ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።
We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
-የዝዉዉር ዜና
-የአሰልጣኞች አስተያየት
-ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
-የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
-ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
አስተያየት ካሎት @ZENA_ARSENAL_BOT
ለማስታወቂያ ስራ +251911052777
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @MKHI7
Last updated 7 months, 3 weeks ago

The voice of Ethiopian football
For Adverisment ONLY : +251940018801
Last updated 7 months, 3 weeks ago
በጋምቤላ ክልል እየተከናወኑ ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል የጋምቤላ- አቦቦ -ፑኚዶ መንገድ ግንባታ በአካባቢው የሚገኙ ሰፋፊ እርሻ ልማትና የአሳ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያበረክተው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።
ከዚህ ባሻገር የመንገድ ግንባታው ህብረተሰቡ የነበረበትን የትራንስፖርት እጥረት ከመቅረፍ በተጨማሪ ለተለያዩ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በር የሚከፍት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ሙሉ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክትአሁን ላይ የግንባታ ሂደቱ ከ50 በመቶ በላይ መድረሱን ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይናው ሬልዌይ ቲዌኒ ፈርስት ግሩፕ አስታውቋል። በስፍራው ቅኝት ያደረገው ባልደረባችን ዓለምሰገድ አሳዬ ተጨማሪ አለው።
https://www.youtube.com/watch?v=vXsI-Tsg3ko
YouTube
የጋምቤላ -አቦቦ -ፑኚዶ መንገድ ግንባታ
#FANA\_TV #FANA\_NEWS #ፋና\_ዜና በጋምቤላ ክልል እየተከናወኑ ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል የጋምቤላ- አቦቦ -ፑኚዶ መንገድ ግንባታ በአካባቢው የሚገኙ ሰፋፊ እርሻ ልማትና የአሳ ሃብትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያበረክተው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል። ከዚህ ባሻገር የመንገድ ግንባታው ህብረተሰቡ የነበረበትን የትራንስፖርት እጥረት ከመቅረፍ በተጨማሪ ለተለያዩ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች…




በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የወይጦ-ቱርሚ 120 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ የግንባታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡
በእስካሁኑ የሥራ እንቅስቃሴ የጠረጋ ሥራ፣ የቆረጣ ሥራ፣ የሰቤዝ እና የቤዝኮርስ ሥራ፣ የአፈር ሙሌት፣ ሥራ እና የስትራክቸር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ የሰባት ድልድዮች ግንባታም በፕሮጀክቱ የተካተተ ሲሆን÷ አሁን ላይ የዲዛይን ስራዎችን አጠናቆ በቅርቡ ወደ ግንባታ ስራ ይሸጋገራል።
ግንባታውን ራማ ኮንስትራክሽን እያከናወነ ይገኛል፡፡ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ፕሮሜ ኮንሰልቲንግ እና ኦሜጋ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ በጥምረት እየሰሩ ነው፡፡ ለግንባታው የሚያስፈልገው 2,843,185,710 ብር ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል፡፡
የወይጦ-ቱርሚ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን ሶስት ሰዓት ተኩል የጉዞ ጊዜ በሁለት ሰዓታት የሚያሳጥር ሲሆን÷ በዋናነት የወይጦ፣ አልቦሬ እና ቱርሚ ከተሞችን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ያገናኛል፡፡ በፕሮጀክቱ ክልል ስር የሚገኙ አነስተኛ የገጠር ቀበሌዎች ወደ ከተማነት የሚያድጉበትን ምቹ እድል ይፈጥራል፡፡
በተጨማሪም ሥፍራው የኩራዝ ስኳር ፋብሪካ፣ የኦሞ ሸለቆ አርኪኦሎጂካል ሳይት እንዲሁም በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ብሔረሰቦች ባህላዊ እና ቁሳዊ የቱሪስት መስህቦች (በተለይም የሐመር ብሔረሰብ) መዳረሻ እንደመሆኑ ፋይዳው ከፍተኛ ነው፡፡
የኦሞ ወንዝን ተከትለው በሚገኙ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች የሚመረቱ የተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ በጥራትና ፍጥነት በማድረስ በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ አለው፡፡
ነባሩ መንገድ በጠጠር መንገድ ደረጃ ያለ እና በአገልግሎት ብዛት በእጅጉ የተጎዳ ነው፡፡ እሁን ላይ መንገዱ ካለው ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ሲሆን÷ በገጠር 10 ሜትር እንዲሁም በከተማ 21.5 ሜትር የጎን ስፋት ይኖረዋል፡፡

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
-የዝዉዉር ዜና
-የአሰልጣኞች አስተያየት
-ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
-የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
-ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
አስተያየት ካሎት @ZENA_ARSENAL_BOT
ለማስታወቂያ ስራ +251911052777
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @MKHI7
Last updated 7 months, 3 weeks ago

The voice of Ethiopian football
For Adverisment ONLY : +251940018801
Last updated 7 months, 3 weeks ago