አስትሮኖሚ ኢትዮጵያ 📡

Description
ስለ ዩኒቨርሳችን መረጃ ያገኛሉ
በተጨማራም የምትፋልጉትን ጥያቄ comment
ላይ ፃፉልኝ የyoutube ቻናላችንን በመቀላቀል በቂ እውቀት ያግኙ
የ መወያያ (group) link👉https://t.me/Astronomy_ethiopia_1

👇👇👇
YouTube channel https://youtube.com/channel/UCu7s3bTjiltwrnHvAZ6UK5w

Creator @tdokit
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

9 months, 3 weeks ago

?በምድር ላይ ሁሉም ሰው የማይሞት ወይም ለዘለዓለም የሚኖር ቢሆን ምን ይፈጠራል??

?ብዙዎቻችን ምናለ ዘለአለም በኖርን ብለን እንመኛለን ነገር ግን ዘለአለም የምንኖር ቢሆን ምን እንደምፈጠር አናውቅም።
ይሄን ጥያቄ በሁለት ሁኔታዎች ከፋፍለን እንመልከት አንደኛው በእኛ (እንደግለሰብ) ዘለአለም በምድር ላይ ብንኖር ምን እንሆናለን? ሁለተኛው ደግሞ የአለም ህዝብ ሁሉ ዘላለም ሲኖር ምን አይነት ችግር ምድርን ያስጨንቃታል?

?በቅድሚያ በየግለሰቡ ላይ የሚፈጠረውን እንይ:-
በርግጥ አእምሯችን ኃይለኛ ነው, ነገር ግን ገደብ የለሽ የማከማቻ ቦታ የለውም. ለምሳሌ የ40,000 ዓመታት ዋጋ ያለው መረጃ እንዲያስታውስ ብናስገድደው ምን ይፈጠራል
?

?የተፈጠርነው በዛ ቢባል ወደ 100 ዓመት ገደማ ብቻ እንድንኖር ስለሆነ፣ ቢበዛ ፣ አእምሯችን 300 አመት አከባቢ ስሞላን አዳዲስ መረጃዎችን ማከማቸት ያቆማል፤እንዲሁም የረጅም ጊዜ ትውስታዎችን መፍጠር አይችልም። ለምሳሌ የ1ሚሊየነኛ አመትህን ስታከብር የሚኖርህ ትውስታ የ100 ምናምን አመት ወጣት እያለህ ያሳለፍከው ነገር ብቻ ይሆናል ማለትም ከ 50 ሺህ አመት በፊት ልጅ ወልደህ ከነበረ ምኑንም አታስታውሰውም ወይም ለመቶ ሺህ አመታት አብራህ የኖረችውን አጋርህ ስም ሁላ አታስታውስም።

?በተጨማሪም በዚህ የዘለአለም ኑሮህ ትልቅ ድብርት ውስጥ ትገባለህ፣  አዲስ መጽሐፍ ማንበብ ወይም ወደ አዲስ ቦታ መጓዝ ፣አለም ላይ አሉ የተባሉ ምግቦችን መቅመስ፣ የማልሞት ቢሆን አደርገው ነበር የምትሉት ነገር ሁሉ፣ በፓራሹት ከሰማይ መውረድ፣ ትልልቅ ባህሮችን መዋኘት ፣ረጃጅም ወንዞችን መቅዘፍ፣እኚህን ሁሉ እልፍ ጊዜ ብታደርጉ በመጨረሻ ፍላጎቶታችሁ ያልቃል። እያንዳንዱ መጽሐፍ ያነበባችሁት፣ እያንዳንዱ አዲስ ቦታ ቀደም ብላችሁ የጎበኛቹት ፤ሁሉም ነገር አሰልቺና ድግግሞሽ ይሆንባችኋል። ስለዚህ ማለቂያ የሌለው ዘላለማዊ ህይወት ተፈቅዶላችሁ ግን ፈገግ የምትሉት ለጥቂት አመታት ብቻ ይሆናል።

?እስኪ አሁን በአለም ደረጃ ምን እንደሚፈጠር እንይ:-

?የማንሞት ብንሆን እንኳ ስለምንዋለድ ቁጥራችን እየጨመረ ይሄዳል፤ ምድር ደግሞ ወደየትም አትሰፋም፤ ስለዚህ እኛ ነባር ሰዎችን ሞተን ለአዳዲስ ተወላጆች ቦታ ካለቀቅን የሰው ልጅ እጅግ በጣም በዝቶ፣ አይደለም የምንጋደምበት የምንቆምበት ቦታ እናጣለን እንዲሁም በዚህ የዘላለማዊነት እሳቤያችን ምድር ላይ ለመኖር ኦክሲጂን የሚያስፈልገን ከሆነ አሱም ከምድር ከባቢ አየር ላይ ሙሉበሙሉ ያልቃል ምክንያቱም ከመጠን በላይ የበዛው ህዝብ የሚያወጣው የተቃጠለ አየር ሚዛኑን ይደፋል፤ ስለዚህ የመኖር ተስፋችን ያከትማል፤ ይሄን እንግዲህ አዳዲስ ልጆችን ባለመውለድ ልታስቆሙት ትችሉ ይሆናል ነገር ግን የማይሞትን ሰው እንዴት ብላችሁ ነው ይህን አድርግ ይህንን አታድርግ ብላቹ የምትቆጣጠሩት? የሰው ልጅ እንዲሁም ሟች ሆኖ እንኳን አስቸጋሪ ነው።ስለዚህ ዘለአለማዊነት የሚለው እሳቤ በዚህ ምድር ላይ የማይታሰብ ወይም የእብደት ሀሳብ ነው።ለነገሩ ካሰብንበት እኮ ህይወትን ጣዕም የሰጣት ሟች መሆናችን ነው።"ዘለአለም የምንኖር ከሆነ ለምን ነገ ጠዋት ከእንቅልፍ እንነሳለን ? ምክንያቱም ሁሌም "ነገ" ይኖረናል" Neil DeGrasse።ባጠቃላይ ህይወት የምትባለው ነገር ትርጉም ታጣለች እናም አሁን ዘላለማዊነትን የምንመኘውን ያክል ሞትን እንመኛለን።

(የOhio ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ተመራማሪ የሆነው ማርከስ ጄዳልድ መላምት

ሀሳባችዉን በ reaction ግለፁ!?

@universeone123
@universeone123
@universeone123

10 months, 1 week ago

"???"

በ1996 አ.ም ጂም ሱልቪያን የተባለ ሙዚቀኛ " UFO " የተሰኘ አልበም ለቆ ነበር። ታዲያ ይሄ የተለቀቀው አልበም የሚያጠነጥነው ቤተሰብን ስለመተው ፣ ሰዎች በባእዳን አካላት ( Aliens ) ስለሚታገቱበት ሁኔታ በተጨማሪም ደግሞ በርካታ እንግዳ የሆኑ ግጥሞችን ያካተተ ነበር ። የሚገርመው ነገር አልበሙ ከወጣ ከ 6 አመት በኋላ የሙዚቀኛው ዱካ ጠፋ ስለሱ የተገኘ ነገር ቢኖር በበረሀ መንገድ ላይ የተተወው መኪናው ብቻ ነው የተገኘው ማስረጃ ::

1 year, 4 months ago

COSMOLOGY ስነ ትዕይንተ አለም

" እውቀት ያሰፋል እንጂ አያጠብም፤ ራስህ ወደ ጥፋት ጎዳና ካልመራኸው በስተቀር "

በፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ የጊዜን አጀማመር የሚያጠናው ኮስሞሎጂስት ፓውል ስታይንሃርት "I think of cosmology as one of the oldest subjects of human interest but as one of the newest sciences" ሲል በአሁን ጊዜ በዘመናዊ ሳይንስ ይጠና እንጅ በጥንቱ አለም የማጥናት ፍላጎት እንደነበራቸው እና እንደሞከሩ ይገልፃል። በጥንቱ አለም የነበሩት ያልተማሩ የሳይንስ ሊቃውንት ሲናገሩ ከሀይማኖት ጋር አያይዘው ነበር።

◈ Physical cosmology

◈ Religious cosmology

◈ Metaphysical cosmology

◈ Esoteric cosmology
እያሉ ከፋፍለዋቸዋል።

በአሁኑ ጊዜ በደንብ ተቀባይነት ያለው ኮስሞሎጂ ከፍልስፍና አንፃር የተሰጠው ትንታኔ ነው። ዘመናዊው ኮስሞሎጅ በመባልም ይታወቃል። ኮስሞሎጅን ከፍልስፍና አንፃር ስንመለከተው  ከስነ ፈለክ ጥናቶች አንዱ ሲሆን ከቢግ ባንግ/ታላቁ ፍንዳታ/ እስከ አሁን፤ ከአሁን እስከ ወደፊት ያለውን የአፅናፈ አለም አጀማመር እና ዝግመተ ለውጥ የሚያጠና ሳይንስ ነው። ታላቁ ፍንዳታ/big bang/ የተካሄደው የዛሬ 13.8 ቢሊዮን አመት ገደማ እንደሆነ የዘርፉ ሊቃውንት ይገምታሉ። እንደናሳ አገላለፅ ከሆነ ፍንዳታው ወቅት በአከባቢው ያለው የሙቀት መጠን 5.5 ቢሊዮን °C አከባቢ ነበር። ሙቀቱም በፍጥነት እየቀሰቀዘ እና እየሰፋ መጥቷል። በአሁኑ ሰአትም እየተለጠጠ ነው። ዩንቨርስ በዋናነት የተገነባው ከማይታወቀው ጥቁር ቁስ አካል (Dark Matter) ጥቁር ሀይል(Dark Energy) ነው።

አፅናፈ አለማችን/ሁለንታ/ መቶ ቢሊዮን ጋላክሲዎች ይኖሩታል ተብሎ ይታሰባል። በእያንዳንዱ ጋላክሲ ውስጥም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ከዋክብት፣ ታላላቅ የጋዝ ደመናዎችን እና የአቧራ ቅንጣጢቶችን ይይዛል።

በ17ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አይዛክ ኒውተን በፕላኔቶች መካከል ያለውን የስበት ሀይል ለማስላት ሞክሯል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የአለማችን እውቁ የሳይንስ ሰው አልቨርት አንስታይን የአጠቃላይ አንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ በሚለው መፅሀፉ ላይ ህዋ እና ጊዜ ያላቸውን ዝምድና ለማሳየት ሞክሯል። በሶስት ወርድ ስፔስ እና በአንድ አቅጣጫ ደግሞ ጊዜ/three dimensional space and one dimensional time/ እንደዶነ ከእርሱ በኋላ በ1990ዎቹ ውስጥ የሳይንስ ሊቃውንት የወተት ጎዳና /milky way/ አጠቃላይ የአፅናፈ አለም አካላትን የያዘ አካል ነው በሚሉ እና የወተት ጎዳና/milky way/ የከዋክብት ስብስብን የያዘ አንድ የአፅናፈ አለም አካል ነው በሚል ክርክር አድርገው ነበር።

በቅርብ አስር አመታት ውስጥ ደግሞ ስቴፈን ሀውኪንግ ዩንቨርስን ገደብ የሌለው አይደለም የራሱ የሆነ ቅርፅ ያለው እንጅ ሲል አብራርቶት ነበር።

ይቀጥላል.........

ምንጭ ዮጵቶኤል
Share???
@universeone123
@universeone123

1 year, 5 months ago

?የተወርዋሪ ኮከብ አና የትክክለኞቹ ኮከቦች ልዩነት

ተወርዋሪ ኮከቦች በተለመዶ ወደ ምድር ሲመጡ የሚታዩ ነገሮች ሲሆን ካሁን አሁን ወደቁ ብለን ስናስብ ተመልሰው በቅፅበት ይጠፍሉ ለማንኛው  ኮከቦች ማለት አደሉም ጭራሽ የማይገናኙ ነገሮች ናቸው እንዚህ ተወርዋሪ ኮከቦች የሚገኙት በኛው ሶላር ሲስተም ውስጥ ሲሆን ትክክለኞቹ ከዋክብት ግን የሚገኙት ከኛ ሶላር ሲስተም ውጭ ነው።

ተወርዋሪ ኮከቦች ከክዋክብት አንፃር እጅግ ትንሽ ነገሮች ናቸው ወይም የተሰባበሩ ድንጋዮች ናቸው  እንዚህ ነገሮች ወደ ምድራች የሚወድቁ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት አያስከትሉም ምክንያቱም በጣም ትንሽ እና የመሬት ከባቢ አየር ውስጥ እንደገቡ ተቃጥለው የሚጠፉ ነገሮች ናቸው እኛ ከመሬት ላይ የምናየውም ይሄንኑ ነው ማለትም ሲቃጠሉ ነገረ ግን ኮከብ ይመስላሉ እንጂ አደሉም።

ተወርዋሪ ኮከቦች የሚመጡት ከማርስ አጠገብ ከሚገኘው ከድንጋዮች ጥርቅም ነው በዚህ ቦታ እጅግ ብዙ ድንጋዮች በመሰባሰብ ፀሐይን የሚዞሯት ሲሆን ድንገት ከእሽክርክሪታቸው እየወጡ ወደ ፕላኔቶች ይወድቃሉ ከፕላኔቶች አንዷም የኛዋ ምድር ስትሆን በየአመቱ እጅግ በብዙ ተወርዋሪ ኮከቦች ትመታለች ግን ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ ፈንድተዋል/ተቃጥለዋል/።
@universeone123
@universeone122

1 year, 5 months ago

ፕላኔቶች ማግኔቲክ ፊልዳቸውን ሲያጡ ምን ያጋጥማቸዋል ? መሬት ማግኔቲክ ፊልድ ባይኖራት እኛ በዚች ምድር ላይ መኖር እንችል ይሆን?

ማግኔቲክ ፊልድ የሚፈጠረው በመሬት ውስጠኛው ክፍል ውስጥ ባለው ሙቀተ እንደሆን ከላይ በፃፍናቸው ፁሑፎች አይተናል እናም ፕላኔቶች ይሄንን ሙቀተ ካጡት መጀመሪያ ማግኔቲክ ፊልዳቸውን የሚያጡ ሲሆን ማግኔቲክ ፊልዳቸውን ሲያጡ ደግሞ እራሳቸውን ከ"solar wind" መከላከል አይችሉም የኛ ፕላኔትም የሚያጋጥማት ይሄው ሲሆን እራሷን ከዚህ አደገኛ ጨረረ የማትጠብቅ ከሆን የኛ መሬት ከባቢ አየሯን በፍጥነት ታጣለቸ።

በተመሳሳይ ምድራችን "ozone"
ሽፍኗን ታጣለቸ ከዚህ በዋላ ምድራችን እራሷን ከአደገኛ ጨሮሮች መጠበቀ ሰለማትችል አለማችን ሕይወት ላላቸው ነገሮች ፍፁም የማትመች ትሆናለች ምድራችን ከባቢ አየሯን በምታጣበተ ወቅት ደግሞ ምድራችን ላይ የሚተነፈሰ አየር ይጠፍል በዚህም ምክንያት በተመሳሳይ ሕይወት ላላቸው ነገሮች የምትመቸ አትሆንም

የኛ መሬት ማግኔትክ ፊልዷን የምታጣው በምድራችን ውስጠኛው ክፍል ውስጥ የሚገኘው ሙቀተ ሲቀዘቅዝ ነው ያኔ በምድራችን ውስጥ ምንም አይነተ ሙቀተ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላኛው ቦታ አይፈስም በዚህ ምክንያት ምድራችን ኤሌክትሪክ ሲቲን መፍጠረ አትችልም ኤሌክትሪክሲት መፍጠረ ካልቻለቸ ደግሞ ማግንቴክ ፊልድ መፍጠረ አትችልም ነገረ ግን ይሄ የሚሆነው ከ90 ቢልዬን አመት በዋላ ነው ይሄም በጣም እረጅም አመት ሲሆን ምድራችን እራሱ እስከዚህ አመት ድርስ  አትቆይም ማለትም የኛ ፀሐይ የኛን ምድር ከ6 ቢልዬን አመት በዋላ ታጠፍታለቸ ወይም ትውጣታለቸ ይሄም የሚሆነው ፀሐይ ወደ "Red jaint" ኮከብ ሰለምተቀየረ ነው

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana