ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
መረጃ ‼️
ከ2004 በሆላ የተገነቡ መንግሥት ህገወጥ ያላቸው ቤቶች ሊወረሱ መሆኑ ተሰምቶል፡፡
የከተማ መሬትን በሊዝ መያዝ በሚል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ምክርቤቱ እየተዋያየ ባለበት ሰአት የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሬት ማኔጅመንት ዴስክ ሃላፊ ገብሩ ባየብኝ ናቸዉ ከ2004 በሆላ ጀምሮ የተገነቡ ህገወጥ ያሎቸውን ቤቶች መንግስት ሊወረስ መሆኑን የተናገሩት ፡፡
የመኪና አደጋ‼️
✔️በአምቦ ከተማ እየተከበረ ያለዉ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለመታደም ሲጎዙ የነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተጋጭተዉ ሞት እና ከባድ ጉዳት ማጋጠሙ ተሰምቶል ፡፡
✔️ተጎጂዎቹ ሲጎዙ የነበሩት ከኢልፋታ ወረዳ በመነሳት ወደ አምቦ ነበር ፡፡
🔕3 ሰወች ወዲያዉ መሞታቸዉ ተሰምቶል
🔕18 ሰወች ከባድ ጉዳት ገጥሞቸዋል
🔕ሌሎች ቀላል ጉዳት ገጥሞቸዉ ወደ ቤት ተመልሰዋል ፡፡
ፈጣሪ በመንገዳችሁ ሁሉ ይቀደም🙏
የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ውሳኔ መዘግየቱ አሳስቦኛል ሲል ኢሰማኮ አስታወቀ!
መንግሥት የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን የየያዘውን ዕቅድ ሊያዘገየው ይችላል መባሉ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አስታውቋል።መንግሥት የዝቅተኛ ደሞዝ ወለልን ለመወሰን ጥናት አጥንቶ የጨረሰ ቢሆንም፤ "ችግር ያመጣብኛል በሚል ስጋት አዝግይቼዋለው" ማለቱን ተገቢ አይደለም ሲሉ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ "ይህንን በሚመለከት ለሚመለከተው የፌደራል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጠን ስንል ጠይቀናል" ብለዋል።"በተጠና ጥናት መሠረት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል" የሚል ነገር መነገሩን የገለጹት አቶ ካሳሁን፤ "ጥናት በትክክል ተደርጎ ከሆነ በጥናቱ ላይ መሳተፍ ነበረብን" ብለዋል።
አቶ ካሳሁን አክለውም "እንደተባለው ኮሚሽኑን ሳያካትቱ ተጠንቶም ከሆነ ጥናቱን እንዲሰጡን ስንል በደብዳቤ ጠይቀናል" ሲሉም ተናግረዋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የስራ ግብር እንዲቀነስ እና የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ሲጠየቅ ይሰማል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ በቋሚ ደምወዝ በሚኖሩ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ተጽእኖ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ ይገለጻል፡፡"የኑሮ ውድነቱ ሠራተኛው ከሚያገኝው ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ኑሯቸውን እንዲገፉ አስገድዷል" ያለው የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፤ ማስተካካያዎች እንዲደረጉ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውቋል፡፡
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን እና የግብር ቅነሳ እንዲደረግ ኢሰማኮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በነበረው ውይይት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፤ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በደብዳቤ ቢጠይቅም ተገቢውን ምላሽ አለማግኘቱ ይገለጻል፡፡(Ahadu)
መረጃ ‼️
ኢትዮጵያ በታሪኮ ከፍተኛ የሆነዉን ምርት ለመሰብሰብ በዝግጅት ላይ ትገኛለች ተባለ
ሀገሪቶ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመኸር አዝመራ 20,5 ሚሊዬን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኖን የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ አስታዉቀዋል ፡፡
11,5 ሚሊዬን ሄክታር መሬት በዘመናዊ መልኩ በተቀናጀ ክላስተር መሸፈኑን ሚኒስተሩ ጠቅሰዋል ፡፡
በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተነሱ ጦርነቶች ምክንያት በቂ ግብአት ገበሬዉ ባለማግኘቱ ማሳዎች አልታረሱም ቢባልም ሚኒስተሩ ግን ሀገሪቶ በታሪኮ ከፍተኛ የሆነዉን ምርት ልትሰበስብ ነዉ ብለዋል ፡፡
ምርጫ ቦርድ ለቀድሞዋ ሰብሳቢ መኖሪያ ቤት አጥር ጨምሮ ለአጃቢዎችና ለሾፌሮች ያወጣው ገንዘብ የኦዲት ትችት ቀረበበት
|የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቀድሞ ሰብሳቢው መኖሪያ ቤት ዕድሳትና አደገኛ የሽቦ አጥር ለማሠራት ወጪ ያደረገው 233 ሺሕ ብር፣ ለአጃቢዎችና ለሾፌሮች ለምሣና ለእራት ያላግባብ የተከፈለ 218 ሺሕ ብር በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኦዲት ግኝት ትችት ቀረበበት፡፡
ትችቱ የቀረበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የ2015 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ፣ ኅዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ውይይት ሲደረግ ነው፡፡
ቋሚ ኮሚቴው የኦዲት ግኝት ሪፖርቱን ካየ በኋላ ባቀረበው ጥያቄ በ2013 በጀት ዓመት 218,500 ብር ለአጃቢዎችና ለሾፌሮች ያለአግባብ የምሣና የእራት አበል ክፍያ መከፈሉ በዋና ኦዲተር ተረጋግጦ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን በኦዲተር አስተያየት ቢሰጥም፣ ቦርዱ ግን ምላሽ አለመስጠቱ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በ2013 ዓ.ም ለቦርዱ ሰብሳቢ መኖሪያ ቤት ዕድሳትና አደገኛ የሽቦ አጥር ለማሠራት በአጠቃላይ ከ233 ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ ለቦርዱ ከተፈቀደው በጀት ላይ ያላግባብ ወጪ መደረጉን፣ገንዘቡም ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እንዲተካ አስተያየት ቢሰጥበትም ቦርዱ መልስ እንዳልሰጠበት በቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ ቀርቧል፡፡
የዋና ኦዲት ግኝት ሪፖርቱን ተመሥርቶ የቀረበው የኮሚቴው ጥያቄ እንደሚያሳየው 981 ሺሕ ብር መነሻ የምዝገባ ሰነድ የሌለው የተከፋይ ሒሳብ ላይ የተመዘገበ ገንዘብ፣ 6.5 ሚሊዮን ብር በተገቢው የሒሳብ መደብ ሳይመዘገብ የተገኘ ገንዘብ፣ በ2014 ዓ.ም. 19 ሚሊዮን ብር ሥራ ላይ ያልዋለ ገንዘብ፣ 138 ሺሕ ብር ለሐረር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ያለ ውድድር በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ ይገኝበታል፡፡
በተመሳሳይ 24.5 ሚሊዮን ብር በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተከፋይ ሒሳብ፣ ሁለት የቦርዱ ሠራተኞች ንብረት ሳያስረክቡ መልቀቃቸውና ቦርዱ የራሱ የሆነ የተሽከርካሪ ጋራዥ እያለው ተሽከርካሪዎቹ በውጭ ጋራዥ እንደሚጠገኑ ጥያቄ ተነስቷል፡፡
ምርጫ ቦርድ ሠራተኞችን ማስታወቂያ በማውጣት መቅጠር ሲገባው፣ በፕሮጀክት ተቀጥረው የነበሩ 55 ሠራተኞችን ያለ ውድድርና ማስረጃዎችን ሳያሟሉ ያላግባብ መቀጠራቸውን ቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ አንስቶበታል፡፡
በተጨማሪም ከሐምሌ 2011 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ከቦርዱ ዋና ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢዎች በመመርያው መሠረት ከደመወዛቸው ያልተቀነሰ የሕክምና ሁለት በመቶ ወጪ፣ በድምሩ 40,000 ብር የሚጠጋ ተቀናሽ ተደርጎ ወደ መንግሥት አለመግባቱ ጥያቄ ቀርቦበታል፡፡
ቦርዱ በ2013 ዓ.ም. 2.7 ሚሊዮን ብር ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ መክፈሉን ቢገለጽምና ፓርቲዎቹ መቀበላቸውን የሚያሳይ የገንዘብ ገቢ ደረሰኝ እንዲያቀርብ ከኦዲተር ጥያቄ ቢቀርብም፣ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ደረሰኝ ማቅረብ አለመቻሉ ተገልጿል፡፡
#አንኳር_መረጃ ሪፖርተር
ትዝብት‼️
የመንግሥት ሚዲያዎች ከሚባለው በታች እየወረዱ ነዉ ፡፡
ብሄራዊ ሚዲያ ሳይቀር ሰወችን ሊሸዉድበት የሚሄድበት እርቀት በጣም ያሳፍራል ፡፡
መረጃ‼️ ትግራይ እክሱም ከተማ አካባቢ የተኩስ ልዉዉጥ እንዳለ አንኳር መረጃ ሰምታለች ፡፡ #አንኳር_መረጃ @Ankuar_mereja @Ankuar_mereja
የትግራይ ዉጥረት ወዴት እያመራ ነዉ⁉️
የፀጥታ ኃይሉ በደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ሕወሓት ላይ ዕርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ቀረበ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር 14ኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ያካሄደው ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ሕወሓት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥራዎች ከማደናቀፍ አልፎ ግልጽ በሆነ መንገድ መፈንቅለ መንግሥት ማካሄዱን በመቀጠሉ የፀጥታ ኃይሉ ዕርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ፡፡
ቡድኑ ወደ ለየለት ሥርዓት አልበኝነት ተሸጋግሯል በማለት የገለጸው የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤቱ፣ ‹‹በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በሚገኙ መንግሥታዊ መዋቅሮች ላይ ሕገወጥ ምደባዎችን በማካሄድና ጫና በመፍጠር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥራዎች በማደናቀፍ ላይ ተጠምዷል፤›› ብሏል፡፡
ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ መንግሥታዊ ኃላፊነት ላይ ተመድበው ሕዝቡን ለማስተዳደር ወንበሩን የተቆናጠጡ አካላት፣ የሚያስተዳድሩት ሕዝብም ሆነ ሀብት እንደማይኖርም ነው ጽሕፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡
ሁኔታው ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መሰል ሥርዓቱ አልበኝነት ከአቅሙ በላይ በመሆኑ የትግራይ ፀጥታ ኃይል፣ የፍትሕ አካላትና ባንኮች እየታየ ያለውን ሕገ መንግሥቱን የጣሰ አካሄድ ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡
በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ሕወሓት ከሁለት ወራት በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚደረገውን ሹም ሽር በተደጋጋሚ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ በታችኛው መዋቅር የሚገኙ ምክር ቤቶች ስብሰባ በማካሄድ አዳዲስ ምደባዎችን እንደማይቀበልና አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በካቢኔያቸው ውስጥ ያሉት አምስት ሰዎች በድርጅቱ መባረራቸውን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ጽሕፈት ቤት ግን ‹‹በግላጭ መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደብኝ ነው፤›› በማለት በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው መግለጫዎች እየገለጸ ነው፡፡
የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት በማከልም፣ በእያንዳንዱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር ውስጥ የሚገኙና በክልሉ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላትና ተቋማት፣ የፌደራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) በሚመራው ሕወሓት በሕገወጥ መንገድ ተመድበው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አካላት፣ መንግሥታዊ ኃላፊነት ይዘው በየትኛውም መድረክ ላይ መሳተፍ እንደማይችሉ በመገንዘብ ፈቃድ ሊሰጡ እንደማይገባ አሳስቧል፡፡
በክልሉ ባሉ የሃይማኖት አባቶች አሸማጋይነት በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) እና በአቶ ጌታቸው በሚመሩት ቡድኖች መካከል ውይይት ተደርጎ ዕርቅ ይወርዳል የሚል ተስፋ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም፣ በአቶ ጌታቸው የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር ኅዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ‹‹መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደብኝ ነው፤›› ብሎ ነበር፡፡
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህንን ያለው ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የድርጅቱ ሌላኛው ክንፍ ሥራ አስፈጻሚ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ተወያይቶ፣ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታና በሕዝቡ ላይ የተጋረጡ በግልጽ የሚታዩ ሥጋቶች ዙሪያ ሙሉ በሙሉ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች መኖራቸውን የተመለከተ አጭር መግለጫ ባወጣ ጥቂት ቀናት ውስጥ ነው፡፡
ስምምነት ተደርጎበታል የተባለውን ውይይት በተመለከተ ከሕወሓት በኩል ዝርዝር መረጃ አልወጣም፡፡ የፀጥታ ኃይሉም ውይይት ስለመደረጉም ሆነ ስምምነት ላይ ተደርሶባቸዋል ስለተባሉት ጉዳዮች ያለው ነገር የለም፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በአራት ቀናት ልዩነት ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ቢያወጣም፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) በሚመራው ሕወሓት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡
ሪፖርተርም ከድርጅቱ ኃላፊዎች መረጃ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡
@ሪፖርተር
መረጃ‼️
የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አስተዳደር የመኪና ስጦታ አበረከተ
ባለፈዉ ሳምንት አንድ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስአበባ የገቡት የአቡዳቢዉ መሪ 30 ያህል ጥይት የማይመታቸዉ ዘመናዊ መኪኖች በስጦታ መልክ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ማብርከታቸዉ ተሰምቶል ፡፡
ከዚህ በፊት የብልፅግና መንግስት ወደ መሪነት በመጣ ሰሞን የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መንግስት ቁጥራቸዉ በርከት ያሉ ኒሳን V8 መኪኖችን ለጠቅላዩ መስጠታቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago