የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

Description
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month ago

Last updated 2 months ago

1 month, 3 weeks ago

https://vm.tiktok.com/ZMrscWwbH/

TikTok

TikTok · የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

Check out የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe’s post.

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
1 month, 4 weeks ago
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር ባሉ …

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር ባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ሥራ ለመቀጠር እንደየደረጃው ከ 3 መቶ ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እጅ መንሻ ክፍያ እንደሚጠየቅ ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል።

በተለይም በከተማይቱ፣ ትልቅ ሀብት የሚያንቀሳቅሱና ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ናቸው በሚባሉ አድባራትና ገዳማት አሥተዳዳሪ፣ ጸሐፊ፣ ሂሳብ ሹም ሆኖ ለመቀጠር ከ 3 መቶ ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እጅ መንሻ (ጉቦ)  እንዲከፍሉ እንደሚጠየቁ ሚዲያው ባለጉዳዮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ይህ የሚያሳየው ምን ያክል ሰዎቹ በከፍተኛ ሙስናና እና ዝርፊያ ውስጥ እንደተዘፈቁ ነው። ይህንን ሁሉ ብር ከፍሎ አስተዳዳሪና ሒሳብ ሹም የሚሆነውም ቄስ ለጽድቅ ሳይሆን ነገ የሚዘርፈውን ከፍ ያለ ንዋይ ከግምት አስገብቶ በመቋመጥ ነው። ይህንን አይነት አሳፋሪ ነገር ከአንድ የአምነት መሪ ማየት እጅግ ይዘገነንናል..!

https://t.me/Yahyanuhe

2 months ago

በሀድያ ምድር ሁሌም የምንመኘውን ትልቅ ስራ አሏህ አሳክቶልናል። በዚህ ስራ ላይ ከመጀመሪያው ጀምሮ የደከማችሁ፣ የተሳተፋችሁ ልበ ቀና የሀድያ ወጣቶች በሙሉ አሏህ መልካም ምንዳውን ይክፈላችሁ። ይህ ጅማሮ ነው፣ ኢንሻአላህ ሀድያ ሁለተኛ ቤታችን ይሆናል።

2 months ago

ሰሞኑን በአንዳንድ ጴንጤዎች ዘንድ በቲክቶክ በኩል ፋሽን የሆነች አባባል አለች። ይኸውም የሆነ የሙስሊም መለያ ነገር ደረብ ያደርጉና "ጴንጤ የሆንኩት ብር ተከፍሎኝ ሳይሆን ኢየሱስ ለሀጥያቴ ዋጋ ከፍሎልኝ ነው" ወዘተ ሲሉ እንሰማቸዋለን። አማርኛውን ለማሳመር ያደረጉትን ደፋ ቀና እንተተውና በአጭሩ ስለሀጥያትና ስለ ክፍያ ግን የሚከተለውን ልበላችሁ፦

በማንም በኩል ይሁን በደም ሊከፈልልን የሚገባ የማናውቀው እዳ የለብንም። ሰው ላልሰራው ሀጥያትና ላላጠፋው በደል "ለሀጥያትህ ሞት ተከፍሎልሀል" ማለት አምላክን መወንጀልም ጭምር ነው። አምላክ አንተ ላላጠፋሀው ሀጥያት የሆነ አካልን የሚያርድ ፍርደ ገምድል ዳኛ አይደለም። ኢየሱስም የዚህ ድራማችሁ አካል አይደለም፣ ያልሆነ ክስተት ያለልክ እየሰፋችሁ የሰበካ ማጣፈጫ አታድርጉት። ሀጥያት የሚሰረየው በባለ ሀጥያቱ ንስሀ ነው። የአዳም ሀጥያት አዳም ጋ የሚቆም እንጅ በደም ስሬ የሚተላለፍ ውርስ አይደለም። "ሀጥያት ከአባት ወደ ልጅ አይተላለፍም" የሚለውን የመጽሀፋችሁን ቃል ብትተውት እንዴት ሰው አእምሮውን በዚህ ልክ ለተቃረነ ትምህርት አሳልፎ ይሰጣል?

2 months, 1 week ago

አብዶ ጃሮ አስቂኙ ግለሰብ

አብዶ ጃሮ ከአንድ ፖድካስት ጋር የነበረውን ቆይታ አንድ ወንድም ላከልኝና አየሁት። ክርስትናን እንዲቀበል ያደረገው እስልምና መሆኑን ለዚህ ሚስኪን ምዕመን ሊያስረዳው ይሞክራል። የክርስትና ትምህርቶችን እስልምና ውስጥ ከዚያም ከዚህም እየቀደደ በመስፋት "አያችሁ እስልምና ስለ እናንተ ምን እንደሚናገር?" እያለ ለክርስትናው ከእስልምና አፕሩቫል ማግኘቱን ይጠቅሳል። በዚህ ውስጥ የፈጸማቸውን አያሌ የሎጂክ መፋለሶች ግን እሱም አብሮ ተቀምጦ ጭንቅላቱን የሚወዘውዘው ግለሰብም ከነአካቴው አያውቁትም። የሰውየውን የአስተሳሰብ ደረጃ ለመረዳት ከቪዲዮው የተወሰኑትን ከዚህ በታች ልጻፍላችሁ፦

▣ የከ*ፈረው በህልሙ አንድ ድንጋይ ኢየሱስን ተቀበል ብሎት ነው። ይህ ድንጋይም እንደ እሱ አገላለጽ ከሆነ ኢየሱስ እራሱ ነው። በህልሙ በምን ቋንቋ እንዳወራው እንደማያውቅ መጀመሪያ ላይ ቢገልጽም ኃላ ግን "ሀል ተዓረፍተል ቁርዓን" ብሎ ጠይቆኛል ሲል "አረብኛ" መሆኑን ተናግሯል። ከድሮ የግሪክ ፈላስፋዎች ንግግር ውስጥ አንድ የሚጠቀስ ንግግር አለ "ጎበዝ አስታዋሽ ካልሆንክ ውሸትን አትሞክረው" የሚል ነው።

▣ ኢየሱስን በህልም አይተን ነው ጴንጤ የሆነው የሚሉ ሰዎችን በተመለከተ ታዋቂው የክርስቲያን አፖሎጂስት ጄምስ ዋይት (ዶ/ር) "የሚታመኑ ሰዎች አይደሉም" ሲል ይገልጻቸዋል። እያንዳንዳቸው ኢየሱስን አየን የሚሉ ሰዎች "ኢየሱስን ግለጽልን" ብትሏቸው አብዛኛዎቹ የሚጠቅሱት የሜል ጊብሰን ፊልም ያለው ያለውን ተዋናይ መልክ ነው። አንዳንዶቹም ፈጽሞ የሚያስቅና እርስበርሱ የተደበላለቀ ምስል ይሰጧችኃል። እንዲህ አይነት ማታለያ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማታለል ይመጥናል ብለው ስለሚያስቡ ያለሰቀቀን በአደባባይ ይነግሩታል።

▣ "ቸርች ላቃጥል ስል ነው ኢየሱስ የተገለጠልኝ" ሲልም በ1970ዎቹ የቀረ ትረካ ይዞ መጥቷል። እንደሱ አይነት ጮሌ ሰዎች "ሙስሊም ነበርን" ከሚሉ ይልቅ "አክራሪ ሙስሊም ነበርን" ቢሉ የድራማው ድምቀት ከፍ እንደሚል ያቃሉ። ምዕመኑ አብሮት እንደተቀመጠው ሰው አንገቱን እየነቀነቀ "አየኸው ተራ ምዕመን አልነበረም፣ ቸርች ሊያቃጥል የነበረ "ዋና ሙስሊም" ነው ኢየሱስ ያመጣልን" እያለ በግርምት እንደሚሸወድለት ያውቃል። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቀደመ ህይወቱ ለተረጎመው አንድ መጽሀፍ የሰጠው ስምም "ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና" የሚልን ነው። መጽሀፉን ስታነቡ ግን የድርሰቷ ዋና ገጸ ባህሪ ናህድ ማሕሙድ ሙተዋሊ በፍጹም ከሳሉት ስዕል ጋር የማይሄድ ስብዕና ኑሯት ታያላችሁ። እናም አክራሪ የምትለዋ አሁን ላይ የቀረች ብትሆንም አብዶ ጃሮ ግን ብዙ ነገሩ የሆነ ዘመን ላይ የተቸነከረ ከመሆኑ ጋር ካርዷን መዟት አሁንም ሊጠቀማት ሞክሯል።

▣ "ሙስሊም እያለሁ ከኦሮምኛ ውጭ አማርኛ ቋንቋ ጆሮየን ብትቆርጡት አልሰማም ነበር" አለን። ታዲያ ጴንጤ ሲሆን ግን ቋንቋውን በቀላሉ እንደቻለውና ኢየሱስ እንደገለጠለት አድርጎ አቀረበው። ሌሎችንም የሀገራችንም ቋንቋዎች ኢየሱስ ለምን እንዳላስለመደው ግን አልነገረንም፤ ኢየሱስን በዚህ መልኩ በፍጥነት ወስዶ ብሔርተኛ ማድረጉን ግን ስክሪፕቱን በጭንቅላቱ ሲተይብ የረሳው ይመስለኛል።

▣ በተገኘበት መድረክ ሁሉ አረብኛ መናገሩን እንደ ትልቅ የአዋቂነት ጉልበት አድርጎ ለማሳየት ፍዳውን ሲበላ እናስተውላለን። ከጉሮሮ የሚወጡ ቃላትን ያለቅጥ በመጫን ይህንኑ ለማያቁ ሰዎች ፕሩፍ ለማድረግ ይደክማል። በቅርብ ርቀት የሚገኙት የግብጽ ኦርቶዶክሶች ቅዳሴያቸው ሁሉ አረብኛ መሆኑን የዘነጋው ይመስላል። አረብኛ መቻል እስልምናን ለማወቅ ይጠቅማል እንጅ አረብኛ ማወቅ ብቻውን የእስልምና አዋቂ ያደርጋል ማለት አይደለም። በዚያ ላይ ቲክቶክ ከወንድሞች ጋር በነበረው ክርክር መሠረታዊ የአረብኛ ህግጋት የሆኑትን ሙአነስና ሙዘከርን እንኳን በቅጡ መለየት ያልቻለ ሰው እንደነበር አስተውለናል።

▣ ሌላው አስገራሚው ነገር "ሼይኽ ነበርኩ፣ ልጆችን ቁርአን በማስቀራቴ የማገኘው የገንዘብ ጥቅም ክርስቲያን በመሆኔ አጥቸው ተቸግሬያለሁ" ይለናል። ሰው በዚህ ደረጃ ኮሜዲ ይሆናል?ይህንን የሚለው እጅግ ዘመናዊ ታብ በእጁ ይዞ ነው። ሌላው ቢቀር እራሱ እንተደተናገረው ለተወሰኑ አመታት ውጭ ሀገር ልከው ያስተማሩትን ከበርቴ ወንጌላውያን እጅ መንከስም ጭምር ነው። ይህችን ኮፍያና አማይማ ለብሰህ ለምን እንደምትመጣ ሁሉም ሰው ያቀዋል። ጥሩ ሽቀላ ስለሚገኝባት ነው። ይህንን ለማለባበስ የቁርአን አቅሪ ደሞዝን ማጋነን አስገራሚም አስተዛዛቢም ነው። ቁርአን አቅሪዎች የሚከፈላቸው ክፍያ እንኳን ሊጋነን ለቤተሰብ እንኳን በመከራ እንደሚብቃቃ ሁሉም ያውቀዋል፣ ያውም ገጠር የሚገኙት ደግሞ ከዚህም የከፋ ነው።

◾️ በጥቅሉ አብዶ ጃሮ ያነሳቸው ነጥቦች ፕሮግራም ተይዞ በቁምነገር ምላሽ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ሁነው አላገኘኃቸውም። አብዛኛው ሰው እያራገበው ከመሆኑ አንጻር ግን እንደ አስፈላጊነቱ በአሏህ ፍቃድ በቪዲዮ መልስ እንሰጥበታለን።

© የሕያ ኢብኑ ኑህ

2 months, 1 week ago

አንድ መጥፎ ነገር ስንመለከት/በተለይም ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ/ ለዚያ ተግባር ይፋዊ ግብረ መልስ ከመስጠታችን በፊት ሁለቴ ማሰብ የሚኖርብን ጥቂት መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ።

1/ ያንን ጉዳይ በይፋ መመለሳችንና አደባባይ ላይ በኛ በኩል ማውጣትችን ያ መጥፎ ተግባር/መልዕክት/ ካዳረሰው መጠን በላይ የኛው አካሔድ ለህዝቡ የሚያስተዋውቀው ከሆነ ልፋታችን ትርጉም አልባ ይሆናል። መጀመሪያውኑም ጉዳዩ በሰፊው ማኅበረሰብ ዘንድ የተዳረሰ ከነበረና የኛ ግብረ መልስ አስፈላጊ ሲሆን ብቻ መሳተፉ ተገቢ ይሆናል። ከዚያ ውጭ ያለው ሒደት ግን ሸሩን/ክፋቱን/ ከማባዛት የዘለለ ሚናው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።

2/ ለተነሳው መጥፎ ተግባር/ሀሳብ የምንሰጠው ግብረ መልስ ሀሳቡን በትክክል አድሬስ ያደረገና መጥፎውን ክስተት የማክሰም አልያም የመቀነስ ጉልበት ካለው መልካምና የሚበረታታ ነው። ከዚያ በዘለለ ግብረ መልሳችን እልህ የበዛበት ሁኖ የበለጠ ክፋት ይዞ የሚመጣ ከሆነና ይህንኑ በአቅማችን ለመመከት የሚችል አቅሙን ዝግጁነቱም ከሌለን ቀድሞውኑ ባንጀምረው የተሻለ ነው።

3/ ከምንም በላይ ይህንን ስራ ስንሰራ በእርግጥም የአሏህን ፊት ፈልገንበት ነው ወይንስ እልህ ስሜታዊ አድርጎን ነፍስያችንን ከማስተንፈስ አንጻር ነው የሚለውም መሠረታዊ ጥያቄ ነው። ኢኽላስ ሊያሳጣን የሚችል ስሜታዊ ምልልስ ውስጥ አለመግባት በጣም ተመራጭና ጠቃሚ ነው።

▣ እነዚህ ነጥቦች በተለይ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ለምታዩት ነገር ሁሉ ግብረ መልስ ከመስጠታችሁ በፊት ደጋግማችሁ ልታውጠነጥኑት የሚገባ ነው። ብልህ ሰው ለክቶ ነው የሚቆርጠው፣ እየቆረጠ አይለካም። በችኮላ ከተደረገ ሰፊ ልፋት ይልቅ በጥንቃቄ የተደረገ ትንሽ ሙከራ የተሻለ ለውጥ ታመጣለች። አደራችንን ቤት ስንገነባ ከተማ እንዳይፈርስ እንጠንቀቅ..!

4 months, 2 weeks ago
እስልምና ላይ ተደጋግመው ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል …

እስልምና ላይ ተደጋግመው ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አስቅለት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥያቄ አንዱ ነው። አሏህ ﷻ ከፈቀደ በዚህ ረገድ የሚነሱ ትችቶችን በቲክቶክ ላይቭ መመለስ እንጀምራለን። ከተለመዱት ውስጥ አንደኛውን በመምረጥ መነሻ አድርገነዋል። ጌታ አሏህ ከፈቀደ ነገ ከቀኑ 10:15 ጀምሮ በቲክቶክ በኩል እናብራራዋለን። የሚመቸው ይቀላቀለን፣ ካልቻለ ደግሞ ላልደረሳቸው መልዕክቱን ሼር ያድርግ..!

4 months, 3 weeks ago
ኢየሱስን ከስቅለት በማዳኑ አሏህ አታሏቸዋል ማለት …

ኢየሱስን ከስቅለት በማዳኑ አሏህ አታሏቸዋል ማለት ይቻላል?| ተከታታይ ምላሽ - 27

https://vm.tiktok.com/ZMMKBUgxB/

4 months, 3 weeks ago
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu …
4 months, 4 weeks ago

በመሠረታዊነት ከሚሰጡ የንፅፅር ትምህርቶች ውስጥ ይህኛው ክፍል ለማህበራዊ ሚዲያውም ሰው ከጠቀመ በሚል አጋርቸዋለሁ። ደቂቃው ረዘም ያለ ደርስ ስለሆነ በድምጽ ማዳመጥ ለምትፈልጉ ቴሌግራም ላይ ታገኙታላችሁ፣ ቪዲዮ የሚቀላችሁም ዩቲዩብ ላይ ታገኙታላችሁ።

___
https://t.me/Yahyanuhe

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 4 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month ago

Last updated 2 months ago