፣፣
🙏*🙏🙏
         ባንተ የልደት ቀን
ደመና ተገልጦ ሰማይ ፍክት ብሏል
*
        ፀአዳው ብሩህ ገና
የመስከረም ዓደይ ፅገሬዳ መስሏል
*
         ጨረቃ ከዋክብት
ምድሪቷን ሊያደምቁ ቁልቁል እያበሩ

      የብርሃን ጮራ እየፈነጠቀ
ከበተስኪያን አፀድ ከቅጥር ደብሩ
*
             አንተን ለማወደስ
             ካህናት ዲያቆናት
ማህሌት ቆመዋል ዜማን በቅላፄ እየደረደሩ

            የአብ አምሳያዋች
ለውልደትህ ተብሲር ምስጋና ሲያደርሱ

           ቡራኬውን ባርከው
          ፅዋውን ተቃምሰው
በዕድሜህ ቁጥር ልኬት ሻማ እየለኮሱ

           በዚህ ሁሉ መሀል
   የግብዣው ሰገነት እንደተከፈተ

           በትልቅ ሸራ ላይ   
ማረኪ ውብ ቃላት ተፅፏል ስላንተ

             የተፃፈው ስንኝ
ከዕውቀት ሰሌዳ የጫረው ጠመኔ
ሀረግ ሆሄ ፊደል ሰምና ወርቅ ቅኔ

             መሆኑን እያየው
ውስጤን ሀሴት ሞልቶ እንደ ተደመምኩኝ
እንኳን ተወልድክ ልል ይህን ግጥም ፃፍኩኝ

"""“
"
"
እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ*@getembate@getembate

1 week, 6 days ago

ሰላም ተወዳጆች

እንደምናውቀው ከፊታችን የሚመጡ ሁለት በአላት አሉ ። አንደኛው የገና በአል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ እንደዚሁ የጥምቀት በአል ናቸው።

እናም እስኪ ወቅቱን የሚመስል ግጥሞች እየላካችሁ ሀሳብ አስተያየት 👍❤️ እንደራረግ። አሪፍ ግጥም ያለው ዋናው ቻናላችን ላይ የምንለጥፈው ይሆናል።

🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄

@getembate
@getembate

2 weeks, 6 days ago

መልካምነት
ሁለቱ ባህታዊያን ....

በተራራ ላይ የሚኖሩ ሁለት ባህታውያን ነበሩ ። ቀንና ለሊቱን ፈጣሪን ሲያመሰግኑ የሚኖሩ ሲሆን ሁለቱም እርስ በእርሳቸው ይዋደዳሉ።

የሁለቱ ባህታዊያን የጋራ መገልገያ የሆነችው የሸክላ ድስት ብቸኛዋ ምድራዊ ንብረታቸው ናት ። ከእለታት በአንዱ ቀን ታዲያ ክፉ መንፈስ በአንደኛው ባህታዊ ገባበት ። ከዛም በልቡ ወዳጁ ባህታዊውን የእውነት ይወደው እንደሆነ እንዲፈትነው ጎተጎተው ። ይህ ባህታዊ ታዲያ ወደ ወዳጁ ባህታዊ በመቅረብ እንዲህ አለው ፦ በጋራ ብዙ ጊዜ ኖረናል ። አሁን ግን መለያየት ይኖርብናል። ስለዚህ  ንብረታችንን እንካፈል "

ይህን የሰማው ሁለተኛ ባህታዊ ወዳጁም " ወንድሜ ሆይ ካንተ መለየቴ ልቤን ያሳዝነዋል ። ከወሰንክ ግን መልካም ይግጠምህ " በማለት የሸክላ ድስቷን አምጥቶ ሰጠው። " እነሆ ላንተ ትሁንልህ ። ልንካፈላት አንችልም እና -ወንድሜ ሆይ " በማለት ብቸኛ የጋራ ጥሪታቸውን ለወዳጁ ሊሰጠው ወሰነ።

ክፉ መንፈስ ውስጡ የተጠናወተውም ባህታዊ መልሶ " ከማንም ላይ ምፅዋት አልቀበልም። የራሴ የሆነውን ድርሻ ብቻ ነውና የምፈልገው የሸክላ ድስቱን መካፈል አለብን" ሲል መፈተኑን ቀጠለ ።

ሁለተኛውም ባህታዊ ፦ "ድስቱ ስንካፈለው ቢሰበር ለማንም አይጠቅምም። የግድ የምትል ከሆነ ግን ባይሆን እጣ እንጣጣል " በማለት አማራጭ አቀረበለት ።

ሆኖም ግን አንደኛው ባህታዊ የወዳጁን መልካምነት ሊበረዝ ባለመቻሉ ውስጡ ያለው ክፉ መንፈስ ፈፅሞ ሊስማማ አልወደደም ። " እኔ የምፈልገው በትክክል የራሴ የሆነውን ብቻ ነው። ፍትኀን በእጣ አልወስንም " በማለት እንቢ አለ።

በመጨረሻም የወዳጁን ያልተለመደ አኳኻን የተመለከተው ባህታዊ ተስፋ ባለመቁረጥ እንዲህ አለ፦ ለብቻህ ውሰደው ብልህ እምቢ ካልከኝ ምን ይደረጋል? እንግዲያውስ ድስቱን እንስበረው ብሎ ማማተብ ጀመረ።

በዚህን ጊዜ በወዳጁ ስር የገባው ክፉ መንፈስ ተናደደ።  በቁጣም እየጮኸ " ምን አይነት ባህታዊ ነህ ! እያለ ከውስጡ ወጣ ።

ከዛም ሁለቱ ባህታዊያን በመልካምነት አብረው በተራራው ላይ ፈጣሪን እያመሠገኑ መኖር ጀመሩ።  ሸክላውም ሳይሰበር ቀረ።

#share🙏🙏🙏#like ማድረግ አይረሳ

@getembate
@getembate

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana