ፍኖተ የሀ

Description
የሀ ማለት የመጀመሪያ ማለት ነው "ሀ" ከፊደላት የመጀመሪየዋ ናት ። እንዲሁም የሀ የመጀመሪያው ስርወ መንግስት ከሚባሉት ውስጥ ነው።።

የሀገራችንን ጥንታዊ ቅርሶች እና መስህቦች ለማስተዋወቅ የተቋቋመ ድርጅት
"ጥንታዊነት የዘመኑ ፋሽን ነው"
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 year, 10 months ago
2 years, 10 months ago

የፀጥታ ድምፆች

አራት የዜን መናኞች ለሁለት ሳምንታት ያህል ካላንዳች
ንግግር በፍፁም ፀጥታ ሆነው በተመስጦ ለማሰላሰል
ተስማሙ፡፡
በመጀመሪያው ቀን ምሽት ፣ በርቶ የነበረው ሻማ ተርገብግቦ
ጠፋ፡፡
የመጀመሪያው መናኝ ተናገረ፡- “ኦ! ሻማው ጠፋ!!”
ሁለተኛው መናኝ ፣ “እንዳናወራ ተነጋግረን አልነበረምን?”
አለ፡፡
ሶስተኛው መናኝ ተበሳጭቶ እንዲህ አለ፡- “ለምንድነው
ሁለታችሁ ፀጥታውን የምታደፈርሱት?”
አራተኛው መናኝ ከት ብሎ እየሳቀ፣ “ሃሃሃ! ሁላችሁም
አውርታችኋል፡፡ እኔ ብቻ ነኝ ያላወራሁት”
@yeha_promotion

4 years, 1 month ago

አዲስ አበባ ለጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻ ዝርዝር ውስጥ ተካተተች!

በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት፣ለጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻዎች ናቸው ከተባሉ ከተሞች ስም ዝርዝር ውስጥ አዲስ አበባ ተካተተች፡፡

@yeha_promotion @maedit1

Condé Nast Traveler የተሰኘ መፅሄት በ2021 አዲሱ የፈረንጆች ዓመት፣ለጎብኚች ጥሩ መዳረሻዎች ናቸው ሲል ከዘረዘራቸው 21 ከተሞች ውስጥ የአዲስ አበባ ስም ይገኝበታል፡፡

መፅሄቱ፣በከተማይቱ የሚገኙትን እንደ አንድነት እና እንጦጦ ያሉ ፓርኮችን ቀዳሚ የጎብኚዎች መዳረሻ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

@yeha_promotion @maedot1

ሙዚየሞችን ጨምሮ፣ቦሌ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ስፍራዎች ለጎብኚዎች ጥሩ መዳረሻዎች መሆናቸውን መፅሄቱ ጠቁሟል፡፡

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ፤ ኒውዮርክ ፣ ኦስሎ እና ኪዮቶ-ጃፓን በዚህ በስም ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ከተሞች ናቸው፡፡

ይህን ለጎብኚዎች ጥሩ-መዳረሻዎች የሆኑ ከተሞችን ስም ዝርዝር ያወጣው Condé Nast Traveler የተሰኘዉ መፅሄት ዋና መቀመጫዉን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገ ሲሆን ፤ በወር ከ5 ሚልየን የማያንሱ አንባቢዎች አሉት፡፡
@yeha_promotion @maedot1
ምንጭ:-ብስራት ራዲዮ#yene tube

4 years, 2 months ago

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጎብኚዎች የክፍያ ተመን ሥርዓት መመሪያ ዙሪያ ከክልሎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ራስ ሆቴል ውይይት አካሄደ።

ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም አዳማ

የዚህ መመሪያ ዓላማ የጎብኚዎች የክፍያ ተመን አወሳሰን፤ ምክንያታዊ መስፈርቶችን በመከተል፤ በተገቢው ስርዓት እንዲመራ የሚያስችል ወጥ፣ ግልፅ እና ፍትሐዊ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ነው ያሉት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላቸው ድሪባ ክፍያዎቹም እንደመዳረሻዎች ሁኔታ በአካል፣ በባንክ ወይም በኤሌክትሮኒክ እንደሚፈፀም ተናግረው ለሀገር ውስጥ ዜጎች በብር ለውጭ ሀገር ዜጎች በአሜሪካ ዶላር እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ በሚቀበላቸው ሌሎች የውጭ ሀገር ገንዘቦች ክፍያ ይፈፀማል ብለዋል።

የክፍያ ተመን ሥርዓትን በበላይነት የሚከታተሉና አፈፃፀሙን የሚገመግሙ 12 ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ሲሆን እንደ ተቋማቸው ሁኔታም ተግባርና ሃላፊነት እንደተቀመጠላቸው ተናግረዋል።

በውይይቱ የተገኙ ክልሎችና ባለድርሻ አካላት እንዳሉት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ችግሩን ተረድቶ ይህንን መመሪያ በዚህ ወቅት ማዘጋጀቱ የሚያበረታታ ስራ ነው ብለው መመሪያው ግልፅና የሚያሰራ እንደሆነ ተናግረው።

ተሳታፊዎችም መመሪያው ከመዳረሻው የሚገኘው ገቢ ለህብረተሰቡ፣ ለመንግስትና ለቅርስ ጥገና ምን ያክል ፐርሰንት መሆን አለበት? መመሪያው የፌድራል መንግስት የሚያስተዳድራቸው መዳረሻዎችን ነው ወይስ በክልል የሚተዳደሩትን ያካትታል ? የሚሉት ጥያቄዎች እና የቅርስ ባለ አደራ ማህበር ፣ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ሰዎች ባለ ድርሻ አካላት ሁነው ቢካተቱ የሚሉ ሀሳቦችን አንስተዋል።
@yeha_promotion

ውይይቱ የመሩት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ቡዜና አልከድር በዚህ ወቅት ይህንን መመሪያ ላዘጋጁት የሚኒስቴሩ ሰራተኞችን ምስጋናቸውን አቅርበው በውይይቱ ለመመሪያው የሚሆኑ በርካታ ግብዓቶች እንዳገኙ ተናግረው መመሪያው የተነሱ ግብዓቶችን ጨምሮ በማነጅመንት ከታየ በኅላ በድጋሜ ውይይት እንደሚደረግበት ተናግረዎል።
@yeha_promotion

ከክልል አመራሮችና ከባለ ድርሻ አከላት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች አስተያየቶች የሚኒስቴሩ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላቸው ድሪባ አመካኝነት ማብራሪያ ተሰጥቷባቸዋል።
@yeha_promotion

4 years, 2 months ago

የአቢጃታ ሐይቅ ወደ ቀድሞ ይዞታው መመለሱን የአብጃታ ሻላ ሃይቆች ብሄራዊ ፓርኮች አስታወቀ!
@yeha_promotion

በመጥፋት ስጋት ላይ የነበረው የአቢጃታ ሐይቅ በክረምቱ ዝናብ ወደ ቀድሞ ይዞታው መመለሱን የአብጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ አስታወቋል።

192 ካሬ ኪሎ ሜትር የነበረው የሐይቁ ስፋት በሰው ሰራሽ ምክንያት በመድረቁ ወደ 54 ካሬ ኪሎ ሜትር ወርዶ እንደ ነበረ የፓርኩ ሃላፊ አቶ ባንኪ ቡዳሞ አስታውሰዋል።

@yeha_promotion

ከፋብሪካ የሚለቀቅ ሶዳ አሽ የተሰኘ ኬሚካልም በሐይቁ ላይ ባደረሰው ጉዳት አዕዋፋትና አሳዎች ጠፍተው ቆይተዋል ብለዋል።
@yeha_promotion
ባለፈው ክረምት በነበረው ዝናብ በስፍራው ላይ ውሀ በመሙላቱ የሐይቁ ይዞታ ወደ 132 ካሬ ኪሎ ሜትር መመለሱን የተናገሩት ሃላፊው በሐይቁ ስፍራ ጠፍተው የነበሩ ስደተኛ ወፎችና የዱር እንስሳትም ተመልሰዋል።

በተለይም የፍላሚንጎ ዝርያ ያላቸው ስደተኛ ወፎች እንዲሁም አሳዎች ተመልሰው ሐይቁ የቀድሞውን ይዘት መያዙንና ለጎብኚዎችም ክፍት መሆኑን አቶ ባንኪ ቡዳሞ ገልጸዋል። (ENA)
@yeha_promotion

4 years, 10 months ago

ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚል በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው PATWA-Award (Pacific Area Travel Writers Association-Award) አሸናፊ ሆነች። በተጨማሪም የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው በዚሁ የ PATWA ሽልማት ላይ ከሰሃራ በታች ምርጥ የቱሪዝም ሚንስትር ሽልማትን አሸንፈዋል። የፓትዋ ሽልማት በየአመቱ በጀርመን በሚካሄደው እና በአለማችን በሆነው ITB (Internationale Tourismuse Börse-Berlin) የቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ የሚሰጥ የእውቅና ስነ-ስርዓት ነው። በዘንድሮው የፓትዋ ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች አስራ ሶስት የአለም አገራት ያሸነፉ ሲሆን ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የአርኪዎሎጂ እና ጥንታዊ ታሪክ መዳረሻ ሀገር በሚለው ዘርፍ ነው በቀዳሚነት ያሸነፈችው።
@yeha_promotion
@yeha_promotion

5 years, 2 months ago

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለሐያት ሪጀንሲ የባለ 5 ኮኮብ ለኤልያና ሆቴል ደግሞ የባለ 4 ኮኮብ ደረጃ ሰጠ። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እያካሄደ በሚገኘው የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ምዘና ሲካሄድባቸው ቆይቶ ውጤታቸው ለተጠናቀቀ ሁለት ሆቴሎች በዛሬው ዕለት የኮከብ ደረጃ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የባለ 5 ኮከብ እንዲሁም የኤልያና ሆቴል የባለ 4 ኮከብ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ባሳለፍነው ነሃሴ 2011 ዓ.ም 12 ባለ አራት፣ 13 ባለ ሶስት፣ 31 ባለሁለት እንዲሁም 27 ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ በአጠቃላይ 81 የኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በሌላ ግዜ ስለ ሆቴሎች ኮከብደረጃ ምደባ በሰፊው እንመለስበታለን እስከዛው ደህና ።
@yeha_promotion
@yeha_promotion
@yeha_promotion

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana