ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 week ago
Last updated 3 days, 6 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 3 weeks ago
"ብናጥስ ሆይ ከዚህ ከረከሰና ከከፋ ምክርህ ተመልሰህ ንስሓ ግባ ለእግዚአብሔርም ለራስህና ለሰውም ሁሉ ጠላት አትሁን"።
❤ እርሱ ግን ከክፋ ሐሳቡ ተመልሶ ትምርታቸን አልተቀበለም። አውግዘውም ከምእመናን ለዩት በትምህርቱ የሚያምኑትንም ሁሉ ለዩአቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ12 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ። ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ። ትኩላ እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር"። መዝ91፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ6፥6፥19-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8 ወይም መዝ 98፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 6፥1-13፣ ይሁ 1፥9-14 ወይም ያዕ 5፥14-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 10፥2-9 ወይም 5፥29-39። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥12-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ የያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል ለወራዊው በዓል መታሰቢያና ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለቅዱሳን_ለአንቂጦስና_ለፎጢኖስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ነድራ፣ ከደብረ እስዋን ከታማኙም #ከቅዱስ_ዮሐንስ ከመታሰቢያቸው፣ ስለ ቀሲስ ብናጥስ በሮሜ አገር ከተሰበሰብ ከኤጲስ ቆጶሳት፣ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት፣ ከዕረፍታቸው፣ #ከቅዱሳን_ሰማዕት_ከአውሲስና_ከእንጦንዮስ፣ ከሮሜው #ከአባ_መሐር ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #በዚች_ቀን_የመላእክት_አለቃ_የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና።
❤ በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ።
❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_አንቂጦስና_ፎጢኖስ፦ ይህም ሰማዕት አንቂጦስ ንጉሡ ምእመናንን ያሥራቸው ዘንድ አሠርቶ በፊቱ ያኖራቸውን የሥቃይ መሣሪያዎች በአየ ጊዜ በቆራጥነት ከሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ተከራከረው ንጉሡም አሥረው ወደ ጨዋታ ማያ ቦታ አውጥተው ክፉውን አንበሳ እንዲለቁበት አዘዘ። አንበሳውም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ እጁን ዘርግቶ ፊቱንና ጒንጩን አሻሽቶ ተወው ንጉሡም ከይቶ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ወታደሩም ሰይፉን በመዘዘ ጊዜ ተንቀጠቀጠ መንቀሳቀስም ተሳነው ሁለተኛም ሰውነቱ ፈጥና እንደትቆራረጥ ከበታቹ የእሳት ፍም ወደተነሠነሠበትና ቆራርጦ የሚለያይ መሣሪያ ወዳለው መንኰራኵር ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ እግዚአብሔርም ከዚህ አድኖት ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው።
❤ ዳግመኛም በውስጧ እርሳስ ወደአፈሉባት ጋን ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ ሕዝቡም እያዩ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከጋኑ ውስጥ ነጥቆ በዲዮቅልጥያኖስ ፊት አቆመው ፎጢኖስም ይህን ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ ልብሱን ጥሎ ተነሥቶ ወንድሙን አንቂጦስን ሳመው። "ከዳተኛውንም ንጉሥ አንተ ጐስቋላ ወንድሜን እንዴት ታሸንፈዋለህ" ብሎ ረገመው ዲዮቅልጥያኖስም ሰምቶ በአንገታቸው ዛንጅር በእግሮቻቸው እግር ብረት አግብተው ወደ ወህኒ ቤት እንዲጨምሩአቸው አዘዘ።
❤ ከዚህም በኋላ ሥጋቸው ሁሉ ይበታተን ዘነድ ጥፍር በአለው ብረት እንዲሰነጣጥቋቸው አዘዘ ዳግመኛም ወደ ጨዋታ መስክ ወስደው በድንጋይ ይወግሩአቸው ዘንድ አዘዘ። ምንም ምን የነካቸው የለም ዳግመኛም በብዛት ገርፈው በቊስላቸው ውስጥ ጨው ጨመሩ ሦስት ቀንም ወደ አንደዱበት የውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩአቸው እርሱም እንደ ቀዘቀዘ ጠል ሆነላቸው የውሽባ ቤቱንም በከፈቱት ጊዜ የእግዚአብሔርን ገናናነት ሲነጋገሩ አገኙአቸው።
❤ ከዳተኛው ንጉሥም በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ነበልባሉም ከፍ ከፍ እስከሚል በማንደጃው ውስጥ እሳትን አንድደው ቅዱሳኑን ወደዚያ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ በውስጡም ቁመው ረጅም ጸሎትን አደረጉ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊታቸውን አማተቡ ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ሥጋቸውም ከቀኑ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት ድረስ በእሳቱ ፍም ላይ ነበር የነካው ነገር የለም የራሳቸው ጠጒር እንኳን አልተቃጠለም ምእመናንም ሥጋቸውን በሌሊት ወሰዱ ለክብራቸውም እንደሚገባ ገንዘው በመልካም ቦታ ቀበሩአቸው። ከእሳቸውም አስደናቂዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት አንቂጦስና ፎጢኖስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የቅዱሳን_ኤጲስቆጶሳት_የቀሳውስትና_የዲያቆናት የአንድነት ስብሰባ በሮሜ ከተማ፦ ይህም የሆነው ከሀዲው ዳኬዎስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት በቆርኔሌዎስ የሹመት ዘመን በእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት በዲዮናስዮስ ዘመን በላንድዮስም በአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ ሳለ ግርማኖስም በኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ሁኖ ሳለ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በስደት ጊዜ የካደ ቢኖር ወይም በዝሙት የወደቀ ወይም በየአይነቱ በሆነ ኃጢአት ቢሰናከል በንስሐ ሊቀበሉት አይገባም በማለቱ ስለ ቀሲስ ብናጥስ ነው።
❤ አባት ቆርኔሌዎስ ስለዚህ አንድ ጊዜ ዳግመኛም ሦስተኛም ጊዜ ገሠጸው መከረውም ግን አልሰማውም ስለዚህም ስልሳ ኤጲስቆጶሳትን መጻሕፍትን የተማሩ ዐሥራ ስምት ቀሳውስትና አርባ ዲያቆናትን በርሱ ላይ ሰበሰበ። እርሱም ስለዚህ ነገር ብናጥስ ቀሲስን ተከራከሩት ቀስሲ ብናጥስም ምክንያት አድርጎ የተነሣው ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች በስድስተኛው ምዕራፍ "ጥምቀትን ከተቀበሉ በኋላ ከሰማይ የሚሰጥ ጸጋውን ከቀመሱ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ አንድ ከሆኑ በኋላ አይቻልም። መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና በኋላ የሚመጣውን የዓለምን ኃይል ከዐወቁ በኋላ ንስሓቸውን ሊአድሷት የእግዚአብሔርን ልጅ ሊሰቅሉላቸው ሊዋርዱላቸው ዳግመኛ ሊወድቁ አይገባም" ያለውን ኃይለ ቃል ምክንያት አድርጎ ነው።
❤ እሊህ አባቶችም እንዲህ ብለው መለሱለት "ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ንስሓ ስለማገባ ሰው ይህን አላለም በኃጢአት በወደቀ ጊዜ በየጊዜው የክርስትና ጥምቀትን ስለሚጠመቅ ነው እንጂ ስለዚህም ሐዋርያው እንዲህ የሚለውን ቃል አስከተለ ዳግመኛ የእግዚአብሔርን ልጅ ሊሰቀሉላቸው ሊያዋርዱላቸው ይገባልን? መከራ መስቀሉ አንድ ጊዜ ብቻ ናትና ንስሓ ግን በሁሉ ጊዜ ትገኛለች። አንተ እንደምትለው ከሆነ በኃጢአት የወደቀ ዳዊትን ጌታችንን ክዶት የነበረ ጴጥሮስን ንስሓ አልተቀበለምን? አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት አልሰጠውምን? በምእመናንስ ላይ በከንቱ ሾመውን? በእጁ የሠራው ሁሉ የተጠመቀውም የጠፋ ነውን? አንተ እንደምትለው ይህ ስንፍናና ድንቁርና ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ግን ሃይማኖቱን ለካደ ወይም በኃጢአት ለወደቀ ለሁሉም ንስሓን ሠርቷል
? "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ?
? #መስከረም ፲፪ (12) ቀን።
? እንኳን #በኤፌሶን_አገር በ_431 ዓ.ም (ሦስተኛው ጉባኤ) ሁለት መቶ ኤጲስ ቆጶሳት በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #በቅዱስ_አባ_ቄርሎስ ሊቀ መንበርነት ንስጥሮስ ለማውገዝ ለተሰበሰቡበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሚካኤል እግዚአብሔር ወደ አሞፅ ልጅ ወደ #ነቢዩ_ቅዱስ_ኢሳይያስ_ለንጉሡ_ሕዝቅያስ ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜው ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደተጨመረለት ንገረው ብሎ ለተላከበት ለወራዊ መታሰብያ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት #ቅዱስ_አፍላሆስ ከመታሰቢያውና ከሥጋው ፍልሰት፣ ከእስክድርያ አገር ከሆኑ ከባልንጀሮቹ ሰማዕታትም ከመታሰቢያቸው፣ #ከሰማዕታት_ከቅዱሳን_ከሉዩራስና_ባሌኒኮስ፣ #ከቅዱስ_ኢያቄምና_ከቅድስት_ሐናም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
? በዚችም ቀን ደግሞ #በኤፌሶን_ከተማ #የቅዱሳን_የሁለት_መቶ_ኤጲስቆጶሳት_ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው።
? ስብሰባቸውም የተደረገው የታላቁ ቴዎዶስዮስ ልጅ አርቃድዮስ የወለደው ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በሃያ ዓመት ነው። የስብሰባቸውም ምክንያት የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በንስጡር ነው። እርሱ ስቶ እንዲህ ብሏልና "እመቤታችን ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ አልወለደችውም እርሷ ዕሩቅ ሰውን ወልዳ ከዚህ በኋላ በውስጡ የእግዚአብሔር ልጅ አደረበት ከሥጋ ጋር በመዋሐድ አንድ አልሆነም በፈቃድ አደረበት እንጂ። ስለዚህም ክርስቶስ ሁለት ጠባይ ሁለት ባህርይ አሉት" የተረገመ የከሐ*ዲ ንስጡር የከፋች ሃይማኖቱ ይቺ ናት።
? ስለ እርሱም የተሰበሰቡ እሊህ አባቶች ከእርሱ ጋር ተከራከሩ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አምላክ እንደሆነ ገብርኤል መልአክ በአበሠራት ጊዜ ከተናገረው ቃል ምስክር አመጡ። እንዲህ የሚል "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው ከአንቺ የሚወለደውም ጽኑዕ ከሀሊ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል"። ዳግመኛም "እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች" ብሎ በትንቢቱ ከተናገረው ከኢሳይያስ ቃል ሁለተኛም "ከእሴይ ዘር ይተካል ከእርሱም ለአሕዛብ ተስፋቸው ይሆናል"።
? ዳግመኛም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ ገሠጸው መከረው ስለዚህም እንዲህ ሲል አስረዳው "ክብር ይግባውና የክርስቶስ የመለኮቱና የትስብእቱ ባሕርያት በመዋሐድ አንድ ከሆኑ በኋላ አይለያዩም አንድ ባሕርይ በመሆን ጸንተው ይኖራሉ እንዲህም አምነን ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንዲት ባሕርይ ነው እንላለን"።
? ከሀዲ ንስጥሮስ ግን ከክፉ ሐሳቡ አልተመለሰም ከሹመቱም ሽረው እንደሚአሳድዱትም ነገሩት። እርሱ ግን የጉባኤውን አንድነት አልሰማም ስለዚህም ከሹመቱ ሽረው ረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለይተው አሳደዱት ወደ ላይኛውም ግብጽ ሒዶ በዚያ ምላሱ ተጎልጒሎ እንደ ውሻ እያለከለከ በክፉ አሟሟት ሞተ።
? እሊህም ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት አባቶች ሃይማኖትን አጸኑዋት በዚህም ጉባኤ ውስጥ እንዲህ ብለው ጻፉ "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእርሷ ሰው የሆነውን የእግዚአብሔርን አካላዊ ቃል በሥጋ ወለደችው"።
? ከዚህም በኋላ ሥርዓትን ሠርተው ሕግንም አግገው በእጆቻቸው ጽፈው ለምእመናን ሰጡ። እኛም የሕይወትንና የድኅነትን መንገድ ይመራን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ለእርሱም ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
? በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ_የቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
? በዚችም ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ላከው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው። ንጉሱም ሚስት አግብቶ ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን። ምንጭ፦ የመስከረም 12 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
? "#ሰላም_ለምቅወምከ_ዘልዑል_ማዕረጋ። እምቅዋመ አእላፍ እንግልጋ። #ሚካኤል_መንፈስ ዘንበለ ሥጋ። ታድኅን ዘተመንደበ ለማዕበለ ባሕር እምጹጋ ወለእለ በበድው ትባልሕ በጸጋ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_12።
✝️ ✝️ ✝️
? #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦"ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታእሙሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8 ወይም 72፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥424-44 ወይም ማቴ 18፥15-19።
ቅዱስ ፓትርያርኩ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በእርቀ ሰላም እንዲፈቱ ተጠየቁ ።
ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጉባኤው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት የሚከበር በመሆኑ በዕለቱ ከበርካታ አህጉረ ስብከት የተሰበሰቡ የጉባዔው ታዳሚዎች ቅዱስ ፓትርያርኩ እረቀ ሰላሙን ለመፈጸም ቃል እንዲገቡላቸው ከመቀመጫቸው በመነሣት በታላቅ አክብሮት ጠይቀዋል በተያያዘም የጋራ መግለጫ አቋም አስነብበዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የሰት ቤቶች ማ/መማሪያ ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት 13ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የቃለ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የጋራ አቋም መግለጫ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት 13 ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 15 እና 16 / 2016 ዓ.ም ከየአህጉረ ስብከቱ የተወከሉ የሀገረ አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አጠቃላይ ጉባኤ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል ፤ በመሆኑም በጉባኤው ከቀረቡ ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ ተዘጋጅተው ከቀረቡ ጥናታዊ ሰነዶች፣ ከአህጉረ ስብከቶች ከቀረቡ አስተያየቶች እና ከጉባኤው ተሳታፊዎች ከተነሱ የውውይት ሐሳቦች የውይይት ግብዓቶች በመነሳት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
በ13ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበውን ሪፖርትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀብለን አጽድቀናል፤ ለትግበራው በጋራ እንሠራለን፤
ቅዱስ ሲኖዶስ በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በሁሉም አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆን እና ለማስጀመርያ መጻሕፍት ኅትመት በጀት በመበጀትና እንዲታተሙ በማድረግ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም እና የመምሪያችን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ አመራር ሰጭነትና ክትትል የመጻሕፍት ዝግጅቱ ውጤት ላይ ደርሶ ከኛ እስከ 4ኛ ከፍል 23 የትምህርት አይነት የያዘ በ4 ጥራዝ 23 መጻሕፍት ታትመው ዛሬ በቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲመረቁ መደረጉ በሰንበት ት/ቤቶች የአገልግሎት ታሪከ አንዱ ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ በልጅነት መንፈስ አድናቆታችንን እንገልጻለን፤
የታተሙት እና በዝግጅት ላይ ያሉ መጻሕፍት በሁሉም አህጉረ ስብከቶች በሚገኙ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች ተደራሽ እንዲሆኑ በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ሁሉም መዋቅራት በጀት በጅተው መጻሕፍቱን ለሰንበት ት/ቤቶች መምህራን ተደራሽ እንዲያደርጉ እና ምዕመናን በማስተባበር ተደራሽነቱ እንዲሰፋ እንጠይቃለን፤
በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መመሪያ ማዕቀፍ መሠረት በሚደረገው የትግበራ ሥራ ከሚስተዋሉ የአፈጻጸም ከፈተቶች መካከል የሀገረ ስብከትና ሀገር አቀፍ ምዘና በ4ኛ፣ 6ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ የነበረው ወደ 4ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ እንዲሆን እንዲሁም ሌሎች የተሰጡ አስተያየቶች በመመሪያው እንዲስተካከሉ ወስነናል፤
ሥርዓተ ትምህርቱን ለማስተግበርና ለአጠቃላይ የሰንበት ት/ቤት እንቅስቃሴ ተገቢው በጀት ከአጥቢያ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ የቤተከርስቲያኒቱ መዋቅር እንዲፈቀድ በአጽንኦት እንጠይቃለን፤
ከመንበረ ፓትርያርከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት ያካተተው ስልታዊ ዕቅድ ዝግጅት በጥልቀት ገምግመናል፡፡ ይህም አገልግሎታችንን ወጥና የተናበበ እንዲሆን መሠረታዊ ስለሆነ በጉባኤው የተሰጡ ማስተካከያዎችን በማካተት ወደ ሥራ እንዲገባ ወስነናል፤
ከመንበረ ፓትርያርከ ጠቅላይ ቤተ ከህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት ዝርዝር የአደረጃጀት መዋቅር በ12ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጸድቆ ለትግበራ የቀረበው ሰነድ ለትግበራ በተሰጠው ግንዛቤ ገለጻ መሠረት ሁሉም የሰንበት ት/ቤት ተዋረዳዊ መዋቅራት በአደረጃጀት ሰነዱ መሠረት በተመሳሳይ ጊዜ የአመራር
ምርጫ በማከናወን እንዲያስፈጽሙ ወስነናል፤
በ2016 ርከበ ካህናት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጸድቆ ወደ ትግበራ እንዲገባ የተወሰነው መሪ እቅድና መዋቅራዊ አደረጃጀት ውሳኔን ጠቅላላ ጉባኤው በአድናቆት ተቀብሎታል፡፡ ለትግበራውም የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ቃል እየገባን በሕገ ቤተከርስቲያን በተደነገገው የካህናት የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የአስፈጻሚነት ድርሻ በየደረጃው ባለው የቤተከርስቲያኒቱ መዋቅር ተግባራዊ እንዲደረግ እንጠይቃለን፤
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሚስተዋሉ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ሁሉ በመሳተፍና እንደ ቤተክርስቲያን ተተኪ ልጅነታችን የበኩላችን ሐላፊነት በባለቤትነት መንፈስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ባለው መዋቅር ትኩረት ሰጥተን የምንመራ መሆናችንን እንገልጻለን።
በዚህ ጉባኤ ላይ በተለያዩ ምከንያቶች ያልተገኙ የአህጉረ ስብከት ተወካዮች እንዳሉ ቢታወቅም በተለይ ግን በትግራይ ከልል ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ጋር በተፈጠረዉ እጅግ አሳዛኝ መለያየት የተነሣ የከልሉ አህጉረ ስብከት ተወካይ ወንድሞች እና እኅቶች ባለመገኘታቸዉ ጉባኤው ከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶታል!! ከዚህም በላይ ችግሩ ወደ ምዕመናን እየሰፋ መሔዱ ጉባኤውን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ ይኸ መለያየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ሔዶ በእንዲቷ ቤተከርስቲያን ላይ ከፍተኛ አደጋና የማይጠገን ስብራት ከመድረሱ በፊት ልዩነቶችን አስወግዶ በሥርዓተ ቤተከርስቲያን አግባብ የክልል ትግራይ አህጉረ ስብከቶች ወደ መዋቅራቸው ጠቅላይ ቤተክህነት ይመለሱ ዘንድ፤ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችም ፍሬ ያፈሩ ዘንድ እግዚአብሔርን ከመለመን ባሻገር የተቻለንን ኹሉ እንደምናደርግ ቃል በመግባት ችግሩን ለመፍታትና እርቀ ሰላሙን ለማምጣት ከፍተኛዉን ድርሻ ሊወጡ የሚችሉት ብፁዕ ውቅዱስ አባታችን እንደኾኑ እናምናለን፡፡ ይኽንኑ ለመፈጸም ቅዱስ ፓትርያርካችን ቃል ይገቡልን ዘንድ በታላቋ ቤተክርስቲያን ስም የቤተከርስቲያን ልደት ተብሎ በሚታወቀው በዛሬው በዓለ ጰራቅሊጦስ ስም ከመቀመጫችን በመነሣት በታላቅ አክብሮት እና ትህትና እንጠይቃለን!!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
❤ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ "ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ። ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ። ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ" አላቸው ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋራ ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት18 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን"። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ 77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ 24፥1-13።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ117፥24-25 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥20-41፣ 1ጴጥ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 2፥1-21 ወይም 2፥22_37። የሚነበው ወንጌል ዮሐ 20፥1-19 ወይም 14፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካች #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለመንፈስ_ቅዱስ (ለጰራቅሊጦስ) በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና ደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ወበ፶ ዕለት ፈነወ ሎሙ #መንፈሰ_ቅዱሰ ከመ ዘእሳት #ወተናገሩ_በነገረ_ኵሉ_በሐዉርት"። ትርጉም፦ #በሃምሳውም_ቀን_በእሳት_አምሳል_መንፈስ_ቅዱስን ሰደደላቸው #በአገሩ_ሁሉ_ቋንቋ_ተናገሩ። #ሊቁ_ቅዳሴ_ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ቅዳሴው_ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ጰራቅሊጦስ፦ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኃጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጉምን ይሰጣል መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ፤ ከትንሣኤ በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠርጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
❤ "እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ" አላቸው። ሁለተኛም "ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል" አላቸው።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው "እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናስበውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ"። ይህንንም ሲነግራቸው እንሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደ ርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ። የተከፋፈለ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ። በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ።
❤ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ "በዓለ ኃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ። ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ መላው የተከፋፈለ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀምጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየአገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና። ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ። "እንሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ፣ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን። በሁለት ወንዝ መካከል በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣ በፍርግያም በጽንፍልያም፣ በግብጽም፣ በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እንሆ እንሰማቸዋለን። ሁሉም ደግጠው የሚናገሩትን አጡ። እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው "ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል" አሉ።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው "የይሁዳ ሰዎቼ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደለም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና። ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለውነው፦ "እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴ አሳድራለሁ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁ ሕልምን ያልማሉ። ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ። ደግሞ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሓይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል"።
❤ ዳዊትም እንዲህ አለ "ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ድኅነትህንም ስጠኝ። በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው"። ሁለተኛም "መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ" አለ። ደግሞ "ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ" አለ። ደግሞም "በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"።
❤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ"።
❤ ጌታችንም እንዲህ አለ "ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ። ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። እኔ ሰላም እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣች። እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም። እኔ እሔዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ"።
❤ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ "እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይምሰክራል። እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና። ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሰዋል። ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንዲህም አታዩኝም ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና" አላቸው። "የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ። ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና"።
❤ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁ የሚለን"። ጌታ ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐውቀባቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ። እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል"።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 week ago
Last updated 3 days, 6 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 3 weeks ago