ልሣነ አምሐራ ሚዲያ

Description
በዚህ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ እለታዊ ዘገባዎች እንድሁም ፈጣን ዜናዎች ይቀርባሉ።

ለማንኛውም ጥቆማ በ @lisaneamhara ያናግሩን‼️
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

5 months, 2 weeks ago

በእጅጉ ሊዳረስ የሚገባው የጥንቃቄ መልዕክት

የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት አዲሱ ዕቅድ… አባሎቹን በህዝብ ማመላለሻና በጭነት መኪኖች በመጫንና ከጭነት ጋር በመመሳሰል ኬላ ላይ ያሉ ፋኖዎቻችን ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመፈፀም ማቀዳቸውንና በአንዳንድ አካባቢዎችም እቅዱን እንደሞከረ ተሰምቷል።

መልእክቱን አዛምቱ
ባህርዳር ዊክለስ

5 months, 2 weeks ago

"መሪውን ለመፍጠር ድርጅት እናቁም"
//////////////////////////////////////////

ሀገር ለማስተዳደር አቅም፣ችሎታ፣እውቀት፣ክህሎት እንድሁም ደግሞ #የመታጋየ መስመሮችና ድርጅታዊ መዋቅር ያስፈልጋል።

ስለሆነም የአማራን ቤት በማይናወጥ አለት ላይ ለመስራት እጅግ ብልሃት የተሞላበትና ለብዙሃን ግልፅ እና አካታች መርሆችን የጠበቀ አሰራርን በመከተል የጋራ ቤታችንን በፍጥነት ልናዋቅረው ይገባል።

ትግሉ የበርካታ ፍላጎቶች ትግል እና ሁሉም ሃይሎች በጋራ በወዳጅነትም በጠላትነትም እየተሳተፉበት ይገኛል።
መፍትሔው ህዝብና ታጋዮ ሰራዊታችን የሚያምንበትን ድርጅታዊ አካሄድ መከተል ብቻ ይጠቅማል።

ጠላቶቻችን የእኛኑ ድክመት እየተጠቀሙ ሃይል እያባከኑብን መሆኑ እየታወቀ ለልዩ ልዩ አጀንዳዎች ተጋላጭ መሆን ተገቢነት ያለው አካሄድ አይመስለኝም።

በሁሉም ዘርፍ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ስክነት፣መተማመን፣መደማመጥ ፣ ተግባቦት እና ድስፕሊን ያስፈልጋል።

ስለሆነም ሁላችንም በትግሉ ሜዳ የምንገኝና በውጭ ሆናችሁ ለምትደግፉ አካላት የሚከተሉትን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ።

1ኛ.ግለሰቦች ከህዝብና ድርጅት በላይ እንዲሆኑ እድል መስጠትም ሆነ መፍቀድ የለብንም።

2ኛ.የሚታገለውን ሰራዊት እና የሚያታግለንን ህዝብ መብት እና ጥቅም አሳልፈን ባለመስጠት ሃላፊነታችንን እንወጣ!!

3ኛ.በመሪዎቻችን፣በአታጋዮቻችንና በህዝባችን መካከል ልዩነት መፍጠርንና አነሳሺ ሃሳቦችን ባለ መስጠት እንተባበር።

4ኛ.የዳያስፓራ ወንድሞቻችንን፣የትግሉን ደጋፊዎች እና ለሀቅ የሚታገሉ አማራዎችን በጅምላ መፈረጅ፣መሳደብ እና አበርክቷቸውን ከማሳነስ እንድንቆጠብ እመክራለሁ።

5ኛ.በታሪክ አጋጣሚ የተገኘውን የፋኖና የህዝብ ትግል በጥቅም ና በመሰል አሻጥሮች አሳልፈው ለመስጠት ከሚሰሩ የትኞቹም ሃይሎች ጋር እገዛ ትብብር ባለማድረግ ታሪካዊ ሃላፊነታችንን በጋራ እንወጣ!!

6ኛ.መደማመጥ፣መነጋገር፣በሀሳብ የበላይነት ማመንና ከአላስፈላጊ ስግብግብነት ራሳችንን መቆጠብ ያስፈልጋል።

ስለዚህ ለህዝብ፣የህዝብ እና በህዝብ የሚታመን አታጋይ መሪና ድርጅት ለመፍጠር የሁላችንም አቅምና ትብብር ስለሚሻ ሁሉም የሚችለውን እንድያደርግ ወንድማዊ ጥሪየን አስተላልፋለሁ።

አሸናፊ ገናን
ከትግል ሜዳ

@ethiozena24

5 months, 2 weeks ago
ልሣነ አምሐራ ሚዲያ
5 months, 2 weeks ago
በአማራ ክልል ጦርነት አውጆ የአገር መከላክያ …

በአማራ ክልል ጦርነት አውጆ የአገር መከላክያ ሰራዊትን ያስጨረሰው ሰውዬ የፓድላማ አሻንጉሊቶችን ለሐምሌ 24/2016 ዓም አስቸኳይ ስብሰባ  ጠርቷል።
የስብሰባው ዓላማም የድሮን ተተኳሽና ሌሎች መሳሪያዎችን ለመግዛት ከዓለም ባንክና ከIMF ብድር ለማግኘት ሲል የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ያንኮታኮትኩበትን ውሳኔ አፅድቁልኝ የሚልና ፋኖንም በአሸባሪነት ሊፈርጅ ይችላል የሚል መረጃ እየወጣ ነው።
የሚኒስትሮች ም/ቤት አባላትም ስብሰባላይ መሆናቸው ታውቋል።
የሚሆነውንና የሚወሰነውን ውሳኔ ወደፊት ተከታትለን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

#ድል_ለአማራ_ፋኖ ?

@ethiozena24

5 months, 2 weeks ago

አስቸኳይ ሸር ይደረግ‼️

ከባሕርዳር ወደ አዴት መስመር አንድ ዲሽቃ የጫነ በግምት 50 የማይበልጥ አራዊት ሰራዊት ጉዞ ላይ ነው።

ሼር በማድረግ ለወገን ሀይል እናድርስ!!!!!

@ethiozena24

5 months, 2 weeks ago
ልሣነ አምሐራ ሚዲያ
5 months, 2 weeks ago
ሲዳማ ክልል በጎፋ የደረሰው ጉዳት መከሰቱ …

ሲዳማ ክልል በጎፋ የደረሰው ጉዳት መከሰቱ ተሰማ‼️

በትናንትናው ምሽት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 (ስድስት) ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም አደጋም ደርሷል፡፡

በተጨማሪም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጓዙ በነበሩት ሰዎች ላይ በውሃ ሙሌት ምክንያት በደረሰው አደጋ የሰው ሕይወት አልፏል፡፡

5 months, 2 weeks ago
[#የድል](?q=%23%E1%8B%A8%E1%8B%B5%E1%88%8D) ዜና!!!

#የድል ዜና!!!
የብልፅግናው ወንበር ጠባቂ ደብረብርሃን ከተማ አቅራቢያ በጀግናው ይገረም ከበደ በሚመራው ነጎድጓድ ክፍለጦር ድባቅ ተመታ።
ሐምሌ 23/2016 ዓ/ም
ሸዋ አማራ
የብልፅግው ወንበር ጠባቂ ደብረብርሃን ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ለልዩ ግዳጅ የተዘጋጁ መብረቁ ፣ጋተውና አንበሳው ብርጌድ የተወሰኑ ሻለቆችን ለመደምሰስ መነሻውን ደብረብርሃን ከተማ በማድረግ በአራት አቅጣጫ ከሃያ በላይ አብቶቢስ አግተልትሎ ትናንት ሐምሌ 22 /2016 ዓ/ም የመጣው የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ድቡት በሚባል ቦታ ከፊሉ ግብዓተ መሬቱ የተፈፀመ ሲሆንየተወሰነው ቁስለኛና እድል የቀናው ተበታትኖ ፈርጥጧል።
ይንን ሁኔታ ይቀይራል በሚል ጊናገር ከተማ አከማችቶት የነበረውን ኃይል ወደ አሳግርት ከተማ በማግተልተል ላይ ሲሆን እስካሁን ባለ መረጃም በመብረቁ፣ጋተውና አንበሳው ብርጌድ ውስን ሻለቆች የተናበበ ዉጊያ ሁለት የጠላት ምሽግ ተሰብሯል።
ዝርዝር ጉዳዩን እንመለስበታለን።
"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

5 months, 2 weeks ago

ጥንቃቄ‼️

ባህር ዳር ዙሪያ በተለይ ሰሜን አቸፈር መስመር ቁንዝላ ጭምባ ያላችሁ ፋኖዎች ጥንቃቄ አድርጉ!
የድሮን ቅኝት አለ!!

@ethiozena24

5 months, 2 weeks ago

ቤተ አምሐራ ላስታ
የአሳምነው እስትንፋሶች?
#ድል_ለአማራ_ፋኖ

@ethiozena24

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana