ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
የስኮትላንድ ክሊኒክ የክሪፕቶ ምንዛሬ ሱስን ለማከም ለሶስት አመታት ሲሰራ ቆይቷል።
የጅማ ዩኒቨርስቲን ስም በመጠቀም የማታለል እና የማጭበርበር ተግባር ስትፈፅም የነበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በኢትዮጵያ አንጋፋ ከሆኑት ዩንቨርስቲ መካከል ግንባር ቀደም በሆነው የጅማ ዩንቨርስቲ ስም በመጠቀም የማታለል እና የማጭበርበር ተግባር ስትፈፅን የነበረችው ግለሰብ በእስራት መቀጣትዋን የጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ገልጿል።የጅማ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አቃቤ ህግ የተለያዩ ወንጀሎች እና የፍታብሄር ጉዳዮች ምርመራ ቡድን መሪ አቃቤ ህግ አሚር መሀመድ ዚን እንደገለፁት ተከሳሽ ራሄል አለሙ የተባለችው ግለሰብ ነዋሪነቷ በጅማ ከተማ ቆጬ ቀበሌ ሲሆን ተከሳሿ ሆነ ብላ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በጅማ ዩንቨርስቲ ስም የተለያዩ የማታለል እና የማጭበርበር ተግባራትን በሶስት ግለሰቦች ላይ የማጭበርበር ተግባር የፈፀመች መሆኑን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።
ተከሳሿ በመጀመሪያ የማታለል እና የማጭበርበር ተግባሯን ሀምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም መንግስታዊ ያልሆነ የኮንስትራክሽን ስራዎች ድርጅት ባለቤት ከሆኑት አቶ አሸናፊ ግርማ ጋር በመገናኘት የጅማ ዩንቨርስቲ በወረዳዎች ለሚያሰራው የማስፋፊያ ስራ ጨረታ እንድታሸንፍ አደርጋለሁ በማለት ከግለሰቡ ላይ 120 ሺህ ብር መቀበሏ ተረጋግጧል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ እኔ የጅማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ነው የምሰራው በማለት ራሷን በማስተዋወቅ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም የግል ተበዳይ የሆኑትን ወይዘሮ እታገኘው ጌታቸውን ልጃቸውን ከመቅደላ ዩንቨርስቲ ወደ ጅማ ዩንቨርስቲ አዘዋውራለሁ በማለት ከወይዘሮዋ ላይ 5 ሺህ ብር መቀበሏ በማስረጃ የቀረበ መሆኑን ገልፀዋል።ተከሳሽዋ ከዚህም ሌላ የግል ተበዳይ የሆነችውን ባንቹ አሰፋ የተባለችውን ግለሰብ ቀርባ በማነጋገር ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጅማ ዩኒቨርስቲ ከሸማቾች ማህበር ስኳር እንደምታመጣ በመነጋገር ከግለሰቧ 20 ሺህ ብር የተቀበለች መሆኗን ገልፀው ተናግረዋል።
ተከሳሽዋ በዩንቨርስቲው ስም የፈፀመችው የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊት ከፈፀመች በኋላ ተሰውራለች። የማታለል እና የማጭበርበር ድርጊት የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ለጅማ ወረዳ አቃቤህግ ቀርበው በማመልከታቸው ጉዳዩ በፖሊስ ክትትል ተደርጎበት ተከሳሽዋ በቁጥጥር ስር ልትውል ችላለች። ተከሳሽዋ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ፖሊስ እና አቃቤ ህግ በጥምረት ምርመራ መዝገብ በማስረጃ በማጣራት ካጠናቀቁ በኋላ አቃቤህግ በወንጀል ህግ አንቀፅ 60 እና 692 ንዑስ አንቀፅ 1 ተከሳሽዋ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ስም በመጠቀም ከፍተኛ የማጭበርበር እና የማታለል ተግባር መፈፀሟን በመጥቀስ ክስ የመሠረተባት መሆኑን ገልፀዋል።
ተከሳሽ የአቃቤ ህግን ማስረጃ የሚያስቀይር የመከላከያ ማስረጃ እንድታቀርብ በሠጠው ትእዛዝ መሠሰት ተከሳሿ የአቃቤ ህግን ማስረጃዎችን ውድቅ ማድረግ ባለመቻሏ አቃቤ ህግ የቀረበባትን ክስ ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ መሆኗ ተረጋግጧል። የክስ ሂደቱን ሲከታተል የነበረው የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ራሄል አለሙ ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ በመሆኗ በ 3 አመት ከ 3 ወር እስሬት እንድትቀጣ የተወሰነባት መሆኑን የጅማ ከተማ ወረዳ አቃቤ ህግ የተለያዩ ወንጀሎች እና የፍትሀብሄር ጉዳዮች የምርመራ ቡድን መሪ አቃቤ ህግ አሚር መሀመድ ዚን ጨምረው ተናግረዋል።
Advert
በዚህ ሀሩር ዝናብ ከየት መጣ
በረከቱ ትደርብንና ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አባታችን አባ ሙሴ ጸሊም በሀገረ ግብጽ ወደ ቅድስና የተጓዘ፣ በአረማውያን እጅ በሰማዕትነት ያረፈ፣ በግብጽና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት የቅድስና ማዕረግ የተሰጠው ታላቅ ገዳማዊ አባት ነው፡፡
በግብጽ በረሀ በበዓቱ ውስጥ ሆኖ ሰሌን በሚሰራበት ወቅት ከእርሱ በረከት ሊያገኙ የወደዱ መነኮሳት ሊጠይቁት መጡ፡፡ እንግዶቹንም ለማስተናገድ ምግብ ሊያበስልላቸው ቢመለከት ምንም አይነት ውሃ የለውም፡፡ ውሃ የሚመጣበት ስፍራ ደግሞ እጅግ ሩቅ ነው፡፡ አባ ሙሴ ጸሊምም በእግዚአብሔር ፊት ለጸሎት ቆመና “ጌታዬ ሆይ ወንድሞች ሊጠይቁኝ መጥተዋልና ምግብ እንዳበስልላቸው ውሃ ስለምትሰጠኝ አመሰግንሃለሁ” ሲል አስቀድሞ በማመን ልብ ሆኖ ጸለየ፡፡
ማመን ይህ ነው፣ አንድን ነገር እግዚአብሔር ያደርግልኛል ብሎ በምስጋና በፊቱ መቆም፡፡ ገዳማውያን አባቶች የሚያደርጉት ይህንን ነው፡፡ የምንኩስናችንን ዋጋ ይሰጠናል ብለው፣ የዓለምን ምቾት ንቀው ስጋቸውን እያጎሳቆሉ ሌሊትና ቀን በጸሎትና በምስጋና ይኖራሉ፡፡
ቅዱስ አባ ሙሴም ጸሊምም አምኖ የጠራው ቅዱስ እግዚአብሔር በደረቁ ግብጽ በረሀ፣ በዚያ ሀሩር ምድር በበአቱ ዙሪያ ብቻ በዘነበ ዝናብ እንግዶቹን ለመሸኘት የሚያስፈልገውን ውሃ አገኘ፡፡ ወደ ቤት ሲገባም ልብሱ በስብሶ ያዩት እንግዶቹ በመገረም “በዚህ ሀሩር ዝናብ ከየት መጣ?” ብለው ጠየቁት፡፡
እርሱም በመታበይ በኔ ጸሎት ወረደ ከማለት ይልቅ የርሱን ጸሎት የእነርሱም አድርጎ “እግዚአብሔር ጸሎታንን ሰምቶ ውሃ ሰጠን” አላቸው፡፡ ከአባታችን ከአባ ሙሴ ጸሊምና ከገዳማውያን አባቶቻችን ጸሎትና በረከት ያካፍለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444
በኢትዮጵያ 47 በመቶ የሚሆነው የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው ከዛፎች ጋር በሚፈጠር ንክኪ ነው፣ በመሆኑም ዛፎችን የማፅዳት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” - አገልግሎቱ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገሪቱ “47 በመቶ የሚሆነው የሃይል መቆራረጥ ችግር የሚከሰተው ከዛፎች ጋር በሚፈጠር ንክኪ መሆኑ አረጋግጫለሁ፣ ለሃይል መቆራረጥ መንስዔ የሆኑ ዛፎችን የማፅዳት ስራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ” ሲል አስታወቀ።
“ዛፎች ሲተከሉ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በሶስት ሜትር መራቅ እንዳለባቸው” መመሪያ ቢኖርም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ሲል የገለጸው ተቋሙ “በአብዛኛው አካባቢዎች በመኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲሁም ከግቢ ውጭ ለኃይል መቆራረጥና ለአደጋ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን ከመሰረተ ልማቱ በእጅጉ ተቀራርበው ይገኛሉ ሲል አመላክቷል።
ተቋሙ ይህን ችግር ለመቅረፍ ብሎም በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ ለሃይል መቋረጥ መንስዔ የሆኑ ዛፎችን የማፅዳትና የቅድመ-መከላከል ስራ እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
በምዕራብ አዲስ አበባ፣ በወልዲያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በሆሳና ሪጅኖች ስር በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከ193 ኪሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር የዛፍ ማፅዳት ስራ አከናውኛለሁ ሲል በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።
ህወሓት ችግሩን ካልፈታ ፌደራል መንግሥት ክልሉን እንደሚረከብ መግለጹን አቶ ጌታቸው ተናገሩ
የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን በመፍታት ያዋጣል የሚሉትን መንገድ የማያቀርቡ ከኾነ፣ ብልጽግና የክልሉን አስተዳደር ራሱ ሊይዘው እንደሚችል ማሳሰቢያ መስጠቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።
እሁድ ለክልሉ ብዙኅን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት ተኩል ከ28 ኩንታል በላይ ወርቅ ወደ ፌዳራል መንግሥት ገቢ የገለጹት አቶ ጌታቸው "የክልሉ መንግሥት ከዚህ ውስጥ ያገኘው ገቢ የለም" ብለዋል።
VoA
FACTS OF LlFE 📚
በአዲስ አበባ ከአንድ ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት እንደሚፈጸም የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ባደረገው ጥናት መሰረት መገንዘብ ችያለሁ አለ
በአሁን ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሕጻናት በሚያምኑትና የቅርብ በሚሉት ሰዎች በተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው እንዳለ ጾታን ሳይለይ በልጆች ላይ አካላዊ ጥቃት ፣ስነልቦናዊ ጥቃት ፣ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ገልጸዋል ።
ወላጆችም የልጆቻቸውን ባህሪ በማጥናት ከልጆቻቸውጋር በግልጽ በመነጋገር ከማንኛውም ጥቃት መታደግ እንደሚቻል ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ እመቤት ተስፋዬ "ይህ ቀን ተከብሮ ሲውል አራት ዋና ዋና ያሉት ሲሆን ለህጻናትን መብቶቻቸውን ማሳወቅ ፣ አለማቀፋዊ ተግዳሮቶችን መሞገት ፣ የመንግስት እርምጃዎች የምናበረታታበትና ህጻናትን የማብቃት ስራዎችን በመስራት ነው " ብለዋል።
ህዳር 11/2017 ዓ.ም " ህጻናት የሚሉት አላቸው እናዳምጣቸው " በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ 19ነኛ ጊዜ ተከብሮ እንደሚውል አስታውቀዋል።
በአሁኑ ሰአት ከአስርሺ ስምንት መቶ በላይ የሚሆኑ ህጻናትን ቢሮው የድጋፍና የክትትል ስራ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
**አየር ላይ ህይወቱ አለፈ!!
ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በሚጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈ**
ባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 2024 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ በበረራ ቁጥር ET 500 ፣ በAirbus A350 አውሮፕላን ተሳፋሮ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ መንገደኛ አየር ላይ እንዳለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈ።
እድሜው ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚገመተው ይህ ተሳፋሪ ከእህቱ አጠገብ አብሮ ቁጭ ብሎ በመብረር ላይ እያለ ፣ አውሮፕላኑ ነዳጅ ሞልቶ እና የበረራ ሰራተኞችን ቀፍሮ ከሮም፣ ጣልያን ተነስቶ ወደ አሜሪካ ጉዞ ከጀመረ ከአንድ ሰዓት በኋላ እህቱ ለበረራ አስተናጋጆች ወንድሟ የመተንፈስ ችግር እንዳጋጠመው ትነግራቸዋለች፣ የበረራ አስተናጋጆቹም የህክምና ባለሞያዎች ካላችሁ ለእርዳታ እንፈልጋችኋለን ብለዉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ በበረራው ዉስጥ የነበሩ ወደ 5 የሚጠጉ የህክምና ባለሞያዎች ወደ ግለሰቡ መጥተው ህይወቱን ለማትረፍ ተረባርበው የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ቢሰጡትም ግለሰቡ አየር ላይ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን በበረራ ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ለመዝናኛ ሚዲያ አስታውቀዋል ።
ምንጭ፡ መዝናኛ መጽሔት ዋሽንግተን ዲሲ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago