ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
“አቶ ክርስትያን ታደለና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ሐኪም ቤት ዛሬም አልተወሰዱም” ቤተሰቦቻቸው
ባለፈው ሰኞ በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል የቅድመ ካንሰር ምርመራ ውጤት የተገለጠላቸውና የደም መፍሰስ እያጋጠማቸው ስለሆነ ቁስላቸው ለኢንፌክሽን ሊጋለጥ ስለሚችል ለዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘላቸው በእሥር ላይ ያሉት አቶ ክርስትያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ዛሬም ሆስፒታል ሳይወሰዱ መቅረታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግረዋል።
ሁለቱም የምርመራ ውጤታቸውን ቼክ አፕ ለማድረግና ለማወቅ ለዛሬ ሐሙስ ቢቀጠሩም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ግን «አጃቢ የለኝም» በሚል ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ ሳይወስዳቸው መቅረቱን ቤተሰቦቻቸው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
እሥረኞችን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወረ መሆኑን በመግለጽ በአጃቢ እጥረት ምክንያት ሁለቱን ተከሳሾች ወደ ሆስፒታል ያላቀረበው ማረሚያ ቤቱ ሌሎች ተከሳሾችን ግን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይዞ መቅረቡን ለማወቅ ችለናል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነፃነት አንደበት !
http://t.me/ethio251media
በወሎ ቀጠና ተጋድሎዎች ሲቀጥሉ አገዛዙ በአስገዳጅነት ያስወጣው ሰልፍ በተለያዩ ከተሞች መክሸፉ ተገልጿል።
የአማራ ፋኖ በወሎ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ አበበ ፈንታው በግንባር ተጋድሎና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋርቆይታ አድርጓል።
ተከታተሉት ....
የላስታው ያልተጠበቀ ጥቃት
በላስታ ቀጠና በፋኖ በተፈጸመ የደፈጣ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ
በወሎ ላስታ ቀጠና ልዩ ስሙ ድብኮ አከባቢ በተፈፀመ የደፈጣ ጥቃት አንድ የሻለቃ እና ሦስት የሻምበል አዛዦችን ጨምሮ በርካታ የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸው ታውቋል፡፡
የደፈጣ ጥቃት የተፈፀመበት ይህ የአገዛዙ ኃይል ከሰሞኑ ወደ አማራ ክልል የገባ መሆኑም ነው የተነገረው።
ከሌሎች የሃገሪቱ ክፍል ተወጣጥቶ ወደ አማራ ክልል ላስታ ላሊበላ ቀጠና እየገባ የነበረው አዲስ የገዢው ቡድን ወታደር ላይ ትናንት መስከረም 11/2017 ዓ/ም አመሻሹን በተፈፀመ የደፈጣ ጥቃት አንድ የሻለቃ እና ሦስት የሻምበል አዛዦችን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን መረብ ሚዲያ ጥቃቱ በተፈፀመበት አከባቢ የነበሩ የአይን እማኞችንና የፋኖ አባላቱን አነጋግሬ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
የደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው በጋሼና እና በላሊበላ ከተማ መካከል በሚገኙ ልዩ ስማቸው ድብኮ እና ግራኝ አምባ በተባሉ አከባቢዎች ላይ ሲሆን፡ በዚህም በገዢው ቡድን ኃይል ላይ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት መድረሱን አማራ ፋኖ በወሎ የአሳምነው ኮር ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ አባራው ገልጿል፡፡
በዚህ ጥቃት አንድ የሻለቃ አዛዥ እና ሦስት የሻምበል አዛዦችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፡ 12 የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያና ሦስት መገናኛ ራዲዮን በፋኖ እጅ መግባቱን ነው የኮሩ ቃል አቀባይ የገለፀው።
"የደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው የአገዛዙ ወታደሮች ከሰሞኑ ነው ወደ አማራ ክልል የገቡት፡ የመጀመሪያውን ጥቃት አድርሰንባቸዋል" ያለው የኮሩ ቃል አቀባይ ፋኖ ሞገስ አባራው፡ "ገዢው ቡድን እያስገባው ያለው ኃይል ካለን የተዋጊ ኃይል ብዛት አንፃር ያሉብንን አንዳንድ የትጥቅ ጉድለቶችን ያሟላልናል" ሲል ተናግሯል።
ዘገባው የመረብ ሚዲያ ነው!
ልዩ መረጃ!
ፋሽስቱ ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት የአሻንጉሊቶች ስብስብ በሆነው ፓርላማ ቀርቦ ሲዘጋጅበት የከረመውን ሴራ፣ ከፋፋይና መርዛማ ንግግሩን ያሰማል።
የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች ያደረሱን መረጃ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር እንደሚከተለው ያቀርበዋል፦
©ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!
Merja tv : Eutelsat 8 West B Freq: 11.636 Vertical. SR: 27.500 FEC: 5/6
Telegram: https://t.me/ethio251media
Twitter : https://x.com/251media?s=21
Rumble : https://rumble.com/user/ETHIO251MEDIA
Facebook: https://www.facebook.com/ETHIO251?mibextid=LQQJ4d
Website: https://www.ethio251media.org
Gofund.me : https://gofund.me/a2d99937
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana