ራፋቶኤል

Description
ኢትዮጵያ የምታድገው ወደፊት ስትራመድ ሳይሆን ወደ ኋላ ስትመለስ ነው።
ስለ መፅሐፈ ሔኖክ እና ጥንታዊ ስለ ሆኑ የአባቶች ጥበብና ስልጣኔ ሄኖክ ስለፃፋቸው ሦስት መቶ ስልሳ የጥበብ እፅዋት ስለ ተሰወሩት ዘጠኝ የኢትዮጵያ ፒራሚዶችና የተሰወሩ የቴክኖሎጂ ከተማዎች ስለ ተሰወሩ ቤተመንግስቶችና በኪሩቤልና በሱራፌል ታንፀው ስለተሰወሩ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አለም ዝም ቢልም እኛ እንናገራለን።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

hace 3 meses, 1 semana
Join the cherry game using this …

https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_356698667
Join the cherry game using this referral link and win prizes!

10$ dollar ykeflal😋

1   level  3 medres keza belay
2   3 ena keza belay sew megabez enesum mesrat alebachew yetegabezut
3  ke telegram wallet magenagnet
4  task mesra

🎈🎈10 days left... 
Share

hace 3 años, 1 mes
hace 3 años, 3 meses
ድርሳነ መስቀል መጽሀፍ ቃልኪዳን መጽሐፉን ቆሞ …

ድርሳነ መስቀል መጽሀፍ ቃልኪዳን መጽሐፉን ቆሞ ላነበበ የ 80 አመት ሀጥያቱ ይሰረይለታል።
ቁጭ ብሎ ያነበበ የ 40 አመት ሀጥያቱ ይሰረይለታል።
@razielethiopia

hace 3 años, 3 meses

+++ #ድርሳነ_መስቀል +++

_ ይህ ድርሳነ መስቀል የተባለው መጽሐፍ የእየሩስአሌሙ ኤጲስ ቆጶስ #አባ_መቃርዮስ የደረሱት ነው።

_ ይህ መስቀል በኢትዮጵያ በየአድባራቱ እና በየገዳሙ ሲዘዋወር 3 አመት ከ3 ወር ቆይቷል።

_ አሁን ያለበት የመስቀሉ ቦታ አስቀድሞ #ደብረ_ነገስት ይባል ነበር።
ሁለተኛ ጊዜ #ደብረ_ነጎድጓድ
በሶስተኛ ጊዜ #ደብረ_ከርቤ ተብላለች።

_ ስለ እጸ መስቀሉ ስናወራ የመስቀሉ እጽ አመጣጥ በጥቂቱ እንመልከት፥-
#እስክንድር ፡-
በአርመንያ ፡ በሶርያ ፡ በአንጾኪያ ፡ በእነኚህ ሀገራት በአራቱም መዕዘን አንድ አድርጎ የገዛ ንጉስ ነው።

_ ይህ ንጉስ ገነት ገብቶ መኖርን በልቡ አብዞቶ ይመኝ ይፈልግ ነበር። በቤቱም እንደ ንስር ክንፍ ያለው ፈረስ ነበረው በዛም ፈረስ ወደ ገነት ሄደ።
በዛም ፈረሰ መሳይ ንስር ገነት ገብቶ ፈረሱን በገነት ውስጥ ባለው የገነት ፍሬ ዛፍ ላይ አሰረው።
ከዛም መለአኩም ሰይፉን መዘዘበት ፈረሱም ደንግጦ የታሰረበትን እጽ ነቅሎ በመብረር ወደምድር አምቶ ከሰለሞን ደጅ አኖረው።

_ ጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እስኪሰቀል ይህ እጽ 2005 አመታት አስቆጥሯል።

#እሌኒ
_ የእሌኒ የዘር ሀረግ የሆኑት ቅዱሳን ነገስታት ከሆኑት ከንጉስ ኢንዳስ ፡ ንጉስ አልዓዳድ ፡ ንጉስ አግድር ፡ የእሌሊ አባት የሆነው ንጉስ ቆስዮስጥስ የተገኘች ቅድስት ንግስት ናት።

_ አባቷ ንጉስ #ቆስዮስጦስ እሌኒን እና ወድሟን ከመውለዱ አስቀድሞ የእግዚአብሔር መልአክ በራዕይ ተገልጦለት እዲ አለው ካንተ ቡሃላ የሚነግሰው (መክስምያኖስ) አህዛብ ነው ክርስቲያንን የሚጠላ ነውና አንተም ልጅ ውለድ ሁለት ልጅም ትወልዳለክ። ሴት ልጅክም የክርስቶስን ቅዱስ መስቀል የምታወጣ ፡ የምትወልደውም ልጅ ቅድስት ቤተክርስትያንም የሚያንጽ ይሆናል ይነግሳልም። ወንዱም ልጅክ በሰማዕትነት ያልፋል ብሎ ነገረው።

#የእሌኒ_የሂወት_ታሪኳ
_ ባሏ ነጋዴ ነው።#ተርቢኖስ ይባላል። ባሏ ተርቢኖስ ከንግድ እስኪመለስ የአመታት ጊዜ ይፈጅበት ነበር። ቅድስት እሌኒም ባሏ ከንግድ እስኪመለስ ድረስ ከቤቷ ሳትወጣ ትጠብቀው ነበር።

_ተርቢኖስም ከንግድ እየተመለሰ ባለበት ጊዜ ከጓደኛው ጋር እንዲህ ሲሉ ተነጋገሩ የኔ ሚስት በንጽህና ሆና ክብሯን ጠብቃ እየጠበቀችኝ ነው ከኔም ውጪ ምንም አታይም አለው።
የተርቢኖስ ጓደኛም እንዲህ አለው ያንተን ሚስት ሄጄ ምግብ አብርያት በልቼ ፍቃዴንም ፈጽሜ ከመጣው አንተም ከልጅነት እስካአሁን የሰራከውን ስጠኝ ግን ይሄን ካላደረኩኝ የእኔን ከልጅነት እስካሁን የሰራውትን ሁብት ንብረቴን እሰጥካለው አለው።

_ ተርቢኖስም በሚስቴ እተማመናለው ከኔ ውጪ ወንድ አታይም በማለት ነገረው። በተነጋገሩበትም ማስያዣም ተስማሙ።

_ የተርቢኖስም ጓደኛ ወደ እሌኒ ቤት ሄደ ይሄ ሃሳቡ እዲሳካለት አሰበ የእሊኒን አገልጋይ የሆነችውን ሰራተኛ በውርቅ በብር ማስማማት ነበር። ከቤቱም ገብቶ ከእሌኒጋ አብሮ እዲበላ እድታመቻችለት ነገራት። የእሌኒም አገልጋይ የሆነችው ይሄን ለማረግ ብዙ ደከመች ግን አልሆነም እሌኒ ለባሏ የታመነች በወርቅ እና በብር ያልተገዛች ሆና ተገኘች።

_ በዚም ተናዶ የእሌኒን አገልጋይን እዲ አላት የአንገት ሀብሏና እድታመጣለት ነገራት ከዛም አመጣችለት።

_ ወደ ተርቢኖስ ሄዶ በሀሰት ንግግር ከቤቷ ገብቶ አብሯት እደበላና ፍቃዱንም እደፈጸመችለት የአንገት ሀብሏን እደሰጠችው ነገረው። በዚም ነገር ተርቢኖስ እውነት መስሎት በጣም አዘነ ንብረቱንም ሰጠው መራራ እንባም አነባ።

_ ከቤቱም ከገባ ቡሀላ በጣም አዘነ እሌኒም ምን እደሆነ ብትጠይቀው ምንም እንዳልሆነ ነገራት። ከዛም አንድ ነገር አሰበ ወደ እርሷ ቤተሰቦች እዲሄዱ። በዚም ሀሳብ ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ።

_ ወደ መርከቡ ከገቡ ቡሀላ ሰው እዳያይሽ በሳጥን ውስት ሁኚ አላት እሷም አምናው እሺ አለችው። የካደችው መስሎት ስለታየው ሳጥኑን ወደባህሩ ጣለው። አሳነባሪ ዋጠው የመንፈስ ቅዱስም ሀይል እየጠበቃት ወደ #ቁስጥንጥንያ ሀገር ደረሰች።

_ በዚያም ሀገር አሳው ከባህር ዳር አስቀመጣት። ይህም ሳጥን ወደንጉሱ #ቁንስጣ ጋር ይደርሳል። ይህም ንጉስ ሲያያት ደነገጠ በውበቷም ተማረከ ከሁሉም በላይ አከበራት።ከዛም ወደ #ሮሐ ሀገር ወሰዳት በዛም ሀገር በምቾት በተድላ አኖራት።

_ ይሄም ንጉስ ሊያገባት ይፈልጋል። እሷም እንዲህ በማለት መለሰችለት ያንተ ሚስት እንድሆን ከፈልክ በክርስቶስ በድንግል ማርያም እመን ተጠመቅ አለችው። እሱም እደፍቃድስ አላት። እሷም ጡቷን በስለት ወግታ ደሟን በውሃውስጥ ከተተችው በዛም ውሀ እሱንም ቤተሰቦቹን አጠመቀቻቸው።

_ ከዛም በግብር አወቃት ከዛም ታላቅ የሆነውን ንጉስ #ቁስጥንጢኖስን ተወለደ።

_ ንግስት እሌኒም ቅዱስ መስቀሉን ለማግኘት በጣም ትጸልይ ነበር። ከዛም ሊቃውንትን ሰብስባ አማክራ ፈልጋ መስቀሉን ለማግነት ለማውጣት ችላለች።

ከብዙ በጢቂቱ ፡ ብዙ ያጎደልኩት የገደፍኩት አለና እናንተ መጽሀፉን ገዝታቹ ታነቡት ዘንድ እጋብዛለው።

ሚኪያስ ተ/ማርያም
16 - 1 - 2014 ዓ,ም
ምንጭ፡ #ድርሳነ_መስቀል ፡ አሳታሚ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሀይማኖት አንድነት ገዳም

@razielethiopia
@razielethiopia ,,, #ሼር

hace 3 años, 5 meses

ኹላችንም ጌታችን በስሙ ሁለትም ሦስትም ኾነን ለጸሎትና ለመልካም ሥራ ብንሰባሰብ እርሱ በመካከላችን እንደሚገኝ የገባልንን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ /ማቴ.፲፰፥፳/ በጾመ ፍልሰታ ሳምንታት በጌታችን፣ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣ ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን፡፡ በኋላም ሰማያዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንችላለን፡፡

ነገር ግን በሕግ የተከለከለ እስኪመስል ድረስ በዚህ ወቅትም ኾነ በሌላ ጊዜ ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉ ወጣቶች ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይኾኑ ወጣቶችም ጭምር የመቍረብና የመዳን ክርስቲያናዊ መብት እንዳለን በመረዳት ራሳችንን ገዝተን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይገባናል፡፡ አምላካችን በማይታበል ቃሉ “ሥጋዬን የሚበላ፤ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው” በማለት ተናግሯልና /ዮሐ.፮፥፶፬/፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን፡፡
@RAFATOOEL
@RAFATOOEL

hace 3 años, 7 meses
hace 3 años, 7 meses

#የካቲት 12 ፦ አንድ ችግረኛ ሰው ያለ ሥራ ቁጭ ብሎ ቅዱስ ሚካኤል ምግብ
እንዲያመጣለት በመነዝነዝ ያስቸግረው ስለነበረ ቅዱስ ሚካኤልም ወደ
ችግረኛው ሰው በመሄድ ‹‹ወይ እርሻ ኖሮህ አልባረኩልህ፣ወይ ገንዘብ ኖሮክ
ንግድህን አልባረኩልህ ዝም ብለህ ለምን ታስቸግረኛለህ›› ብሎት ወቅሶት
በቅዱስ ሚካኤል ገንዘብ ነግዶ ተአምር የሰራለት ቀን ነው፡፡

#መጋቢት 12 ፦ ኢአማኒ የነበረውን ቂሶንን ወደ ክርስትና የመለሰበት ቀን ነው፡፡

#ሚያዝያ 12 ፦ ነብዩ ኤርሚያስን በአመጸኛው ሴዴቅያስ ከተጣለበት የቆሻሻ
ጉድጓድ ያወጣበት ቀን ነው፡፡

#ግንቦት 12 ፦ ወደ ነብዩ ዕንባቆም ተልኮ ዕንባቆምን በባቢሎን ዳንኤልን
በአንበሳ ጉድጓድ በተጣለበት ጊዜ ምግብ እንዲያደርስለት ከምድረ
ፍልስጥኤም በተአምር ተሸክሞ ፋርስ አውርዶት ዳንኤልን የረዳበት ቀን ነው፡፡

#ሰኔ 12 ፦ ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን የታደገበት ቀን ነው፡፡ ባሕራንንም
የሞቱን ደብዳቤ አጥፍቶ፣በሠርግ ተክቶ ተአምር እንደሰራለት ድርሳኑ
ይነግረናል፡፡

#ሐምሌ 12 ፦ እግዚአብሔር የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስን ጸሎት ሰምቶ ቅዱስ
ሚካኤልን ልኮለት ከሰናክሬም መቅሰፍት ኢየሩሳሌምንና የይሁዳ ሰዎችን
ያዳነበት ቀን ነው፡፡

#ነሐሴ 12 ፦ ንጉሡ ቆስጠንጢኖስን የረዳበት፤አርባ ዘመን ቤተ ክርስትያንን
ሲያቃጥሉ ክርስትያኖችን በእሳት ሲማግዱ፣በሰይፍ ሲያርዱ የነበሩትን
ዲዮቅልጥያኖስንና መክስምያኖስን ከምድረ ገጽ ያጠፋበት ቀን ነው፡፡
ሺህ በክንፉ ሺህ በአክናፉ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ
አቅፎ ደግፎ ከክፍ ነገር ይሰውረን፡፡ የቅድስት አፎሚያ፣የቅዱስ ላሊበላ ጸሎት
በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
ሼር በማድረግ ለወዳጆ በቅዱስ ሚካኤል ስም ይዘክሯቸው፡፡
@razielethiopia
@razielethiopia

hace 3 años, 7 meses

#ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!
የቅድስት አፎሚያ እና የቅዱስ ላሊበላ እረፍት ነው!
በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
@razielethiopia

ሰኔ 12 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ደገኛዋን ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን ተንኮል
የታደገበት ዕለት እንደሆነ ድርሳኑ መዝግቦልናል፡፡
ቅድስት አፎሚያ አስተራኒቆስ የተባለ ደግ ባል ነበራት፡፡ ይህ ሰው ሊሞት ሲል
የቅዱስ ሚካኤልን ስዕል አዘጋጅቶ በመስጠት፤በየወሩ በቅዱስ ሚካኤል ቀን ለድሆች፣ለጦም አዳሪዎች ምጽዋት እንድትሰጥ፤መስጠት ብቻ ሳይሆን ወደ
ፈጣሪዋ አጥብቃ ከመጸለይ እንዳታቋርጥ ነግሯት ያርፋል፡፡
ቅድስት አፎሚያም ይሄንን ርህራሄና ሰብአዊነት የተመላበት በጎ ሥራ አጥብቃ
መስራት ጀመረች፡፡ የበጎ ነገር ጠላት የሆነው ሰይጣን የቸርነት ሥራዋን
ተመልክቶ ወደ ቅድስት አፎሚያ መጣ፡፡ አዛኝ በመምሰልም ‹‹ለምን ገንዘብሽን
ታባክኛለሽ፤ይልቁንስ ገንዘብሽ ከማለቁ በፊት ባል አግብተሽ አትኖሪም ባልሽ
እንደሆነ ጸድቋል ምጽዋት አያስፈልገውም›› አላት፡፡ ሰይጣን የአስተራኖቆስን መጽደቅ የተናገረው አፎሚያን ለማስደሰት ሳይሆን
እንደ አዳምና ሔዋን ለማሳት ነው፡፡ ዘፍ 3÷1-8

ቅድስት አፎሚያም ‹‹ሌላ ባል ላላገባ ከፈጣሪዬ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ››
አለችው፡፡ ሰይጣንም የሚያስትበት የጥፋትና የተንኮል መንገድ ብዙ ነውና
መነኩሴ በመምሰል ብዙ ቢዘበዝባትም አፎምያ ግን ለሥጋዊ ምክሩ ቦታ
ሳትሰጠው እንቢኝ አለችው፡፡
ሰይጣንም በዚህ ሳያበቃ ያስትልኛል፣አፎሚያን ያሳምንልኛል ያለውን ሐሳብ እያመጣ ቢነግራትም በእንቢታዋ ጸናች፡፡ ለሰይጣን ውሸት የየዕለት ሥራው ስለሆነ ይባስ ብሎ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ እርፍ አለው፡፡ ሰይጣን በአምሳለ መልአክ ሰውን እንደሚያስት ያወቀው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰይጣን ራሱን የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል›› ብሎ ነግሮናል፡፡ 2ኛ ቆሮ 11÷14

ስለዚህ አፎምያ በቅዱስ ሚካኤል ተመስሎ ቢነግራትም አልቀበልም አለችው፡፡ ወዳጆቼ እስቲ እራሳችንን እናስብ ስለ እውነት እኛ ብንሆን ይህንን ፈተና እናልፍ ነበር? ይህ የአፎሚያን የእምነት ጥበብ የሚያሳይ ነው፡፡ ሰይጣንም አሉኝ የሚለውን ሰይጣናዊ ማሳመኛ ጥበብ ተጠቀመ፡፡ አፎሚያም
ምንም ይበል ምንም አለተቀበለችውም፡፡ ምክንያቷ ደግሞ ንግግሩና ገጽታው
ስላልተካከለ፡፡ በአፎምያ መንፈሳዊ ቆራጥነት የተበሳጨው ሰይጣንም ዓይኑን አፍጥጦ፣ጥርሱን አግጥጦ አንቆ ሊገላት ሲል ቅዱስ ሚካኤል ብርሃናዊ
ክንፉን እያማታ በቅጽበት ደረሰላት ከሰይጣንም እጅ አዳናት፡፡ ቅዱስ
ሚካኤልም ስለ እረፍቷ ‹‹ብጽዕት አፎሚያ ሆይ ሄደሽ የቤትሽን ሥራ
አዘጋጂ፣ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለሽ፣እነሆ እግዚአብሔር ዓይን
ያላየውን፣ጆሮም ያልሰማውን፣በሰው ልብ ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻል›› ብሎ
የምስራቹን ነግራት ከእሷ ተሰወረ፡፡
ቅድስት አፎምያም የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን ዝግጅት ከፈጸመች በኃላ ወደ
ኤጲስቆጶሱና ወደ ካህናቱ መልዕክት ላከች እነሱም መጡ፡፡ ለእነሱም ቀሪ
ገንዘብዋን ለድሆች ለጦም አዳሪዎች ይሰጥዋቸውም ዘንድ አስረከበቻቸው፡፡
ከዚህ በኃላ ተነስታ ጸለየች፣የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልንም ሥዕል
አንስታ አቅፋ ሳመችው/አፎሚያ ለሰይጣን ይህንን ስዕል ስታሳየው ነው አሳች መልኩ ወደ ሰይጣንነት የተቀጠረው/ ያን ጊዜም ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም የከበረች ነፍሷን በብርሃናዊ ክንፉ አቅፎ ደግፎ የፈጣሪውን መንግስት እንድትወርስ አድርጓታል፡፡ ከቅድስት አፎምያ ሁለት ነገር እንማራለን፡፡ አንደኛው ጥቅም አዘል ፈተናን አልፋ ሰይጣንን ድል መንሳትዋ ሲሆን ሁለተኛው አፎምያ ጽድቅ ሰርታ የሥጋ
ፈተናዋን ድል ነስታ፣ሰይጣንን ማሸነፍ የቻለችው ጫካ ገብታ ሳይሆን በዓለም
ሆና ነው፡፡ ስለዚህ ጽድቅ ሰርቶ ለመጽደቅ ሥራ እንጂ ቦታ እንደማይወስነው
ታሪክዋ አስተማሪ ነው፡፡

፨ ሰኔ 12 ቀን እረፍቱ #ለቅዱስ_ላሊበላ ፨ቅዱስ ላሊበላ በነገሠ ጊዜ እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ ድሆችን ሳይንቅ፣በአገዛዙ
ሰዎችን ሳያስጨንቅ የኖረ ጻድቅ ነው፡፡ ጌታችን ቅዱስ ላሊበላን የፍቅሩን ጽናት
በማየት መልአኩን ላከለት፡፡ መልአኩም ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጠቀው፡፡
በዚያም ቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደሚያንጽ ጥበብን ገለጠለት፡፡
ቅዱስ ላሊበላም ሥጋ የለበሱ ሰዎች ሳይሆኑ ቅዱሳን መላእክቶች በስውር
እየተራዱት እነዛን አስደናቂ፣ለውጭ ጥበበኞች አጨቃጫቂ የሆኑትን ፍልፍል
አብያተ ክርስትያናትን አንጿል፡፡
ጌታችንም ሰኔ 12 ቀን በብርሃን ሰረገላ ተቀምጦ፣የሚያስፈራ መብረቅን
ተጎናጽፎ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ ወደ ቅዱስ ላሊበላ መጣ፡፡ ጌታም
‹‹ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁንልህ፡፡ እኔ በማይታበል ቃሌ
እነግርሃለሁ፤ማደርያህ በክብር ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ይሁን፡፡ በጸሎትህና
በቃል ኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ
ይሆንለታል፡፡

ወደ ቤተ መቅደስህ የሔደ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ እንደ ሄደ
ይሆንለታል፡፡ መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደተሳለመ
ይሆንለታል፡፡ በየወሩ የተራቡትን እያበላ፣የተጠሙትን እያጠጣ መታሰብያህን ለሚያደርግ እኔ የተሰወረ መና እመግበዋለሁ፤የህይወትንም ጽዋንም አጠጣዋለሁ፡፡ በመታሰብያህ ቀን ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋሁ፤በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ
ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ፡፡፡ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይህን የማይታበል ቃል የተናገርኩ የህያው እግዚአብሔር ልጅ እኔ ኢየሱስ ነኝ›› አለው፡፡

ቅዱስ ላሊበላም ይህንን ቃል ኪዳን ስለሰጠውና ስላጸናለት ጌታችንን
እያመሰገነ እግሩ ላይ ወድቆ አመሰገነው፡፡ ሰኔ 12 ቀንም አረፈ፡፡ ቅድስት ነፍሱንም ቅዱሳን መላእክት ይዘው የዘላለም ማረፍያው አስገቡት፡፡

፨ የቅዱስ ሚካኤል የወር በዓላት ከነምክንያት
#መስከረም 12 ፦ ቅዱስ ፋሲለደስን በመከራው ሰዓት የረዳበት እና
የሰማዕትነት ተጋድሎውን ከፍጻሜ እንዲያደርስ ከጎኑ ተገኝቶ ያጸናበት

#ጥቅምት 12 ፦ ነብዩ ሳሙኤል ዳዊትን ቅብዐ መንግስት እንዲቀባው የነገረበት
ቀን ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ከቅዱሳን መላእክት ረድኤት በደንብ ስለተጠቀመ
ክብራቸውን በመዝሙሩ በደንብ መዝግቧል፡፡

#ህዳር 12 ፦ የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ በዚህ ቀን እግዚአብሔር
የመላእክት አለቃ አደርጎ ሾመው፡፡ የመላእክት ሹመት እንደ ሰው በተጽእኖ
አይደለም፡፡ ሰው በሰው ላይ የሚሾመው ለመገልገል ነው፡፡ የመላእክት ሹመት
ግን ለማገልገል ነው፡፡ እንደ ሰው አንዱ መልአክ አንዱን መልአክ
አያገለግልም፡፡ አገልግሎታቸው እግዚአብሔርንና ሰውን ነው፡፡
በዚህም ቀን ለሰው ልጆች ከፈጣሪው ምህረት የሚለምንበት እና በቃል ኪዳኑ
ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣበት ቀን ነው፡፡ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በታላቅ ክብር
በንጉሥ ጭፍራ አምሳል የታየበት ቀንም ነው፡፡

#ታህሳስ 12 ፦ ዱራታኦስና ቴዎብስትያን የረዳበት ቀን ነው፡፡

#ጥር 12 ፦ ያዕቆብን ከኤሳው፣ተላፊኖስን ከአመጸኛው ያዳነበት ቀን ነው፡፡

hace 3 años, 7 meses
[#ግንቦት](?q=%23%E1%8C%8D%E1%8A%95%E1%89%A6%E1%89%B5) 26 ጻድቁ አባታችን የተወለዱበት ቀን …

#ግንቦት 26 ጻድቁ አባታችን የተወለዱበት ቀን ነው።
በረከታቸው ፡ ጸሎታቸው ፡ ቃልኪዳናቸው ፡ አማላጅነታቸው አይለየን።

ሀገራችንን ኢትዮጵያን በጸሎታቸው ይጠብቁልን።
@razielethiopia

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana