ናሁ ሰማን(Nahu seman)

Description
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን

🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers የንግስ ዝማሬ ማግኝት ከፈለጉ የyoutube አካውንታንት ይቀላቀሉ።
https://youtube.com/@nahu-seman-zema25?s
በማድረግ ይጎብኙ።
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago
4 months, 1 week ago

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞

✞✞✞ እንኩዋን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+" መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "+

=>ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው
የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ
ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ
ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

+ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::

+በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ
6,666 ገረፉት::

¤ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው
ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
¤6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው
ሰቀሉት::

+7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
¤ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን
ተናገረ::
¤ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን
ከቅዱስ ሥጋው ለየ::

+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ
ፈታ::

¤11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና
ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ::
ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት
አንስት በዋይታ ዋሉ::

+ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27
ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት
አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት
27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ
በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

+ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ
አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን
እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ
ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት
27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ
ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም
17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::

+"+ ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ +"+

=>በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ
መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ
ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው
ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ:
መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ
ናቸው::

+ቅዱሱ የ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ
ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ
ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው
አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ
ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: (መዝ. 91)

+ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ
ሙሐዘ ማይ" (መዝ. 1:3) እንዳለው ቅዱስ መቃርስ
እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ
በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው
እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::

+"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም
ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው
የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ
ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ
ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል
እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::

+ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው
ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ
ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው
በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ
ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው:
ይለምንላቸውም ነበር::

+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን)
636 ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ
ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም"
በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ
ደሴት አሳደዷቸው::

+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ
መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር
ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን
ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን
አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ
ተአምራትን ሠርቷል::

+አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው
እንዲህ ይጸልዩ ነበር:-
"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" (አርኬ ዘጥቅምት 27)

+" አቡነ መብዓ ጽዮን "+

=>ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ
አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን
በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን በሽዋ (ሻሞ) አካባቢ የተነሱ
ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን
ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::

+በ3 ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ
ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም
ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው:
ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::

ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ
ይዘረዝረዋል!

+በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን 13 ሕማማት ለማዘከር
ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ
ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ::
በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን
ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት (ኮሶ) ሞልተው ይጠጣሉ::

+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ27 ስለ መድኃኔ
ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና
ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ
ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ
ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም
(በትረ ማርያም)" ይባላሉ::

+ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን
ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር::
ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ
በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን
ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ
ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::

+"+ አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ +"+

=>ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም
ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ
ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ
ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም
"ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ
ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ
ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር
ተገናኙ::

4 months, 1 week ago

? በብርሀን_ፀዳል ?

በብርሀን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የፅጌውን ዜማ ስዘምር በደስታ
በምስጋናሽ ምድር ሲሰማኝ እርካታ(፪×)

እምባዬ ሲቀዳ ናፋቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ 
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼዉ
የሌሊቱ ህልሜ የቀን ምኞቴ ነዉ(፪×)

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

እሩሩ ነሽና የህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህልናዬ ረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይትጋ(፪×)

✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥

ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርጋ
የምስጋናሽ ብእር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይፃፋብኝ በልዩ ህብር(፪×)

✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
    ✞ @Nahuseman256
    ✞ @Nahuseman256 ✞        
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯

4 months, 1 week ago

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

=>+"+ እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ሰማዕት አቡነ አቢብ": "አባ ዕብሎይ" እና "ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+" አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) "+

=>ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን!

¤እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል!

¤ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ - የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::

¤ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::

¤እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::

¤አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ!

¤ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ!

¤ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ!

¤የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::

+"+ ልደት +"+

=>አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::

+በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"

+"+ ጥምቀት +"+

=>ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ 1 ዓመት ቆየ::
ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው::

+ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::

+"+ ሰማዕትነት +"+

=>የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ10 ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ10 ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::

+በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ 18 ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::

+"+ ገዳማዊ ሕይወት +"+

=>ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::

+ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል::
ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::

+"+ ተጋድሎ +"+

=>አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::

+በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::

+የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ (ሃቢብ) ይሁን" አለው::

"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ:
ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::

+" ዕረፍት "+

=>አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::

+ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::

+"+ ታላቁ አባ ዕብሎይ +"+

=>ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት "ርዕሰ ገዳማውያን" ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ በመሆኑ በዕለተ ዕረፍቱ (የካቲት 3 ቀን) እንመለከተዋለንና የዚያ ሰው ይበለን::

+"+ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት +"+

=>ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::

+ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ እንኩዋን የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ - የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78:3)

+እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::

+በወቅቱ የክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር::
በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::

4 months, 2 weeks ago
4 months, 2 weeks ago

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

+" ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ንጉሥ "+

✞✞✞ የሰው ልጅ 'ንጉሥ' ተብሎ 'ቅዱስ' መባል ግን ምን ይደንቅ?! ይህ ታላቅ ኢትዮዽያዊ መሪ ንጉሥ ሲሆን: እንደ ደናግል ድንግል: እንደ ባሕታውያን ገዳማዊ: እንደ ቀስውስት ካህን: እንደ ሐዋርያት ሰባኪ ሆኖ መገኘቱ ይደንቃል::

+የሚያሳዝነው ይህንን እንቁ ንጉሣችን ብዙ ኢትዮዽያውያን መዘንጋታችን ብቻ ነው:: የላስታ አካባቢ እጅግ የታደለችና የተቀደሰች ናት:: እንደ ሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ሁሉ እሷም መካነ ቅዱሳን ናትና::

+ቅዱስ ይምርሐ የዘር ሐረጉ ከዛግዌ ነገሥታት ሥር ሲሆን አባቱ ግርማ ስዩም ይባላል:: ይኸውም በመጀመሪያው ሺህ ዓመት (Millenium) መጠናቀቂያ ላይ ነግሶ የነበረ ነው:: ዣን ስዩም
(የላሊበላ አባት): ጠጠውድም (ንጉሡ) እና ግርማ ስዩም ወንድማማቾች ናቸው::

+ቅዱሱ ሲወለድ አባቱ በሕይወት አልነበረም:: እናቱና የወቅቱ አባቶች "ይምርሐነ ክርስቶስ-ክርስቶስ ይምራን" አሉት:: ገና ከሕጻንነቱ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ረቡዕና ዓርብ ቀን እስከ 9 ሰዓት ድረስ የእናቱን ጡት አይቀምስም ነበር:: እናቱ ግን ባለመረዳት ትጨነቅ ነበር::

+የወቅቱ ንጉሥ ጠጠውድም "ከእኔ ቀጥሎ የሚነግሠውን ባወኩት" እያለ ሲመኝ በሕልሙ "ሕጻኑ ይምርሐ ነው" የሚል በማየቱ ሕጻኑን አስመጣው:: ከደም ግባቱ የተነሳም ቅንዓት አድሮበት አማካሪዎቹን "ምን ላድርገው?" አላቸው::

+እነርሱም "ብትገድለው እግዚአብሔር በደሙ ይጠይቅሃል:: ግን እንዳይወርስብህ ከፈለክ እረኛ አድርገው" አሉት:: (የዋሃን! ቅዱስ ዳዊት ከእረኝነት መጠራቱን ዘንግተውታል) ከ7 ቀናት በኋላ ግን መጥተው "ንጉሥ ሆይ! ፈጣሪ ካለ የሚቀር ነገር የለምና በቃ ዝም ብለህ ግደለው" አሉት::

+በዚያች ሰዓት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ እናቱን "ይምርሐን ስጭኝ" አላት:: እናት ናትና ጨነቃት:: መልአኩ ግን እንደሚጠብቀው ቃል ገብቶላት ከላስታ ነጥቆ ኢየሩሳሌም አደረሰው::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም ለዓመታት ተምሮ ዲቁናን ተቀበለ:: በኢየሩሳሌም አካባቢም በጾምና በጸሎት ተወስኖ ፈጣሪውን እያገለገለና ወንጌልን እየሰበከ የወጣትነት እድሜውን ገፋ::

+አንድ ቀን ግን መድኃኒታችን ተገልጦ "ወዳጄ ይምርሐ! ሚስት አግብተሀ: ቅስና ተቀብለህ አገልግለኝ" አለው:: ቅዱሱ ይህንን ሲሰማ አዝኖ "ጌታየ! የእኔስ ፈቃዴ በድንግልና አገለግልህ ዘንድ ነው" አለው:: ጌታችንም "ግዴለህም! ሁሉም አይቀርብህም" ብሎ አንዲት ሕዝባ የምትባል ደግ እሥራኤላዊት ጠቆመው::

+ቅዱስ ይምርሐም ቅድስት ሕዝባን በተክሊል አግብቶ: ቅስናን ተቀበለ:: ግሩም የሚያሰኘው ግን 2ቱ ቅዱሳን ከ40 ዓመታት በላይ በትዳርም: በድንግልናም መኖራቸው ነው:: "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" ይል የለ ቅዱስ መጽሐፍ!

+ቅዱሳኑ ወዲያው ለአገልግሎት ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያ ለጥቂት ዓመታት እንደቆዩ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ወደ ኢትይዽያ መመለስ ፈለገ:: አንድ ቀን ሕዝቡ ተሰብስበው ጸሎተ ኪዳንን ሲመራ "እግዚአብሔር አብ ወሐቤ ብርሃን-ብርሃንን የምትሰጥ እግዚአብሔር አብ" ከሚል ሲደርስ ወደ ሰማይጮኸ::

+ከሰማይም "አቤት ልጄ ሆይ!" የሚል መልስ መጣለት:: ይምርሐም "ምነው ጌታየ በሰው ሃገር ረሳኸኝ?" ቢለው "አልረሳውህም:: ይልቁኑ ሊገድልህ የሚፈልግህ ንጉሥ ሙቷልና ሒደህ ንገሥ" ሲል አዘዘው::

+ቅዱሱም ሚስቱን ሕዝባን ይዞ ላስታ ሲደርስ ሕዝቡ በዕልልታ ተቀብሎ ወዲያው አነገሠው:: በዚያም ለ15 ዓመታት ቅዱስ ሩፋኤል እየተራዳው: ሕብስትና ጽዋዕ ከሰማይ እየወረደለት ቀድሷል:: ሃገሪቱንም መርቷል::

+አንድ ቀን ግን ክፉ መካሪዎች "ተጨማሪ ሚስት አግባ" ቢሉት ተቆጣቸው:: በኋላ ደግሞ 'ለምን ተቆጣሁ' ብሎ አዘነ:: ስለዚህም ሃሳቡ ሰማያዊው ስጦታ ቀረበት::

+እያለቀሰ ጌታን ቢማጸን ጌታችን "ስላሰብከው ክፉ ሃሳብ (ለምን ተቆጣሁ ማለቱ ወደ ምክራቸው ማዘንበሉን ያሳይነበርና) ይቅር ብየሃለሁ:: ነገር ግን እኔ ወደ ማሳይህ ቦታ ካልሔድክ 2ኛ አይወርድልህም" አለው::

+ቅዱሱ ለጊዜው ትንሽ ቢከራከርም "እሺ" ብሎ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ዛሬ ወደ ምናውቀው አካባቢው ሔደ:: በዚያም አራዊትን በጸሎቱ አድክሞ: መሠሪዎችን አስተምሮ: ሕዝቡንም አሳምኖ አጠመቃቸው::

+ጌታም "ከኢየሩሳሌም በደመና እየጫንክ በዚህ ባሕር ላይ ቤቴን ሥራልኝ" አለው:: ቅዱስ ይምርሐም መስከረም 13 ቀን (በበዓለ ባስልዮስ) ጀምሮ ሰኔ 20 (በበዓለ ሕንጸታ) ፈጸመና ታቦተ ገብርኤልን ሰኔ 21 ቀን ቀደሰው::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ግን በዚያ ቦታ እየቀደሰ ለ25 ዓመታት ሃገሪቱን አስተዳደረ:: አንድ ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ለንጉሡ ከሰማይ ሕብስትና ጽዋዕ ሲያወርድለት 1 ባሕታዊ አይቶ "ለምን?" ብሎ ተቆጣ:: መልአኩ ግን የንጉሡን ክብር ነግሮ "እየዞርክ ስበክ" ብሎታል::

+በዚያ ባሕታዊ ስብከትም ከመላው ዓለም ብዙ ሺህ ሰወች መጥተው ቅዱስ ይምርሐን "ቀድሰህ አቁርበን?" ብለውለምነውታል:: ቅዱሱም ሲያቆርባቸው በመምሸቱ ጸሐይን አቁሟታል::

+ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ እንዲህ ባለ ጣዕመ ሕይወት ኑሮ: ለ40 ዓመታት ሃገራችንን አስተዳድሮ ጥቅምት 19 ቀን ዐርፎ በዚያው ሥፍራ ተቀብሯል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን: ደጅህን የረገጠውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::

+" ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም "+

✞✞✞ በምድረ ግብጽ በዘመነ ጻድቃን የተነሳው ታላቁ አባ ዮሐንስ "ሐዋርያዊ ጻድቅ" ይባላል:: ወላጆቹ ደጋግ: የተወለደው በጾምና ጸሎት: ያደገውም በሥርዓት ነው:: በወጣትነቱ ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ የአባ ስምዖን ደቀ መዝሙር ሆኗል::

+በዚያም በፍጹም ትሕርምት ሲኖር ባልንጀሮቹ ይጠፉበታል:: እነሱን ሊፈልግ ሲሔድ ግን አረማውያን ይዘው አሠሩት: አሰቃዩት:: መንገድ ላይ ውሃ ጠምቷቸው ሲጨነቁ "ውሃ ባጠጣችሁሳ?" አላቸው:: "እንለቅህ ነበር" አሉት::

+ጸልዮ: ውሃ አፍልቆ ቢያጠጣቸው "አንተማ ታስፈልጋለህና አንለቅህም" አሉት:: ወስደውም ጸይለም በምትባል ሃገር ለባርነት ሸጡት:: በዚያ ሲያሰቃዩት ተአምራትን አድርጐ በክርስቶስ አሳምኗቸዋል::

+ወደ ጐረቤት ሃገር ሔዶም ዛፍ ሲያመልኩ አገኛቸው:: "ወደ ክርስቶስ ተመለሱ" አላቸው:: "እንቢ" ሲሉት ምሳር (መጥረቢያ) ይዞ: ወደ ዱሩ ውስጥ ገብቶ ጸለየና ምሳሩን አነሳ::

+"በስመ ሥላሴ እገዝመክሙ" ብሎ ቢቃጣቸው አጋንንት የሠፈሩባቸው 10,000 ዛፎች ባንዴ ወደቁ:: በዚህ ምክንያትም 400,000 ሰዎች አምነው ተጠምቀዋል:: ወደ ሌላ ሃገር ሒዶም ስቃይን ታግሦ: ተአምራትን ሠርቶ ብዙዎችን አሳምኗል:: በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::

✞✞✞ አምላከ ይምርሐ ደጉን መሪ: አምላከ ዮሐንስ ቸሩን አስተማሪ ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

+ጥቅምት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

4 months, 2 weeks ago
4 months, 2 weeks ago
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago