Muktarovich Ousmanova

Description
Ethiopia forever
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

2 months, 3 weeks ago
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዉጤት ለማየት

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዉጤት ለማየት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የውጤት መግለጫ አማራጮች ከዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ማወቅ ይችላሉ።

በዚህ መሰረት

  1. ፖርታል፡- https://result.eaes.et
  2. በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- https://t.me/EAESbot
  3. በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡- 6284 ላይ ‘R’ን በማስቀደም የመለያ ቁጥር በማስገባት (ምሳሌ R1234567) መልዕክት በመላክ ውጤትዎን ማወቅ ይችላሉ፡፡ ይህ አማራጭ ኢትዮ ቴሌኮም የሚያስከፍለው መደበኛ የSMS ክፍያ ይኖረዋል።

ከውጤት መግለጫ ፖርታልና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድ ይችላሉ፡፡

2 months, 3 weeks ago
ጌታቸው ረዳ ሹመት እንዳይሰጥ ታገደ ***‼️***

ጌታቸው ረዳ ሹመት እንዳይሰጥ ታገደ ‼️

የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች፥ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አዲስ ሹመት መስጠትም ሆነ ማውረድ እንዳይችል አገዱት።

የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ፖለቲካ ላይ በቀጥታ እጃቸው በማስገባት የተፈጠረውን ውጥረት እያባባሱ ይገኛሉ።

ፍጥጫው ተባብሷል። የተለያዩት ሀይሎች የሚደግፉአቸው የፀጥታ ሀይል አላቸው። ግጭቱ ከተባባሰ ለትግራይ መልካም አይደለም። ሰላም ለትግራይ ህዝብ። የትግራይ ህዝብን በቃህ ይበለው?

2 months, 3 weeks ago
ህወሓት የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ወነጀለ

ህወሓት የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ወነጀለ

በፖለቲካዊ አቋማቸው በአባላቶቼ ላይ ከሓላፊነት የማንሳት፣ የማገድና የማሰር እርምጃዎች በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እየተወሰደባቸው ነው ሲል ህወሓት ከሰሰ። የህወሓት ከፍተኛ አመራር የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እርምጃዎች ሕገወጥ ሲሉ ገልፀዋቸዋል። በሌላ በኩል የህወሓት አባላት እና አመራሮች በሽረ ልያካሂዱት የነበረ የተቃውሞ ሰልፍ ተከልክሏል።
በዚህም ፍጥጫው ተካሯል
DW የዘገበው ነው

5 months, 2 weeks ago
Muktarovich Ousmanova
5 months, 2 weeks ago
Muktarovich Ousmanova
5 months, 2 weeks ago

"ከወጣቶቹ ጋር በገንዘብ ተደራደሩ"... መፍትሄ የሚያሻው በተደጋጋሚ የሚደርሰኝ ጥቆማ

ጉዳዩ እንዲህ ነው፣ በሸገር ከተማ ስር ባሉ በርካታ ከተሞች በህጋዊ መንገድ ቤት ሰርተው፣ ካርታ አውጥተው ያሉ በርካታ ዜጎች አሉ። ነገር ግን ውሀ እና መብራት ስላልገባላቸው ብዙዎቹ ባለቤቶች ገና ኑሮ አልጀመሩባቸውም።

በዚህ መሀል የአካባቢው ወጣቶች ቁልፍ ሰብረው እየኖሩበት ወይም ለሌላ ሰው በኪራይ ያስገቡበታል። ባለቤቶቹ ስለጉዳዩ ክስ ለማቅረብ በአካባቢው ለሚገኙ ፖሊስ እና ሚሊሻ ቢሮ ሄደው ክስ ቢያቀርቡም ለጉዳዩ መልስ ከመስጠት ይልቅ ምላሹ "ከወጣቶቹ ጋር በገንዘብ ተደራደሩ" ሆኗል።

ቤት ኪራይ ተወዶባቸው ካለ መብራት እና ውሀ እንግባ ያሉ የቤት ባለቤቶች እንኳን በዚህ ምክንያት ቤታቸው መግባት እንዳልቻሉ ያደረሱኝ መረጃ ያሳያል።
ኤሊያስ መሰረት

5 months, 3 weeks ago
ብሔራዊ ውርደት ነው። የትውልድ ምክነት ነው። …

ብሔራዊ ውርደት ነው። የትውልድ ምክነት ነው። ያሳዝናል

5 months, 3 weeks ago
“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር …

“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ

የተፈጻሚነት የጊዜ ወሰኑ ባለፈው ሳምንት ካበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች፤ “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ። አቤቱታውን በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።

➡️ ጋዜጠኞቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” በማድረጉ መሆኑን ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ “ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

➡️ ሶስቱ ጋዜጠኞች “ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዛቸው”፣ ከተያዙም በኋላ “በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲኖርባቸው” ይህንን መብታቸውን መነፈጋቸውን ጠበቃው ገልጸዋል።

➡️ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ፤ ጋዜጠኞቹ “ከፍርድ ውጭ ተገድደው የተያዙ” መሆናቸውን ይገልጻል።

➡️ የፌደራል ፖሊስ የጋዜጠኞቹን “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር ላይ ማቆየቱ ሕገ ወጥ ተግባር ነው” ሲሉም የጋዜጠኞቹ ጠበቆች በአቤቱታው ላይ አመልክተዋል።

? ዝርዝሩን ለማንበብ ? https://ethiopiainsider.com/2024/13301/

@EthiopiaInsiderNews

5 months, 3 weeks ago
የጌታቸው ረዳ ጠባቂዎች ተቀየሩ***❗***

የጌታቸው ረዳ ጠባቂዎች ተቀየሩ
የፌዴራል መንግሥቱ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አዳዲስ ጠባቂዎችን እንደመደበላቸው ዘ-ጆርናሊስት ከታማኝ ምንጮች ሰምቷል።

የጌታቸው ረዳ አጃቢዎች መቀየር በሕወሓት እና ጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለውን የሰፋ ልዩነት ያሳያል ተብሏል።

ምንጮች እንደገለጹት፣ "ነባሩ ሕወሓት" በሚባለው እና እርሳቸው በሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለው ልዩነት በፕሬዝዳንቱ ላይ የደህንነት ሥጋት ሳይፈጥር አልቀረም።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለው ልዩነት የፖለቲካ ብቻ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳምንታት በፊት ከትግራይ ክልል ከመጡ ሰዎች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ደጋግመው "ጌታቸውን አግዙት፤" ሲሉ ተደምጠዋል።
?ያልተሰሙ አዳዲስ አለማቀፍና ሀገርአቀፍ ዜናዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join አድርጉ???
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

6 months ago
ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ …

ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ መፈጸማቸውን ተናገሩ።

ፖሊስ በአማራ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን አባላት ናቸው ያላቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሽብር ድርጊት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሶባቸው መገደላቸውን መግለጹ ይታወሳል።

የሁለቱ ወጣቶችን ሞት ተከትሎ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ለፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብ እና በወዳጆች የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው የናሁሰናይ አንዳር ጌ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት በርካታ ሕዝብ ታድሞ እንደነበር አንድ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት ሥነ ሥርዓትም በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago