የተዋሕዶ ፍሬዎች

Description
Buy ads : here
https://telega.io/c/yetewah
🎯 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
👉 መዝሙር
👉ብሒለ አበው
👉ስብከት
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
🎯የሚለቀቅበት መንፈሳዊ ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ

የተዋህዶ ፍሬዎች መንፈሳዊ ቻናል
ለአስተያየት 👉 @Teyaka_Lemtykebot
ማስታወቂያ ለማሰራት ከፈለጉ @fikreabe ላይ ያናግሩን
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

2 weeks ago

[✞ ይለይብኛል ሚካኤል ✞

ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

አዝ====
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

አዝ====
ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ===
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ](https://t.me/yetewahedofera)

2 weeks ago

ኅዳር 12

~ ለውጦ ማክበር ~

ንግሥት ክሌዎፓትራ "ሳተርን" ለሚባል ጣዖት ያሠራችው ቤት በእስክንድርያ ነበር። ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እለ እስክንድሮስ ፓትርያርክ ዘመን 212-326 ድረስ ነበር። እለእስክንድሮስም ሊያጠፋ ሲነሣ በሕዝቡ ልቡና ገና አምልኮ ጣዖት ስላልጠፋላቸው 18 ፓትርያሪኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት። እለእስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል  ይውልበት የነበረበትን ዕለት ወደ ቅዱስ ሚካኤል የበዓል ዕለት አደረገው። (ስንክ ሳር ኅዳር 12፣ Coptic Encyclopedia, Vi S.p 1617)።

ከእምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የእስክንድርያ ሰዎች በእለ እስክንድሮስ በኩል እየበረሩ ገቡ። የጣዖት መክበሪያ የነበረው በእለ እስክንድሮስ ጸሎት የቅዱስ ሚካኤል መክበሪያ የእግዚአብሔር መመስገኛ ኾነ። ይህን ቤተ ጣዖት ሳስብ ምናልባት በኃጢአታችን ምክንያት የእኛን ሰውነት የሚወክል ይኾን እላለሁ። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን የአጋንንት መርኪያ ቤተ ዘፈን አድርገነዋልና።

የሰው ልቡና የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ነው። ኾኖም ሰዎች ሰውነታቸውን እያረከሱና ከእግዚአብሔር ፍቅር እየራቁ ሲሄዱ የአጋንንት መኖሪያ ሊያደርጉት ይችላሉ። በመኾኑም የሕይወታችን ዋና ጉዳይ መኾን ያለበት መቅደስ ሰውነታችንን መጠበቅ ነው። በእለእስክንድሮስ አምሳል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ካህናትን በቅዱስ መስቀል ባርከው እንዲያነጹን መቅረብ ነው። ዝሙት የተባለ ጣዖት በልቡናችን ውስጥ የያዘውን ቦታ በካህናት ፊት ተናዘን እንድንነጻ የሚያደርገውን የንስሐን ቀኖና መቀበል ነው። ሕይወታችንን እያዛጉ ያሉትን ማናቸውንም ባዕድ የኾኑ ነገሮች በልቡናችን ውስጥ ሥር እንዳይዙ መጠንቀቅ ነው።

በእርጥም እኛ ፈቃዳችንን ለእለእስክንድሮሳዊ ፈቃድ ካስገዛን ሰውነታችን የቅዱሳን መላእክት በዓል መክበሪያ ወደ መኾን ይታደሳል። ቅዳሴ፣ ማኅሌትና ልዩ አገልግሎት ያለማቋረጥ የሚቀርብበት ንጹሕ መቅደስ ይኾናል። እንግዲያውስ ኹላችንም በሰውነታችን ውስጥ ቅዱስ ሚካኤልን እንፈልገው፤ በበዓልነት በእኛ ውስጥ እንዲከብር እንፍቀድ። ሰዎች የቅዱስ ሚካኤልን ያማረ የምልጃ ሽታ በእኛ ሰውነት ውስጥ እንዲያሸቱት እናድርግ! ወደ ቅዱስ ሚካኤላዊ የአገልግሎት ሕይወት ለመግባት እንመኝ፤ ደጋግመንም እንሻ!

( "ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው" fb የተወሰደ ።)

እንኳን አደረሳችሁ!!

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

2 weeks, 1 day ago
3 months, 1 week ago

?በዚህ በ2016 የቀረችዋን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ‼️
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
? ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ ግእዝ መማማሪያ ቻናላችን ግእዝ በነፃ እየገለፅን  ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  ስለሆነ ትምህርቱም በonline ስለሆነ በዚህ #ዙር ላይ 1000 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠ ለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለመማር የምትፈልጉ ለመመዝገቢያ ብቻ 150 ብር   ብቻ ነው ክፍያው መማር ለሚፈልጉ ሼር አድርጉ ።

? የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም?‍?
?በዚህ አንዱን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ‼️

ለመመዝገብ ምትፈልጉ ከታች ባለው አካውን አናግሩን
@rufael_yiliybegal
@rufael_yiliybegal
@rufael_yiliybegal

የቻናሉ ሊንክ ???
https://t.me/+MQhYKhzFQK05ZmY0
https://t.me/+MQhYKhzFQK05ZmY0
https://t.me/+MQhYKhzFQK05ZmY0

3 months, 2 weeks ago

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን

ነሐሴ ፲፮ ቀን በየዓመቱ የነሐሴ ኪዳነ ምህረት ተብሎ የሚከበርበትን ምክንያት ከዚህ እንናገራለን እናስረዳለን እመቤታችን
በስድሳ ዐራት ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ባረፈች ጊዜ ሐዋርያት በክብር እንቀብራታለን ብለው ሲያስቡ አይሁድ አስከሬኗን ለማቃጠል
በመሞከራቸው ማኅደረ መለኮት ናትና «በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና ስሙ ቅዱስ ነው» ያለችው ልጇ በታላቅ ኀይል ተገልጦ
በመላኩ አማካኝነት ሥጋዋን ከአይሁድ ነጥቆ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ምስክር አድርጉ ወስዶ በገነት አኖራት።
ዮሐንስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ተመልሶ ለሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋዋ በዕፀ ሕይወት ሥር መኖሩን ነገራቸው። ቅዱሳን
ሓዋርያትም ቅዱስ ዮሐንስ ያየውን ይህን ድንቅ ምሥጢር እንድናይ ሱባዔ ገብተን እንልምን ብለው ሰኞ ቀን ነሐሴ አንድ ቀን
ሱባዔውን ጅምረው ደጅ ሲጸኑ ሳለ በሁለተኛው ሱባዔ መጨረሻ በ፲፬ኝው ቀን እሑድ አምጥቶ አስከሬኗን ሰጥቷቸው
ቀብረዋት በሦስተኛ ቀን መግሰኛ ተሥታ«አዕርግዋ መላእክት ውስተ ሰማያት» እንዳለው ቅዱስ ያረደ በዝማሬ ዳዊት በይባቤ
መላእክት ዐርጋለች።
ትንሣኤዋና ዕርገቷም ከሁሉ ቀድሞ የተገለጸው ለሐዋርያው ቶማስ ነበር «ከውኃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን
ነጠቀው … ፊልጶስ ግን በአዛጦን ተገኘ» (የሐ/ሥራ.፰፥፴፱)። ተብሎ እንደተጻፈው ሐዋርያው ቶማስ በመንፈስ ተነጥቆ በደመና
ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ደንግል ማርያም ከሞትና መቃብር በልጇ ኅይል ተነሥታ ስታርግ በሕዋው
ላይ ተገናኝተዋል። እርሱም ተባርኮ ለሐዋርያትም ምስክር የሚሁን ሰበኗን ሰጥታው ይዞ ወደ ሐዋርያት ደረሰ። እርሱም
የያዘውን በልቡ ይዞ የእመቤታችን ነገር ሚሥጢሩ ምን ይሆን እንዴት ሆነች ያወቃችሁት የተገለጸላችሁ ምሥጢር አለን? 
ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም ሱባዔ ገብተን ሁለት ሱባዔ ደጅ ፀንተን ጌታችን ሰጠን በክብር በጌቴ ሴማኒ ቀበርናት አሉት።
እርሱም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እኔ አላምነም እንዲህ ያለውን ነገር አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ ሁል ጊዜ
እንደተጠራጠርክ ትኖራለህ የልጇን የጌታችንን ትንሣኤ ተጠራጥረህ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ደግሞ የእመቤታችን ትንሣኤ
እንሄድ መቃብሯን አይተህ እመን ብሎ ይዘውት ሄዱ። መቃብሯን ቢያዩ ባዶ ሁኖ አገኙት ደነገጡ። እርሱም አትደንግጡ እመቤታችን ተንሥታለች ዐርጋለች ብሎ የሚያቁትን ሰበኗን አሳያቸው ወይም ሰጣቸው እነሱም እውነት ነው በዚህ ነው
የገነዝናት ብለው አምነዋል ደስም ተስኝተዋል።
ሰበኗንም ተካፍለው ወስደው ድውይ ሲፈውሱበት ሙት ሲያስነሡበት ኑረዋል። በዓመቱ ቶማስ ያየውን ዕርገቷን ለማየት
በመጓጓት ድንግል እሜቤታቸውን ስልሚናፍቋት ለማየት ሺተው እግዚአብሔርም የተለመደውን ቸርነቱን
እንደሚያደርግላቸው በማመን በድጋሜ ሱባዔ ገቡ። እንደ ሊቃውንተ ኦርቶዶስ ትምህርት ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ነበር። እንደ
ዘንድሮው የ፳፻፲ ዓ/ም ነሐሴ ማለት ነው። ያን ጊዜ ነሀሴ ማክሰኞ ይብታል፤ ከማግሰኞ እስከማግሰኞ ስምንት ከማግሰኞ እስከ
ማግሰኞ ፲፭ ረቡዕ ፲፮ ይሆናል በዚህ ዕለት ጌታ ራሱ ተገልጾ ሠራዒ ካህን ሆኖ ከሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳዒ ካህን
አድርጎ፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ወተቄረበት በዕደ ወልዳ ይላል
እርሷም በልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ሁሉ ደስ የሚያሰኝ ክንውን በኋላ ስምሺን የጠራውን መታሰቢያሺን ያደረገውን
እምርልሻለሁ ብሎ ለእመቤታችን፤ ስማችሁን የጠራውን መታሰቢያችሁን ያደረገውን ስብከታችሁን ስምቶ ያመነውን ሁሉ
እምርላችኋለሁ ብሎ ለሐዋርያት ተፋውን ነግሯቸው ቶማስ ያየውን ዕርገቷን እየሳያቸው ወደሰማይ ዐርጓል። 
በሰጣት ተሰፋ በገባለት የምህረት ኪዳኗ በየዓመቱ ለሰፊ ዘመናት በዓሏን እንድናክብር ይርዳን፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera

3 months, 2 weeks ago

እንኳን ለእናታችን ቅድስት ኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

3 months, 2 weeks ago

[?ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? ? ?

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
? ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
? ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
? ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
? ዘማሪ አቤል መክብብ ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
?ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
?ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
? ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
? ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ ?
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

?? የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት ? ?
??????????????

3 months, 2 weeks ago

[ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና

ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው

ሼር ያድርጉ
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera](https://t.me/yetewahedofera)

3 months, 2 weeks ago

[ሌሎች የደብረ ታቦር ግጥም ምዝሙር ጭውውት ለማግኘት ከላይ ያለውን forward በመንካት የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ

መንፈሳዊ ግጥም

ደብረ ታቦር

ከደብሮች ሁሉ ልቀሽ
እውነት ብርሃንን አጥልቀሽ
ተንቀሽ የነበርሽ ተራራ
አንቺ የምሥጢር ሥፍራ
የመለኮት ብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ምሥጢር
ልቆ የታየብሽ መንደር
ደብረ ታቦር!!!
ከአድማሳት ከፍ ከፍ ብሎ
የስምሽ ተረፈ ውሉ
የተዘከረው በዓለሙ
ምን ይሆን ወርቅ ሰሙ?
ምን አገኘሽ ያኔ ታቦር
እንዲያ ተከፍቶ የብርሃንሽ በር
የክብሩ ግርማ የዋጠሽ
እኮ ማን ነው የረገጠሽ?
ጌታሽ ነው አሉ ስሰማ
ከተራራሽ አናት ማማ
የብርሃን ጉንጉን ሸማ
ያጎናፀፈሽ በግርማ
ግሩም እኮ ነው!
ከተራሮች አንቺን መርጦ
ከነአባቱ ተገልጦ

ደጅሽን ሳይንቅ ማክበሩ
እንዴት እንዴት ይሆን ምሥጢሩ?
ይህንንም ደግሞ ዳዊት
ተናግሯል አሉ በትንቢት
ታቦር ወአርሞንኤም በሚል ቅኔ
በስሙ ተደሰቱ ያኔ
እያለ ዘመረ በክብር
የዚህችን ተራራ ምሥጢር
ያ ልበ አምላክ ዳዊት
የተናገረው ትንቢት
ለካ ይህ ኖሯል ግቡ
ደጅሽ በብርሃን ማበቡ
ኧረግ! አንቺስ ታድለሻል
የማይቻለውን ችለሻል
እሳተ መለኮትን ይዘሻል
ለመሆኑ እንዴት ቻልሽው ታቦር
ያን እውነተኛ ፍቅር?
ከመንበሩ የሳበው ንጉሥ
በብርሃን ሠረገላው ሲፈስ
መሠረትሽ ሳይናጋ
ባለበት ቆሞ የረጋ
ምን ይሆን ምሥጢሩ የፅናትሽ
በፊቱ ቆመሽ መታየትሽ?
ልብሱ ነጭ ሆኖ በረድ
አብም ከሰማይ ሲወርድ
ዙሪያው በክብር ደመና
ተመልቶ በብርሃን ፋና
ሙሴ ከመቃብሩ ተጠርቶ
ኤልያስ ከብሄረ ሕያዋን መጥቶ
በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው
ሲወያዩ ላስተዋለው
ምን ይመስል ይሆን ገጹ?
የብርሃን መለኮት መገለጹ
ደግሞ የሐዋርያቱ
የእነዚያ የሦስቱ
ሲጋልቡ ርደው
እንደ ቄጤማ ወርደው
ከሰሩ የተነጠፉቱ
ምንድን ይሆን ምክንያቱ?
ጴጥሮሰማ ተሽብሮ
ናላው በድንጋጤ ዞሮ
ለእያንዳንዳችሁ በጋራ
ሦስት ዳሶችን እንስራ

ብሎ በዚያች የብርሃን እልፍኝ
የዘለዓለም ደስታን ሊያገኝ
አስቦ በቅጽበት መመኘቱ
ገርሞትም አይደል ክስተቱ
የብርሃን ፀዳል ድምቀቱ?
እኮ እንደምን አይገርመው
ሙሴና ኤልያስ ቆመው

ክብሩን ሲያውጁ እያዩ
ማነው የሙሴን አምላክ ሙሴ ባዩ?
ሲል ሙሴ ባሕር ከፋዩ
የኤልያስንስ ክብር ጌታ
አውርደውት ከሰው ተርታ
ኤልያስ ባዮቹ እነማን ናቸው?
ሲል ኤልያስ ገርሟቸው

ይህን ሲሰሙ ሐዋርያቱ
በድንጋጤ ሲመቱ
ደግሞ ወርዶ አባቱ
ልጄን ስሙት በማለቱ
በፍርሃት ማዕበል ሲንገላቱ
ይህ ሁሉ ምስጢር መታየቱ
በአንቺም አይደል ታቦር
መገለጹ የሦስትነት ምስጢር
ጥንትስ ታሪክሽ ተዘክሮ
መቼ ያልቅና ተነግሮ
እንዲያው ድንቅ
እንበል እንጂ ድንቅ ድንቅ!
የብርሃንሽ ሰንደቅ
ከአድማሳት ልቆ ሲደምቅ

ክብር እንበልሽ ክብር!ክብር!
አንቺ እውነተኛ የምስጢር በር
የሥሉስ ቅዱስ ነገር
የተገለጸብሽ መንደር
ደብረ ታቦር!!!
ያበራሽ ይብራ ስሙ ይግነን
ዛሬም ለእኛ ብርሃን ይሁነን
ገኖ ያግነን በፈቃዱ
በራ ይሁንልን መንገዱ
ክብሩም ከፍ ከፍ ወደ ላይ
ከሰማየ ሰማያት በላይ
እንዲሁም በምድር በቀላይ
የአምላካችን አዶናይ
ክብርሽ ዛሬም ነገ ይነገር
መሆንሽ እውነተኛ የብርሃን በር
የሥሉስ ቅዱስ ምስጢር
የተገለጠብሽ መንደር ደብረ ታቦር!!!

ወስበሐት ለእግዚአብሔር።
https://t.me/yetewahedofera](https://t.me/yetewahedofera)
ሼር ያድርጉ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago