መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

Description
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад

1 week, 6 days ago
**በሃገራችን በአንዳንድ አካባቢዎችና ህንጻዎች የሚቀቡ ቀለማት …

በሃገራችን በአንዳንድ አካባቢዎችና ህንጻዎች የሚቀቡ ቀለማት ምርጫ ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ

ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአንዳንድ አካባቢዎችና ህንጻዎች ላይ የሚቀቡ ቀለማት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጥሩት አዎንታዊና አሉታዊ ተፅኖን በተመለከተ መናኸሪያ ሬዲዮ ባለሙያዎችን አነጋግሯል ።

አርክቴክት ቤንጀዲድ ሚካኤል እንደገለጹት፤ በመኖሪያ ቤት ፣ በስራ ቦታ ፣በመዝናኛ ስፍራ ፣ ት/ቤት እና ሆስፒታል እንዲሁም በእምነት ተቋማት ፤ የሚቀቡ ቀለማት በእያንዳንዱ የህይወት እንቀስቃሴያችን ውስጥ ትርጉም እና ተፅዕኖ አላቸው ብለዋል፡፡ በምግብ ቤቶች የሚቀቡ ወጥ እና ደማቅ ቀለማት ረጀም ጊዜ ለማሳለፍ የምንፈልግባቸው ሌሎች ቦታዎች ቢቀቡ ለተጠቃሚው ስነ-ልቦናዊ መረጋጋት ላይ ተፅዕኖ ሊኖረዉ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ቀለማት የሃገርን አስተዳደር እና መልክ የሚወከሉ ናቸው፤ በሃገራችን እንኳን በየዘመኑ የተቀያየሩ መንግስታት የራሳቸው መለያ ነበራቸው፤ በተለይ አሁን በከተማችን ህንጻዎች ላይ እየተቀባ ያለው የግራጫ ቀለም በራሱ አሰልቺ ፤ ደብዛዛ እና ተመሳሳይ ነው ሲሉ የሚገልጹት ባለሙያው ፤ ከተፈጥሯዊ ቀለማት ጋር በማዋሃድ በተጠና መልኩ ለእይታ ሳቢ ማድረግ ላይ ሊታሰብበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ሌላኛው የቀለምና የስነ ውበት ባለሙያው ሰአሊ ኪሩቤል መልኬ እንደገለጸው ፤ቀለም በራሱ ሞቃት እና ቀዝቃዛ ተብሎ የሚከፈል ቢሆንም ሁሉም የቀለም አይነቶች በራሳቸው የትርጉም እና የስነ ልቦና ተፅዕኖ አላቸዉ ብሏል፡፡ ባደጉት ሃገራት እያንዳንዱ ቀለም የሚቀባው ጥናት ተደርጎ ነው ሲል ገልጾ፤  በስዕል ዘርፉም ብቻ ሳይሆን በፊልም እና በሌሎች ዘርፎች የራሱ የሆነ ትርጉም አለው፤ በተለይም በህንጻዎች ላይ የሚቀቡ ቀለማት የስነ ልቦና ፋይዳ አላቸው፤ በዚህም ቀለማት የስሜት መለዋወጥን ያመጣሉ ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በዘፈቀደ የሚቀቡ ቀለማት የ ስነ -ልቦና ተጽኖ በሎም የትርጓሜ ለውጥ የሚያመጡ በመሆናቸው ጥንቃቄ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ባለሙያዎቹ አመላክተዋል ።
__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52 *👉011-639-37-63
*የቀጥታ ስርጭት
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲  Youtube

1 week, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
1 week, 6 days ago
**በጊቤ ብሄራዊ ፓርክ የሚደረገውን ህገ-ወጥ ወረራ …

በጊቤ ብሄራዊ ፓርክ የሚደረገውን ህገ-ወጥ ወረራ ለመከላከል ፖለቲካዊ ወሳኔዎችን የሚሹ ጉዳዮች መኖራቸው አፈጻጸሙን እንዲጓተት አድርጎታል ተባለ

ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በጊቤ ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ ሰፍረው፣ ፓርኩ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎችን ለማንሳት በሚሰሩ ሰራዎች ላይ፣ የፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈልጉ ውስብስብ ችግሮች መኖራቸው ፈተና እንደሆነ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታወቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ፓርኩ በቀድሞው የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውሰጥ በነበረበት ወቅት፣ ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ፣ ለጉዳት እና ለህገ ወጥ ወረራ መጋለጡን የተናገሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ፣ ሳሙኤል መንገሻ ናቸው፡፡

በፓርኩ አካባቢ የሰፈሩ እና ወረራ ለማድረግ የሚሞክሩ አብዛኞቹ ሰዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ሳይሆኑ፣ ሰፊ የእርሻ መሬት በመፈለግ፣ እና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ሰዎች መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

ቢሮው ከጉራጌ ዞን የጸጥታ አካላት፣ ካፓርኩ ጠባቂዎች እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን፣ ለፓርኩ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን የመለየት ስራ እየተሰራ ነዉ ያሉ ሲሆን ፣ የጥናቱን ውጤት መነሻ በማድረግ፣ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች እና መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ዙሪያ፣ ውይይት በማድረግ፣ የሚታዩ ችግሮችን ሊቀርፉ በሚችሉ መንገዶች፣ የተቋምን አደረጃጀት ጭምር በማሻሻል ወደ ስራ መግባታቸውን አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

በፓርኩ ዙሪያ የሚደረጉ የመሬት ወረራዎችን ለመከላከል እና በፓርኩ ክልል የሰፈሩ ሰዎችን ለማንሳት በሚሰሩ ስራዎች፣ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚሹ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮች መኖራቸው ስራቸውን እንዳስተጓጎለባቸውም የቢሮ ኃላፊው አንስተዋል፡፡

የጊቤ ብሄራዊ ፓርክ በአዲሱ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ የቱሪዘም መዳራሸ ቦታዎች በቃዳሚነት ከሚጠቀሱት አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52 *👉011-639-37-63
*የቀጥታ ስርጭት
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲  Youtube

2 weeks, 6 days ago
**የታይሰን ፊውሪ እና የአሌክሳንደር ኡዚክ ሁለተኛ …

የታይሰን ፊውሪ እና የአሌክሳንደር ኡዚክ ሁለተኛ ፍልሚያ ዛሬ ይከናወናል

ታኅሳስ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የጊዜው እና ዘመኑን የሚወክለው ምርጡ ፍልሚያ በድጋሜ በዛሬው እለት በሳውዲ አረቢያ በሪያድ ከተማ ላይ የሚከናወን ይሆናል።

በቦክስ ታሪክ ትልቅ አንድምታን ያገኘ እና ለሁለተኛ ጊዜ ሁለት ትልቅ ተቀባይነት ያላቸውን የከባድ ሚዛን ቡጢኞችን የሚያገናኘው የአሌክሳንደር ኡዚክ እና የታይሰን ፊውሪ ሁለተኛ ፍልሚያ  የፈረንጆቹ አዲስ አመት አስታኮ ለቦክስ አፍቃሪያን ትልቅ ስጦታ ሆኖ ብቅ ብሏል።

ይህ ፍልሚያ አሁንም ምስጋና ለተከበሩ ተርኪ አላልሺክ የሳውዲ አረቢያ የመዝናኛ ዘርፍ ሀላፊ ይግባና ለሁለተኛ ጊዜ በሪያድ ከተማ እውን እንዲሆን የአምበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል።

ይህ ፍልሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ነው የሚከናወነው ሽንፈት የሚባል ነገር ቀምሶ የማያውቀው ዩክሬናዊው ቡጢኛ አሌክሳንደር ኡዚክ እንግሊዛዊው ታይሰን ፊውሪን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ በመርታት የWBA ቀበቶ ክብርን ነጥቆ የግሉ ማድረጉ አንዘነጋም።

ከዛ በተጨማሪ Undisputed heavyweight champion የሚለውን ወይም አይበገሬው የከባድ ሚዛን ተፋላሚ የሚለውን ክብር ከ1999 ህዳር ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳካህ መቻሉ የሚታወስ ነው። ያኔ እንግሊዛዊው ሌነክስ ልዊስ ይህንን ስኬት ተጎናፆፎ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ታዲያ ዛሬ ኡዚክ እና ታይሰን ለሁለተኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን የWba,wbo,wbc እንዲሁም IBO የቀበቶ ክብሮች ታይሰን የግሉ ለማድረጥ ኡዚክ ደግሞ ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ፍልሚያ አለም በጉጉት ይጠብቀዋል።

በዚ ፍልሚያ ላይ ልክ እንደ ቼዝ ጨዋታ ሁለቱም የፍልሚያው ቀለበት ውስጥ የተጋጣሚያቸውን ክፍተት ለመጠቀም ጥረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። Gypsey king እየተባለ የሚጠራው ታይሰን ፊውሪ ቁመቱን በመጠቀም ከአሌክሳንደር ኡዚክ የሚኖሩ ጫናዎችን የሚቋቋምበት እና ርቀቱን እየጠበቀ ፍልሚያውን እንዲያከናውንም ጭምርጰያግዘዋል ተብሎ ይገመታል። ሁለቱም የከባድ ሚዛን ቡጢኞች ለዚህ ተጠባቂ ፍልሚያ ተዘጋጅተዋል።

ታይሰን ክብሬን አስመልሳለሁ ሲል ኡዚክ ደግሞ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው የሚሆነው እንደመጀመሪያው ፍልሚያ አሸናፊ ተብዬ በዳኛው እጄ ከፍ የሚደረገው እኔ ነኝ ሲል ሀሳብ ሰጥቷል።

ከተለያዩ አለም የተወጣጡ ታዋቂ እንዲሀም ተፆእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፍልሚያውን ለመከታተል ወደ ሪያድ ያቀናሉ ተብሎ ይገመታል።

ዩክሬናዊው አሌክሳንደር ኡዚክ በፕሮፌሽናል የቦክስ ታሪኩ ሽንፈት አስተናግዶ አያውቅም። ዛሬስ የሚለውን ጥያቄ ሳውዲ አረቢያ ዋና ከተማ እና የተለያዩ የስፖርት ክንውኖች መናኸሪያ የሆነቸው ሲያድ ከተማ ምላሽ የምትሰጥበት ይሆናል።
__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52 *👉011-639-37-63
*የቀጥታ ስርጭት
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲  Youtube

2 weeks, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
2 weeks, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
2 weeks, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
2 weeks, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
2 weeks, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
2 weeks, 6 days ago
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio …
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад