ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

Description
የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች

Yasin Nuru

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}

ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month, 2 weeks ago

አስተማሪና መሳጭ ታሪክ!

በስዑዲ የሚኖር አንድ የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ሄድን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5000 ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳን-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡

ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
“ከየት ነው ወንድም?”
“ከየመን”
“የት ነው የምትሄደው?”
“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”
“ህጋዊ ነህ?”
“አይደለሁም”
“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
“ለዋስትና 2000 ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
“ስድስት ቀን!”
“እየፆምክ አይደለም?”
“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው
“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡
“ለስራ ነው አመጣጥህ?”
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”

“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡
“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡

ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
“አዎ!” አለ፡፡
“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡ “ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡

ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡ ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡

“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡

ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡

በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡

“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru         

1 month, 2 weeks ago

አንድ ቀን እንዲህ ሆነ…
ረሱል ሰ,አ,ወ ቢላልን ጠርተው ያ ቢላል አሰላቱ ጃሚአ ብለህ ህዝቤን ሰብስብልኝ አሉት ያኔ ቢላል ረ,ዐ ወዲያውኑ አሰላቱ ጃሚአ ብሎ ህዝቡን ሰበሰበ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ወደ ሚንበር ላይ ወጡና እሚገርም ቁጥባ ማድረግ ጀመሩ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ይጠይቃሉ ሰሀባወች ይመልሳሉ ።
.
ረሱል ሰ,ዐ,ወ የእኔ ነብይነት ለእናንተ እንዴት ነበር ???
በደንብ አስተምሬአችሆለሁን ?
ሀቃችሁን ሁሉ ተወጥቻለሁ ወይን? ብለው ጠየቁ።
.
ሰሀባወችም አንቱማ በጣም ረሂም አባት ነበሩ እንዲሁም መካሪ ወንድም እናት ነውት እኮ ለእኛ አሎቸው በሉ እንግዲያውስ በአላህ ይዧችሆለሁ ምናለልባት የበደልኩት ሰው ካለ ነገ አኼራ ላይ እንዳይጠይቀኝ ዛሬ ላይ ይኸው የበደልኩት ካለ ንብረቱን የወሰድኩበት ሰውም ካለ የመታሁት ዛሬ ነውና እድሉ ይምጣ እና ይበቀለኝ ብለው አሉ።
.
ሁሉም ፀጥ አሉ ማንም አልተነሳም አሁንም ለ2ኛ ጊዜ ደገሙና በአላህ ይሁንበት የበደልኩት ይምጣና ይበቀለኝ ይሄው አለሁ ሁሉም ፀጥ አሉ።
.
ለ3ኛ ጊዜ ደገሙና ያመእሸረል ሙስሊሚን አስኪ ማነው እኔን መበቀል እሚፈልግ ትላንት በእኔ የተከፋ አለን? በአላህ ይሁንባችሁ ይኸው እኔ እዚህ አለሁ የበደልኩት ሰው ይምጣና ይበቀለኝ ሲሉ ይህኔ በእድሜ የገፋው ኡካሻ የሚባሉ ሰሀባ ተነሱና ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ ወላሂ ያረሱለላህ በአላህ ይሁንባችሁ አያልክ ደጋግመው ባይጋብዙ
ኖሮ ወላሂ እኔ ለእዚህ ጉዳይ እምቆም አልነበርኩም ።
በእርግጥ አንድ ቀን ከእርስዎ በደል ደርሶብኛል ፊዳክ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ☞ ከእለታት አንድ ቀን አንቱ ጋር ጦርነት ላይ አላህ ማሸነፍን አድሎን ሰጥቶን ወደየቤታችን ልንመለስ እያልን ሳለን ያንቱ ግመል ከእኔ ግመል አጠገብ ለአጠገብ ሆነው ነበር።
እናም እኔ የእግረዎትን ጡንቻ ለመሳብ ከግመሌ ወረድኩ ወደ እግረዎ ዝቅ ስል በእጅዎ የያዙትን አለንጋ ዝቅ ሲያደርጉ ወገቤን እስከ ሆዴ
ጭምር መቱኝ ሆን ብለው ነው የመቱኝ ወይስ አለንጋውን ከፍ ለማድረግ አላቸው?
☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ አሉ ኧረ አውቄ እማ ከመምታት አላህ ይጠብቀኝ አላወኩም አሉት ።
.
እና አሁን ምን ትፈልጋለክ ሲሉት እኔማ እምፈልገው የመቱብኝ ቦታ መምታት ነው አላቸው ለረሱል (ሰዐወ)
☞ረሱል ሰ,ዐ,ወ ቢላልን ጠሩትና ያ ቢላል በል ከፋጡማ ረ,ዐ ቤት ሂድና አለንጋዋን አምጣ ብለው አሉት።
.
ቢላልም ሄዶ ያ ፋጡማ ቢንት ረሱል ሰ,ዐ,ወ
ረሱል ሰ,ዐ,ወ አንቺ ጋር ያስቀመጡትን አለንጋ ላኪ ብለውሸል አላት።
ያ ቢላል ዛሬ የሀጅ ቀን ወይም የዘመቻ ቀን አይደለም ምን ሊያደርጉት ነው አለችው።
ቢላልም ቀጠለና ያ ፋጢማ አልሰማሽም እንዴ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የደረሰባቸውን የተባሉትን አልሰማሽምን?
.
ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ከዚህ አለም አየሞቱ ወደ እዛኛው አለም እየተሸጋገሩ እኮ ነው ። ያ ፋጡማ አልሰማሽም እንዴ መሄዴ ነው እና በቀል ካላችሁ ተበቀሉኝ አሉ እኮ ታዳ ማነው ነብዩን እሚመታ እሳቸውን እሚገርፍ?
ያ ቢላል ማነው ሀሰን እና ሁሴንን ውሰድ እና በረሱል ቦታ ይገረፉው እነሱ እያሉ ረሱል ሰ,ዐ,ወ አይገረፉውም አለች አለንጋውን ለረሱል ሰ,ዐ,ወ ወስዶ ሰጣቸው።
.
እሳቸውም ተቀበሉና ያ ኦካሻ በል ወገቤም ሆዴም የሄው ምታኝ አሉት ኦካሻም ሊመታቸው ተነሳ ያኔ አቡበከር ረ,ዐ ቆሙ ኡመርም ረ,ዐ ተነሱ ያ ኦካሻ እኛ እያለን ረሱልን እንዳትነካብን አሉ ።
.
ይሄው እኛ ቆመናል እኛን ግረፍ አሉት ።
እሳቸውን እንዳትመታብን ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑት ጀመር።
ረሱል ሰ,ዐ,ወ እንቢ ያ አቡበከር እንቢ ያ ኡመር አላህ ሱ,ወ ለእኔ ያላችሁን ቦታ አውቋል አይቷል ወዶታል እና ተቀመጡ አሉ ።
ምታኝ ያ ኦካሻ ሲሉት አልይ ኢብን አቡጣሊብ ረ,ዐ ተነሳና ያው እኔን እንደፈለክ ወገቤም ሆዴም አደራ ብየሀለሁ ረሱልን እንዳትነካብኝ እኔን እንደፈለክ አርገኝ አለ።
ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ አልይ አላህ ያንተንም ለእኔ ያለህን ቦታ ወዶታል ቁጭ በል አሉት ።
.
የዛኔ የፋጡማና አሊ ረ,ዐ ልጆች ሀሰንና ሁሴን ተነሱ እና ያ ኦካሻ የረሱል ሰ,ዐ,ወ የልጅ ልጆች መሆናችንን አታውቅምን ነብዩን እንዳትነካ እኔን እኔን ግረፍ አማና ያ ኦካሻ እያሉ የማፀኑ ጀመር ።
ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ቁረተል እዩኒና አይደለም ተቀመጡ አሎቸው።
.
☞ያ ኦካሻ እምትመታኝ ከሆነ ምታኝ አሉት።
ያረሱለላህ እርስወ እኮ የመቱኝ ሆዴ ክፍት ሆኖ ነው እንዴት አድርጌ ከእነ ልብስዎ ልምታወት ይህኔ የኸው ሆዴ በለው ገለጡለትና ምታኝ አሉት ።
.
ይህኔ ሰሀባዎች በእንባ ተራጩ ። ያ ኦካሻ አይከብድህም አታፍርም ነብዩን ልትመታ ነው? እያሉ ይጮሀሉ ።
.
የነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሆድ በሚያይ ሰአት በሚገርም ሁኔታ ፊዳከ ቢአቢ
ወኡሚ ፊዳከ ቢአቢ ወኡሚ እያለ ይስማቸው እየላሳች ይጮሀል ።
ይህኔ ረሱል ሰ,ዐ,ወ ያ ኦካሻ ወይ ምታ ወይ አፉው በል አሉት።
አላህ የውመል ቂያማ አፉዉ እንዲለኝ አፉው ብየዎታለሁ እኔ እኮ ልመታወት ፈልጌ አይደለም ቆዳየ ከቆዳወ ጋር አንዲላተም እንዲገናኝ ብየ ነው።
.
ረሱል ሰ,ዐ,ወ ተናገሩ ጀነት ውስጥ የእኔ ጎደኛ የሆነን ሰው ማየት እሚፈልግ ካለ ወደ እዚህ ሽማግሌ ይይ አሉ። እንዳለ ሰሀባዎች የኡካሻን ግንባር እየሳሙ የረፊቅል አእላ ባለቤት እያሉ ያለቅሳሉ ኦካሻም ያለቅሳል
ሰሀባዎች ይህን ያህል ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ያፈቅሮቸው ነበር ።
እኛስ?

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru       

1 month, 3 weeks ago

🌟ህፃኑ ከእናቱ እና ከአንዲት እንስት ጋ ሁኖ ሳያየው የሞተበትን የአባቱን ቀብር ለመዘየር የዐረቢያ በረኃዎችን እያቆራረጠ ይጓዛል።

ናፍቆትን የቋጠሩ የህፃኑ አይኖች የአባቱን ቀብር ተመልክተው ከህፃን አንጀት የሚንጠፋጠፉ የእዝነት ስሜቶችን ቋጥሮ ወደ መጣበት በረኃውን እያቆረረጠ ሊመለስ ጉዞውን አብረው ጀመሩት።

እልም ባለው በረኃ፣ ደራሽ በሌለበት እና የጮኺ ሰሚ ባማይታይበት የአሸዋ ውቅያኖስ ላይ ህፃን እናቱ በጠና ታመመችበት።

እናት የቲም ልጇን ከበረኃ ላይ ሁና በእዝነት ተመለከተችው፣ ወደራሷ ጠጋ አድርጋ አቀፈችውም፣ ከጉንጯ እንባዎች እየፈሰሱ የተሰናባች አሳሳምም ልጇን ስማ እስከ ወድያኛው አሸለበች።

ከጎኑ አንዲት እንስት ብቻዋን ቀረች፤ የ 6 አመት ህፃኑ አባት እና እናቱ ለበረኃ ሲያይ ሁነው በማይራራው በረኃ ባይተዋር ሆነ።

አብራው የቀረችው እንስት ህፃኑን ጠርታው ከሚያቃጥለው የበረኃ አሸዋ በትናንሽ እጆቹ ለእናቱ ማረፍያ የሚሆን ቀብር ቆፍሮ እንዲያግዛት አዘዘችው።

እንስት ከልብሷ ቀንሳ ሟቿን ገነዘች። በህፃን ጣቶች ተቆፍሮ በተዘጋጀላት የማረፍያ ስፍራ እናት አፀደ ገላዋ አረፈ። አፈር ተመልሶ እናት ከቀብር በታች ቀረች።

ህፃን የቀበራትን እናት ትቶ ጎዞ ሲጀምር ከትናንሽ አይኖቹ የሚፈሱትን እንባዎች በአዋራማ እጆቹ እየጠራረገ ከእንስቲቱ ጎዞን ቀጠለ።

ያላየውን አባቱን ቀብር ልይ ብሎ ወጥቶ ያያትን እናቱን በበረኃ ቀብሮ ሲመለስ ህፃን ልቡ ተሸበረ። ባይተዋርነት ወረረው።

ሰዎች ሆይ! እስቲ ፍረዱ፤ ከዚህ በላይ ሀዘን አለ?
እስቲ ተናገሩ የዚህ ብላቴና ልብ ይህን ሁሉ ህመም ይቋቋማል?

ይህ አሳዛኝ ብላቴና ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?
«ነብያችሁ ሙሀመድ ዐሰወ ነው።»
ያ በልጅነቱ የባይተዋርነትን ህመም ሲቀለብ አድጎ፤ በጉልምስና ዕድሜው በኛ የመዳን ጉዳይ የጭንቀትን ምሬት በልቅሶ ሲጋት የኖረው ሙሀመድ ሰዐወ ነው!!!

"ረመዳን ገጥሞት ሳይጠቀምበት ምህረት ሳያገኝ የሄደበት ሰው በአፍጢሙ ጀሀነም ይደፋ!"፡ ጂብሪል(ዐሰ)፤ አሚን በል ሲላቸው
ነብዩ(ሰዐወ) "አሚን"ብለዋል! ጠንቀቅ እንበል አደራ!!

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru       

1 month, 3 weeks ago

ኢናሊላሂ ወኢና አሊይሂ ራጂዑን😳😳

ፔንጤዎች እንደ ሙስሊም ሆነው ምን እንደሚያረጉ ተመልከቱ😭😭

"በመሲህ ኢሳ የጀነትን መንገድ አገኘን እያሉ ነው ያልቀሩ ሙስሊሞችን ለማሳሳት"

@yasin_nuru @yasin_nuru

1 month, 3 weeks ago

በአላህ ፈቃድ ኋላ ስናፈጥር (ኢፍጣር ላይ) የሚባል ዱዓእ፦

( ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إن شاء الله)
[صحيح الجامع :٤٦٧٨]

«ዘሃበ ዞመዑ ፣ ወብተለቲ-ል -ዑሩቁ፣ ወሠበተል አጅሩ ኢንሻ አላህ!»
[ሶሒሑ-ል-ጃሚዕ ፤ 4678 ]

የዱዓው ትርጉም፦

«ውሃ ጥምም ተወገደ፣ የደም ስሮችም ረጠቡ/ለዘቡ፣ በአላህ ፈቃድ አጅሩ/ምንዳውም ጸደቀ።»

አላህ ፆማቸውን ከሚቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን።

@yasin_nuru

1 month, 3 weeks ago

ረመዷን 1
*🌙 خمسُ خِصالٍ عظيمة 🌙***

ከዚህ በፊት ለማንም ያልተሰጠ ለነብዩ ኡመት ብቻ በረመዷን ወር የተሰጠን ልዩ የሆኑ 5 ነገራቶች

1ኛ የፆመኛ ሰው የአፍ ሽታ አላህ ዘንድ
የፆመኛ ሰው የአፍ ሽታ አላህ ዘንድ ከሽቶ የበለጠ ነው

2ኛ እሰከሚያፈጥሩ ድረስ መላዕክቶች ከአላህ ምህረትን ይለምኑላቸዋል

3ኛ አመፀኛ የሆኑ ሸይጣናት ይታሰራሉ

4ኛ አላህ የደጋግ ባሮቹ የወደፊት ማረፊያ የሆነችውን ጀነትን በእያንዳንዱ ቀን ያስውባታል

5ኛ በሌሊቱ መጠረሻ ላይ ወንጀላቸው ይማርላቸዋል

ስለሆነም እነዚህን ትሩፋቶች ለማግኘት በመልካም ስራዎች መሽቀዳደም አለብን

🌘ቁርዓን በማስተንተን በማንበብ

🌘ሰላቶችን በሌሊት በቀን በማብዛት

🌘ኢስቲግፋርን በማብዛት

🌘ተህሊል ተክቢር ተህሚድ ተስቢህ

🌘ሰደቃን ለድሆች በመስጠት

🌘ዝምድናን መቀጠል

🌘ለወላጆች በጎ በመዋል

🌘ህመምተኛን በመጠየቅ

🌘ዱዓን በሌሊት በቀን በማብዛት በተለይ ዱዓ ይበልጥ ተቀባይ በሚሆንበት ወቅቶች እና ሁኔታዎች የሌሊቱን መጨረሻ ወቅት ላይ ይመስል በሰላት መጨረሻ ላይ በሱጁድ ላይ በአዛን እና ኢቃማህ መካከል በጁሙዓ ቀን ላይ በሆነች ሰዓት በነዚህ መሰል ወቅት እና ሁኔታዎች ላይ ዱዓን እስቲግፋርን ማብዛት አለብን

🔈 የተከበሩ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ቢን ባዝ አላህ ይዘንላቸውና

"ረመዳን ገጥሞት ሳይጠቀምበት ምህረት ሳያገኝ የሄደበት ሰው በአፍጢሙ ጀሀነም ይደፋ!"፡ ጂብሪል(ዐሰ)፤ አሚን በል ሲላቸው
ነብዩ(ሰዐወ) "አሚን"ብለዋል! ጠንቀቅ እንበል አደራ!!

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru   

1 month, 3 weeks ago

በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️

1) አንድ ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16 መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20 ገጽ መቅራት!!
||

ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

"ረመዳን ገጥሞት ሳይጠቀምበት ምህረት ሳያገኝ የሄደበት ሰው በአፍጢሙ ጀሀነም ይደፋ!"፡ ጂብሪል(ዐሰ)፤ አሚን በል ሲላቸው
ነብዩ(ሰዐወ) "አሚን"ብለዋል! ጠንቀቅ እንበል አደራ!!

@yasin_nuru  <>  @yasin_nuru   

1 month, 3 weeks ago
በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ላላችሁ የረመዿን ስኬጁል!

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ላላችሁ የረመዿን ስኬጁል!

የሶላት ወቅቶች፣ የኢፍጣርና የሰሑር ወቅቶች!

@yasin_nuru

1 month, 3 weeks ago
ጨረቃ ስለታየች ነገ ሰኞ ጾም ነው።

ጨረቃ ስለታየች ነገ ሰኞ ጾም ነው።

BREAKING NEWS: The Crescent of Ramadan 1445/2024 has been sighted in Saudi Arabia!

Subsequently, Ramadan 1445/2024 begins tomorrow, 11 March 2024

Taraweeh Prayers will begin in the Two Holy Mosques after Isha Prayers

@yasin_nuru

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas