ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ያላያችሁ ስማችሁን እና ID ላኩላቸው ያይሏቹሀል ኢንሻአላህ
@onlyone08
@originalkalid1
@husnitu
@meaningful0
@Hikrum
@AmirAloneM
@Ayubsultan
ሰላምአለይኩም አህባቢ ውጤት ላላዩ ልጆች አሪፍ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ያላችሁ ሰዎች ተባበሯቸው!
ኮሜንት ላይ አሳውቁኝ ዩዘርኔማችሁን እዚህ እፖስተዋለው። የላ አህባቢ??
አብሽሩ አትጨነቁ አላህ ያለው ብቻ ይሆናል?
◣የእናት ውለታዋ◥
:
"እናቴ አንድ አይና ስለነበረች በጣም እጠላት ነበር።" ይላል ባለ ታሪኩ..... "እጅግም ታሳፍረኝ ነበር ፣ እኔ የምማርበት ትምህርት ቤት ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች ምግብ በማዘጋጀት ነበር ቤተሰባችንን የምታስተዳድረው።
:
የአንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ እናቴ ትምህርት ቤት ሰላም ልትለኝ ስትመጣ እጅግ እሸማቀቅ ነበር። እንዲያውም "እንዴት እንዲህ ልታደርግ ቻለች?" በማለት በመጥፎ አስተያየት ገላመጥኳትና ዘግቻት ከፊቷ ሄድኩ።
በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ አንዱ ጓደኛዪ " አንተ! እናትህ አንድ አይን ነው ያላት?" ሲለኝ ያኔ ምድር ብትውጠኝ በወደድኩ : ራሴን ባጠፋ ደስ ባለኝ ነበር። ስለዚህ ከዚህ ሁሉ ነገር እናቴም አንደኛውን ብትጠፋልኝ ምኞቴ ነበር።
:
ያን ቀን ቤት ከሄድኩ በኋላ "መሳቂያና መሳለቂያ ከምታደርጊኝ ለምን አትሞችም?" ብዬ ጮህኩባት ፣ እናቴ ግን ምንም አልመለሰችልኝም ፣ እኔ በጣም ተበሳጭቼ ስለነበር የምናገረውን አላወኩም፣ በተናገርኳት ነገር ምን ሊሰማት እንደሚችል ደንታም
አልሰጠኝ።
ከዚህ በኋላ ግን ከእሷ ጋ መኖር ስላልፈለኩ ከቤት ወጣሁና ጠንክሬ እየተማርኩ ባለሁበት ጊዜ የውጭ ትምህርት እድል አጋጥሞኝ ከሀገር ወጣሁ ፣ ከዚያም ሚስት አገባሁ ፣ ልጆችን ወለድኩ ፣ ቤት ገዛሁ ፣ ደስ የሚል ህይወት ነበረኝ።
:
ከአመታት በኋላ ተገናኝተን የማናውቀው እናቴ ወዳለሁበት መጣች፣ በሬ ላይ በቆመችበት ወቅት ልጆቼ በሹፈት አይን እየተመለከቱ ሳቁባት፣ እኔም "ማን ነይ ብሎሽ ነው ፣ የመጣሽው? ፣
አንቺን ማየት አልፈልግም ፣ ከዚህ ውጪ በቃ" ብዬ ጮህኩባት....እሷም በለሰለሰ ድምፅ " ወይኔ! በጣም ይቅርታ አድራሻ ተሳስቻለሁ ማለት ነው" ብላ በፍጥነት ወጥታ ሄደች።
ይህ ከሆነ በኋላ የስብሰባ ደብዳቤ ከድሮው ትምህርት ቤት ደረሰኝ ባለቤቴን ተሰናብቼ ሄድኩ ፣ ስብሰባዬን ጨርሼ ስመለስ በዚያውም አሮጊቷን እናቴን ልያት ብዬ ወደ እናቴ ቤት አቀናሁ ፣
እሷ ግን ቤት አልነበረችም ፣ ጎረቤት የነበሩትን ሰዎች ስጠይቃቸው ሞታለች አሉኝ። ይህን ስሰማ ምንም የተሰማኝ ነገር አልነበረም። ግን ልታገኘኝ ፈልጋ እንደነበረና ደብዳቤ እንዳስቀመጠችልኝ ነገሩኝ።
:
ደብዳቤው እንዲህ ይላል ..."
:
" ውድ ልጄ! ምን ጊዜም አስብሃለው ፣ ያኔ ቤትህ መጥቼ ልጆችህን ስላሳፈርኩብህ በጣም ይቅርታ። ለትምህርት ቤት ስብሰባ ልትመጣ ነው ሲባል በሰማሁ ጊዜ ደስ ብሎኝ ነበር ፣ ነገር ግን የአልጋ ቁራኛ ስለነበርኩ ላገኝህ አልቻልኩም።
በህይወትህ ዘመን በጓደኞችህ ፊት ሁሉ ስላሳፈርኩህና ስላሸማቀኩህ ይቅርታ ፣ አየህ ልጄ ...... በህፃንነትህ ጊዜ አደጋ ደርሶብህ ነበር ፣ በዚያ አደጋም ሳቢያ አንድ አይንህን አጣህ ...
ነገር ግን እኔ እናትህ አንተ አንድ አይና ሆነህ እንድታድግ እድሜህን ሙሉ በሙሉ እንድትሆን ብዬ አይኔን ሰጠውህ። በሁለት አይንህ አለምን ስትቃኝ ሳይህ እጅግ ደስ ይለኝና እኮራም ነበር ፣ ውድ ልጄ ...በእኔ ምትክ አንተ ሙሉ ስለሆንክ ደስ ይለኛል።"
:
አፍቃሪ እናትህ !
።።።።።።።።።።።።።
:
ስንቶቻችን በወላጆቻችን እናፍር ይሆን? ስንት አይነት መስዋዕት ከፍለው አሳድገውን ይሆን? ዛሬስ ምላሻችን ምንድነው?
ጊዜው ያልመሸባችሁ በቻላችሁት አቅም ሁሉ ‘አለሁልህ አባቴ ፣ አለሁልሽ እናቴ’ በሏቸው። እኛን ሰው ለማድረግ ከሰውነት ተራ ወጥተው ያሉ ወላጆችን ቤቱ ይቁጠራቸው። እናስተውል!
እንዳይቆጨን!
:
ብዙ ወላጆች እኛን ራሳችንን እንጅ የእኛን ነገር አይፈልጉም ፣ በተቃራኒው ደግሞ እኛ የእንሱን ነገር እንጅ እነሱን አንፈልግም። እነሱን በመፈለግ ፍቅራችንን እናሳያቸው! ይህ ታሪክ ከደረሳችሁ እናንተ ጋር እንዲቀር አትፍቀዱ
እናት ልጇን በምትድርበት ሰዓት የመከረቻት ምክር❤️
አንዲት እናት ሴት ልጇን በምትድርበት ሰዓት ልጇ ከቤቷ ከመውጣቷ በፊት መከረቻት። ለባልሽ እንደ ሴት አገልጋይ ሁኚለት እሱም እንደ ወንድ አገልጋይ ይሆንልሻል። #አስር ምክሮችን ከልብሽ ያዣቸው እኔ በነዚህ ምክሮች ሰርቸባቸው ከአባትሽ ጋር ደስተኛ ሁኛለሁ .....
① ከባልሽ ጋር ስትኖሪ ባለው ነገር ተብቃቂ።
② የሚልሽን በመስማት የሚያዝሽን በጎ ነገር በመስራት ተኗኗሪው።
③ አይኑ ተዝረክርከሽ አይመልከትሽ።
④ አፍንጫው ከአንች መጥፎ ሽታን አያሽትትብሽ።
⑤ የምግቡን ነገር ተከታተይ ሆዱ ባዶ እንዳይሆን እንዲመገብ አድርጊ።
⑥ የእንቅልፉን ጉዳይ ተከታተይ በቂ እረፍት እንዲያገኝ አድርጊ።
⑦ ገንዘቡን ተጠባበቂለት። ገንዘብን በመያዝ ጉዳይ ዋናው ነገር አጠቃቀሙ ነው።
⑧ ልጆቹን፣ ቤተሰቦቹን እና ለሱ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ትኩረት ስጫቸው (ተንከባከቢያቸው)
⑨ አደራ! እሱ በተጨነቀበት ሰዓት እንዳትደሰች።
10/ አደራ! እሱ በተደሰተበት ሰዓት እንዳተጨነቂ። በስተመጨረሻም ዕወቂ አንች የምትፈልጊውን አታገኚም ስሜትሽን ከስሜቱ የምትወጅውን ከሚወደው እስካላስቀደምሽ ድረስ።
አሏህ ያዘነለት ቢሆን እንጂ በዚህ ዘመን እንደዚች አይነት እናት ከየት ይገኛል! አሏህ ያዘነለት ቢሆን እንጂ በዚህ ዘመን በነዚህ ምክሮች የሚሰራ ከየት ይገኛል!
እህቴ ሆይ! እናት ለልጇ የመከረቻትን አንችም በትዳርሽ ተግብሪው ደስተኛ ትሆኛለሽ።
እህቴ ሆይ! በትዳር ይህወት ውስጥ ከነዚህ 6 አይነት ሴቶች እንዳትሆኚ .....
① አል አንናናህ/ ለባሏ ብሶት የምታበዛ።
② አል መንናናህ/ በባሏ ላይ እንዲህ እንዲህ አላደረኩልህም እያለች የምትመፃደቅ።
③ አል ሐንናናህ/ ሌላ ባል ማግባት የምትፈልግ።
④ አል ሐድዳቃህ/ አይኗን ወደ ሁሉ ነገር እየጣለች ባሏን ካልገዛህ እያለች የምታስቸግር።
⑤ አል በርራቃህ/ ፊቷን በመወልወልና በማስዋብ የሚያበራ ለማድረግ ቀኑን በሙሉ የምትውል።
⑥ አሽሸዳቃህ/ ጥቀም የለለው ወሬ የምታበዛ።
አደራ እህቴ! ከነዚህ ከስድስቶች ከመሆን ተጠንቀቂ!
ጥሩ ወንዶች ለጥሩ ሴቶች ናቸው
ጥሩ ገንዘብ ለጥሩ ሰው ነው ይባላል እና አሏህ ከጥሩዎች ያድርገን!?
?እስኪ ላስታውሳችሁ ወንድም እህቶቼ .....
?ለመጀመሪያ ጊዜ የፈሰሰው የሰው ልጅ ደም የእናታችን ሀዋ የሀይድ ደም ነው።
? ለመጀመሪያ ጊዜ በሶፋዋና በመርዋ የሮጠች ሀጀር ኡሙ እስማዒል ናች ።(ዓለይሃ ሰላም)
? ለመጀመሪያ ጊዜ የዘምዘም ውሀ የጠጣው ነብዩ ኢስማዒል አለይሂ ሰላም ናቸው።
? ከነብዩሏህ ኢብራሂም በመቀጠል ከነቤተሰቡ ለኢስላም የተሰደደው ዑስማን ኢብን ዐፋን እና ባለቤቱ ሩቅያ ቢንት ሙሀመድ ﷺ ስደቱም ወደ ሀበሻ ነበር።
? ለመጀመሪያ ጊዜ ሳሙና የሰራው ነብዩ ሱለይማን ዐለይሂ ሰላም ናቸው።
? ለመጀመሪያ ጊዜ በአረብኛ ቋንቋ የተናገሩ ነብዩ ኢስማዒል ዐለይሂ ሰላም ነው።
?ለመጀመሪያ ጊዜ ቁርዓን እንዲሰበሰብ ያደረጉ አቡበከር አስሲዲቅ ረድየላሁ ዓንሁ ናቸው።
?የመጀመሪያዋ በኢስላም ሸሂዳህ (ሰምአት ) የሆነችው ሱመያ ( ኡሙ አማር )ነች
?ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዕታት አለቃ የተባሉት ሀምዛ ቢን ዐብዱልሙጦሊብ እንደሆኑ ፤
@Dinel_islam
?ለመጀመሪያ ጊዜ አህመድ በሚለው ስም የተጠሩ ነብዩ ሙሀመድ ﷺ እንደሆኑ ፤ እንዲሁም ለመጀመርያ መሐመድ የሚል ስም የተሰየሙ ነብያችን ﷺ ናቸው።
?ክፍል 2 ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ
ሼር ማድረግ እንዳትረሱ
❌ለፖርኖግራፊ ሰለባዎች❌
?ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!
♻️እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!
?እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!
☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!
① የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?
② እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?
③ እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያረግህ ታውቃለህ?
④ እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ? ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!
⑤ ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያረግህ ታውቃለህ?
⑥ የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል? (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)
⑦ እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያረግህ ታውቃለህ?
⑧ ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ! የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?
⑨ በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?
⑩ ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?
⑪ እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?
⑫ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?
⑬ እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?
⑭ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?
⑮ በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?
⑯ ጌታህ ቻይ ነው! ለግዜው ይተውሀል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ! ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!
⑰ ለአላህ ብሎ አንዳች ነገር የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?
⑱ አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?
⑳ ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?
⑳ ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ?
②① ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?
②②ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
✅✅✅✅✅
☞ለላጤዎች ምክር!
♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!
♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!
♻️ ማግባት ካልቻልክ ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......
♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብቀ
♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያረግህ ተማፀን!
♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!
♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
☞ለባለ ትዳሮች ምክር
♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ወሲብ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!
♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ከወሲብ ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!
♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!
♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማረግ ባለቤቷን በየግዜው ማስደመም አለባት!
✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህች አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን!
♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል አስተንትን በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታርጋቸው!
♻️ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ሁሉ ይርዳን!
✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
⭕️በፖኖርግራፊክ የተጠመደው ወጣት
ልብ የሚነካ እውነተኛ ታሪክ⭕️
----------------------------------------------
ሸይኹ እርሳቸው ጋር ቀርቦ ስላጫወታቸው ወጣት አስገራሚ ታሪክ በመስጅድ ለተሰበሰበው ሰው እንደሚከተለው አወጉ....
ወጣቱ — የልጅነት ጊዜዬ ብሩህ ፣መልካም እና የቤተሰቤ የኢስላማዊ ተርቢያ ውጤት ነበርኩ ። በመንደራችን የጥሩ ሰዎች ሞዴል ተደርጌ እቆጠር ስለነበር አንድ ደግ ሰው ወጣትነቴን አይቶ ሳሊህ(ሳሊሃ) የሆነች ሴት ልጁን ዳረኝ ።
ነገር ግን የኔ ኢማን ከመብረቅ በፈጠነ ተምዘግዝጎ ሲወርድ ይታወቀኛል ። የስሜቴ ተገዥ የሸይጣን ሰረገላ ሆንኩ ወደፈለገው ቦታ ይነዳኛል። በስራ ያወቅኳቸው ጓደኞቼ በየእለቱ በ cd እያዘጋጁ በሚሰጡኝ ፀያፍ(porngraphic) ፊልሞች ተጠመድኩ ።
ምንም እንኳ ሚስቴ ያማረ ስነ ምግባር ቢኖራትም ቅሉ ተደብቄ በማያቸው ፊልሞች ምክኒያት በትዳሬ ደስተኛ መሆን አልቻልኩም በሆነውም ባልሆነውም መነታረክ ባህሪዬ ሆነ ነገር ግን ለስላሳው የሚስቴ ምላሽ ሁሌም ከህሊናዬ አይጠፋም አይደርስ የለምና ደረሰ። አላህ ውብ የሆነች ልጅን ሰጠኝ ።እናት መድረሳ ናትና ሚስቴ በኢስላማዊ አደብ ኮትኩታ ማሳደጉን ተያያዘችው እኔም በአመፄ ቀጠልኩ ነገር ግን ሚስቴና ልጄ እንዳያውቁብኝ ከፍተኛ ጥንቃቄ አደርጋለሁ።
ከቀናቶች አንድ ቀን ይህን ፀያፍ ፊልም አንደያዝኩ ቤቴ ገባሁ ሁሌም እንደምታደርገው ሚስቴ ልጄን ቁርአን እያስተማረቻት ደረስኩ። ሁለቱንም ስሜ ወደ መኝታ ክፍሌ አመራሁ ። መተኛታቸውን እንዳረጋገጥኩ ይህን ኸቢስ መመልከት ጀመርኩ ለካስ ቀደር ሲመጣ አይን ይታወራል አይደል የሚባለው ተኝታለች ብዬ የገመትኳት የ 7 አመቷ ልጄ ልብስ ሳይለብስ ተኝቶ ይሆናል ብላ በማሰብ በሩን ከፍታ ገባች።
ዋ ጥፋቴ በዛች ቅፅበት ምድር ተከፍታ ቃሩን እንደዋጠች ብትውጠኝ ብዬ ተመኘሁ ። ልጄ ያየችውን ማመን አቃታት በሳሊህነቱ የምታውቀው አቧቷ አልመስልሽ አላት ። ባባዬ ኢተቂላህ ብላ በሩን ከፍታ ወጣች ።በቃ አለቀልኝ ልጄ ያየችውን ሁሉ ለእናቷ መናገሯ አይቀር የት ልጥፋ የት ልሂድ ይሄኔ ፈጅር አዛን አለ "ሃያ አለል ፈላህ" ሻወር ወስጄ ወደ መስጅድ አመራሁ
ኢማሙ ሲቀራ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ኢማሙ
الم يعن للذين امنو أن تخشع قلوبهم لذكر الله
ለነዚያ ለአማኞች ልቦናቸው ለ አላህ ግሳፄ የሚ ፈሩበት ግዜ አልደረሰምን?
የሚለው ቦታ ሲደርስ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ
በስጁዴ ላይ ጌታዬ እባክህ ነውሬን ደብቅልኝ ። አይነጋ የለም እና ነጋ ቤት ሳልደርስ ወደ ስራዬ አመራሁ ነገር ግን ስራዬን መስራት አልቻልኩም በአቅራቢያ ካለ መስጊድ ገባሁ ሰው አለመኖሩ አላህን ብቻዬን እጄን ወደርሱ ዘረጋሁ ያ አላህ ያ አላህ አለቀስኩ ይህን ወንጀሌን ከሸፈነልኝ ሁለተኛ እንደማላምፅ ከውስጤ ቃል ገባሁ ።
ሲመሽ ወደ ቤት መመለስ ነበረብኝ እና ተመለስኩ ሚስቴን በር ላይ ቆማ ሰወችም ወዲህ ወዲያ ይላሉ በቃ ሚስቴ ጉዳዩ ላይ ደርሳበት ፍቺ ልትጠይቅ ሰው ሰብስባ ነው አልኩ
አንገቴን እንደደፋው አጠገቧ ደረስኩ ፊት ምንኛ ያበራል ብላ አቅፋ ሳመችኝ ትንሽ ተረጋጋሁ ቀጥላ ልጃችን ፈጅር ላይ ጀምሯት በነበረ ትኩሳት ረፋዱ ላይ በአቅራቢያችን ካለ ሆስፒታል ህይወቷ ማለፉን አረዳችኝ እግሬ ተንቀጠቀጠ ተዝለፍልፌ ወደኩ ነገር ግን አላህ ነውሬን ለመጠበቅ የሰጠኝን ሀዲያ እንዳስከፈለኝ ገባኝ ።
Copied!
"ቆይ አባት መጣሁ"
"አባቴ!"
"አቤት ልጄ?"
"እየሱስ ያድናል"
"ምነው ልጄ ሰላምታ አይቀድምም?"
"እሺ ይቅርታ! ደህና ዋሉ አባት?"
"አልሀምዱሊላህ የኔ ልጅ:: አንቺስ ታዳ?"
"ደህና ነኝ ጌታ ይመስገን"
"እዚህ አደባባዩ ላይ ቆመሽ እየሱስ ጌታ ነው ስትይ ሰማሁ ልበል?"
"አዎ አባባ እየሱስ ጌታ ነው::ጌታን ይቀበሉ"
"ለመሆኑ ልጄ እንዲህ ሰው በተሰበሰበበት እንድትሰብኪ ማን ፍቃድ ሰጠሽ?"
"አልገባኝም"
"መፅሀፋቹ አደባባይ ላይ እንድታወሩ ይፈቅድልሻል ልጄ?"
"እንዴታ! ወንጌልን ለዓለም ሁሉ እንድንሰብክ ጌታ አዞናል::ወንድ ሴት እያሉ መለያየት የእስልምና ብቻ ነው፣ በዛ ላይ ሴቶች በእስልምና ነው የተበደሉት ::"
"ተይ ልጄ የማታውቂውን አታውሪ: እስቲ 1ኛ ቆሮንጦስ 14:34 ክፈቺና አንብቢ"
"ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ: ህግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና:: ለሴት #በማህበር መካከል #መናገር_ነውር_ነውና ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ" (ፊቷ እየቀላ ነው ) ማንበቧን አቋረጠች
"ምነው ልጄ ዝም አልሽ?"
"በፍፁም ይሄን አንቀፅ ከዚህ በፊት አንብቤው አላውቅም"
"አውቃለው ልጄ፣1ኛ ወደ ጢሞቲዎስ 2:12 ብታነቢ ደሞ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም ይላል"
"በእየሱስ ስም"
"አሁን ውይይታችንን እንቀጥል ወይስ...?"
"ቆይ አባት መጣሁ" (በዛው እብስ አለች!!!)
.
"እነዚያ ተውራትን የተሸከሙ ምሳሌያቸው ማር እንደተሸከመች አህያ እንጂ ሌላን አይደለም"
አል ጁሙዓህ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago