ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 days, 23 hours ago
Last updated 4 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 2 days ago
አሳዛኝ ዜና‼️
በትግራይ ክልል ላዕላይ ማይጨው ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በትግራይ ክልል ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ዱራ በተባለው አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ።በትራፊክ አደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ስምንት ሰዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው።አደጋው ከሽረ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሃይሩፍ ተሸከርካሪ ከሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ መሆኑን የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።አደጋው ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ በማሽከርከር የተከሰተ እንደሆነም የፖሊስ መረጃ ያመላክታል። አሽከርካሪዎች ከዚህ አደጋ ትምህርት በመውሰድ ፍጥነት በመቀነስ በሰው ህይወት እና ንብራት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቀነሱ የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ምንጭ: ፋና
@realkana
በድሬዳዋ በችኩንጉኒያ ወረርሽኝ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ማሻቀቡ ተገለጸ፡፡
ችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ኤደስ በምትባል ትንኝ ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ችኩንጉኒያ በሚባል ቫይረስ የሚመጣ ህመም ነው፡፡የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ከሀምሌ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ የተከሰቱ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥር ባሳለፍነው ሳምንት ከደረሰበት 15 ሺህ አሁን ላይ ወደ 20 ሺህ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ህብረትሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡በወረሽኙ እስከ አሁን ድረስ የሞተ ሰው አለመኖሩንም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል። እስካሁን በተደረገ የቤት ለቤት አሰሳ 86 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች ወረርሽኙን የሚያስተላልፈው ትንኝ እጭ እንደተገኝባቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቃል፡፡
ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች የተውጣጣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን በቦታው በመገኘት የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡ወረርሽኙን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር በከንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃል ተቋቁሞ በቅንጅት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ የቤት ለቤት ርጭት፣ የቅኝት እና አሰሳ ስራዎች፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ የህክምና አገልግሎት በሁሉም ጤና ተቋማቶች እየተከናወኑ እንደሆነ ተገልጿል።ማህበረሰቡ ከበሽታው እራሱን መከላከል እንዲችል ለሃይማኖት አባቶች፣አመራሮች፣ለማህበረሰብ መሪዎች እንዲሁም ለብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ለ125 ሰዎች ስልጠና መሰጠቱንም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡
ምንጭ: Ethio FM
@realkana
የወላይታ ሕዝብ ላቀረበው ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ወሕዴግ/ ዛሬ ጠየቀ። የግንባሩ ኃላፊዎች በጋዜጣዊ መግለጫቸው «ለጥያቄያችን ሕገመንግሥታዊ ምላሽ እንሻለን ወታደራዊ የእዝ ጣቢያ፣ ኮማንድ ፖስት ከወላይታ እና አካባቢዋም ይነሳ» ሲሉ ሳስበዋል። «ገዢው ፓርቲ የችግር ምንጭ እየሆነ በሌላው ላይ ጣት የመቀሰር አዝማሚያ ያሳያል» ሲሉም ወቅሰዋል። «የክልሉ ገዢ ፓርቲ ደኢሕዴን የዜጎች ሃሳባቸውን የማንሸራረሸር መብት ከመገደብ ይቆጠብ፣ ከሕገ መንግሥቱ ውጪ ጥናት ነው እየተባለ በቀረበው ሃሳብ ሕዝቡን በአስገዳጅ ከማወያየት ይቆጠብልን» ብሏል። በወላይታ እና አካባቢዋ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባስቸኳይ እንዲነሳም ጠይቋል። ምክትል ሊ/መንበሩ አቶ ብስራት ኤሊያስ ፤ «በሕገ መንግሥታዊ መብቱ መሠረት ከ1,5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ክልል ይገባኛል ብሎ ላቀረበው ጥያቄ፤ አይገባህም የለም ተሳስተሃል ብሎ እንደገና ጥናት በማካሄድ ፤ ክልል መሆን አይፈቀድልህም የማለት ያህል ነው» ሲሉም ተችተዋል። ሊ/መንበሩ አቶ ተክሌ ቦረና በበኩላቸው ስለሐዋሳ ጉዳይ ከዶቼ ቬለ DW ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ «እስካሁን ድረስ የምናውቀው በሐዋሳ ታሪክ፤ ሐዋሳን እንደ ሐዋሳ ስንመለከት፣ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ሆና የቆየች ከተማ ነች። ብዙ ሕዝቦች የተሰባሰቡባት ከተማ ነች። እንደግለሰብ ወይም እንደ ድርጅት አስተያየትም ሐዋሳ የጋራ ከተማ ሆና እንድታገለግል ነው እኛ ሃሳባችን።» ብለዋል። ከሁሉም የተውጣጡ ሰዎች በከተማው ምክር ቤት እና በከተማዋ መዋቅሮች ውስጥ ተሰልፈው የሚያስተዳድሯት እንድትሆን እንደሚያስቡ በማመልከትምም፤ የወላይታ የክልልነት ጥያቄ የቆየ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
Via DW
የሱማሊያ መንግሥት የጁባላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ጸጥታ ሚንስትርን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የሞቃዲሾው ዳልሳን ሬዲዮ ዘግቧል፡፡ ሃላፊው አብዲረሽድ ጀናን ትናንት የታሰሩት ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ ሲሉ ነው፡፡ መንግሥት በጌዶና አጎራባች ክልሎች በተፈጸሙ ወንጀሎች እጠረጥራቸዋለሁ ብሏል፡፡ ራስ ገዟ በቅርቡ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካካሄደች ወዲህ፣ ከሞቃዲሾ ጋር ውጥረቱ ተባብሷል፡፡
-Wazema Radio
@realkana
ከጳጉሜ 1 እስከ 6 ለ1 ሺሕ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ከጳጉሜ 1 እስከ 6/2011 ”ጳጉሜን ለጤና” በሚል መሪ ቃል ለ1 ሽሕ ሰዎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል። በውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል የሚሰጠው ነፃ የምርመራና የሕክምና አገልግሎት አጠቃላይ የውስጥ ደዌን ጨምሮ የአንገት ፣ የጉበት፣ የካንሰር፣ የጨጓራ፣ የልብና ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
የኮሌራ በሽታ በሶስት ክልሎች ላይ በድጋሚ ተከስቷል ተባለ፡፡
በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የኮሌራ ወረርሽኝ በአብዛኛው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በሶስት ክልሎች ላይ በሽታው ተከስቷል ተባለ፡፡
በአሁን ወቅት ወረርሽኙ በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ወረዳ 15 ሰዎች በፈዲስ ወረዳ 20 ሰዎች፣ ሀረሪ ክልል በ6 ወረዳዎች 15 ሰዎች ተይዘዋል ተብሏል።
እንዲሁም በደቡብ ክልል በሃዋሳ ከተማ 14 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተገልጿል።
በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ከወራት በፊት በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 19 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ማህበረሰቡ በዚህ ሳይዘናጋ አሁንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አስጠንቅቋል፡፡
Via:- Ethio FM
@realkana
⚽️ጨዋታው 3 ለ1 ተጠናቀቀ
አዛም ፋሲል ከነማን 3 ለ1 አሸንፏል።⚽️
በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የታንዛንያው አዛምን ከሜዳው ውጭ የገጠመው የኢትዮጵያው ፋሲል ከነማ 3 ለ1 ተሸንፏል።በድምር ውጤትም 3-2 በመሸነፉ ፋሲል ከነማ ወደ ተከታዩ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል።
Via Walta
@realkana
አሳዛኝ ዜና!
የቀድሞ ኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ተስፋዬ ገ/ኢየሱስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ተስፋዬ ገ/ኢየሱስ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽንንም በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል፡፡
የቀድሞ ኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ተስፋዬ ገ/ኢየሱስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ተስፋዬ ገብረየሱስ በስድስት የአፍሪካ ዋንጫዎች፣ በአንድ የዓለም ዋንጫ ላይ የዳኙ ታላቅ ዳኛ የነበሩ ሲሆን በ1980 የተደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜንም በመሐል ዳኝነት መርተዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው በአስመራ ከተማ በነገው ዕለት የሚፈፀም ይሆናል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
Via #FBC
@realkana1
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ አመት የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሠባ በኢትዮጵያ ምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን ለማሻሻል እየመረመረ ነው።
የምክር ቤቱ የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን አቅርቧል።የአዋጁ ሥያሜም የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ በሚል ተስተካክሏል ተብሏል።
ከአምደ ወርቅ ተከዜ የተገነባው የ48 ኪ/ሜ መንገድ በርእሰመስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተመርቀ።
መንገዱ ከ2006 ጀምሮ በ 146 ሚሊየንብር የተሠራ ሲሆን በአከባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የጎላ ሚና እንደሚኖረው በአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ የተመረቀው መንገድ ታምኖበታል።
መንገዱ ዋግኽምራ እና የደጎንደርን ዞኖች የሚያስተሳስር ነው።የዋግ አካባቢ የእንስሳት እና የማር ምርትን፣ ከደቡብ ጎንደር ደግሞ የሠብል ምርትን በማገበያየት ህብረተሰቡን በንግድ የሚያስተሳስር ነው።መንገዱ ከእብናት አምደወርቅ ከተያዘው የመንገድ ፕሮጀክት 90ኪሜ አካል ሲሆን በአጠቃላይ ግንባታው የፈጀው ገንዘብ መጠን 276 ሚሊየን ብር ነው። ግንባታው አራት አመታትን የፈጀው ከእብናት ተከዜ የተገነባው መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆኖ የቆየ ነው።
Via EBC
@realkana
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 days, 23 hours ago
Last updated 4 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 2 days ago