ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад
የአገዛዙ ጦር የፋኖን ቦተሰቦች እያገተ መሆኑ ተሰማ!
በአማራ ክልል ከአንድ አመት በላይ የሆነው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉ የሚታወቅ ሲሆን በአውደ ውጊያ የተሸነፈው የብርሀኑ ጁላ ዙፋን ጠባቂ ወታደር በሜጫ እና ሌሎችም አካባቢወች ያሉ የፋኖ ቤተሰብ አባላትን በማፈን ግፍ እየጸፀመ መሆኑን የአሻራ ሚዲያ የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል። አንድ የፋኖ ቤተሰብ ለአሻራ እንደገለፀው'' እኔን ልጀ ፋኖ ስለሆነ ብቻ ከቤቴ ከተኛሁበት በጥዋት መጥተው መሰዱኝ ከዛም በግት እኔን ከወሰዱኝ ከ ሁለት ሰአት በሗላ ባለቤት እና ሴት ልጀን አመጧቸው ሁላችንንም በንድ ክፍል አሰገብተው ከደበደቡን በሗላ አሳድረው ልጃችሁን አምጡት ካላጣችሁት በቀጣይ ስንመጣ እንገላችሗለን ብለው እንደዛቱባቸው ''ባለታሪካችን ስሙ እንዳይጠቀስ በመግለፅ ለአሻራ ሚዲያ ተናግሯል።
ለዚህ አፈና እግታ እና እንግልት ደግሞ በዋነኛንት መሪ ተዋናይ በመሆን የሚያገለግሉት የሚኒሻ እና የፖሊስ አባላት መሆናቸውን ተናግሮ እኛን ብቻ ለቀቁን እንጅ ከአምስት እና ስድስት ቀን በላይ የሆናቸው ምግም ውሀም የማይቀርብላቸው ቤት ተዘግቶባቸው የሚውሉ የፋኖ ቤተሰቦች ታፍነው እንደሚገኙም ግፍ የደረሰበት የፋኖ ቤተሰብ ከአሻራ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ አስረድቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የፋኖ ምላሽ ምን እንደሆነ አጣርተን የምመለስ ይሆናል!!
#አሻራ_ሚዲያ
ጎጃም‼
ዳሞት አውራጃ ቡሬ እስከ ቁጭ እንዲሁም እስከ ሽንዲ ወንበርማ ዙርያውን የአዬር ቅኝት ተደርጓል።
አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ መረጃው ይዛመት‼
አሻራ ሚዲያን ይወዳጁ
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@asharaashara-124?si=iM_9tCLjVjVhx-0N
ረምብል
https://rumble.com/v5etpbu-327231354.html
ቴሌግራም
https://youtube.com/@asharadaily?si=OOO1RL2rDjF-2ngM
https://t.me/ashara_media
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900
በተጨማሪም ማነኛውም አይነት መረጃ ለማድረስ
በቀጥታ የስልክ መስመር
👇👇👇👇
0993111700 ወይም
በቴሌግራም
👇👇👇👇
@asharamedia2
ማድረስ ይችላሉ።
ለልማት በሚል ስም ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች የተሰጣቸው ግዚያዊ መኖሪያ ቤት የባለቤትነት ውል የሌለው እና ማንም አካል በፈለገው ሰዓት ውጡ ብሎ ማባረር የሚችል ዋስትና የሌለው መሆኑ ታወቀ።
አንዳንዶች ይህ ደባ እየተሰራ ያለው በሚቀጥለው ምርጫ ብልጽግናን ካልመረጣችሁ ይህ ቤት በስማችሁ አይጸድቅም ብሎ በማስፈራራት ከወዲሁ ሆዞቡን ወደ ማነቂያ ጉድጓድ እየከተቱት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
#አዲስ_አበቤ_ተበላ..!!!
ስትሞት አንተ ብቻ ትሞታለህ - በአንተ ቦታ ማንም አይሞትም። ሞትህ ፍፁም ግለሰብ ይሆናል። ሞት አንድ ነገር ብቻ ያረጋግጣል, እያንዳንዱ ግለሰብ (ግላዊ) ነው። ሞትም ያንተ ይሆናል፤ ታዲያ ህይወትህ እንዴት የሌላ ሰው ትሆናለች። የተበደረከውን ህይወት መኖር አትችልም። ስለዚህ የራስህን ህይወት መኖር አለብህ። ሞትም ያንተ ይሆናል - ማንም አይሞትልህምና።
፦ ኦሾ/Osho
ወዳጄ በእውቀቱ እንደፃፈው... #ሼር አድርጉት!
የሚያሳስበኝ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዶስተየቨስኪይ የተባለ የሩስያ ደራሲ ልቦለድ ውስጥ የሚገኝ ኢቫን የተባለ ገጸባህርይ ” ሰውን አውሬ ብሎ መጥራት አራዊትን እንደ መስደብ ይቆጠራል ይላል ፤” ሰው የበጎነት አቅም ያለውን ያህል ፥ በጭካኔ የሚወዳደረው የእንስሳ ዝርያ የለም፤ አንበሳ ሚዳቆን የሚገድለው በልቶ ማደር ስላለበት ነው፤ ሳይቸግረው ያለ አላማ መሰሉን፥ የሚገድል፥ ብጤውን በማሰቀየት የሚደሰት ፍጡር ሰው ብቻ ነው፤
ልጅ ሆኜ በጎችን አሰማራ ነበር፤ ግልገል በግ የሚደፍር ትልቅ በግ አይቼ አላውቅም ፤ ወንዱ በግ ፥ደረሰች በግ ላይ ለመውጣት ራሱ ወቅት ይጠብቃል፤ ለርቢ መድረሷን አሽትቶ ካላረጋገጠ በቀር አይደርስባትም፤
የሰባት አመትዋን ሄቨንን ለመስማት በሚገዘገንን ጭካኔ ደፍሮ የገደላትን ሰውየ “ እንስሳ ፥ወይም አውሬ” ብሎ መጥራት ፍትሀዊ የማይሆነው ለዚህ ነው፤ እንዲህ አይነቱ ቀፋፊ ፍጡር የሚገልጽ ሌላ ቅጽል ተፈጥሮ መዝገበቃላት ውስጥ መካተት አለበት፤
ህግ ካለ ይህ ወንጀለኛ እንደ ምግባሩ ፍዳውን መቀበል ይገባዋል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሞከሩ እና የዶለቱ ሁሉ ከቅጣቱ ድርሻቸውን ማንሳት አለባቸው፤
አስገድዶ ደፈራ በዋናነት የወሲብ ጉዳይ አይደለም፤ የፈሪዎች እና የግፈኞች “ሀይል “ መግለጫ ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰባ ምናምን አመት ሴት የደፈረ ጎረምሳ በአስራት መቀጣቱን የሚገልጽ ዜና ማንበቤ ትዝ ይለኛል ፤ የሰባ አመት ባልቴት እና የሰባት አመት ሴት ሁለቱም ለሩካቤ የሚያሳስብ ነገር የላቸውም፤ ግን ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው አቅም አልባ መሆናቸው ነው፤ ራሳቸውን ከደፋሪው መከላከል አይችሉም፤ ደፋሪዎች ብዙ ጊዜ ፈሪዎች ናቸው፤ ከሚበልጣቸው ጋራ ወይም ከእኩያቸው ጋራ ጉልበት እንደማይፈታተሹ ያውቁታል፤ በጉልበት የሚያንሳቸውን፤ ሀብት ስልጣን ወይም ወገን የለውም ብለው የሚያስቡትን ከማጥቃት ግን አይመለሱም፤ ብዙ ጊዜ የጥቃት ሰለባዎችን ስናይ ህጻናት፥ የቤት ሰራተኞች፥ እንግዶች፥ የመንገድ ዳር ተዳዳሪዎች ወይም በጦርሜዳ ላይ ያለ ታዳጊ የቀሩ ሴቶች ናቸው፤
ለወላጆች አንድ የጭንቅ ቀን ምክር አለኝ፤ ጨካኝ ፤ጭቦኛና ቀፋፊ ባህርይ ያላቸው ሰዎች
የትም እና መቼም ይኖራሉ፤ሰርሲ ላንስተር እንደተናገረችው Everywhere in the world they hurt little girls ."
ፈታኝ አለም ውስጥ እንደምንኖር አንርሳ፤ ሁሌም በህግ በፈሪሀ እግዚአብሄር እና በባህል በጭምት ፊት ተማምነህ መዘናጋት የለብህም፤የልጆችህ ወታደር መሆን አለብህ ፤ ልጆችሽን እንደ አይንሽ ብሌን ጠብቂ ! ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ግን ሌላ ምን አማራጭ አለ?
#ሼር አድርጉት
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад