Shalom Dental Clinic

Description
For your teeth and oral cavity
0911424242
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 23 hours ago

Last updated 5 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 3 days ago

1 год, 2 месяца назад

Gingival bleeding (የድድ መድማት)
• የዲድ መድማት በጣም የተለመደና በብዙ ሰዎች ላይ የሚታይ የጤና ችግር ቢሆንም ብዙዎች ግን እንደ ቀላል ነገር ያዩታል።
ምክናየቶቹ
1. በዘፈቀደ ጥርስን በማይመከርና በማይጠቅም መንገድ መቦረሽ
2. የማይገጥም ሰው ሰራሽ ጥርስ ለማስገባት የሚደረግ ጥረት
3. የደም ካንሰር
4.የቫይታሚን "ሲ እና ኬ" እጥረት
5.ደም እንዳይፈስ የሚያደርገው ፕላትሌት የተባለ የደም ክፍል መቀነስ
6. እርግዝና
7. የዲድ ኢንፌክሽን(Gingivitis, Periodontitis)
8. የጥርስ መነቃነቅና ስሩ መቦርቦር
9. ጥርስን በተለያዬ ባእድ ነገሮች መጎርጎር
10. የተለያዩ ህመሞች
ህክምናው
• በቫይታሚን ሲ እና ኬ የተለፀጉ ምግቦችን መመገብ
• የአፍን ንፅህና መጠበቅና መንከባከብ
• ሻካራ የጥርስ ቡርሽ አለመጠቀም
• ሌላ የጤና ችግር ካለ ማረጋገጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

1 год, 3 месяца назад

✍️ ለመልካም የአፍ ጠረን እነዚህን ተግባራዊ ያድርጉ….

?ጥርሶትን ጠዋት እና ማታ በብሩሽ እና በጥርስ ሳሙና ያጽዱ
?ሁልጊዜ ከተመገቡ በኋላ አፎትን በውሀ የመጉመጥመጥ ልምድ ይኑሮት
?ጥርሶትን በብሩሽ ሲያጸዱ አብረው ምላሶትን መቦረሽ አይርሱ
?የአፍ ጠረንን የሚቀይሩ ምግቦች ማለትም እንደነጭ ሽንኩርት  ከመመገብ ይቆጠቡ
?የማጨስ ልምድ ካሎት አሁኑኑ ለማቆም ይሞክሩ
?በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ማስቲካ የማኘክ ልምድ ይኑሮት
?በቂ ውሀ የመጠጣት ልምድ ያዳብሩ
?በአመት 2 ጊዜ የጥርስ ሀኪም ጋር የመታየት ልምድ ይኖረወት.
0911424242
0970517151

1 год, 3 месяца назад

መጥፎ የአፍ ጠረን | Halitosis.

መጥፎ የአፍ ጠረን ማህበራዊና  ስነ ልቦናዊ ጫና ያሳድራሉ ከሚባሉ የበሽታ ዓይነቶች ኣንዱ ነው። ይህ የበሽታ ዓይነት ከስነ-ልቦና ጫና ባለፈ በትዳር አጋሮች መካከልም የሻከረ ግንኙነት የመፍጠር አቅምም ኣለው።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከመቶ አዋቂ ሰዎች ሶስቱን ያጠቃል። በበሽታው ተጠቂ ከሆኑት ከመቶ ሰዎች ዘጠናዎቹ ላይ አፋቸው ውስጥ በሚፈጠሩ ችግሮች የሚከሰት ሲሆን ከመቶ አስር ሰዎች ላይ ደግሞ ከአፍ ውጪ ባሉ ችግሮች የሚፈጠር ነው።

አፍ ውስጥ በሚፈጠሩ ችግሮች የሚመጣ  መጥፎ የአፍ ጠረን:

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ይህ በሽታ አፍ ውስጥ በሚፈጠሩ ችግሮች የመከሰት ዕድሉ የሰፋ ነው። በመሆኑም ብዙውን ጊዜ የአፍ ንፅህና ካልተጠበቀ አፍ ውስጥ በሚገኙ በ መቶዎች የሚቆጠር ዝርያ ባላቸው ባክቴሪያዎች የፕሮቲንና ሌሎች የምግብ ዓይነቶችን ተመግበው እንደ ተረፈ ምርት ከሚለቁት ቮላታይል ሰልፈር ኮምፓውንድ (VSC) የሚመነጭ ነው።

ሌላኛው ሰው ሰራሽ ወጪ ገቢ ጥርስ ለረጅም ሰዓታት ያለማፅዳትና ሌት ተቀን አድርጎ በመታየት፣ የምራቅ ምርት መቀነስ። ሰው በእንቅልፍ በሚያሳልፍበት ወቅት የምራቅ ምርት ከመቀነስም በሻገር ሙሉ ለሙሉ ሊቆምም በመቻሉ ለባክቴሪያዎች መራባት የጎላ አስተዋፆ ያደርጋል፣ ፆም ላይ በሚኮንበት ወቅት (የተለያዩ ምግብ ዓይነቶች አፍ የማፅዳት አቅም ስላላቸው መጥፎ የአፍ ጠረን ይቀንሳሉ)፣ በቀን ውስጥ በቂ ውኃ አለመውሰድ፣ አፍ ውስጥ የቆሻሻ ክምችት ሲኖር፣ የተለያዩ የአፍ ውስጥ ካንሰሮችና ቁስለቶች ሲኖሩ የአፍ መጥፎ ጠረንን የመጨመር አቅም ኣላቸው።

ከአፍ ውጪ ባሉ ችግሮች የሚፈጠሩ መጥፎ የአፍና የአፍንጫ ጠረኖች:

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከነዚህ ችግሮች መካከል በአፍንጫ ምክንያት የሚመጡት 2% የሚይዙ ሲሆኑ ከነዚህ ችግሮች መካከል አፍንጫ ውስጥ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች፣ ያልተለመደ የአፍንጫ ፈሳሽ መመንጨትና የሳይነስ ህመም የኣንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ።

ከአፍንጫ በመቀጠል ከአፍ ውጪ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ምክንያት ከሆኑት መካከል የተለያዩ ጉሮሮ ውስጥ የሚታዩ ዕጢዎች፣ የሳንባ ኢንፌክሽንና ዕጢ ፣ የቆዩ የኩላሊት በሽታዎች፣ የከፋ የስኳርና የጨጓራ በሽታዎች።

የመጥፎ አፍ ጠረን ህክምናዎቹ:

ህክምናው ከመጀመሩ በፊት የመጥፎ የአፍ ጠረኑን ምክንያትች መለየት ኣለበት። መጥፎ የአፍ ጠረን ካለባቸው መቶ ሰዎች ዘጠናዎቹ አፍ ውስጥ በሚፈጠሩ ችግሮች ስለሆነ በቂ የአፍ ንፅህና መጠበቅ። አፍ ውስጥ የተከማቸ ቆሻሻ ካለ በሐኪም ማፀዳት ፣ መድኃኒትነት ያላቸው የአፍ መጉሞጥሞጫዎችን በሐኪም ትዕዛዝ መጠቀም፣ በቀን ውስጥ በቂ ውኃ መውሰድ ፣ የጥርስ ሳሙናና ብሩሽ ተጠቅሞ በቀን ሁለቴ ጥርስን ማፅዳት፣ ከፍተኛ ፕሮቲን የያዙ ምግቦችን አለማዘውተር ለመጥፎ የአፍ ጠረን ምክንያት ከሆኑት ከቮላታይል ሰልፈር ኮምፓውንድስ ተጋላጭነትን ይቀንሳል ፣ የምራቅ የመመንጨት መጠን የሚጨምሩ ነገሮችን ለምሳሌ ከስኳር ነፃ የሆኑ ማስቲካዎች ማዘውተር የምራቅ መመንጨትን ስለሚጨምር ምራቅ ውስጥ የሚገኘውን ላይሶዛይም(Lysozyme) የተባለውን ኢንዛይም መጠን ስለሚጨምር የባክቴሪያዎች ቁጥር እጅጉን ይቀንሳል፣ የተለያዩ ቁስለቶችና የካንሰር ዓይነቶች ካሉ በተገቢው ህክምና ማስወገድና ሰው ሰራሽ ጥርስ ማታ ሲተኙ አፅድቶ በንፁህ ውኃ ነክሮ ማሳደር መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ ከሚረዱ መንገዶች መካከል ኣንዱ ነው።

በዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ: Dental Surgeon

1 год, 6 месяцев назад

ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈጠር ህመም | Alveolar Ostitis

ጥርስ በተለያዩ ምክንያቶች ሊነቀል ይችላል ከተነቀላ በኋላ ግን የከፋ ህመም በብዙ ምክንያት ሊከሰት ይችላል ይህም የሚፈጠረው ሐኪምዎ እንዲተገብሩ ያዘዝዎትን ትዛዝ ሳያከብሩ ሲቀሩ፣ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰዓት ጥርስ የሚነቀሉ ከሆነ፣ የወሊድ መቆጣጠርያ መድኃኒት እየወሰዱ የሚነቀሉ አሆነ፣ ጥርስ ከተነቀለ በኋለ በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምባሆ የሚያጨሱ ከሆነ የተባለው ህመም ሊከሰት ይችላል።

የህመሙ ዓይነት የሚጠዘጥዝ ህመም ሲሆን የተነቀለበት ቦታ ቁስሉ ወደ ግራጫ መልክ የመቀየር፣ የአፍ ጠረን የማምጣት እና ብሎም እብጠትም ጭምር ሊኖረው ይችላል።

ነገር ግን ጥርስ ከተነቀለ በኋላ ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ ዓይነቶች አሉ እነሱም

  1. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያን ለ 30 ደቂቃ ያህል ሐኪምዎ ያስነከሰዎትን ጥጥ በተነቀለበት ቦታ ነክሰው ማቆየት

  2. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ትኩስ ነገር መብላትም ሆነ መጠጣት አይመከርም መመገብ ካለብዎ በረድ ወይም ለብ ያለ ነገር መሆን አለበት

  3. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት ደምም ይሁን ምራቅ መዋጥ እንጂ መትፋት በፍፁም የተከለከለ ነው

  4. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ለተከታታይ 24 ሰዓታት የትኛውም ዓይነት ፈሳሽ ነገር ሲጠጡ መምጠጫ(Straw) መጠቀም አይመከርም

  5. ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጥርስ የተነቀለበትን ቦታ በእጅ፣ በምላስ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች መነካካት አይመከርም

  6. ምግብ ከበሉ በኋላ የበሉት ምግብ በቁስሉ በመከማቸት ለኢንፌክሽን የማጋለጥ ዕድሉ የሰፋ ስለሆነ እንደተመገቡ ጨው በውኃ በመቀላቀል ለብ አድርገው ተጉሞጥምጦ መትፋት

  7. ቁስሉ እንዲድን አጋዥ ይሆናሉ ተብሎ በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶች ካሉ በትዕዛዙ መሰረት መውሰድ

  8. ጥርስ ከተነቀለበት ደቂቃ አንስቶ ቢያንስ ለተከታታይ 10 ቀናት ትምባሆ ማጨስ አይመከርም።

  9. ከላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዛት ሁሉ ተግብረው ነገር ግን ህመም እየበረታ ከሔደ እና እብጠት ካመጣ ፈጥነዉ ሐኪምዎትን ያማክሩ።

እነዚህን ትዕዛዛት ከተገበሩ ሊመጣ የሚችለውን ህመም መከላከል ይችላሉ።

በ ዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ ፡ Dental Surgeon

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 23 hours ago

Last updated 5 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 3 days ago