ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
**ተማሪው መምህሩን ይጠይቃል
??
በህይወቴ ምን አይነት ውሳኔዎችን ልወስን?
መምህሩ ይመልሳል?
??
የባርኔጣ: የፀጉር ቁርጥ እና የንቅሳት ውሳኔዎች አሉ
አንዳንድ ውሳኔዎች ባርኔጣ ናቸው - ባርኔጣ አንድ ጊዜ ትሞክረውና ካልተስማማህ እና ካላማረብህ አውልቀህ ሌላውን ትቀይረዋለህ: የሚያምርብህን ታደርጋለህ
አንዳንድ ውሳኔዎች የፀጉር ቁርጥ ናቸው - ፀጉርህን ትቆረጣለህ ግን አትወደውም: አዲስ ቁርጥ ልትሞክር ትችላለህ ነገር ግን ካልወደድከው እና ከአንተ ስታይል ጋር ካልሄደ እስኪበቅል የመጠበቅ ሁለተኛ እድል አለህ: ፀጉርህ ወደ ቦታው እስኪመለስ ትእግስት ማድረግ ብቻ ነው
አንዳንድ ውሳኔዎች ንቅሳት ናቸው - ንቅሳት አንድ ጊዜ ገላህ ላይ ካረፈ የሰውነትህ አካል ነው: አትቆርጠውም አትፍቀውም:: በመስታወት ስታየውም ሆነ ሰዎች ሲያስታውሱህ ያለፈውን ተቀብለህ የወደፊቱን ከመራመድ ውጪ አማራጭ የለህም
??
ሁላችንም የባርኔጣ: የፀጉር ቁርጥ እና የንቅሳት ውጤቶች ነን
❤️??**
**ጊዜ ከሚበላብን ዛሬ እንሸሻለን ፣ ለውጥ የማናመጣበት ጉዳይ ጋ ግዜ አንገልም ፣ ተስፋችንን አጠንክረን እንይዛለን ዘውትር እንኮተኩተዋለንም ፣ ህልማችን በስራ ይደገፋል ፦
የምንወዳቸውን መውደዳችንን እንነግራቸዋለን ። ስለሰጠን ጤና እናመሰግናለን የጎደለም ካለ እንፀልያለን ?
እንከን ላይ ከሚያተኩሩ ፣ ቦታ ከማይሰጡን ፣ለኛ ግድ ከሌላቸው ፣ ነገራችንን ጉዳዬ ከማይሉ ግለሰቦች ገለል እንላለን ፦
ስለወደቅነው ትላንት ዘውትር አንዘበዝብም ዛሬ እምንሰራውን አጥብቀን እንይዛለን ነገ እምናሳካው ላይ እንመሰጣለን ፦
ከሄደው የሚመጣው ይበልጣል ።
ችርስ ለአዲስ ዘመን ❤
ችርስ ለተስፋችን ❤**
**"ትንሽ ቦታ"
ስሜታዊ ሆኖ ለተናገረን ፣ ሊረዳን ፈልጎ ለሳተ ፣ ኑሮ አስክሮት ለገፋን ፣ ንዴት ገፍቶት ላጠፋ ፣ ግዜ አጣሁ ብሎ ላልጎበኘን ፣ ስናሸንፍ ላላጨበጨበ፣ ስንወድቅ ላላነሳን ፣ ስናስብለት ላልተረዳን ፣ ማደጋችንን ላላየ ፦
"ትንሽ ቦታ ለይቅርታ" አኑረናል
አማረልን ብለን ላሳዘንን ፣ አጉል ተስፋ ለሰጠነው ፣ ውድቀት ላይ ለሳቅነው ፣ ብልግናን ላጎላናው ፣ ድድብናን ላነፈስነው ፣ ማድረግ ችለን ላላደረግነው ፣ ችለን ለተጣመምነው ።
ለራሳችን ይቅርታ አደርገናል...
ቺርስ ለአዲስ ዘመን
ቺርስ ለተስፋችን
ቺርስ❤?.
©Adhanom Mitiku**
✨✨በህክምናው አለም ላይ የሚያጠነጥን ተከታታይ ፅሁፍ ሰሞኑን ይጀመራል ይጀመር የምትሉ ?*?**✨*✨
እማ "trend" ምንድነው? ልጁ ይጠይቃል
እናት መለሰች "ወረት"
**አንዳንድ ቀን ገና ከእንቅልፍ ስተነሳ ትከሻህ ቅልል ይልሃል። ተንደርድረህ ሻወር ትገባለህ በስልክህ የሮፍናንን ዘፈን ከፍተህ እርቃንህን ሆነ እየዘፈንክህ ትወናወናለህ ።
ባዘቦት ልብስህ ገድግደህ የዘነጥክ ይመስልሃል ። የጠዎቷ ፀሃይ ደስስ ትልሃለች። ጎረቤትህን እትዬ ጌጤ... ጋሽ ይልማ እንዴት ኖት ብለህ ድምፅህን አጮኸህ ሰላም ትላቸዋለህ ።
የምታቃቸውን ሰዎች ድምቅ ያለ ሰላምታ እየገጨህ ትሄዳለህ ። እጮኛህ በፍቅረኛዋ ከተበደለችው ጓደኛዋ አንፃር አይታህ አንተ የኔ ቅዱስ አፈቅርሃለሁ ትልሃለች። እኔ ራሴ አፈቅርሻለሁ እስትንፋሴ ትላታለህ።
መንገድ ላይ ያገኘከው ወዳጅህን አስጨንቀህ እንደው ስሞት ብለህ ወስደህ ጋብዘኸው ተጨዋውታቹ ቢል ስትል ተከፍሏል ትባላለህ።
እንደው ምን ይሻለኛል ማን አለ እንደ እኔ እድለኛ የሚል ዘፈን ማውጣት ያምርሃል።
የሞከርከው ስራ ተሳክቷል ለበለጠ መረጃ ቢሮ ና ትባላለህ።
ቱግ ያለብህን ገለሰብ ዛሬ ደብሮት ነው የሚሆነው ብለህ ትረዳዋለህ።
መንገድ ላይ አንድ ብር ስጠኝ የሚልህን ሰዎዬ ለምን አንድብር ብቻ ትጠይቃለህ ብለህ አስር ብር ትሰጠዋለህ ። ።
ጤንነትህ ካንተ ጋ እንዳለ ይታወቅሃል ፤ በዙሪያህ ያሉ ፀዴ ፀዴ አብረውህ የሚሰሩ ፤ ወዳጆችህ፤ የሰፈር ሰዎች እንደሚወዱህ ይሰማሃል።
እውነት ዛሬ ህይወት ደስ ትላለች። እወድሻለሁ ህይወት ?❤**
የስነ-ልቦና አቅሞን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦
?*?
እይታን የሚያሰፉ፤
ማንነትን የሚያንፁ፣
መልካምነትን የሚዘክሩ፣
ስብዕናን ከፍ የሚያደርጉ ውብ ምክረ ሀሳቦች በየእለቱ የሚነገርበት የምንጊዜም ግሩም ቻናል ተጋብዘዋል*?
አሁን ይቀላቀሉ ?*?***
@mikreaimro
@mikreaimro
@mikreaimro
**ውጥረት ላይ የነበርኩኝ ሰዓት፥ ምስቅልቅሌ ሲወጣ 'ተረጋግቼ ማሰቢያ ሰዓት ስላጣሁ ነው' ብዬ አስብ ነበረ። ከዛ ግን የናፈቅኩትን ትርፍ ሰዓት ሳገኘው አስቤ.... አስቤ... ደከመኝ ምክንያቱም ምንም የሚለወጥ ነገር የለም ሁሉም ሰው የራሱ ኑሮ ጡዘት ላይ ነው።
ዘመኑ ከራስ ተርፎ ለሌላ ለማሰብ የማይበቃ የስስት ዘመን ነው። 'ሰው ለወዳጁ እንደሚሳሳው ለራሱ ቢሳሳ' ብዬ አስብ ነበረ፥ ዳሩ ግን ድሮ ድሮ አንዱ ለሌላው ሲጨነቅ ለርሱም የሚጨነቅለት አያጣም ነበረ። አሁን ግን ሆደ ቡቡነት ብርቅ ሆነ፤ ለሌላው መጨነቅ ድሮ ቀሩ ከሚባሉ እሴቶች ሊመደብ አንድ ሀሙስ ቀረው።
አሁን...በእኛ ዘመን..."በዘመነኞቹ" ሆ!ሆ!! መቼ ከራሳችን ተርፎን ነው ለሰው ምናስበው?! ዳሩ ምን ያደርጋል ለራሳችንም አልሆንን፥ ራሳችንን ሸሸግን፤ ደበቅን ፥ማጣት፣ መጎዳት፣ መከዳት ምን በወጣን ብለን የብረት አጥር በልባችን ዙርያ አጠርን ልባችን የፍቅር ያለህ ብላ ስታለቅስ የብረት አጥራችን ዛገ።
ሊያውቀን የተጠጋንን በሙሉ የዛገው አጥራችን ቦጫጭሮ አባረረው በዛው ልክ ከውስጥ የእኛም ልብ አብራ ተቦጫጭራ ደምታ... ደምታ... ብዙ ግዜ እንደወደቀ ህፃን ልጅ ጉልበት፥ ጠባሳ እንደለመደው፥ ድጋሜ ቢቆስል ህመም እንደማይፈጥረው ልባችንን አደነዘዘናት።
ደግነቱ...ወይ ክፋቱ እንጃ ግን ልብ ሞቶ አይሞትም... ትንሽ ተስፋ... ትንሽ ብርሀን...ቆስቁሶ ያስነሳታል ወይ ደግሞ ትንሽ ትዝታ... ትንሽ መከፋት... መልሶ ያደቃታል ከዛስ? ምን ከዛ አለው እንደምታዩት ጓደኞቻችን ራሳቸውን እያጠፉ ነው ለምን? ሁላችንም ለሌላችን ራስ ወዳድ ሆንን ዳሩ ራሳችንን መደበቅ እንጂ መውደድ አልተማርንም!! እንደውም ከራሳችን የበለጠ ጠላትም ኖሮንም አያውቅም!! "የሰው ልጅ ጠላት ራሱ የሰው ልጅ ነው" አለ የሆነ ሰውዬ ...ብቻ ግን አዝናለሁ...እየሆንን ላለነው ነገር አዝናለሁ
ለሁላችንም...
✍ናኒ**https://t.me/justhoughtsss
Telegram
Thoughts
ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው እና እናንተስ ጎራ አትሉም? For any comment: @nhymn Since: Dec-10-2022 discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk
ምንም አይነት ነገር ቢመጣ ከዚህ የሚከብድ አይመስለኝም....ከዚህ በላይ ከባድ ምሽት የሚኖረኝ አይመስለኝም...የልጆቼን እጅ ይዤ እያለቀስኩኝ ነው....በተኙበት ይቅርታ እየጠየኳቸው ነው....በብርሀን አይናቸውን እያየሁ ማድረግ አልቻልኩም...."ጥያቹ ልሄድ ነው" ለሚል መርዶ የሚሆን ይቅርታ ይኖራል...?....."ካሁን በኃላ አይኔን ስለማታዩት ይቅር በሉኝ..."....ይባላል...?
አሁን ልጆቼን እያየሁ ነው...."ነገ እንገናኛለን..."....ብዬ ስጠፋ መገናኘት ማለት ትርጉሙ መጣለሁ ብሎ መቅረት ይመስላቸው ይሆን....ከነገ ጋር ይጣሉ ይሆን....አላውቅም....
"ለምን እውነቱን አልነገርኳቸውም...?"....እልና ደግሞ እንዳይጎዱ በሚል ሽኝገላ እተወዋለሁ...አሁን ማን ይሙት ለዘመናት ከእናት መለየት ቆዳ ተልጦ ጨው እንደተነሰነሰበት ሰውነት እንደሚለበልብ ጠፍቶኝ ነው....?....የቱ ነው ይበልጥ የሚጎዳው....ተስፋ አድርጎ ጉም መጨበጥ ወይስ ቁርጥን ማወቅ....
እውነቱ ግን ራስ ወዳድ መሆኔ ላይ ነው...የልጆቼን እምባ እና ድንጋጤ በአይኔ ማየት የሚፈጥርብኝን ከባድ ስሜት ለማምለጥ ነው...ሁላችንም እንዲህ አይደል የምናደርገው....እኛ ሳናይ ስለሚወርዱት ዘላዎች ማሰብ አንፈልግም....ብቻ ማምለጥ....ብቻ መፈርጠጥ...
ብናምንም ባናምንም ሁላችንም ስለሚጎዳው ስሜታችን ስናስብ እንደደነበረ በሬ የሚያስፈረጥጥ ራስ ወዳድነት አለብን...
✍Shewit
ድንቅ ታሪክ || ይነበብ
"ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ፡፡ ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች። ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡
እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች፡፡ በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት “እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርጉዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡
ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ፡፡ አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ...ችግር አለ??”
ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡
ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል... የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ”
የዚህ አጭር ተረት መሰል ታሪክ ጭብጡ፡-
ሰዎች ለጥያቄዎቻቸዉና ለጸሎቶቻቸዉ መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ፡፡ በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡
የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ ለራስህ እንዲህ በለዉ "ጊዜዬ እየደረሰ ነዉ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን ይመለከቱታል"
?**
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago