ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ሰላም ሚኒስቴር የተባለው መንግስታዊ ተቋም ሞፈረን በልጆቻቸው አንገት አስገብተው የሰላምን አስፈላጊነት ከተናገሩ፣በጋሞ እርጥብ ቄጤማ ይዘው የደም አቢዮትን ከተከላከሉ ሃገር ሽማግሌዎች በተለየ ምን ሰራ?
በአገሪቱ የሚፈጠሩ ቀውሶችን ለማስቆምስ ለምን አልቻለም?
ሚኒስትሮችን በመቀያየር ለውጥ ማምጣት ይቻላል ወይ የሚለው እሳቤስ መጨረሻው ወደ የት የሚወስድ ነው? የሚሉና ከተቋሙጋር
የተያያዙ ያልተሰሙ አስገራሚ ጥያቄዎችንና መረጃዎችን በአዲስ ማለዳ ትንታኔአችን ልንመለከተው ወደናል፡፡
ሙሉ ዝግጅቱን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይከታተሉ፡፡
በላሊበላ ከተማ በጸጥታ ችግር ምክንያት ሆቴሎች እና አስጎብኝዎች መስራት አለመቻላቸው ተገለጸ
ረዕቡ ህዳር 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በላሊበላ ከተማ 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸውን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በተመሳሳይ በጦርነቱ ምክንያት ወደ ስፍራው የሚመጡ ቱሪስቶችን ማጣቱን እና በዚህም 200 የሚደርሱ የላሊበላና አካባቢዉ አስጎብኝዎች ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጋቸዉን የላሊበላ ከተማ አስጎብኝ ማኅበር ማስታወቁን ዶችቬለ ዘግቧል፡፡
የአቶ ጌታቸው ረዳን የፕሬዚዳንትነት ውክልና አንስቻለሁ’’ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት
ረቡዕ ኅዳር 25/2017 (አዲስ ማለዳ) በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት ባወጣዉ መግለጫ ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረውን የፕሬዚዳንትነት ውክልና ማንሳቱን ገልጿል፡፡
በመሆኑም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንደሚተኩ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታዉቋል።
ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39575
አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ትግበራ ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ
ቅዳሜ ጳጉሜ 02 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን መምጣት ተከትሎ በመንግስት ቃል ከተገቡት ጉዳዮች አንዱ የሆነው የደሞዝ ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መሠረት ሚድያ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያለው አንድ የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ደብዳቤው ለታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ እንደተመደበ እና ጭማሬው ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልቷል።
ይህ በፋይናንስ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ተጠንቶ የቀረበው የደሞዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡም ነው የተነገረው።
በየወሩ በአማካኝ 560 ሰዎች በግጭት ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገለጸ
ቅዳሜ ጳጉሜ 02 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ 10 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 'የሰላም ጥሪ' ባቀረቡበት ወቅት ነው እነዚህ የግጭት አህዞች የተገለጹት፡፡
በአዲሱ 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፤ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን ጨምሮ 10 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሰላም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በ2016 ብቻ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,792 በላይ የግጭት ኩነቶች የተመዘገቡ መሆኑን ገልጸው በነዚህ ግጭቶችም በጥቅሉ ከ6,164 በላይ ሰዎች መሞታቸውን አንስተዋል።
በፔሩ ሊማ በተካሄደው የአለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ ከአለም ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች::
ከፍተኛ ስኬት በታየበት በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ 6 ወርቅ 2 ብር እና 2 ነሀስ በድምሩም 10 ሜዳሊያ አግኝታለች:: ይህንንም ውጤት ተከትሎ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን አጠናቃለች::
በመጨረሻ ቀን ውድድር በወንዶች 1500 ሜትር አብዲሳ ፈይሳ በ 3:40.51 ሰአት ማሸነፍ ችሏል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago