Prip➠Official3

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 2 weeks ago

ብቸኝነት ይሰማኛል። ብቻ ድብርታም ነገር ነኝ እና አባ እየጠራኝ ነው በቃ ሰአታችን ደረሰ አንተም ስልክ አላነሳህም ማስታወሻዬን ላንተ ሳላደረስ መሞት አልፈልግም ወይ የምድንበት መንገድ ከተገኘ በጣም ደስስ ይለኛል። ባይሆንም ፈጣሬን አላማረውም" ዕዝራ ሁለተኛውን ገፅም ጨረሰ። እና ከደነው የሲማይን ስእል ሳመው ደጋግሞ ሳመውና ማታወሻውን  ከትራሱ ሾር አረገው እና ተኛ። እንቅልፍ ወዲያው ነበር የወሰደው ወዲያውም ቅዠት ጀመረው።

፨ ከሲማይ ጋር በፍቅር ክንፍፍ እያለ የምታምር ልጅ ይዘው ልጅትዋን እያፈራረቁ ሲስሞት ነበር የያየው። በጣም ደስስ ብሎታል የእውነት አለም ውስጥ ያለ መስለው። በእዛ ደስታ መሀል ግን ነጭ ልብስ የለበሰች ሲማይን መሳይ ሴት መጣችና ሲማይን እና ህፃንዋን ይዛቸው ሄደች። ዕዝራ "አይሆንም አትውሰጃቸው ስለፈጠረሽ አምላክ ተያቸው ተያቸው እያልኩሽ ነው ተይ ተይ ተይይይይይይተይይይይይይይይይይይይ
ብንን ብሎ ባነነ። ከባነነ በኋላ "አይይይ
ልትወስጃቸው አትችይም የትኛዋ ነሽሽሽ ወሳጅዋ ወይስ ተወሳጅዋ ለምን አተይኝም ተይኝ አይ አይ በጭራሽ ግን አትተይኝ ሲማይ አታገላችኝ እባክሽን" እያለ ሲጮህ አባቱ ለዶክተሩ ደወሎ "ልጄ አበደ  በለሊት ሲጮህ ይህ ሁለተኛ ቀኑ ነው በቃ ልጄ ለየለት" አሉ። ዶክተሩ የዕዝራ አባትን "በሉ ተረጋጉ መጀመሪያ ምን ተፈጥሮ ነው"አሉት። የዕዝራ አባት ስልካቸውን ወደ ዕዝራ መኝታ ቤት ይዘው ሄደው ዕዝራ የሚለውን አስሙት።
       ፨ ዶክተሩም "ዕዝራ ወደ እራሱ ለመመለሾ እየታገለ ነው። አይፍሩ በቃ አሁን ወደ አልገመዎት ሄደው ይተኑ። ዕዝራ የሀይምሮ እክል እንደገጠመው ሁላችንም እናውቃለን አላቸው። "እሺ " ብለው አልጋቸው ላይ ሄደው ጋደም ከማለታቸው። የሆነ መስታወት ፎጭ ብሎ ሲከሰከስ ሰሙ። የዕዝራ አባት ወደ ዕዝራ ለመሄድ ሲሮጡ ደረጃው አንሸራቷቸው ተንከባለው ወደቁ።

ክፍል 12
ይቀጥላል........

1 month, 2 weeks ago

ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ

ሳልሳዊ
ክፍል። 11

፨ የሲማይን ስእል ሲያቅፈው ሲማይን ያቀፉት ነበር የመሰለው። ውሰጡ በሀሴት ተሞላ የሆነ አይነት ደስታ ሳያስበው ወረሰው። ዕዝራ በድንገት ነው ፍክት ያለው ይህ ህይወት ለዕዝራ ከስር ከስር ደስታ ከስር ከስር ሀዘን መስማቱ ህሌናው ምን ያክል እንደተጎዳ ያስብቃል። ዕዝራ ሲማይ አጠገብ ያለች የመስለውን ስሜት መፋቅ አይፈልግም የሲማይን ስዕል እየዳበሰ አይኑን ጭፋን አረጎ "ሲማይዬ የኔ ልእልት ካላንቺ ሁሉም ነገር ከባድ ነው አንዳንዴ ታቂያለሽ አንቺን የማግኘት ፈላጎቴ ሲንረ እና ሳጣሽ ሁሌም ያመኛል" አለና ዝም አለ እንባው በጨፈናቸው አይኖቹ ፈሰሱ። ለደቂቃዎች ከቆየ በኋላ ተነስቶ ወኔ እና ቅጥልጥል የሆነ ስሜት ውስጥ ሆኖ "ከእዚህ በኋላ ግን አንቺ እንደፈለግሽው ህይወቴን እቀጥላለሁ ያልሽኝን ነው የማረገው አለ።
ተነስቶም ወደ ሳሎን ሄደ። ዶክተር ፣ አስሚ እና አባቱ ሳሎን ቁጭ ብለው እያወሩ ነው። ዕዝራ አብሯቸው ቁጭ አለ። ሶስቱም የዕዝራ ሁኒታ ግራ ተጋበተዋል። ዶክተሩ ግን ግራ ከመጋባቱ በዘለለ የዕዝራ ሁኔታ ወደ ማንነቱ ለመመለስ በሚሞክረበት ጊዜ የተፈጠረ መሆኑ በጥቂቱም የገባው ይመስላል። ዶክተሩ "እእ ዕዝራ ዛሬ ወደ ሲማይ መሄድ ትፈልጋለህ?" አለው። ዕዝራ "አዎ ምን ጥያቄ አለው እሷን ለማየት ሁሌም ዝግጁ ነኝ ከፈላጎት ጋር " አለ። አስሚም "ጥሩ እኔም አብሬያቹ ብሄድ ደስ ይለኛል" አለች። ዶክተሩ "እሺ በቃ የዕዝራ አባት እዝህ መቆየት ይችላሉ እኔ ዕዝራን ወስጄ እመልሰዋለሁ መኪናዬ ውጪ አለች።" ሲል የዕዝራ አባት "ጥሩ በቃ በጊዜ ተመለሱ" አሏቸው።
         ፨አሁን ከእረዥም ጉዟ በኋላ የሲማይ መቃብር ጋር ደረሰዋል። ዕዝራ ሲማይ መቃብር ጋር ተንበረክኮ "ልእልቴ ያስቀመጥሽልኝን ማስታወሻ እያነብኩት ነው። ቆይ አንቺ ለምን የማይመስል ነገር ታወሪያለሽ አለሽ አንቺ ሁሌም አለሽ ውስጤ ምን ያህል ጊዜ በተስፈ ልጠብቅሽ እንደሆነ ልትፈትኚኝ እንደሆነ ይሰማኛል" አለ። ዶክተሩ ወደ አስሚ ጆሮ ጠጋ ብሎ "እሱ እስኪጨረስ ወደ መኪናው እንሂድ የምነግረሽ ነገር አለ" አላት። አስሚ ግራ እየገባት "እሺ" ብላ ተከታትለው ወደ መኪናው ሄዱ።
        ፨ ዶክተሩ ከአስሚ ጋር መኪና ውስጥ ገባና።  "እእእ አስሚ የሆነ ነገር ልጠይቅሽ ነው እኔ ቃላትን ለእራሴ ህይወት ሲሆን አመቻችቼ መናገር አልችልም ኡፍፍፍፍ" አለ። አስሚ ሳቅዋ እየተናነቃት አንገቷን ደፈታ "ምነው የሆንከው ነገር አለ ዶክተር አለችው" ዶክተሩም "ዶክተር ብለሽ አትጥሬኝ በፈጠረሽ" አላት። አስሚ በድጋሜ አንገቷን ደፈታ ሳቅ እየተናነቃት "እሺ ምን ልበልህ ዶክተር?" ስትለው ዶክተሩ "ፈጣሪዬ ኧረ ምን ይሻለኛል እየሳቅሽብኝ ነው አደል እስቲ ቀና በይና እይኝ" አላት። አስሚም ከሳቅዋ መለሾ ብላ ቀና አለችና
ዶክተሩን አየችው ዶክተሩም "ቆይ ለምን ዶክተር ትይኛለሽ" አላት። አስሚም "እንዴ ዶክተር ስለሆንክ ነዋ" አለችው። ሳቋ ጮፍ ደረሷል። ዶክተረም "አዎ አቃለሁ ዶክተር ነኝ ኡፍፍፍ እሺ ከእዚህ በኋላ በስሜ ጥሪኝ" ሲላት አስሚ "እንዴ ዶክተር እሺ ስምህ ማነው" አለችው። ዶክተሩ እረረ ብሎ " አኪም " አላት። አስሚ የተቆጣጠረችው ሳቅ ፈንድቶ አመለጣትና እየሳቀች "እና ዶክተር እና አኪም ምንድነው ልዩነቱ" አለችው። ዶክተሩ "አስሚ ስሜ ሀኪም ሳይሆን አኪም ነው" አላት። አስሚ ሳቋን ማቆም አቃታት እንባ በእንባ እየሆነች እና እንባዋን እየጠረገች "እሺ ዋናው ሀሳብህ ምንድነው?" ሰትለው። "ዋናው ሀሳቤማ" ብሎ የስሚን ከንፈረ በንፈስ ፈጥነት ከከንፈሩ ለጠፈው  አስሚ ደነገጠችም ደስም አላት። አይኑዋን በስሱ ጭፍን አረገችው። እና እሷም መልሳ ሳመችው።
           ፨ዶክተሩ በቀስታ ወደ አስሚ ጆሮ ጠጋ ብሎ ከእዚህ የዘለለ ነበር አላት" አስሚ "ማለት?" አለችው። ዶክተሩ አስሚን አቀፈትና "አስሚ አፈቀረኩሽ አንዳፈቀረሽኝ አቃለው ላገባሽ እና አብሬሽ ልኖርም እፈልጋለሁ አስሚ  አፈቅርሻለሁ" አላት። አስሚ "እኔም ካንተ ይምጣ ብዬ እንጂ በጣም አፈቅርሀለው ብላ አጥብቃ አቀፈችው" አስሚ በድንገት ወይኔ "ዕዝራስ ግን" አለች። ከመኪናው ወረደው
ወደ ዕዝራ ሄዱ። ዕዝራ ግን የለም  ደነገጡ መቃብር ቦታዎቹን ሁሉ ዕዝራን እየጠሩ መፈለግ ጀመሩ።
          ፨የመቃብር ቆፋሪዎቹን ሲጠይቁ የዕዝራን ምልክት ሲነግሯቸው አንደኛው "እእ የሆነ ቀይ ቆንጆ ልጅ ወደ ፊት እየሳቀ ቆይ አትሂጂ ጠብቂኝ እንጂ" እያለ  እየሮጠ እንዳየው ነገራቸው። ዶክተሩ እና አስሚ እስከማታ ዕዝራን መቃብሩ ቦታን አስሰው ቢፈልጉትም ሊያገኑት አልቻሉል ዕዝራ ቢሉም አሜት የሚላቸው ሰው አጡ። ቀኑ እየመሸ ሲሄድ የዕዝራ አባት ለአስሚ እና ለዶክተሩ መደወል ጀመሩ ማናቸውም ማንሳት አልቻሉም። እያለ እያለ ሰአቱ ሄደ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ሆነ። የሲማይ መቃብር ጋር ቁጭ ብለው ጠበቁ ዕዝራን ሊያገኑት ግን አልቻሉም። አስሚም አሚር በቃ የግድ ለአባቱ ማሳወቅ አብን ያለ በዝያ አማራጭ የለንም ስትል። ዕዝራ "አዎ እኔን ከማመን ውጪ አማራጭ የላችሁም" አለ። አስሚ እና ዶክተር ደንግጠው ዞር ሲሉ ዕዝራ ፊቱ ጭው ብሎ አዩት። አስሚ "ዕዝራ የት ነበረክ ሰትለው እራሱን ስቶ ወደቀ። ተደናግጠው ወዲያው ወደ ሀኪም ቤት ወሰዱት። ከ3ቀናት በኋላ ዕዝራ ተሻለውና ቤት ገባ።
          ፨ከዛን ቀን ጀምሮ ዕዝራ ሰው ፊት ወደ እራሱ የተመለሰ ለመምሰል መታገል ጀመረ ግን አልቻለበትም።  እንደውም ሲማይ ህይወቱ ውስጥ ሳይሆን ልቡ ውስጥ ብቻ እንዳለች ሲያስበው አሳበደው ሲማይ በጣም ስትናፈቀው የፃፈችለትን ገልጦ ባለፈው ካቆመበት ለማንበብ ወዳስቀመጠበት እጁን ሰዶ አወጣው። ገለጠው ሁለተኛው ቀን ላይ የፃፈችው ማስታወሻ ነው ማንበብን ቀጠለ። "ዕዝሬ ስምህን ስፅፈው ከአንደበቴ ሳወጣው ልቤ በደስታ እየጨፈረች እንደሆነ ታቃለህ ዕዝሬ ፍቅሬን ልገልፅልህ አልችልም ሰው ማፈቀር ማለት ደሞ የግዴታ ያፈቀሩት ሰው መሆን ሳይሆን በአፈቀሩት ልብ ውስጥ መኖረም ነው። እኔ አልቆልኛል አንተ ግን ዕዝረዬ ገና ብዙ ነገር ይጠበቅብሀል እየውልህ ዕዝሬ ወደፊት የምታገባት ሴት ካስከፋችህ ግን አለቃትም እየውልህ መቃብር ፈንቅዬም ቢሆን ተነስቼ ልኳን ነው እማሳያት ግን አንተን አግኝታ መላክ የማትሆን ሴት አለች? ዕዝሬ ደግሜ ደጋግሜ ብፈጠረ እና የተፈጠረኩበት አለም ላይ ሁሌም አንተ ብትኖር ሁሌም አንተን ደግሜ ደጋግሜ ባፈቅርህ አይቆጨኝም ፈጣሪ ሁሌም ልክ እንዳንተ ለአንድ ስከንድም ቢሆን አፋቃሪ ቢገኝ ትልቅ ሽልማት ነው። ውይ ዕዝሬ ብታይ ዛሬ በረራ አለኝ ደውዬልህ ስልክም አታነሳም
ለምን ወዴት ልትሄጂ ነው ካልከኝ የተፈጠረውን ለአባቴ ስነግረው እኔ ጋር ነይና የመጨረሻ እድል ሞክሬ አለኝ። ዕዝሬ አንተን ሳላገኝ በፊት ቢሆን ይህንን ዜና የሰማውት ለህይወቴ ምንም ስለማልሳሳ ሞቴን ቁጭ ብዬ እጠብቅ ነበር ምክንያቱም አባ አጠገቤ ስላልሆነ

1 month, 2 weeks ago

እቀጥልልሀለው ይላል።

፨ ዕዝራ ቀጣዩን ማንበብ ጀመረ። "ዕዝሬ ተመልሻለሁ እሄድበታለሁ ያልኩክ ቦታ እኮ ሄድኩ። ዕዝረዬ ምን ልበልህ ምን አባቴ እንደምልህ ጭንቅ አለኝ እኮ ግን ያው መናገሬ ግድ ነው ይህንን ዜና ስሰማ እኔም ደንግጫለሁ ምን መስለህ ዕዝረዬ
በተደጋጋሚ ሲነስረኝ ለህክምና ስሄድ የምርመራዬ ውጤት ውጪ ተልኮ ደረሷል ተብዬ ሄጄ ነበር። ዕዝረዬ በቃ አልቆልኛል ልሞት ነው" ዕዝራ ፊቱ ቀላ አለቀሰ ደነገጠ ጥረሶቹን በሀይል እያንቀራጨጨ ማንበብን ቀጠለ "ያን ያክል የከፈ ነገር አልመሰለኝም ነበር በዛ ላይ ፍቅር ካንተ ሲይዘኝ ጥሩ ህይወት እንደምኞር ተሰምቶኝ ነበር ግን አልሆነም በቃ እኔ ሳታፈቅሬ አትሙቺ ፍቅረን አይተሽ ሳታጣጥሚው ሙቺ የተባልኩኝ ነኝ። መቀየር የማልችለው ፈተና ውስጥ ገባው። ዕዝሬ እኔ የደም ካንሰር ህመም ይዞኛል ምልክቱ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ስላሳየ ከፈጣሪ በቀረ አዳኝ የለኝም። አንተ ግን ጠንካራ ሁን እሺ ሁሌም እየመጣህ ጠይቀኝ ምክያቱም ዕዝሬ ትናፈቀኛለህ። " የሲማይ እንባ ወረቀቱ ላይ አረፎ ከለሩን አልፎ አልፎ ቀይሮታል አሁን ደሞ የዕዝራ እንባም ወረቀቱ ላይ እየዘነበ ነው።
          ፨ ዕዝራ ማንበቡንም ማልቀሱንም አላቆመም "ዕዝረዬ ምን ማለት እንዳለብኝ እራሱ እኮ ግራ ነው የገባኝ። እኔ ቅድም እንዳልኩክ ፈጣሪ ፍቅርን ሳታይ አትሙቺ ብሎኝ ነው። አንተን ግን ምን አልባት ዳግመኛ ፍቅር እንደሚይዝ  ሊያሳህ ይሆናል በእረግጠኝነት እንደዛ ነው። ህይወትህን ቀጥል እሺ ያለ በለዝያ በጣም እከፋብሀው እንድኩፋ ደሞ አትፈልግም አደል ስለዝህ የወደፊቷን ሚስትህን እስክታገኝ ብቻህን አንዳዴም ከአስሚ እና አባቴ ጋር እየመጣህ እየኝ ውስጤ ከአስሚ ጋር እንደምትቀራረብ ይነግኛል ጥሩ እህት ትሆንሀለች ደሞ አባቴን አደራ ዕዝረዬ" ይላል የመጀመሪያው ገፅ። ዕዝራ ሊላኛውን ገልፆ ለማንበብ ፈራም ፈለገም። ማስታወሻውን ከደነውና ክፍሉ ውስጥ ካለው የልብስ ማስቀሙጫ ቁም ሳጥን ከፈቶ ሲማይን የሳላት ስእል አውጥቶ መሬት ላይ ተንጋሎ  አቅፎ  ማልቀስ ጀመረ።

ክፍል 11
ይቀጥላል...

2 months, 2 weeks ago

ቆጣ ብላ አንቺስ ስላት ቁጣዋ ወደሳቅ ተቀይሮ ሳቀችና አቀፈችኝ
ሁለቱንም እኮ አደለም የምስጥክ አንዱን ነው ብላ ለቀቅ አድርጋ
አይኔን እያየች እኔ ደሞ ቆይ እሺ አንቺን ኩላሊት ቢያምሽስ ልክ
እንደኔ አልኳት ፀባይክ ካላማረና ካመመኝ ትመልሳክ አለች ፍገግ
ብላ ከዛ እጄን ልቦ ላይ አደርገችው እና ሁሉ ነገሬ ያንተ እና ያንተ
ብቻ ነው አለችኝ እኔ ምን እንደምላት ግራ ገባኝ ያኔም የመኪና
አደጋ ሲደርስብኝ ደም ለግሳኝ ነበር በነገራችን ላይ አንደኛው
ጓደኛዬ ካደጋው ተርፎ አሁን ደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ
እየተመላለስን ንግድ ነው የሚስራው የሄዋን ጥሩነት ከአቅሜ
በላይ ሆነ ከ15 ቀን በኋላ ወደ ውጭ ሀገር ሄደን ንቅለ ተከላውን
አደረግን ትንሽ ሳገግም ደሞ ወደ ዱባይ ሄደን እቴቴ ባወርስችኝ
ቤት ዘና አልን ዲና በጣም ደስ ይላል ከሚያፍቅሩት ጋራ አብሮ
መዋል እና ማደር ስትል አዳም አዎ በጣም ግን ከሄዋን ጋር
አብርን አናድርም እንውላለን እንጂ እስክንጋባ አብርን አንተኛም
አላት ዲና በመገርም እና እስካሁን ምንም አርጋቹ አታቁም አለችው
አዳምም አዎ አናቅም ዲና ግርም አላትና እሺ ሌላው ቀርቶ ስትል
አዳም እሩቅ አትሂጂ ከንፍሯንም ስሚያትም ስማኝም አታቅም
ምክንያቱም ያረከስኳት ነው የሚመስኝ እኔ እሷን የምፈልጋት
ለደቂቃ ስሜት ሳይሆን ለዘላለም ደስታ ነው አላት ዲና በጣም
ተደመመች።
ዲና ከሩቅ አንድ ዶክተር አየች አዳምን ወደሱ እንዲያይ በአይኗ
ምልክት እየስጠችው ተመልከት ይህንን ልክስክስ ዶክተር ከህፃን
ታካሚ እስከ ጉልማሳ አይቀርውም ሲባልግ ነርስ ዶክተር ዘበኛ
አይመርጥም በእሱ ያለተበላሽነው ጥቂቶቻችን ነን ምክንያቱም
እዚህ ሀኪም ቤት ሁሌ አፓረንት ስንወጣ አየዋለው አለችው
አዳም ግራ እደተጋባ ተማሪ ነሽ እንዴ አላት አዎ ነኝ ስትለው
አዳም ግራ በመጋባት ነርስ መስለሽኝ ነበር ለካ ነርስነት
እየተለማመድሽልኝ ነው አላት አይ አይ ያኔ አንተን ለማዋራት
ሰለፈለኩኝ ነበር የቆየውት እና እልካለው ኮማ ውስጥ ሴት ካለች
እሷንም አይምርም ምክንያቱም ገና ሲታይ እንደምታየው ፍቅር
የሚያሲዝ ነው በተለይ አቋምና መልክ ላላቸው ሴቶች እንክብካቤ
ያበዛል ሄዋን ግን ሰውነቷ እንዴት ነው ያምራል? አለችው ጠቀስ
አድርጋው በቀኝ አይኗ ስለ ስውነት አቋሟ ልነግሽ አለችም
ምክንያቱም እሱን አይቼ ስላላፍቅርኮት ልነግርሽ የምችለው አይቼ
ስላፍቀርኩት ልቧ ነው አላት ዲና በአግራሞት ጭንቅላቷን
ነቀነቀች በነገራችን ላይ ያንተ ፍቅር የመጨርሻ ደረጃ ላይ ነው
ስትለው የፍቅርም ደርጃ አለው አላት ዲናም እንዴ አዎ
የሳይካትሪስት ተማሪ አይደለው እሱን ያላወኩኝ ምን ላቅ ነው
አለችው አዳምም እሺ እስቲ ንገሪኝ አላት ዲናም ፈገግ ቀልጠፍ
ብላ የመጀመሪያው love ይባላል ይህ ማለት ደሞሞ
ይህ እጅግ በጣም መውደድ ነው ከዛ ሌላው ደሞ like ነው
በጣም መውደድ ማለት ነው ሳስተኛው Adore ይባላል ይህ
ማለት ደሞ ማፍቀር ነው ስትለው አዳም ፍገግ ብሎ እና እኔ
Adore ላይ ነኝ ሲላት አይ አይ አልጨርስኩም አራተኛው
worship ejik ነው ይህ በጣምምምም ማፍቀር ነው
አለጨርኩም ይቀራል አለች ዲና አዳም ሊያወራ ሲል
አምስተኛውእና የመጨርሻው ፍቅር ደሞ become crazy
ይባላል ይህ ማለት የፍቅር ጥግ ላይ ደርሰካል አብደካል ማለት
ነው አምስተኛው አንተን ይገልፅሀል አለችው አዳም በለው ኧርር
ጓበዝ ጥሩ ማብራሪያ ነው ወደጄዋለው
ሄዋን ነቅታ ይሆን አለና ዶክተሩ እሷ ጋር ብዙ እንዳይመላለሱ
የነገር ትዝ አለው ግን አልቻለም እና ብድግ ብሎ ሄደ ሄዋን
ለጥጥ ብላለች ሄዶ ግንባሯን በቀስታ ስሟት ወጣ እና ወደቦታው
ተመለስ ዲና ጎን ተቀመጠ ያ ልክስክሱ ዶክተር ወደ እነሱ
እየቀርበ መጣ ከዛም በጣም ቀርበ እና ሄዋን የተኛችበትን ክፍል
በር ለመክፍት የበር እጀታውን ያዘው አዳም ሊያብድ ደርስ ወደ
ዶክተሩም ተጠጋ

✨ይቀጥላል......

2 months, 2 weeks ago

😘አለሜ ነሽ😘

🔥ክፍል 12

✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ

""
""
አዳም ፈገግ ብሎ አስቢው እስቲ ሄዋኔ ስታወራ በጣም
የምትጮህ ካልጮከች የምታወራ የማይመስላት ናት ግን ያኔ
የወሰደችኝ ሰዎች ድምፅቸውን ቀንሰው የሚያወሩበት ሁለት
ሰዎች በብዛት ደሞ ፍቅረኛሞች እየመጡ የሚያወሩበት ማንም
ማንንም መረበሽ ፍፅሞ እንደማይፈቀድ መግቢያው ላይ የተፃፈበት
ነው ከዛ በውስጤ ቢቆይም ከሄዋን ጋር እንደዚህ አይነት ቦታ መምጣት
አግባብ ነው አልኩኝ ና ብላ እጄን ጎትታ የሆነ መቀመጫ ላይ
ተቀመጥን መቀመጫው ያንዠዋዥዋል ልክ እንደ ዥዋዥዊ እና 2
ሰው የሚይዝ ነው ከዛም ከተቀመጥን በኋላ ሄዋን በእግሯ
መሬቱን እየገፋች መንዠዋዠው ጀመርች እኔ ደሞ ጥሎብኝ
ዥዋዥዌም ሆነ ምንም አይነት ተንቀሳቃሽ ነገር ላይ መቀመጥ
አልወድም እንድታቆም ለመንገር ፈራው የሰውነቴ እና የፊቴን
እንቅስቃሴ በማየት እንዳልተመቸኝ አውቃ ነው መሰለኝ
ማንዠዋዠውን አቆመች እና ዝም ብላ ታየኝ ጀመር ያኔ ልቤ
በጣም ደነገጠ መምታት ጀመር ወደኔ ተጠጋች ላብ በላብ ሆንኩኝ
ከዛ ወደ ከንፈሬ አከባቢ ያለውን ጉንጬን ሳመችው እና ግጥሜስ
አለችኝ ጮክ ብላ ሰዉ ዞሮ አፈጠጠባት ከዛም ወደራሳቸው ወሬና
ተመስጦቸው ተመለሱ ። እኔም የያዝኩትን የተጣጠፈ ወረቀት
አወጣው ወረቀቱ ላይ ለሄዋን የገጠምኩት ግጥም ነበር። ሲል
ዲና ምን የሚል እስቲ በልልኝ አለችው አዳምም በደስታ አለና
ጉሮሮውን ጠራርገው የግጥሙ
ርዕስ እኔስ ገረመችኝ ይላል

እኔስ ገረመችኝ ኧረ አስደመመችኝ
ይህቺ ሴት በድንገት መጥታ የሳመችኝ
ኧር እንደውም በጣም አስደነገጠችኝ
ክው ብዬ ቀርው የሳመችኝ እለት
ሳስባት አደርኩኝ ቀን አልቀርኝ ለሊት
ጉንጬን ስትስመኝ ደንገጥገጥ አልኩና
ግንባሪን ስስመኝ ልቤ ተናጋና
ይህቺ ሴት ልቤ ውስጥ ገባች በጠና
ልቤ ታመመላት ተጨናቀላትም
ታቀዉ ይሆን እንዴ የልቤን መታመም
ወይስ ልብ ሳትል ቀርታ ይሆን እንዴ
ግራ ይገባኛል ዘወትር አንዳንዴ
ብዬ ግጥሙን ጨርሼ ቀና ስል ሄዋን ኩስትርትር ብላ ነበር
በጣም ደነገጥኩ ምነው ልልላት ብዬ ፈራው ምን አልባት ግጥሙ
ላይ ለእሷ ያለኝን ስሜት ስለገለፅኩ ተናዳ ይሆን ብዬ አስብኩኝ
ከዛም ሄዋን እየቀለድክብኝ ነው እንዴ አለች ደነገጥኩ
ሰዉ ሁሉ ዞሮ አየን በጥፊ መታችኝ ግራ ገባኝ ለመሳም
ያዘጋጀውትን ጉንጬን ጥፊ አረፈበት ለነገሩ እኔም ይህንን ግጥም
ስፅፍ በግጥሙ አመካኝቼ ፍቅሬን ልገለፅ ነበር አሀ በቃ
ስለማታፈቅርኝ ነው በእዚህ ግጥም የተናደደችው ብዬ አስብኩ
የመታችን ጉንጭ ይዤ ቀረው ደንዝዤ ፍዝዤ በነገራችን ላይ
በሰአቱ እሷ ስለተናደደችብኝ አዘንኩ እንጂ ሰው ፊት ስለመታችኝ
ምንም አለመስለኝም ከዛ ጮክ ብለክ ያነብክለኝ ግጥም በልልኝ አለችው እ አልኳት አዎ በልልኝ አለችኝ ከዛም ጮክ ብዬ አነበብኩት የሰው ሁሉ ትኩርት እኛ ላይ ነበር
ከዛም ሄዋን ጮክ እና ከት ብላ ሳቀችና የእኔ ውድ ቆይ ምን
አይነት ስው ነክ እእ ብላ ጉንጭ እና ግንባሬን ሳመችኝ ከዛ ሁሉም
እንደ ትንግርት እኛን ማየት ጀመረ ፈገግ አሉ ዲና ቆይ ይህ
የሆነው ሀኪም ቤት ገብተክ ፍቅራችውን ከተገላለፃቹ በኋላ ነው
አለችው አዳምም አይ ከዛ በፊት ነው ያኔ እኔና ሄዋን ከመናፈሻው
ስንወጣ እራሱ ሄዋን ግጥሙ እንዳልገባት ሆና ዝም ብላ ሌላ ወሬ ነበር ስታወራ
የነበርው ሄዋን ግቢያችን በተቀላቀለች በነጋታው ብዙ ወዳጅ ነበር
ያፈራችው ወንዶችን በፍቅር ሴቶችን በመውደድ ጠብ አርጋን ነበር እውነት ለመናገር እሷን አለመውደድ በጭራሽ አይቻልም ተጨዋች ያልሆነውን ተጫዋች
ጉልበተኛ የነበርውን ከጉልበተኝነት እንዲላቀቅ ሱሰኛ የነበርውን
ከሱሱ እንዲላቀቅ እረድታለች ሱስ ስልሽ ለአደንዛዥ እፅ
፣የነገር፣የመላከፍን ይጨምራል ለጥናትም እንደዛው ጥናታቸው
ላይ አተኩርው ጭብጥ ብለው የሚማሩትን ፣ በተለያየ ችግር
ጭምት የሆኑትን ፈታ እንዲሉ አድርጋለች ሄዋን ማለት ስለ ሰው
ችግር ሰምተው እና ይሄ ከእኔ ህይወት ጋር ምን አገናኘው የሚሉት
አይነት ስው አደለችም ብዙ ወንዶች ሄዋንን አፈቀርኩሽ ማለት
ሲጀምሩ እንዳውም በእየ ኮሊደር እና ክፍል ውስጥ 12 ሆነን
ሄዋንን ወደው ኛል እሷ ትስቃለች እኛ ተጨንቀናል ብለው ብዙ
ተማሪዎች ፅፈዋል።
ከ 2አመት በፊት ትምህርት ተዘግቶ እረፍት ልንወጣ ስንል በጣም
ያመኝ ጀመር ጎኔን ይጠዘጥዘኛል ብዙ መራመድ ያቅተኛል ምናምን እንደምንም
ትምህርቱን ስጨርስ ህክምና አደርኩ ይህ የምነግርሽ የመኪና
አደጋው ከተፈጠር በኋላ ነው ፊቴ መበላለዝ ሲጀምር የግቢ ልጆች
ሁሉም ጓደኞቼን በማጣቴ ሀዘኑ በርትቶብኝ ነበር የመስላቸው አንድ
ቀን ከሄዋን ጋር እየሄድን መንገድ ላይ ወደኩኝ ከዛም ሄዋን
በመጮህ እና ሰው እንዲረዳት በማድርግ ሀኪም ቤት ወስደችኝ
ያኔ ያመመኝ እንደ ነገ የግቢው ተማሪ በሙሉ ለእርፍት ሊሄድ ነበር
ስመርመር ሁለቱም ኩላሊቶቼ ፌል እንዳደረጉ እና ከተቻለ
በአፋጣኝ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልግ ዶክተሩ ተናገር ሄዋን
ይህንን ስትስማ እኔ እስጠዋለው አለች ፈጠን ብላ ዶክተሩ ምኑ
ነሽ አላት እና መልሷን መጠባበቅ ጀመረ እኔ በቀስታ ደምፅ ሁሉ
ነገሬ ናት አልኩኝ ዶክተሩ ግራ ገባው ሄዋን ምርመራ አድርገሽ
ለእሱ መስጠት ከቻልሽ ልስጭው ነው ማለቴ እርግጠኛ ነሽ?
አለቻት አዎ ያው ፀባዩ ካላማረ እቀበለዋው አለች እና ፈገግ
አለች ከዛ ዳክተሮቹ እዚህ አልጋ እንድይዝ እና ኩላሊት ከተገኘለኝ
ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ እንደምታከም ነገርኝ ዘመድ ካለኝም ጠየቀኝ
የሩቅም ቢሆን ሲለኝ አይ የማደጎ ልጅ ነኝ አልኩት እና የመታከሚያ
ብር አለህ ሲለኝ በሚገባ አልኩት ምክንያቱም ከማደጎ በኋላ እንደ
ልጃቸው ያኖሩኝ ወይዘሮ ብርትካን በጣም ብዙ ሚሊየን ብር
አውርስውኝ ስለሞቱ ። እማማ ብርትካንን እቴቴ ነው የምላት እኔ
ባደኩበት ማደጊያ እርዳታ በመስጠት ይታዉቃሉ ሲመጡ ሁሌም
ሰላም ይሉኛል ከዛ 15 አመት ሊሞላኝ ከድርጅቱ አስወጥተው
እንደ ልጃቸው ተቀብለው አኖሩኝ የአበባ እርሻ እና የአበባ ማሽጊያ ድርጅት እና ደሞ 2 ሀገር ውስጥ 3 ደሞ ውጪ ቤት አላቸው በየ ሀገሩ በበረሩ ቁጥር ማራኪ አበባ
ካለ ይዘው ይመጣሉ ባላቸው ሞቷል መሀን ስለነበሩ አልወለዱም
ባለቤታቸው አቶ አሰፋም ምርጥ ሰው ነበሩ እቴቴን አንቱ እያልኩ
ነው የማናግራት አንቺ ስላት ያረከስኮት ያክል ነው የሚስማኝ
የሆነ ቀን እቴቴ ዱባይ በረው ሲመለሱ አውሮፕላን ውስጥ ነው
በድንገተኛ አደጋ የሞቱት ግን ከመሞታቸው በፊት ሙሉ
ንብርታቸው ለእኔ 18 አመት እንደሞላኝ መታወቂያ አውጥተውልኝ
ያሸጋገሩት ለእዛም ነው ለዶክተሩ ብር አለኝ ያልኩት
በ3 ቀን በኋላ ሄዋን ምርመራውን አድርጋ ለእኔ መለገስ
የምትችልበት ደርጃ ላይ እንደሆነች ተነገራት ሄዋን
እየተፍለቀለቀች መጥታ እንኳን ደስ አለክ የኔ ፍቅር የኔ ሁሉ ነገር
ዛሬ ደስስስ ብሎኛል እንኳን ደስስስ አለክ አለችኝ ዲያሊስስ
ተደርጌ ስጨርስ ምን ተገኘ አልኳት እኔ ላንተ ኩላሊት መለገስ
እንደምችል ተነገርኝ አንተ ብሩን አዘጋጅ እኔ ደሞ ኩላሊቴን ብላ
በሳቅ አለች ከዛ እኔ አይ አይሆንም አልኳት እሷም ለምን አለችኝ

2 months, 3 weeks ago

ነው አልኳት ከተቀመጠችበት ተነሳች ወደየት ልትሄድ ነው ብዬ
ቁጭ ካልኩበት ቀና ብዬ ተመለከትኳት ወደ እኔ ቀረበች ግጥም
አድርጋ ጉንጬን ሳመችኝ ይህንን ግጥም እማ አለች እየሳቀች
ይህን ግጥምማ የሆነ እምወደው ቦታ አለ እዛ ነው ምታነብልኝ
አለችኝ ውስጤ ደስ እያለው እሺ ብያት መሄድ ጀመርን መንገድ
ላይ እየተራመድን ስሟን ጠየኳት ሄዋን አለችኝ እኔ ደሞ አዳም
አልኳት ከዛም ኦኦኦኦ አዳምና ሄዋን አለችኝ አዳም እና ሄዋን ምን
አይነት አጋጣሚ ነው ሁለታችንም ስማችን አስገርሞን ነበር ።
ከምንራመድበት ገታ ብለን ያው ይህ ነው ቦታው አለችኝ ቦታውን
በአይኔ በደንብ ቃኘሁት ሄዋኔ እዚህ ባታ ትሄዳለች ይህንን ቦታ
ትወዳለች ብዬ አልጠበኩም ነበር እና ገርመኝ ዲና ስፍ ብላ ምን
አይነት ቦታ አለችው

✨.....ይቀጥላል.....

5 months, 2 weeks ago

‍ ​​?ሴና?

#የመጨረሻው ክፍል!

#ደራሲ: በ ኬቤክ (kebek) እንደተፃፈ✍?✍?✍?

#ክፍል3⃣7⃣

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ሴና?

. . . አይኔን ስገልጥ ነጭ ኮርኒስ ነው የታየኝ፡፡ አልጋ ላይ እንደተኛው ይሰማኛል፡፡ አንገቴን ወደ ጎን ዞር ሳደርግ አጠገቤ አንድ ነጭ ጋወን የለበሰ ሰው ቆሞ የአይዞሽ አሁን ደና ነሽ" አለኝ ግንባሬን በመዳፉ እየዳበሰ፡፡ የተኛውት የሀኪም ቤት ክፍል ውስጥ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ወዲያው የክፍሉ በር ተከፍቶ እነ ሚጣ ተከታትለው ገቡ፡፡ "አሁን እንዴት ነሽ?" እያሉ ጥያቄ ያከታትሉብኝ ጀመር፡፡ "አሁን ደና ስለሆነች ይዛቹሀት መሄድ ትችላላቹ ፡፡ትንሽ ድንጋጤው እንጂ ሌላ ምንም ችግር የለባትም" አለ ባለ ነጭ ጋወኑ ሀኪም፡፡ እነ  ሚጣ ደግፈው ከአልጋ ካወረዱኝ ብሀላ ጫማዬን አድርገውልኝ ከተኛውበት ክፍል ይዘውኝ ወጡ፡፡
              ከክፍሉ ስወጣ ከግቢ ውጪ ያለ ሀኪም ቤት እንደነበርኩ ገባኝ፡፡ አይኔ ያነባል፡፡ እነ ሚጣ አይዞሽ ይሉኛል ፣ ጥያቄ ይጠይቁኛል ፣ማብራሪያ ይሰጡኛል ፣ሊያረጋጉኝ ይሞክራሉ፡፡ እኔ ግን ማልቀሴን አላቆምኩም፡፡ ከሀኪም ቤቱ በር ላይ ስደርስ ያየውት ግራ ገባኝ ፡፡ የወንድሜ መኪና ቆሞአል፡፡ እንዴት እንደሰማ ግራ ገባኝ፡፡ "ቆይ ውስጥ ነው ይመጣል"አለችኝ ሚጣ በቀኝ በኩል ደግፋኝ እንደቆመች፡፡ እንዴት መጣ? ማን ነገረው? ቆይ እኔ እንዴት እዚ መጣው?' ጠየኳት ሚጣን እንባዬ አሁንም እንደወረደ ነው፡፡ ድምፄ ጉንፋን እንደያዘው ሰው ተዘግቶአል፡፡ "ቆይ ሁሉንም እናውራለን፡፡ አሁን ተረጋጊ"አለችኝ ሚጣ ጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን በሹራቧ ጫፍ እየጠረገች፡፡ በዚ መሀል ወንድሜ መጣ "አይዞሽ ምንም አልሆንሽም"ብሎ አቀፈኝ፡፡ ጥያቄ ሆነብኝ፡፡ ወዲያው የመኪናውን ሁዋላ በር ከከፈተልኝ ብሀላ ወደ ውስጥ ገባው፡፡ ሚጣ ተከትላኝ ገባች፡፡ ሌሎቹ ከተሰናበቱኝ ቡሀላ ሄዱ፡፡
             ወንድሜ ወኪናውን አስነስቶ መሄድ ሲጀምር 'ቆይ ምንድነው ነገሩ ግራ አጋባቹኝ እኮ 'አልኩኝ በደከመ ድምፅ፡፡ ማንም መልስ አልሰጠኝም፡፡ ወንድሜ መኪናውን እየነዳ ከከተማ ወጣ ወዳለ ቦታ ከወሰደን ብሀላ መኪናውን ከአንድ ሜዳማ ስፍራ አቁሞ ሞተሩን ካጠፋ ብሀላ ከመኪናው ወረደ፡፡ሚጣም ተከትላው ወረደች፡፡ ግራ ገባኝ እኔም ተከትያቸው ወረድኩኝ፡፡ ወንድሜ መኪናውን ተደግፎ ቆመ፡፡ ገና ከመኪና ከመውረዴ ሚጣ ማውራትጀመረች፡፡ "የውልሽ ሴና ያኔ ለ እረፍት ወደ ቤት የሄድን ሰአት ነበር ፍሬ በድንገተኛ አደጋ ያረፈው፡፡ እና የዛን እለት ላንቺ ይሄንን ልነግርሽ አስቤ ነገር ግን እንደዚ አይነት ነገር በስልክ ብነግርሽ ያለሽበት ሁኔታ ደሞ ጥሩ ባይሆን ይሄንን ስትሰሚ የሆነ ነገር ቢፈጠር ወይም የሆነ ነገር በራስሽ ላይ ብታደርሺ ብዬ ስለፈራው ለወንድምሽ ደወልኩለት፡፡ የሱን ስልክ ከየት አገኘሽው ካልሽኝ እኛ ግቢ ምትማረው የባልደረባችን ልጅ ያልሽኝ ከሷ ነው የተቀበልኩት፡፡ የሷን ስልክ ደሞ ያገኘውት እነሱ ዶርም የምትኖር ልጅ ጉዋደኛ እሱን ጠይቄ በሱ በኩል አድርጌ አፈላልጌ ነው፡፡ ያ አማራጭ ባይኖረኝ የዛኔ ቀጥታ ሀዋሳ ቤታቹ መጣ ነበር፡፡ ይሄንን አድርጌ ለወንድምሽ ደውዬ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፡፡ የዛን እለት ወንድምሽ ሰበብ ፈልጎ ስልክሽን ተቀበለሽ፡፡ ያንን ያደረግነው ደሞ ከሌላ ሰው እንዳትገናኚ እና ከሌላ ሰው እንዳትሰሚው አስበን ነው፡፡"
         ሚጣ ይሄንን ስትነግረኝ ወንድሜን እየተመለከትኩት ማንባቴን ቀጠልኩ፡፡ ሚጣ ቀጠለች፡፡ " . . .ለ ዴቭ ስትደውይለት አጠገቤ ነበር፡፡ ፍሬን እንዳላየው እና ሀዋሳ እንሆነ እንዲነግርሽ የነገርኩት እኔ ነበርኩኝ፡፡ ሰኞ ለምዝገባ መጥተሽ ምዝገባ አርብ ነው ሀሙስ እንመጣለን ያልኩሽ ግዜ እኔ ግቢ ነበርኩኝ፡፡ ሌሎቹም የዶርም ልጆች መጥተው ከተመዘገብን ብሀላ ወንድምሽ ንቺን ግቢ እንዳደረሰሽ በሌላ በር ገብቶ አንቺ መምጣት እንደማትችይ ነግሮ ግቢ ውስጥ በሚያውቀው ሰው አማካይነት እንድትመዘገቢ አደረግን፡፡ ከዛ እኔና የዶርም ልጆች እናንተ ቤት ነበርን፡፡ ምክንያቱም ሀሙስ ነው ምንመጣው ያልንሽ ብቻሽን እንድትሆኚ ነበር፡፡ ብቻሽን እንድትሆኚ ካደረግን ብሀላ ወንድምሽ ኪሩቤልን ላከው፡፡ ኪሩቤል በአጋጣሚ ካፌ ውስጥ የተዋወቅሽው ተማሪ ሳይሆን የስነልቦና ባለሙያ የሆነ የወንድምሽ ጉዋደኛ ነው፡፡ የፍሬ ስልክ ሲሙ የወጣው በዴቭ ስም ነው፡፡ስለዚ ፍሬ ሲያርፍ ዴቭ ሲሙን አውጥቶ ስለነበር በዛ ስልክ ሚደወሉ ጥሪዎችን በሙሉ ለፍሬ የተደወሉ ይሆናሉ ስለሚል አያነሳውም፡፡
            እኔና ወንድምሽ ይሄንን ስናደርግ ሀሳቡ የኪሩቤል ነበር፡፡ እኛ ያሰብነው ፍሬን ቀስ በቀስ እንድትረሺው ነበር፡፡ ለዛ ነው ኪሩቤል ቢዚ ያደረገሽ፡፡ ያው ባልጠበቅነው መንገድ እውነቱን አወቅሽ እነጂ" ፡፡ሚጣ ይሄንን ሁሉ ስታወራ እኔ እያነባው በግርምት አዳምጣት ነበር፡፡ ወንድሜ መኪናውን እንደተደገፈ ቆሞ ያዳምጣት ነበር፡፡ ወደወንድሜ እየተመለከትኩ ላወራ ስል "ሴና ከህፃንነችሽ ጀምሮ ሳደርግ የነበረው ነገር አንቺ እህቴን በጣም ሰለምወድሽ ነበር፡፡ ታላቅ እንደመሆኔ ደሞ አንቺን ከብዙ ነገር ጠብቄ ትልቅ ሰው ማድረግ ነበር እቅዴ ፡፡ እኔ ይህን ሳደርግ ደሙ ሙሉ ቤተሰባችን ስለሚቀበለኝ አንቺ ይሄንን ከጥላቻ ትቆጥሪያለሽ፡፡ በርግጥ እኔም አበዛውት ግን ላንቺው አስቤ የማደርገው ነገር ሾለ. . . " አላስጨረስኩትም ወንድሜ ላይ ጥምጥም አልኩበት፡፡ ይሄንን ሁሉ ነገር ያደርግ የነበረው ለኔው ሲል መሆኑን ሳስብ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ ወንድሜን ለቅቄ ሚጣን አቀፍኳት፡፡ ተቃቅፈን አለቀስን፡፡
         ወደ ከተማ እየተመለስን በጭንቅላቴ ብዙ ሀሳቦች ተመላለሱ፡፡ ዠእውነት ለካ ቤተሰቦቼ ለኔ ፍቅር አላቸው፡፡ የተከተሉት መንገድ የጎዳኝ ቢመስለኝም ሁሉን ሚያደርጉት ለኔ ብለው ነው፡፡ የዶርሜ ልጆች እውነትም ለካ ከልባቸው ነው ጉዋደኝነታቸው፡፡ ለኔ ሰሜት ምን ያህል እንደሚጨነቁ አሰብኩኝ፡፡ እውነት እኛ ሰዎች ባሰቡልን ልክ እያሰብናቸው ነው?' ብዬ ራሴን ጠየኩት፡፡ ዶርም ስገባ ስለሁሉም ነገር ጉዋደኞቼን አመሰገንኳቸው፡፡ ከኪሩቤል ጋርም ጉወደኝነታችን ቀጠለ፡፡ ወንድሜና ጉዋደኞቼ ባደረጉት ነገር በጣም ብዙ ተማርኩኝ፡፡ ጉዋደኝነት ፣ቤተሰብ እውነተኛ ፍቅርን ከነሱ አገኘው፡፡ የፍሬ ህልፈት እጅጉን የከፋ ሀዘን ቢያደርስብኝም ቤተሰቦቼ እና ጉዋደኞቼ ከጎኔ በመሆናቸው ብርታት ሰጡኝ፡፡
             ይሄ ታሪክ ከተፈጠረ አመት አለፈው፡፡ አሁን እኔ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆኛለው፡፡ ዶርም ስሄድ ቤቴ ቤት ስሄድ ዶርሜ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ በትምህርቴ ውጤታማ እየሆንኩኝ ነው፡፡እስካሁን የፍቀር ጉዋደኛ አልያዝኩም፡፡ ፍሬ ዛሬም በልቤ፥ አለ፡፡ ነገር ግን ቤተሰቦቼና ጉዋደኞቼ አብረውኝ ስላሉ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለሁሉም ነገር ደሞ ፈጣሪን አመሰግናለው፡፡ አምላክ የፍቅርን ጉልበት በቤተሰቦቼና በጉዋደኞቼ በኩል አስተምሮኛል፡፡

ይህንን ታሪክ ያነበባቹ በሙሉ ከዚህ እንደምትማሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡

. . . . ህይወት ይቀጥላል  . . .

???? ተ  ፈ  ፀ  መ????

5 months, 3 weeks ago

‍ ​​​​?ሴና?

#ክፍል 3⃣6⃣

❤️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

. . . ዛሬ በጥዋቱ ነው የተነሳውት፡፡ ኪሩቤል ልክ በሰአቱ ሲደውል እኔ ቀድሜው መነሳቴን ነግሬው ጉዋደኞቼን ጨምሮ አብረን ቁርስ በላን፡፡ ዛሬ ምንመዘገብበት ቀን ነው፡፡ ኪሩቤል ሲቀር ሁላችንም ተያይዘን ሄድን፡፡ምዝገባ ቦታ ስንደርስ ማንም ተማሪ የለም፡፡ "ተማሪው ምን ነካው ? ቀኑ አልፍ ነው ወይስ እኛ ቀድመን ነው?" ስንባባል ሚጣ "መታወቂያ ነው አስቀምጠው ሚሄዱት መታወቂያቹን አምጡ እና እዚ ጠብቁኝ "ብላ መታወቂያችንን ሰብስባ ወደውስጥ ገባች፡፡ ትንሽ ቆይታ "በቃ መታወቂያ ነገ ነው ምንቀበለው" ብላን ተያይዘን ቡዙ ግዜ ተሰብስበን ምኅቀመጥበት ቦታ ሄድን፡፡ እስከ ምሳ ሰአት ከዛ ቦታ አልተነሳንም፡፡ ያለፋት ሳምንታት ምን ይመስሉ እንደነበር ተራ በተራ መጨዋወት ጀመርን፡፡ የኔ ተራ ሲደርስ 'ብዙም ደስ አይልም ይልቅ ተነሱ ወደ ምሳ ርቦኛል 'አልኩዋቸው ተጨማሪ ጥያቄ እንዳይጠይቁኝ ስል ከተቀመጥኩበት እየተነሳው፡፡ ሁሉም ተከትለውኝ ተነሱ ፡፡ ማንም ምንም አልተናገረኝም፡፡ በፊትም ቤት ውስጥ ያለውን ነገር የተወሰነ ያህል ስለሚያውቁ ይረዱኛል፡፡
        ምሳ ልንበላ ወደ ካፌ እየሄድን ኪሩቤል ደወለ "እስኪ አምስት ብር ሙይልኝ የምሳ " አለኝ በአሳዛኝ ድምፅ፡፡ በጣም ነው ያሳቀኝ፡፡ ከጉዋደኞቼ ጋር እየመጣው እንደሆነ እና እዛው ካፌ እንዲጠብቀኝ ነግሬው ስልኩን ዘጋውት፡፡ በስልክ ያለኝን ለጉዋደኞቼ ስነግራቸው ሁሉም ሳቁ፡፡ ኪሩቤል ከሁሉም ጋር ተግባብቶአል፡፡ ገና በመጀመሪያ ቀን እንደዛ ሲጫወት ሳየው ጉዋደኞቼን ከድሮ ጀምሮ ሚያውቃቸው ነው ሚመስለው፡፡ካፌ ስንደርስ ኪሩቤል ዝርዝር ብር ይዞ ካፌው በር ላይ ተቀምጦአል፡፡ ገና አንዳየነው ሁላችንም ሳቅን፡፡ ተሰብስበን ምሳ አብረን በላን፡፡
              ከምሳ ብሀላ ሌሎቹ ጉዋደኞቼን ከ ኪሩቤል ጋር  ትተን እኔ እና ሚጣ ወደ ዶርም እየሄድን ሳለ አንድ ልጅ መጥታ ሚጣን ተጠምጥማባት ካቀፈቻት ቡሀላ እኔን ጨበጠችኝ፡፡ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ጠይቃን ሚጣን "እንዴት ነው በረታቹ ? እኔም እኮ ወደ ግቢ መጣው ተመልሼም ሳልጠይቃቹ፡፡ ወይዘሮ አዲስ እንዴት ናቸው? በረቱ ? " አለች፡፡ ሚጣ በጣም ደነገጠች ምትመልሰው መልስ አጣች፡፡ "ሴና እኔ መጣለው እየሄድሽ ጠብቂኝ" አለችኝ፡፡ ግራ ገባኝ የሆነ ነገር ውርር ሲያደርገኝ ይሰማኛል፡፡ እሺ ብዬ መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ትንሽ ከሄድኩኝ ብሀላ አንድ ጥግ ቆሜ ማጣን መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ሚጣና ልጅቱዋ ሚያወሩትን ባልሰማም ግን በደንብ ይታዩኛል፡፡ ሚጣ እያለቀሰች ነው፡፡ ከእጅ ቦርሳዋ ውስጥ ሶፍት አውጥታ እንባዋን ትጠራርጋለች፡፡ ቡዙ ቆመው ካወሩ ቡሀላ ሚጣ ወደኔ መጣች፡፡ በጣም ደንግጫለው ሚጣ አይኗ ቀልቶአል፡፡ ምን እንደሆነች ብጠይቃትም ምንም መልስ አትሰጠኝም አይኗን በሶፍት እየጠረገች ዶርም ደረስን፡፡
            ምን ተፈጥሮ እንደሆነ ስጠይቃት "ጎረቤት ለቅሶ ነበር አብሮ አደጋችን አርፎ ለቅሶ ላይ ነበር የቆየውት ሾለሹ ነው ያነሳችብኝ፡፡ "አለችኝ ሚጣ እንባዋን እያፈሰሰች፡፡ ደነገጥኩኝ! . . . እግሬ ተንቀጠቀጠ . . . ቅድም ልጅቷ "ወይዘሮ አዲስ በረቱ?" ያለችው ትዝ አለኝ፡፡ የሆነ ግዜ ፍሬ ስለቤተሰቦቹ ሲነግረኝ የእናቱ ስም አዲስ እንደሚባል ነግሮኝ ነበር፡፡ መናገር አቃተኝ የሙት የሙቴን "ፍሬስ?" አልኳት ሚጣን፡፡ "ፍሬ ምንም አልሆነም አለ" አለችኝ እያነባች፡፡ "ሚጣ አትዋሺኝ! ፍሬ የታለ? ስልኩን አያነሳ ! ግቢ አልመጣ ! ፍሬ ምን ሆኖ ነው! ሚጣ በፈጠረሽ አትዋሺኝ ፍሬ ምን ሆነ!?" የሚጣን ትከሻ ይዤ በጩኸት ጠየኩዋት፡፡" ፍሬ ምንም አልሆነም ተረጋጊ "አለችኝ ሚጣ ራሱዋን ለማረጋጋት እየሞከረች፡፡ "ሚጣ አትዋሺኝ የቅድሙዋን ልጅ ጠይቃታለው ፍሬ ምን ሆነ!? ሚጣ በምትወጂው ይሁንብሽ ! በፈጠረሽ ፍሬ ምን ሆኖአል?" እንባዬ መውረድ ጀመረ፡፡ መጠየቁ አልሆን ሲለኝ መለመን ጀመርኩ "ሚጣ ፍሬ የት ነው ያለው? ፍሬ ምን ሆኖ ነው የጠፋው?"
         "ሴና ፍሬ አርፎአል" አለችኝ ሚጣ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች፡፡ አላመንኩም በሁለት አጄ ጭምድድ አድርጌ የያዝኩትን የሚጣን ትከሻ ለቀኩት፡፡ ከዚሁ ብሀላ ማስታውሰው የሆነ ነገር ኩሀላ ጭንቅላቴን ሲመታው ነው . . .

.............ይቀጥላል............✍

5 months, 3 weeks ago

‍ ​​​?ሴና?

#ክፍል 3⃣5⃣

❤️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️?

. . . ዛሬም እንዳለፉት ቀናት የኪሩቤል ስልክ ነው የቀሰቀሰኝ፡፡ ቁርሳችንን ከበላን ብሀላ ትንሽ ተጨዋውተን ወደ ዶርሜ ተመለስኩ፡፡ ጉዋደኞቼ ይመጣሉ ፤ዶርሙን አስተካከልኩ፡፡ ዶርም እንደተቀመጥኩኝ ጉዋደኞቼ ደወሉልኝ፡፡ ሁሉም አንድ ቦታ ተገናኝተው ወደ ግቢ እየመጡ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ በጣም ደስ ቡሎኛል፡፡ ከዛሬ ቡሀላ ብቻዬን አላድርም ማለት ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ቀናት ሙሉ ሰአት አብሮኝ የነበረው ኪሩቤል ምንም ብቸኝነት እንዳይሰማኝ አድርጎኛል፡፡
               ድንገት የዶርሜ በር ተንኳኳ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከፈትኩት፡፡ በሩን ከፈት ከማድረጌ ሚጣ ፈገግ ብላ እያየችኝ በሩ ላይ ቆማለች፡፡ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ሁሉንም አንድ በአንድ አቅፌ ሰላም እያልኩኝ ወደ ውስጥ አስገባዋቸው፡፡ ገና እየመጣን ነው ያሉኝ ለካ ደርሰው ነው፡፡ እየተሳሳቅን እና እየተጨዋወትን ናፍቆታችንን እንገልፅ ጀመር፡፡ ሁሉም ስለደከማቸው ሻወር እንዲወስዱ ነግሬያቸው መጣው ብዬ ከዶርም ወጣው፡፡ ለኪሩቤል ደወልኩለት፡፡ የጠራሁት ቦታ መጣ፡፡ ጉዋደኞቼ ከመንገድ ስለመጡ ስለደከማቸው ከዶርም ከሚወጡ ምግብ እንድንገዛላቸው እኔ ቴካዌ አዝዤ ስለማላውቅ እንዲያጋዛኝ ነገርኩት፡፡ "አረ አንቺም ባትመጪ ብታዢኝ ይዤ መጣ ነበር ብር የለኝም እንጂ ፡፡ "አለኝ እየሳቀ፡፡ ገዛዝተን ከመጣን ቡሀላ ዶርም መግቢያ ድረስ ሸኝቶኝ ተመለሰ፡፡ ዶርም ስገባ ከ ሁለቱ በስተቀር ሌሎቹ ሻወር ሊወስዱ ወጥተዋል፡፡ ምግቡን ካቀራረብኩ ቡሀላ ሁሉም ሲመለሹ ተሰብስበን ምሳችንን በላን፡፡ ምናልባት ከደከማቸው ብዬ እንዳደረኩት ስለገባቸው በጣም አመሰገኑኝ፡፡
              ጨዋታችን ቀጠለ፡፡ ስለገጠመኞቻችን እያወራን መሳሳቅ ጀመርን፡፡ በመሀል ሾለ ፍሬ ጠየኩዋቸው፡፡ ሁሉም ዝም ዝም አሉ፡፡ "ምነው አግኝታቹት አታውቁም?" አልኩኝ ወደ ሚጣ እያየው፡፡ 'አረ ከዚ እንደሄድን እኮ በስንተኛው ቀን አጎቴጋር ምናምን ብሎ ወደ ባህርዳር ሄደ ከዛን ቡሀላ አንድ ቀን ነው እንዲሁ ለሰላምታ የተገናኘነው፡፡" አለችኝ፡፡ 'እና ለምንድነው ስልክ ማያነሳው?' አልኩኝ በድንገት ተናደድኩ፡፡ "የደወለልኝ ግዜ ስልኩን ሌላ ቦታ ረስቶት እንደሄደ እና ወደ ቤት ሲመለሾ በዛው ተቀብሎ እንደሚመጣ ነው የነገረኝ፡፡ የዛን ቀንም የደወለልኝ በሰው ስልክ ነበር፡፡ "አለችኝ፡፡ እንደመንተባተብ እያለች፡፡ ሌሎቹ እንዳለ ዝም ብለው ያዪኛል፡፡ ምክንያቱ ምንም አልተዋጠልኝም፡፡ ግን ምንም ማለት አልፈልግም በይሁንታ ራሴን ነቅንቄ ወደ ሌላ ጨዋታ ገባን፡፡ በመሀል ሾለ ኪሩቤል ማውራት ጀመርኩ፡፡ ከቀልዶቹ እያካፈልኩዋቸው ያደረግናቸውን ነገሮች እየነገርኳቸው ዶርሙን ሳቅ በሳቅ አደረግነው፡፡ እየተጫወትን ሳናስበው መሸ፡፡ መምሸቱንም ያወቅነው ኪሩቤል ሲደውል ነው፡፡
        "ዛሬ ቀጣሽኝ አይደል? አይ ሰው ገና ለገና ጉዋደኞቼ መጡ ብለሽ ነዋ? እሺ እራት አንበላም ወይስ እሱንም ቴካዌ ላስመጣላቹ?" አለኝ ገና ስልክ ከማንሳቴ፡፡ ጉዋደኞቼ እራት ወጥተን  እንድንበላ ስነግራቸው ተስማሙ፡፡ "እንደውም ጊቢውም ናፍቆናል እራት ብቻ ሳይሆን ጉብኝትም ጭምር ነው፡፡" እያሉ እየተሳሳቅን ልብሳችንን ቀያይረን ወጣን፡፡ ካፌ ስንደርስ ኪሩቤል በቁጥራችን ልክ ወንበር አስተካክሎ ጠበቀን፡፡ ከሁሉም ጋር ካስተዋወኩት ቡሀላ ሁላችንም ተቀመጥን፡፡ በኪሩቤል አቀባበል ሁሉም ተደስተዋል፡፡ ከግቢ ውጪ ሌላ ሆቴል ያለን ነው የመሰለን፡፡ እራት ከተመገብን ቡሀላ ጨዋታ ተጀመረ፡፡ ኪሩቤል አልተቻለም፡፡ ክብ ሰርተን ስንስቅ ካፌ ውስጥ ያሉት ተማሪዎች አይን በሙሉ እኛ ላይ ሆነ፡፡ በጣም ተጫወትን፡፡ ኪሩቤል ከጉዋደኞቼ ጋር በጣም ነው የተግባባው፡፡ ደስ የሚል ምሽትን አሳለፍን፡፡ ዶርም ከገባው ቡሀላ እንደለመድኩት ከኪሩቤል ጋር በስልክ አወራና እስቅ ጀመር፡፡ በድምፅ ካወራን ቡሀላ በፅሁፍ ማውራት ቀጠልን፡፡ አሁንም ግን የፍሬን ስልክ ሞክራለው፡፡ ይጠራል . . . አይነሳም፡፡ ጉዋደኞቼ ሁሉም ተኝተዋል፡፡ እኔ ግን በፍሬ ትዝታውስጥ ኪሩቤልን

.............ይቀጥላል............✍

5 months, 3 weeks ago

‍ ​​​​?ሴና?

#ክፍል 3⃣2⃣

♥ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ❤️

. . . ልክ ዶርም እንደደረስኩ በሩን ልከፍተው ስል ቁልፍ ነው፡፡ ማንም የለም ማለት ነው፡፡ የኔን ቁልፍ አውጥቼ በሩን ከፍቼ ገባው፡፡ ዶርሙ ያኔ ስንሄድ ትተነው እንደሄድነው ነው፡፡ ደነገጥኩኝ! ማንም አልመጣም ማለት ነው? ቦርሳዬን ካስቀመጥኩ ቡሀላ ስልኬን አውጥቼ ለሚጣ ደወልኩላት፡፡ ስለተነፋፈቅን ብዙ አወራን፡፡ ሰሞኑኑን ስልኬ ተበላሽቶ እንደተዘጋ እና አሁን ዶርም እንደሆንኩ ስነግራት ብዙ ቀን ደውለው እንዳጡኝ ነግራኝ" ምዝገባ ሀሙስ ስለሆነ እሮብ እንግባ ተባብለን ነው " አለችኝ፡፡ በጣም ተበሳጨው፡፡ ግን ወደቤት ከምመለስ ሁለት ቀን ዶርም ብቻዬን ባድር ይሻለኛል ብዬ ወሰንኩ፡፡
              አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ለፍሬ ደወልኩለት ፤አያነሳም፡፡ ደጋገምኩ መልስ የለም፡፡ ለ ዴቭ ደወልኩለት ገና ከማንሳቱ በወሬው ሳስቀኝ ጀመር፡፡ በመደወሌ በጣም ነው የተገረመው፡፡ ትንሽ ካወራውት ብሀላ ሾለ ፍሬ ጠየኩት፡፡እሱ ሀዋሳ እንዳለና ፍሬን በስልክ እንጂ በአካል እንዳላገኘው ነገረኝ፡፡ ለመጨረሻ ግዜ ከሰአታት በፊት መደዋወላቸውን ገልፆ ደህና እንደሆነ ሲነግረኝ ተረጋጋው፡፡ ጊቢ ከመጣ እንዲደውልልኝ ነግሬው ስልኩን ዘጋውት፡፡
             ዶርም ውስጥ ብቻዬን መቀመጡ ሲጨንቀኝ ራሴን ዘና ለማድረግ ወደ ካፌ ሄጄ ሻይ እየጠጣው ቲቪ ማየት ጀመርኩ፡፡ ካፌው ውስጥ ብቻዬን የተቀመጥኩት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ከአንድ ጥግ ተቀምጬ ቲቪ እያየው ሻይ ጠጣለው፡፡ በመሀል በመሀል ስልኬን እያነሳው ለፍሬ ደውላለው፡፡ አሁንም አያነሳም፡፡ምናልባት ሾል ላይ ይሆናል ስል አሰብኩ፡፡ስልኬን አስቀምጬ ቲቪውን መመልከቴን ቀጠልኩ፡፡ ብቻዬን ቁጭ በማለቴ ጨንቆኛል፡፡ ግን ዶርም ገብቼ ከምተኛ አዚህ ብቀመጥ ይሻለኛል ስል አሰብኩ፡፡
            ቲቪውን እየተመለከትኩ ድንገት "ቲቪ ውስጥ ማንን እየፈለግሽ ነው? እንደዚ ያፈጠጥሽበት?" አለኝ አንድ ወንድ አጠገቤ ቆሞ፡፡ ቀና ብዬ አየውት፡፡ ምንም መልስ ሳልሰጠው አይኔን ወደ ቲቪው መለስኩኝ፡፡ " ከቅድም ጀምሮ እያየውሽ ነበር ብቻሽን ሆነሽ የቀጠርሽው ወይ የቀጠርሻት አሊያም የቀጠርሻቸው ቀሩ መሰለኝ፡፡ ቅር ካላለሽ ልቀመጥ? እኔም የቀጠርኳት ቀርታ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ከምቆዝም ይሻላል" አለኝ አጠገቤ እንደቆመ፡፡ በእርግጥ ለኔም ብቻዬን ከመቀመጡ የተሻለ ነው፡፡ "እና ለምን ቆምክ አትቀመጥም?" አልኩት፡፡ "አረ ሳላስፈቅድ የመቀመጥ ልምዱም ስርአቱም ድፍረቱም ወጉም የለኝም፡፡ አስፈቅዶ በመቀመጥ አንቱታን ያተረፍኩ ተቀማጭ ነኝ፡፡ የቱጋ ልቀመጥ ታዲያ አንቺ የመረጥሽልኝ ወንበር ይመቸኛል?" አለኝ ፈገግ እያለ፡፡ ንግግሩ አዝናንቶኛል፡፡ የፈለከው አልኩት ፈገግታዬን ሳልደብቅ፡፡ ፈገግ ስል ይበልጥ ቀለል አለው መሰለኝ ከፊት ለፊቴ ያለውን ወንበር እየሳበ ወሬውን ካቆመበት ቀጠለ፡፡
             "እናም እልሻለው ባትመጪም ቅጠሪኝ ብያት ላትመጣ ቀጥራኝ ይኸው ጠብቃታለው " አለኝ ወንበሩ ላይ ተስተካክሎ እየተቀመጠ፡፡ ታሪኩን ከመሀል ጀምሮ መሀል ላይ አቆመው፡፡ ምንም አላልኩትም ፈገግ ብዬ ተቀበልኩት፡፡ "ኪሩቤል እባላለው "አለኝ ቀኝ እጁን እየዘረጋልኝ፡፡ "ሴና እባላለው "አልኩት እየጨበጥኩት፡፡ ጠይም ረዘም ያለ ተጫዋች ቆንጅዬ ነገር ነው፡፡ ገና ከመምጣቱ ጀምሮ ፈገግታ ከፊቱ አልተለየውም፡፡
             ከኪሩቤል ጋር ብዙ ተጨዋወትን፡፡ እሱ እየተናገረ እኔ እያዳመጥኩ አልፎ አልፎ እኔም እየተናገርኩ እየተሳሳቅን ሳናስበው ብዙ ቆየን፡፡ ምሳ ሰአት ሲደርስ ኪሩቤል የእጅ ሰአቱን ከተመለከተ ብሀላ "ካፌ ሳይዘጋ ልሂድ ምሳ ትሄጃለሽ ወይስ እዚ ነሽ?" አለኝ፡፡ አይ እኔ እዚሁ ነኝ አልኩት፡፡ "እንደዛ ከሆነ በቃ እዚሁ በላለው" አለኝ "እንዴ ታዲያ ለምን መጀመሪያ ልሂድ አልክ?" ስለው "አይ ምሳ እዚ ልብላ ምናምን ስል ጉራ እንዳይመስል ነው ለዛሬ እዚ ለመብላት ሚሆን አላጣም" ብሎ ከኪሱ ብዙ ዝርዝር ብር አወጣ፡፡ ነገረ ስራው አሳቀኝ፡፡ "አትሳቂ ይደርስብሻል እኔም ደርሶብኝ ነው" አለኝ ከሌላኛው ኪሱም ዝርዝር ሳንቲም እያወጣ፡፡ "ምንድነው የደረሰብክ?" አልኩት ሳቂን በግድ እያፈንኩ፡፡ "ብዙ ብር የያዝኩ እንዲመስለኝ ከቤት የተሰጠኝን 100ብሩ በሳንቲም እና በአንዳንድ ብር ዘርዝሬ ነው" አለኝ ጠረቤዛላይ የዘረገፈውን ሳንቲም እያስተካከለ፡፡ ከዚ በላይ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ . . .ለቀኩት 'ይሄሁሉ 100ብር ነው? አልኩት፡፡ አዎ አለኝ በጭንቅላቱ አነቃንቆ፡፡ ሳንቲሙን አስተካክሎ ከጨረሰ ብሀላ ወደ ኪሱ እየመለሰ "በቃ አንዳንድ ምግብ አዘን በአንድ ላይ አድርገን እንብላ ?" አለኝ ፈገግታ በማይለየው ፊቱ፡፡ እኔ ሳቅ በሳቅ ሆኛለው . . .

.............ይቀጥላል............✍

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana