ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የያቤሎ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክትን በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው
ያቤሎ፣ ታኅሣሥ 03፣ 2017 ዓ.ም (ኢ መ አ):- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ቦረና ዞን በ304 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የያቤሎ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
የመንገድ ፕሮጀክቱ 7 ነጥብ 44 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ የዞኑ መቀመጫ ለኾነችው ያቤሎ ከተማ ተጨማሪ አማራጭ ኾኖ የሚያገለግል ነው። በተለይም በያቤሎ -ኬላ ነባር መንገድ ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ ጭንቅንቅ ያስቀራል፡፡
ከዚህም ባለፈ በአቅራቢያ ከሚገኙ የጎሮቤት ሀገራት ጋር ያለውን የወጪ እና የገቢ ንግድን በማቀላጠፍ በኩልም አዎንታዊ ሚና ይጫወታል፡፡
አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 91 ነጥብ 43 በመቶ ደርሷል። እየተከናወኑ ከሚገኙ የግንባታ ሥራዎች መካከል የ87 በመቶ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የ99 በመቶ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የ7 ኪሎሜትር ሰብቤዝ፣ የ6 ኪሎሜትር ቤዝኮርስ እና የ5 ኪሎሜትር አስፋልት ሥራዎች ተከናውነዋል። በተጨማሪም የአንድ ድልድይ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።
ግንባታው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
መንግስታዊው የልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግንባታውን ያከናውናል። ቤስት ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ፕሮጀክቱን የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ይሠራል። የግንባታው ወጪ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግስት ይሸፈናል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana