Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

እንማር

Description
@Enmare1988

ለተጨማሪ ጥያቄ አስተያየት
@kiya23q3 አናግሩኝ

https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month, 2 weeks ago

**Sister ነበር ያሳደገችኝ።

አራት ወይ አምስት አመት እያለሁ ነበር ወላጆቻችን ወደ ሞት የሄዱብን ። ሁለት ብቻ ነበር የወለዱት : እኔን እና እህቴን ። ስምንት አመት ትበልጠኝ ነበር ። መቼ ወደ አባትነት ፣ መቼ ወደ እናትነት እንደተቀየረች አላውቅም ።

ቤታችን ውስጥ አባትና እናት የሚወጣውን ሃላፊነት ተሸከመች ። ሸክሙ አላስጠናትም መሰለኝ ትምህርት አልገፋችም። አስረኛ ክፍል  የሙያ ውጤት መቶላት ነበር፤ እሱንም ተወችው ።*✅️*አልምልም : ከማልኩ ኤልዱ ትሙት እላለሁ በቃ ። ምድር ላይ ሞት መጥቶ ቻው ማለት የምትፈልገው ሰው ብባል፣ ዘመድ ጥራ ብባል ፣ አንደኛ ማን ያስብልሃል ብባል ፣ የማን ወዝ እና ህልም አልፎብሃል ብባል መልሴ ኤልዳና የሚል ብቻ  ነው ።

ተሰብስበን ህልም ስንናገር ኤልዳና ህልሟ እኔ ነበርኩ ። እንደዚህ ሰው ይወደዳል እንዴ? እንደዚህ በፍቃድ ህልም ይሰዋል ? የሆነ ቀን ከስራ ስመጣ ኤልዳ ታማ ጠበቀችኝ ። ክሊኒክ ወሰድኳት ቀላል አይደለም ብለው ሪፈር ላኩን ።

ፊቷ ችፍፍፍ ፣ ቁስልስል አለ ። ቀኝ እግሯ እምቢ  አልራመድ አለ ፣ ምግብ አልበላ አላት ። ብዙ ቦታ ሄድን መፍትሄ  አጣን ።

ኢ- አማኝ ነበርኩ ፤ እንዲ አደረክብኝ ብዬ የምጠይቀው ፣ እንዲ አድርግልኝ ብዬ የምለምነው አካል  የለም ።  ነፍስ ካወኩ እንዲ ሀዘን ተጣብቶኝ አያውቅም ። የመኖር ፍላጎት እና ህልሜ ከሰመ። ህመሟን አለምደው አልኩ ። ሃኪሞች ተስፋ የላችሁም አሉን ።

የሆነ ቀን አስራ አንድ ሰዓት ለሊት ቀስቅሳኝ
"በዓታ ማርያም ሶስት ቀን ፀበል ተጠመቂ  ትድኛለሽ ተባልኩ" አለችኝ ።  ማመን የማይደክማት ልጅ ፤ መሞኘት የማይሰለቻት ልጅ ።
"እሺ እንሂድ" አልኳት ።**አማራጭ የሌለው ሰው ምንም አይፈላሰፍም። እንኳን ቤተክርስቲያን ስምጥ ሸለቆ እሄዳለሁ ። በርግጥ እኔ ከ 'Bible'  የ  Sigmund Freud - 'The Future of an Illusion' የተሻለ ያሳምነኛል።

ግን፤ ኤልዱ እድናለሁ ካለች የት አልሄድም ??

ሄድኩ : ተጠበለች ወደቤት መጣን ። እሷ በህልሟ፣ እሷ በበኣታ ፣እሷ በፀበል ያላት እምነት ትልቅ ነበር እና ውጤት ጠበቀች በርግጥ እኔ የምጠብቀው ነገር የለም ።*✅️*በነጋታው ጠዋት ፊቷ ለውጥ ያለው መስሎኝ ነበር እሷ አረጋገጠችልኝ ። በሁለተኛው ቀን ሄድን "እግሬ  ቀለለኝ" እያለች ነበር ። የዛ ቀን በነጋታው "እግሬ ሰራ " አለች ።

የሆነ ነገር ማለት ፈልጌ ነበር ደስታ፣ እምባ አላናግር አለኝ እና ዝም አልኩ።  ሶስተኛ ቀን ተጠመቀች ፊቷ፣ እግሯ ፣የምግብ ፍላጎቷ እንደነበረ ሆነ ።

ሶስተኛ ቀን እሷ ተጠምቃ ስትጨርስ "ወደቤት እንሂድ ወይ?"  አለችኝ።**"እኔ ልጠመቅ እና እንሄዳለን" አልኳት። ስትድን ደስ ያላትን ያህል ደስ አላት። ሆድ ብሶኝ ነበር ፣ደስ ብሎኝ ነበር ፣ ማመን አቅቶኝ ነበር። እያለቀስኩ እያመሰገንኩ እየተደሰትኩ ተጠመኩ  አመንኩ ።

ሄሌ ሉያ
©  Adhanom Mitiku**

1 month, 2 weeks ago

ከ"አለማወቅ" መፅሀፍ የተውጣጡ ድንቅ ሀሳቦች እና አባባሎች

-ስለራሳችን የማናውቀውን ማወቅ ያስፈራናል
-ስለሰው ማወቅ ደስ ይላል ለምን? ስለራስ ከማወቅ ስለሚቀል
-አንድ ሰው በጥልቀት የሚያውቀው ነገር መከወን ካልቻለ ምኑን በጥልቅ አወቀው
-በድንገት ትልቅ ወንበር ላይ የተቀመጠ ሰው ብነሳና ብቆም ይወስዱብኛል ብሎ ይፈራል
-አሁን ላይ ሳስበው የእድሜ ጥቅም የፍላጎት እና የምኞት እየቀነሰ መምጣት ነው
-ልጆች እና አዋቂዎች "እኔ ያልኩት ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ ማለታቸው የእናቶች ችግር ሆኖ ቆይቷል
- አብዛኛው ታዛዥነት አማራጭ ከማጣት ይመነጫል
-ዘመኑ በጣም ጮክ በማለት ላለመሰማማት ፉክክር የሚደረግበት ነው
-መማር ከባህል ማፈንገጥ አይደለም
-ሙሉ ሰው የምትሆነው ማሰብ ስለቻለች ነው
-ያለንና የሌለንን የምናውቀው በማሰብ ብቻ ነው
-ሊደርስብን የሚችል መጥፎ ነገር ሁሉ ቀድሞ ደርሶብናል
-በህይወታችን የሚደርስብን ከባድ ነገር አልፏል እሱም መወለድ ነው
-የቱ ነው የሚሻለው? የምንወዳቸው ወጥረው ቢይዙን ወይስ የማናያቸው ቢተዉን
-ነገን የማያውቁ ማህበረሰብ ስህተት ነኝ
-አንድን ሰው ከሌላው ሰው የምናለካካበት መንገድ አብዛኛው ውሸት ነው
-ሰው በውስጡ ፍላጎት እየተገፋ ግን በውጩ እያስመሰለ የሚኖር የፍላጎቱ ባርያ ነው
-ሰው በመሆኔ በህይወት ድግግሞሽ መሰልቸት በተፈጥሮዬ የተፃፈልኝ ይመስለኛል
-ማስተዋል ምርጫ ነው
-ማስተዋልን መምረጥ አለማወቅን መቀበል ነው
-ደሀ ከአፈር አይደለም የተሰራው ደሀ አፈር ነው ሌላው ሁሉ የሚሰራበት
-የማውቀውን ከየት እንዳወቅኩ ካላወቅሽ የራስሽ ይመስልሻል
-ለአዋቂዎች መሰልቸት የኑሮ አጋር ስለሆነ አይሰለቻቸውም
-ጉልበተኞች የሚተባበሩት በጋራ የሚያጠቁት ሲኖር ነው
-የጥያቄው መልስ አንድ በሆነበት ሁኔታ ብዙ ትክክል ያልሆነ አማራጭ ማድረግ ምን ይጠቅማል
-ገና ለገና የዚህ ትውልድ ልጆች ተረትና ምሳሌ አያውቁም ብላችሁ የራሳችሁን ንግግር ምሳሌያዊ አነጋገር ማድረግ ተክናችሁበታል
-የአዕምሮ ሀኪም ማለት የቋንቋ መርማሪ የቃላት አንጥረኛ የሀሳብ ቀማሪ
-እውነተኛው ማንነትሽ ግን ባልተሰበረው ሳይሆን በተሰበረው መስታወት ውስጥ ያየሽው ነው
-ከባዱ የአዕምሮሽ መከላከያ መርሳት ነው ብዬሻለው እሱም ቀስ እያለ መዳከሙ አይቀርም
-ብዙ ሰው ማን አስተማረህ ሲባል የአስማሪውን ስም ይጠራል እንጂ ከሌላው ህመም የተማረ መሆኑን አምኖ አይመሰክርም
-የሚጨቆኑት ጨቋኝነት የበዛባቸወሰ ናቸው
-ደፋር የሆንኩት ፈሪ ስለኾንኩ ነው
-"ደህና ነኝ" በጅምላ ለጅምላ መዋሻነት የተፈጠረ አባባል
-መዝጊያ የሌለው መድረሻ ያለው ህየወት
-ያለ ቅድመ ሁኔታ እና ያለ እውቀት ሰውን ማየት ከቻልሽ ለመስማት ፍላጎት ይኖርሻል
-የሚንቀሳቀሰው ልጅነትሽ በትውስታ ብዛት እንዳልደበዘዘ ይታየኛል፥ እድሜ ይህ ነው ከፊትሽ ብዙ እድል እንዳለ አመላካች ነው
-የምታርፊበት እና የሚያነሳሽ ካለ በፍቅር መውደቅ ጥሩ ነው
-ፍቅር የሚይዘን ከሙሉ ማንነታችን ላይ ተቀንጭቦ ከተስፈነጠረው ጋር ስለሚሆን ማስፈራቱ ግድ ነው
-የሰው ልጅ ሌሎችን የሚያውቀው ራሱን በሚያውቀው ልክ ነው
-መከላከልና መጠበቅ ላይ ያተኮሩ ወላጆች የልጆቻቸውን እድገት ይወስናሉ ስለወደፊት ማስታጠቅ የጀመሩት ደግሞ ልጆቻቸውን ያለጊዜ ያጣሉ
-መኖር ከፍርሃት በላይ መመንጠቅን ይሻል
-ሁሉም ግንኙነች መውደድ እና ጥላቻ አለው
-ሰው ያጠፋም ያላጠፋም ሲመስለው አደገኛ ነው ምክንያቱም ለመታረም እና ለማረም ብቻ ሳይሆን ያደረገውን ከመድገም አይቆጠብም
-የነፃነት ጥቅም ህልም ማለም መፍቀድ ነው
-የሁሉም ወላጅ ፍርሀት ነው ህይወትሽ ካንቺ ቁጥጥር ውጪ በሚሆነው ሁሉ ከመንገድ እንዳይቀር ነው
-ካሬ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ባይገባኝም የራስን ሳጥን እስኪያገኙ እያነከሱም ቢሆን መዝለልን ተለማምጄበታለሁ

1 month, 3 weeks ago

በህይወትህ ትልቁ ጠላትህ ውስጥህ ያለው መጥፎ ሃሳብ ነው መጀመርያ እሱን ታግለህ አሸንፍ ከዛ ሌላው ይደርሳል ኧ

1 month, 3 weeks ago
**የፊልም ግብዣ

**የፊልም ግብዣ

Miller's Girl

Jenna Ortega ብዙ ፊልሞች ቢኖራትም ተወዳጅነትን ያፈራቸው Wednesday ፊልሟ ነው Miller's Girl በያዝነው አመት January ላይ ነው የተለቀቀው*❤️**የሃብታም ልጅ ቤተሰቦቻ ምንም ግዜ የሌላቸው ለሷ እረጅም ግዜዋ በብቸኝነት የምታሳልፍ ልጅ ብቸኛ ምርጫ ያደረገችው ካለችበት ብቸኝነት ለመውጣት ስነፅሁፍን ነው ማንበብና መፃፍን የምትፈልገውን ህይይወት በንባብና እሷም በመፃፍ ትኖረዋለች*✅*በዚ መሃል አንድ የ university መምህራ ፕሮፌሰር መፅሃፍን ምርጫ ታረጋለች ፕሮፌሰር ቢሆንም የሚፅፋቸው ነገሮች ወጣ ያሉ ስለሆኑ ትችት ይበዛባቸው ነበር እሷ ግን ሃሳቦቹን ከመውደድ አልፋ ከሱ ፍቅር ይይዛታል ባለትዳር እና በረጅም እድሜ ቢበልጣትም እንኳን*✅️****እሱም ባለትዳር ይሁን እንጂ ደስተኛ ህይወት የሚመራ አልነበርም ይዋደዳሉ ግን አብረው መሆን አይችሉም ደራሲያን የሚፅፉትን ሁሉ እንዳልሆኑ የሚያምኑበትን ሁሉ እንደማይፅፉ ትረዱበታላቹ እንደሷ ያሉ ሴቶች sapiophile ይባላሉ attracted የሚያደርጋቸው intelligence smart የሆነ ወንድ ነው እድሜው ገፅታው ግድ አይሰጣቸውም

anyway ፊልሙን እዩት ትወዱታላቹ ኧ**

1 month, 3 weeks ago
***⭐*****እግዜር አለምን ሁሉ ከፈጠረ በኃላ አዳምን …

እግዜር አለምን ሁሉ ከፈጠረ በኃላ አዳምን ፈጠረ ። አዳም ድብርት ሊገለው ሆነ ፣ አለም የሆነ ማጣፈጫ ቅመም እንደጓደለው ታውቆት ሲዶክከው ። ፈጣሪው ያጣውን ያቅ ነበር እና ከጎን አጥንቱ ወስዶ ሄዋንን ፈጠረለት።*✅️*አለምም ፦*🟢*በእናትነት ፣በእትነት ፣በሚስትነት ፍቅር ደመቀች ።

ሴቶቻችን
🙏**

1 month, 3 weeks ago

ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

1 month, 4 weeks ago

📔📖ርእስ ኮዛ ኖስትራ*📚*📚**ትርጉም [ መኩሪያ መካሻ]*➡️*የተወሳሰበ ታሪክ ያለው የሲሲሊ ማፊያ አስደናቂ ታሪክ*➡️*ኮዛ ኖስትራ የሲሊሊ ማፊያ ምስጥራዊ ድርጅት ነው። ማፊያ '' በደም መሃላ '' የሚሰራ ከመቃብር በኋላም ቢሆን ደመኞቹን  የማይለቅ እጅግ ጠንካራና አደገኛ ሚስጥራዊ ማህበር ነው ፤*➡️*ይህ የተወሳሰበ ታሪክ ያለው የማፊያ ማህበረሰብ እንዴት
ለመረዳት የሚያስቸግር ሆነ??
*➡️*በመጀመሪያው ሲሲሊያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍራንቸስኮ ኮረስር አማካይነት ጣልያን ቀውስ ባልተጠበቀ አደገኛ መንገድ ለመፍታት ታቀደ፤ ይኸውም
የቅኝ ግዛትን ድል ለመጎናፀፍ በሚል ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ "ሆነ፣
**በጣም አጓጊ የማፋያ ታሪክ ያንብቡ

*💠*📚እንማር 📚*📚*💠* *▬▬▬▬▬▬▬▬▬ #shaer#share#share#ሼር#ሼር#ሼር ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ለተጨማሪ መፅሐፍት 
▬ ▬   ▬▬    ▬▬     ▬▬

*✅️@Enmare1988✅️*✅️****@Enmare1988

1 month, 4 weeks ago

📔📖ርእስ ኤክሶዲያ*📝*✏️**ደራሲ ሰለሞን አበበ*🔴*በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ግሩም ልብወለድ*📕*"መፅሐፉ በስነ ጽሁፍ ደረጃ የተዋበ፤ ማህበራዊ ሂስን ከነመፍትሄው የያዘ በእውነተኛ ስደተኞቹ ጫማ ውስጥ ሁነን ምክንያታቸውን፤ ፍቅራቸውን፤ ደስታቸውን፤ ሀዘናቸውን፤ መከራቸውን፤ ትዝታቸውን፤ የኑሯቸውን ከፍታና ዝቅታ አብረን እንድንቋደስ የሚያደርግ በሁሉም ሰው መነበብ ያለበት ድንቅ ስራ ነው""

2 months ago

**ከህመሙ ያልዳነን ሰው አታፍቅር

ይፃናናብሃል
እንጂ #አያፈቅርህም..!*👌*❗️*❗️*

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas