Ikrima tube

Description
والله غفور رحيم
አሏህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው::

Channel created on may 6/2023E.C

Any comment and
Cross? @hafu_unique
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago

1 year, 2 months ago

----------♡♡♡----------
#heru_fkr
----------♡♡♡----------
ምዕራፍ፦2
ክፍል፦#62
በፀሀፊ፦hafu

የደወለችው ኢክሩ ነበረች።ለህይወቴ መመሰቃቀል እሷን መነሻ አርጌ ስለማስባት ስልኩን አላነሳሁትም ነበር።ሀዘን እኔ ላይ ቤት ከሰራ ሰነባበተ።ድብርት ጭንቀት እና ፀፀት ውስጤን አተራመሱት።

ከህይወት ጋር ትንቅንቅ ገጥሜ ውድቀቴ እያስለቀሰኝ ያለፈው ታሪኬ እያሳመመኝ ሳለሁ በአንድ ወቅት ከኢምሩ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሳሳት ከግቢ ወደ ቤት ልመለስ ስል የጎዳናዋ ጓደኛዬ እዩ የሰጠችኝ ደብዳቤ ትዝ አለኝ።ከሻንጣዬ ውስጥ ሳተረማምሰው አገኘሁት እና ማንበብ ጀመርኩ

"ሄሩ ፍቅር....ህይወት አጋጣሚ ናት።በእያንዳንዷ ክስተት ስህተት እና ልክነት አለ።ሰው እስከሆነሽ ታፈቅሪያለሽ ታጫለሽ ትሰቃያለሽ ትሰበሪያለሽ ትደክሚያለሽ ትሳሳቻለሽ።አፍቅሮ በማጣት ውስጥ መስዋትነት አለ።የምታፈቅሪውን ላለማጣት የምትከፍይው መስዋትነት ግን የከፈልሽው መስዋትነት ይባሱኑ ስህተት ይሆንና የሁሉንም እድል ማጫ ሰበብ ሆኖ ታገኚዋለሽ።ኢምሩን እንደምትወጂው አውቃለው እናውቃለን እሱን ላለማጣት ከሱ ጋር ይባሱኑ ለመዋደድ ስትዪ ሀይማኖትሽ የማይፈቅደውን ነገር ሰራሽ ሆኖም እሱ ራሱ ኢምሩን ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገር ያሳጣሻል።

ግን ሄሩዬ ምን መሰለሽ?ይሄ ህይወት ነው በብዙ ስብራቶች የተሞላች።ይቺ አለም ግን ለስብራቶቿ ለሚያለቅሱት ቦታ የላትም።ለወንድ አታልቅሺ... በወንድ የተነሳ አንቺነትሽን እንዳታጪ ለከዳሽ ለተወሽ ስትዪ መቼም እንዳትወድቂ ሴትነትሽን ችሎታሽን አሳያቸው።ሄሩ ምን አይነት ጠንካራ እንደሆነች አስተምሪያቸው።ጎዳናት ወይ ብለው እስኪጠራጠሩ ድረስ አስደምሚያቸው።መቼም ደካማ እንዳትሆኚ የሴት ደካማ ከፀፀት እና ለቅሶ ውጪ አታውቅም።በጎዱሽ ልክ ጠንክሪ

ከእዩ"ነበር ሚለው ደብዳቤውን አጣጥፌ ፈገግ አልኩ።ምናልባት የጣልኳትን ሄሩ አሁን አድሳት ይሆናል።

ማግስቱን ለረዩ ደውዬለት አዲስአበባ እንደምመጣ ነገርኩት።በደስታ ሀሳቤን ተቀበለኝ። በቃሌ መሰረት ትዝታዬን እዛ ጥዬ እቃዬን ሰብስቤ አዲስ አበባ ሄድኩ።ጉዳዬን ለረዩ ሳማክረው በፀጥታ ሁሉንም ካዳመጠኝ ቡኋላ ከዛሬ ስንት አመት በፊት ወክ ስንወጣ የነገረኝን ነገር ደገመልኝ
"ብልጥ ከሰው ይማራል...ሞኝ በራሱ እስካልደረሰበት አይማርም የሞኝ ሞኝ ደሞ ደርሶበትም አይማርም..."
"እንድትወቅሰኝ አደለም የምነግርህ እንድትረዳኝ ነው።ከማንም እርዳታ ባልጠይቅ ደስ ይለኛል ግን ሰው ነኝ ብቻዬን ማድረግ የምችለው ምንም ነገር የለም"
"ሰው ለመሆኔ እዚ ለመድረሴ ትክክለኛዋ ምክንያት አንቺ ነሽ...ከጎንሽ ነኝ አይዞሽ"አለኝ። ስራ እንዳገኝ ረዳኝ።በአጭር ጊዜ ራሴን ማቋቋም ቻልኩ ከወደቅኩበት ተነሳሁ።ካሸለብኩበት ነቃሁ።አዋራዬን አራግፌ የድሮዋን ጠንካራ ሄራ ለመመለስ ሳልሰስት ሰራሁ።

በመሀል ብዙ ደስ ሚሉ ነገሮች ተፈጥረው ነበር ወንድሜ ሀሱ ከእስር ተፈታ።ዶክተር ድንገተኛ መልዕክት ላከልኝ።ከበፊቱ በበለጠ ማውራት ጀመርን ኢሙ በሀሱ ሰበብ አውርታን እህትነታችንን መመለስ ቻልን።የኔና የረዩ መደጋገፍ የብረት ያህል ጠነከረ።ከኢምሩ ጋር በልጄ case መነጋገር ጀመርን።እየመጣሁ እንዳገኘው ፈቀደልኝ።ብቻ ብዙ

መጥፎ ክስተቶችም ነበሩ።የአሚሬ አሳዳጊ(እናቱ) ሞተች።በሞቷ እጅግ ማዘኔን ለረጅም ሰአት ተደዋውለን ስናወራ ገለፅኩለት እንዳገባው ከሚችለው በላይ ተማፀነኝ።
"አልችልም።ይቅርታ!"ብዬ በአቋሜ ፀናሁ።

እሁድ ቀን ጠዋት መኪናዬን የኢምሩ ቤት ግቢ ጋር አቁሜ ለአብደላህ ቃል የገባሁለትን መፅሀፍ እና ሌሎች ስጦታዎች ይዤ ወርጄ የጥሪ ደውሉን ተጫንኩት እንደ ሁልጊዜው ሞግዚቱ ሀናን በሩን ከፈተችኝ።የረፍት ቀን ስለነበር ኢምሩ ቤት ነበር በረንዳ ላይ ተቀምጦ ጋዜጣ እያነበበ ሳለ እኔም ስገባ እሱም ቀና ሲል ተገጣጠምን።አይኔን ሰብሬ ወደ ዋና መግቢያው አመራሁና
"እንደ ሽማግሌ ጋዜጣ እያነበብክ ነው?"
ረጅም ሳቁን ለቀቀውና "ግቢ ገና ቁርስ እየበላ ነው ኢክሩም አለች"አለኝ።እቃዎቹን እንደያዝኩ ወደ ውስጥ ዘለቅኩ።ከአብደላህ ጋር ስንሳሳቅ ስንተቃቀፍ ስንጫወት ቆይተን መሄጃዬ ሲደርስ
"በቃ ልነሳ..."ብዬ የአብደላህን ጉንጭ ሳምኩት። አትሂጂ አይነት ተጠመጠመብኝ
"አሰብኩት ይሄ ነገር ዘውታሪ ቢሆን...በቃ ለምን አብራቹ አትሆኑም?በርግጥ ልጁ በለራም ስለተወለደ አባት የለውም ግን በቃ ጥምረታቹ ነገሩን ያሳምረዋል"ኢክሩ ነበር ያለችው።ኢምሩ እና እኔ በመተፋፈር ተያይተን አብደላህን አላቅቄ ከቤት ወጣሁ...

ማግስቱን ቁርስ ከወንድሜ ሀሱ ጋር እየበላን
"ልድርሽ ነው ምን ታስቢያለሽ?"አለኝ
"እስኪ አቀልድ...ይልቅ ከኢሙ ጋር አውርተን ነበር አንተ ራስህ መች ነው ምታገባው?"
"ካንቺ ሰርግ ቡኋላ"
"ባክህ ከዚ ቡኋላ ተስፋም የለኝም"
"ወርቅ እኮ ጭቃ ውስጥ ወደቀ ተብሎ አይተውም ታውቂያለሽ አደል?ይልቅ ቁምነገሬን አስጨርሺኝ ልድርሽ ነው"
"ለማን ነው ደሞ ምትድረኝ?"
"ለ....

ስፍራው ድምቅ ብሏል።አብሮ አደጎቼ ከጥንዶቻቸው ጋር በየቦታው ይታያሉ።የሰርግ መንዙማ ተከፍቶ ይባስ ነገሩ ልዩ ሆኗል።ከሁሉ በላይ አሚር ሰርግ ሳይሆን ለቅሶ እንደታደመ ሰው ከጥግ ተክዞ ተቀምጦ ሳይ ይባስ ትኩረቴን ሰርቆታል
"እ...ማንን ነው ምታዪው?በሰርግሽ ቀን ልትኮበልዪ ነው እንዴ?"አለኝ ኢምሩ ወደኔ በፈገግታ እየተመለከተ። አልሃምዱሊላህ ጥሎ የማይጥለው ጌታ ከዛ ሁላ የሀራም ጊዜያት ቡኋላ ቀልብ አስገዝቶን ወደ ሀላሉ መንገድ አምጥቶን ኢምሩ ወንድሜን አውርቶት እየተዘወጅን ነበር
"ወይ አሚሬ...እናቱን አናግሮ እኔንም ከዛ ስብራት መታደግ እየቻለ አሽቀንጥሮ ከጣለኝ ቡኋላ ዛሬ ተስፋ ቆርጦ ብቸኛ ሆኖ ሳየው የምድር መገለባበጥ አስገረመኝ...ያንተንም የረሳውልህ መስሎህ"ወደሱ በፈገግታ ዞርኩ
"ተካካስንኮ ሄሩ ፍቅር አንቺም ልጄን ባለመስጠት ተበቅለሽኝ ነበር"
"ላለፉት የሀራም ጊዜያት ምህረትን በመፈለግ ብዙ የኢባዳ ጊዜያት እንዳለብን እንዳትረሳ እሺ"
"እሺ የኔ ሚስት"
"አትሟዘዝ አሁን"ፈገግታዬን ብልጭ አረኩለት

በትዳር ውስጥ ስላለው ደስታ መብራሪያ ያንሰኛል።መጨረሻው የኔ አይነት ህይወት ላይኖራቹ ይችላል ምናልባት ግን የሀራም ፍቅር ሴትን ልጅ ርካሽ ነው የሚያረጋት።የሴት ልጅ ክብሯ ሂጃቧ ሀያእ እና ሀይማኖቷ ነው።ቁጥብ ከመሆንሽ የምታገኚው መልካም እና የተረጋጋ ባል ነው በሀራም ፍቅር ውስጥ ካለሽ ግን አላህ ካላለ በስተቀር መጨረሻሽ ገደል ነው...

#ተፈፀመ

@ikrima_tube

1 year, 3 months ago

ሁቦች ሄሩ ፍቅር የተሰኘውን ታሪክ ዛሬ አንለቅም?ነገ ማታ የመጨረሻው ክፍል ይለቀቅ እና ሁላችንም ሄሩን እንገላገላታለን?‍??ለዛሬ አልፎናል?

1 year, 4 months ago

----------♡♡♡----------
#heru_fkr
----------♡♡♡----------
ምዕራፍ፦2
ክፍል፦#45
በፀሀፊ፦hafu

"ምንድነው ምትዪው?አለቃዬኮ ነው እንዴት ከዚ ጋር ትጠረጥሪኛለሽ??"
"በቃ ነግሬሻለው....ቆይ ግን ያምሻል እንዴ?ጀግናዋ ሄሩ የታለች ቆይ?የሚጠቅማትን ምታቀው ለአላማዋ ለራሷ ምኖረዋ ሄሩ የት ገባች?ማማ ልክ ናት አንቺ አእምሮሽ ልጅ ሳለሽ ነበር የሚሰራው...አእምሮሽን መጠቀም ባለብሽና ልብና ስሜትሽን መርገጥ ባለብሽ ሰአት ግን ሞኝ ሆንሽ"
"አደብ ይኑርሽ ስለረሳሁት ነገር አታውሪ"
"ዞሮ ዞሮ ስህተትሽን የመድገም መንገድ ላይ ነሽ"በንቀት
ተመለከተችኝ።ከአልጋ ላይ ቦርሳዬን አንስቼ ወጣሁ።

ወደ ስራ ቦታ ለመሄድ ያሰብኩ ቢሆንም ኢሙ ስላቃጠለችኝ የአሚርን ጥያቄ ተቀበልኩት።ሀዋሳን ከመኖር እና ከስራ በዘለለ ብዙ ስለማላውቃት በሱ ምርጫ ቦታ ተመርጦ ጉዞ ጀመርን።
"ምንድነው ፊትሽን ጥለሽዋል?"አለኝ ዝምታ ሳበዛበት። ከኋላ ወንበር ተቀምጬ በመስኮት አሻግሬ አያለሁ። ህይወቴን ስላበላሸው ኢምሩ፣ህይወቱን ስላበላሸሁበት ረዩ፣እምነቴን ያጓደልኩባቸው ቤተሰቦቼ...ስለሁሉም አስባለሁ።እውነትም አእምሮዬን ሳላጣማ አልቀርም
"እንዲው ነው ቀኑ ይደብራል"
"አረ የኔንም ውሎ ሽክክ አታርጊው ቆፍጠን በይ ዱካክሽን አራግፊ"አለኝ ላይ በተሰቀለው መስታወት በጨረፍታ እያየኝ።ፈገግታው ንግግሩ ወንዳወንድነቱ ኢምሩን ነው።ምናልባትምኮ ፀባዩም የኢምሩ ይሆናል ማን ያውቃል?

"እኔ ምልህ ፍቅረኛ አለህ??"አልኩት ቁርስ ስንበላ በመሀላችን የነበረውን ዝምታ ለመስበር ጨዋታ እያዘጋጀው
ሳቀ።"ቢኖረኝ ካንቺ ይደበቅ ነበር??"
"Maybe..."ፈገግ አልኩለት እና"ኖሮህስ አያውቅም?"
"በፍቅር አላምንም.... ሰዎች እንደሚሉት አይነት ፍቅር ተሰምቶኝም አያውቅም"
"እንዴት?"አልኩት በመገረም
"ለምሳሌ....ካንቺ ብጀመር መጀመርያ ያፈቀርሽው ልጅ ራስሽን ክብርሽን አሳልፈሽ ሰጠሽው እኔ የዚን ያህል የሚደርስ ፍቅር ውስጤ ተፈጥሮም አያውቅም... ያኔ ስለሱ ደስታ እንጂ ስለ ራስሽ ክብር አልተጨነቅሽም ሲቀጥል እሱ ራስሽን አሳልፈሽ ከሰጠሽው በፊት ራሱ አያፈቅርሽም ቢያፈቅርሽ ኖሮ ሰጠሽውም አልሰጠሽውም ይወድሻል...ፍቅርኮ በክብር ጉዳይ መለያየት አደለም ፍቅር በሆንሽለት ልክ ሲወድሽ ነው የሰፈርሽም ልጅ ይወድሻል ለማለት ይከብደኛል መውደድ የትኛውንም ክፋት የትኛውንም ጥፋት በይቅርታ ብቻ ሳይሆን ያለ ይቅርታም ይታበሳል.."
"ግን አልገባኝም..."
"ሄሩ ምን መሰለሽ??በዚ ሰአት ፍቅር መጠቃቀም ነው ሴት ገንዘብ ታያለች ወንድ መልክ እና ንፅህናን ያያል ከወደደሽ ስለወደደሽ ላይጎዳ ሲል ይጠይቅሻል.... ያፈቀረ አይገባውም ተይው"ሳቀብኝ።ግራ ነው ያጋባኝ
"ያምሀልኮ የምር"ብዬ ፈገግ አልኩለት።

አንድ ሳምንቱ ከሱ ጋር ነበር ያለፈው ማለት ይቀላል ኢሙ በየቀኑ ስታጉረጠርጥብኝ አንዳንዴም ስታስጠነቅቀኝ ማየት የተለመደ ነው።እኔ ደሞ ጓደኛዬ እሱ ነው።ቢፈላሰፍብኝም ንግግሩ ልቤን ይሞላዋል በህይወት ተስፋ ስቆርጥ እያላገጠብኝም ቢሆን motivate ሚያረገኝ እሱ ነው።ኩራቱ ወንድነቱ ከሱ ጋር ስሆን ይባስ እንድወደው እንጂ እንድሰለቸው አያረጉኝም።

ዛሬ አዲስ አበባ የምሄድበት ቀን ነው።ኢሙ እና አሚሬ ሊሸኙኝ በር ጋር ይጠባበቁኛል።የሚያስፈልገኝን ሁሉ ይዤ አብደላን ስሜ ፋፊን ተሰናብቼ ወጣሁ።ኢሙ ከመኪናው በር ጋር ተለጥፋ ጥርሷን ትበላለች።እሱ ጋቢና መነፅሩን ገርግጮ እንደ ዲያስፖራ በኩራት ተቀምጧል።ኢሙና እኔ ከኋላ ተቀምጠን መንገድ ጀመርን።
"ምንድነው ስለኔ መጥፎነት ነግረሻታል እንዴ?"አለኝ አሚር በፈገግታ ከላይ ባለው መስታወት እየተመለከተኝ ወደ ኢሙ ስዞር ጀርባውን በግልምጫ እያፈረጠችው ነው
"ሼህ ነገር ናት ወንድ አትወድም ለዛ ነው..."አልኩት እኔንም ገልምጣኝ ወደ መስኮቱ ዞረች።አሚር በየመሀሉ ቀልድ ጣል እያረገ ብቻውን ይስቃል።እኔ በዝምታዬ እየፀናሁ ነው።ኢሙማ ጭራሽ የለችም ማለት ይቻላል

"ስደርስ እደውልላቹዋለው..."አልኳት ኢሙን አቅፌ
"እሺ...ሀሱን ሰላም በይልኝ እንደናፈቀኝ ንገሪው እንደምንገናኝ እኔም በቅርቡ መጥቼ እንደማየው ንገሪው አደራ"አይኗ ስር ኩልል ያለውን እምባ እየጨመቀች
"እሺ የኔ እህት ወድሻለው"
"እኔም"አለችኝ ደግማ እያቀፈችኝ።አሚር ስንሟዘዝበት ራቅ ብሎ ቆመ።እኔና እሷ ረዥም ስንብት አድርገን አሚርን እጄን አውለብልቤ ተሰናበትኩት።

የደረስኩት ማምሻውን ነበር።ረዩኒ ስለተቀበለኝ እነ ከሪማ ቤት ነበር ያረፍኩት።ሚሸክክ ነገር አለው።የከሪማ
ፊት ላይ ማየው ነገር አልመችሽ አለኝ።ረዩ ወጣ ነገር ካለማ ጭራሽ ግልፅ ታወጣዋለች።እሱ መጥቶ ስናወራ ደሞ ያቅለበልባታል።የሚሄድባት ይመስል ከሷ ጋር ብቻ እንዲያወራ ትፈልጋለች።እኔ መጅሊሱን ደገፍ ብዬ የነሱን ጨዋታ መከታተልን መረጥኩ።ረዩ በግድ አውሪ አይነት የሷን ወሬ አቋርጦ ከኔ ጋር ርዕስ ይጀምራል ጣልቃ ትገባለች....

"ሀቢቢ..."ብረቱን የያዘበት እጁን ያዝኳቸው።ፀጉሩ አድጎ ከስቶ ሳየው ጫካ የኖረ ሽፍታ እንጂ ሀሱን አልመስልሽ አለኝ።
ክፍል፦#46 ይቀጥላል....

@ikrima_tube

1 year, 4 months ago

ቀናቶች በኔ ላይ ሲሆኑ ታጋሽና ውሳኔህን ወዳጅ አድርገኝ፡ ቀናቶች ለኔ ሲሆኑልኝ አንደበቴን ለምስጋና የተገራ አድርግልኝ፣በዋልክልኝ ፀጋም ውዴታህን ምሸምት አድርገኝ?....
ያአላህ ያረቢ ያረቢ??

@Ikrima_tube

1 year, 4 months ago

አላህዬ ቀልቤን ባንተ ፍቅር❤️
የተንጠለጠለ አድርግልኝ!
ካንተ ከሚያርቀኝ ነገሮች ሁሉ አርቀኝ?

እስክገናኝህም ድረስ ጽናትን ለግሰኝ!
?ያአላህ?

@Ikrima_tube

1 year, 4 months ago

----------♡♡♡----------
#heru_fkr
----------♡♡♡----------
ምዕራፍ፦2
ክፍል፦#43
በፀሀፊ፦hafu

<<ዶክተር ምን መሰለህ ስለኔ ህይወት በደንብ ታውቃለህ።እናም አንተ ይሄን ሁሉ እያወቅክ እኔን ለማግባት መጠየቅህ በጣም ጥያቄ ሆኖብኛል። አእምሮዬ ቀልድነው አደለም በሚል ሁለት ሀሳብ ተወጥሯል።አንተ እንደ ሌሎች ወንዶችነህ አደለህም ማለት አልችልም።እዚ ለመድረሴ እናም የተሻለ ለመኖሬ በጣም ትልቅ ድርሻ ተወጥተህልኛል ከቃል በላይ ነህ ውለታህን በምን መክፈል እንዳለብኝ ሁላ እንጃ ግን ወንድ አንዳንዴ እስኪወድቁለት ነው ለሰው ሚኖረው ከወደቁለት ቡኋላ ረጋጭ ይሆናል።አላቅም ብቻ ላምንህም ላላምንህም አይቻለኝም ግን ለጥያቄህ መልሴ እሺ ነው።እኔ ማግባት እፈልጋለው አንተ ከዚ ደባሪ ማንነቴ ከተቀበልከኝ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ.." ሚል ፅፌ ከላኩለት ቡኋላ ስልኬን አጥፍቼ ወደ ቤት ገባሁ።ሹ እና ኢሙ ተኝተዋል በቀስታ ወደ ቦታዬ አመራው.....

"የሀዋሳ አሳ ቀምሰሽ ታውቂያለሽ?"
"አው እንደሚወራለት ግን አላገኘሁትም"አልኩት በፈገግታ
"ፕፍ ማን የሰራውን በልተሽ ነው ባክሽ?ከፈለክሽ እንዴት እንደዚ ዝቅ አድርገው ያወሩለታል የሚያስብል አሳ ልጋብዝሽ"ወንዳወንድ፣ጠይም፣ረጅም፣ደረቱ ሰፊ፣ ፀጉሩ ሉጫ ቆንጅዬ ወንድ!...አለቃዬ አሚር(ያኔ ፋፊ እና ኢሙ ሙድ የያዙብኝ)
"ደስ ይለኛል"ከማለቴ ከተቀመጠበት ተነሳ።

ቦታው ነፋሻማ ነው።እጅግ ለአይን የሚስብ.....፤ አረንጓዴ ምድር ከውሃ አጠገብ ሲሆን ደስ ይላል።ቦታ ይዘን ተቀመጥን።ቡዙ ባል እና ሚስቶች፣ሽማግሌዎች፣ ወጣት ጓደኛሞች፣ፈረንጆች አሉ።ውሃው ላይ በመርከብ የሚሳፈሩ፣በየቦታው ፎቶ የሚያነሱ፣አእዋፋትን የሚመግቡ አካላትም ይታያሉ።እጅግ ሀሴት ሚፈጥር ስፍራ ነው።
"እማምዬ የተለመደችዋን"አላት ከርቀት። ከተቀመጠችበት ተነስታ መጥታ ሞቅ ያለሰላምታ ሰጠችን።
"የማናት ቆንጆ..."አለች ወደኔ በእናትነት ፍቅር እያየች
"የኔ ናት ቆንጆ"ብሎ ሚያምርበትን ፈገግታ አስከተለ
"ውይ ማሻአላህ የሀዋሳ ልጅ አመስልም ኬት አመጣሀት?"አለች ሳም እያረገችኝ
"የሸገር ሰው ናት ለዛ ነው አውራሬስ ሚያስወድስ ፊት ያላት.."
"ቲ...አፈር"አልኩት በብሽቀት
"ራሱን መስለሽው ነው የኔ ልዕልት ዝም በይው... ተጫወቱ ይዤላቹ ልምጣ"ብላ በመጣችበት ፍጥነት ተመልሳ ሄደች።
"ቦታው ራሱ ያምራል..."
"ልክ እንደኔ"አለ በኩራት።በጣም ኩራት አለበት እኔ እኔ ማለት ይወዳል።ለሱ ቀልድ ቢሆንም የምሩን የሚል ነው ሚመስለው።እኔ ምንም አይመስለኝም ምክንያቱም ኩራት ይመስላል እንጂ እውነቱን ስለሚናገር!በስራ ጉዳይ ነው የተዋወቅነው የሱ መስሪያ ቤት የተቀጠርኩት በዶክተር እርዳታ ነው። ፈገግታ አያበዛም ኩስትር ያለ አለቃ ነው።ከኔ ጋር ለመግባባት ብዙም ጊዜ አልፈጀብንም።የኔን ስልክ love ብሎ ሴቭ አርጎት ሳፋጥጠው አረሳስቶኝ ነበር።ሆኖም ከቀናት ቡኋላ ከራሱ አፍ ከእህትነት በዘለለ ተመኝቶኝ እንደማያቅ ነግሮኛል።በየሆነ ቀኑ ይነሳበት እና ባል ባል ይሰራራዋል።የማይጨበጥ ባህሪ ስላለው አልታዘበውም...

"ደሞ...."አለኝ ወደኔ እየተመለከተ።አይኖቹ ከሌላ ጊዜ በተለየ እኔ ላይ ሲያፈጡ አንገቴን ደፍቼ
"ምን?"አልኩት
"እኔ...እ....
ክፍል፦#44 ይቀጥላል.....

@Ikrima_tube
@Ikrima_tube

1 year, 4 months ago

ሴት?

አዲስ የተጋቡ ጥንዶች የተከራዩት ቤት ሄደው 1 ህግ ያወጣሉ።ህጉም
"ለ3 ቀን የባልም ሆነ የሚስት ቤተሰብ ቢመጡ ማንንም ሳያስገቡ ብቻቸውን ጊዜ ማሳለፍ"የሚል ነበር።

አንድ ቀን ሙሉ የሁለቱም ቤተሰቦች መተው በር ቢደበድቡ መልስየለም። ሚስትም ባልም ለቤተሰቦቻቸው በር ለመክፈት ፍቃደኛ አልነበሩም በዚ መንገድ የመጀመሪያው ቀን ህጉ ሳይፈርስ አለፈ።

2ኛው ቀን ጠዋት አካባቢ የባል ቤተሰብ መተው ቢያንኳኩ መልስ የለም።ከብዙ ደቂቃ ማንኳኳት በኋላ ተሰላችተው ሄዱ።ብዙም ሳይቆይ የሚስት ቤተሠብ መጡ።ሲያንኳኩ ስትሰማ ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች።አላስቻላትም ስምምነቱን አፍርሳ በሩን ከፈተች።

.....አወሩ,ተጫወቱ።
.
.
.
ከወራት በኋላ
ቤት ውስጥ ባል እና ሚስት እንዲሁም የባል እና ሚስት ቤተሰቦች ተሰብስበው ሳለ ስለ ልጅ እያወሩ
ሚስት፦ለምን?ወንድ ነው ምፈልገው ትለኝ አልነበር? ሀሳብህን ምን አስቀየረህ???
ባልም በዝምታ ሲመለከታት ቆይቶ፦ምክንያቱም ነገ አግብታ፣በር ምትከፍትልኝ እሷ ስለሆነች!።

??????

ክብር ለሴቶቻችን?❤️

@ikrima_tube

1 year, 4 months ago

ያን ሁሉ ፈተና
በምን አቅምሽ አለፍሽው?
الله❤️
الله?
الله?
አላህ አነሳኝ ደርሶ እንደገና?

@Ikrima_tube

1 year, 5 months ago
አጂብ ትረፍ ያለች ነብስ ኢላሂ***?******?***

አጂብ ትረፍ ያለች ነብስ ኢላሂ??

በከባድ የልብ ህመም የሚሰቃይ በሽተኛን ያሳፈረ አንቡላንስ ቀይ ማብራቱን እያንቦገቦገ በፍጥነት ወደሆስፒታል ጉዞ ጀመረ። በመንገዱ መሐል ከከባድ መኪና ጋር ተላትሞ ዱቄት ሆነ። ሹፌሩ፣ ነርሶችና አስታማሚው ሁሉ ሲሞቱ በህይወት የተረፈው....

መጨረሻውን ለማንበብ ከታች ባለው link join ይበሉ
?????????????

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago