Kesis Getnet Aytenew

Description
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month ago

Last updated 4 weeks, 1 day ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 day, 4 hours ago

5 months, 1 week ago

እንኳን አደረሳችሁ! <ነሐሴ ፲፫/13>
[በዓለ ደብረ ታቦር ወልደቱ ለሙሴ ወብንያም ወጋልዮን መስተጋድል]

=> የዕለቱ ግጻዌ

ምስባክ ዘነግህ
ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል።
ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን።
ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ።
ትርጉም፦
የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው።
የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?
እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ ይህን ተራራ ወደደው።
(መዝ ፷፯ : ፲፭ - ፲፮ /67:15-16)

  • ወንጌል ዘነግህ
    የማቴዎስ ወንጌል ፲፯ : ፩ - ፲፬ /17:1-14

    ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።

    በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።

    እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

    ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡— ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ፡ አለ።

    እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፡— በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፡ የሚል ድምፅ መጣ።

    ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

    ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡— ተነሡ አትፍሩም፡ አላቸው።

    ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

    ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፡— የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፡ ብሎ አዘዛቸው።

    ደቀ መዛሙርቱም፡— እንግዲህ ጻፎች፡— ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።
    ፲፩
    ኢየሱስም መልሶ፡— ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
    ፲፪
    ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው፡ አላቸው።
    ፲፫
    በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።

  • መልእክታት:-

  • ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፳፫ - ፴ /11:23-30
  • ፪ኛ ጴጥሮስ ፩ : ፲፭ -ፍጻሜ /1:15-ፍጻሜ
  • ግብረ ሐዋርያት ፯ : ፵፬ - ፶፩ /7:44-51

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ።
መዝራእትከ ምስለ ኃይል።
ትርጉም፦
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል።
ስምህንም ያመሰግናሉ።
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤
(መዝ ፹፰ : ፲፪ - ፲፫/88:12-13)

  • ወንጌል ዘቅዳሴ
    የሉቃስ ወንጌል ፱ : ፳፰ - ፴፰ /9:28-38
    ፳፰
    ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
    ፳፱
    ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

    እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
    ፴፩
    በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
    ፴፪
    ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
    ፴፫
    ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
    ፴፬
    ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
    ፴፭
    ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
    ፴፮
    ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ። ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
    ፴፯
    በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ / ዘዲዮስቆሮስ {በዕዝል ዜማ ቀድስ}

በቅዱሱ ተራራ መለኮታዊ ክብሩን የገለጸ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ዕውቀቱን ጥበቡን ማስተዋሉን ያድለን። በመንግሥቱም ያስበን። የክብርት እናቱ ምልጃም አይለየን።

፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠
❀❀❀✿❀❀✿ ❀❀❀
________
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

5 months, 2 weeks ago

☞ ነሐሴ ፫ (ሦስት)
[ስምዖን ዘዐምድ ወቅድስት ሶፍያ]

✞ መልእክታት:-
፩. ፩ኛ ወደ ተሰሎንቄ ፫ : ፩ - ፍጻሜ
፪. ፩ኛ ጴጥሮስ ፫ : ፲ - ፲፭
፫. የሐዋርያት ሥራ ፲፬ : ፳ - ፍጻሜ

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ።
ወለገጽኪይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር።
ኲሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን።
ትርጉም:-
የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል።
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትህ ይማለላሉ።
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤
(መዝ ፵፬ : ፲፪-፲፫ /44:12-13)

✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፲፰ : ፱ - ፲፰ /18:9-18

ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥

እንዲህ ሲል። ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።
፲፩
ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
፲፪
በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።
፲፫
ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።
፲፬
እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።
፲፭
እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ደግሞ ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ዐይተው ገሠጹአቸው።
፲፮
ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ። ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉአቸው አትከልክሉአቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
፲፯
እውነት እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አለ።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) ~ (በግዕዝ ዜማ)
...................................................
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

5 months, 2 weeks ago

• ነሐሴ ፪ (ሁለት) •
[አትናስያ ቅድስት ወደሚና ሰማዕት ወአኃዊሁ ወኢዮጰራቅስያ ብፅዕት]

  • መልእክታት
    ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፪ : ፰ - ፲፭ /2:8-15/
    ፩ኛ ጴጥሮስ ፫ : ፩ - ፯ /3:1-7/
    የሐዋ/ሥራ ፲፮ : ፲፫ - ፲፱ /16:13-19/

  • ምስባክ ዘቅዳሴ
    ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ።
    ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ።
    ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት።
    ትርጉም:-
    በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፥
    ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤
    በደስታና በሐሴት ይወስዱአቸዋል፥
    (መዝ ፵፭ : ፲፬ - ፲፭)

.
+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ፰ : ፬ - ፲፪ /8:4-12

መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች።

ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት።

የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤

መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።

ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት።
፲፩
እርስዋም። ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም። እኔም አልፈርድብሽም፤ ሒጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።
፲፪
ደግሞም ኢየሱስ። እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ (ጎሥዐ) ~ (በግዕዝ ዜማ)
................................................
+ ቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/kesisgetnetaytenew

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month ago

Last updated 4 weeks, 1 day ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 day, 4 hours ago