ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ወርሃዊ የጾም ጸሎት ፕሮግራም
ከነገ ጥር 19 - 23/2017 ዓ.ም ድረስ
ከሰኞ - ዓርብ
ጠዋት ከ3:00 - 7:00
ከሰዓት ከ10:00 - 1:30 ይሆናል።
በፀጋ ድናችኋል።
በዶክተር እንዳለ ሰብስቤ
በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ጥር 18/2017 ዓ.ም እሁድ ጥዋት በሁለት ፈረቃ የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም
በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት ዶክተር እንዳለ ሰብስቤ ኤፌሶን 2፡1-10 ላይ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቃል መሰረት በማድረግ "በፀጋ ድናችኋል " በሚል ርዕስ ባለፈው ሳምንት ካስተማሩት ትምህርት የቀጠለውን የትምህርት ክፍል ቀጥለው በቀረቡት ነጥቦች ላይ አስተምረዋል።
"ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥"(ኤፌ 2:4-5)።
ፀጋ የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ምህረትናፍቅር ማለት ነው። ምህረት ማለት ይቅርታ ማለት ብቻ አይደለም፤ በችግር ውስጥ ችግረኛውን በፍቅር ለመርዳትና ችግሩን ለመፍታት ጣልቃ መግባት ማለት ነው።
ፍቅር የሚለው ቃል በእግዚአብሔር አተረጓጎም እንደ ሰው ፍቅር ስሜት ማለት አይደለም፤ ትእዛዝ ነው። ይህም ትዕዛዝ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍሰ በፍጹም ሃይልህ ውደድ የሚል ትእዛዝ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ስንል እግዚአብሔር የሚያደርጋቸው መልካም ነገሮች ማለት ነው። ጌታችን በመስቀል ላይ ሲሞት ፍቅሩን በተግባር በድርጊት ነው የገለጠው።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ችግራችን ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ከገባንበት ማቅ፣ ችግር ውስጥ ነፃ ለማውጣት ነው።
በፀጋ ድናችኋልና... ይህ ጸጋ ምንድነው ያደረገልን?
1. ከክርስቶስ ጋር ህይወት ሰጠን።
ሰጠን/መስጠት የሚለው ቃል ከመቀበል ያልፋ። ሕያው መሆን፣ ሕያው ማደረግ ማለት ነው። የአዳም ስራ የሰውን ልጆች ከእግዚአብሔር የተለዩ ሙታን አመፀኞች የማይታዘዙ አደረገ። በራሳቸው ሃሳብና ስሜት፣ በራሳቸው መንግስት የሚኖሩ ቁጠኞች አደረጋቸው። ይህ የአዳም መንግስት ስርዓት ነው። በክርስቶስ ስራ ግን ከነበርንበት የሀጥያት ማንነት አውጥቶ ህይወትን ሰጠን። ህያው አደረገን።
የማንነት ለውጥ ነው የተሰጠን። በፊት ከአዳም ጋር የሞትን ሰዎች ነበርን። አሁን ግን ከክርስቶስ ጋር ህያው ሆነናል። የኢየሱስ ማንነት ነው የተሰጠን። የህይወት ለውጥ፣ የማንነት ለውጥን ነው ያደረግነው። ስለዚህ ሙታን ነበራችሁ ግን ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጣችሁ ማለት ከነበርንበት የህይወት ስርዓት እና ድሮ ከነበረን ማንነት ወጥተን ሌላ ማንነት መልበስ ማለት ነው። ድሮ ሙታን ነበራችሁ፤ አሁን ግን ህያዋን ሆናቹሃል ነው የሚለን።
2.ከሞት አስነሳን/ ትንሳኤ ሆነልን።
ትንሳኤ በሞት ላይ የተገኘ የመጀመሪያ ድል(ማሸነፍ) ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነሳ የማይበሰብሰውን እንደገና ሊሞት የማይችለውን አዲስ አካልና አዲስ ማንነት ነው ይዞው የተነሳው። ሲነሳ የሞት ጉልበት ነው የተሰበረው።
ይህ የትንሳኤ ህይወት የማይጠፋ፣ የማይበሰብስ ሆኖ የሚቀር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ይህ ትንሣኤ አሁን እንደተካሄደ ነው። በእርግጥ ይህ ሰጋችን የሚለወጥበት የመጨረሻው ትንሳኤ አለ። አሁን ግን እኛ በእግዚአብሔር አይን ከክርስቶስ ጋር ተነስተናል፤ ሞትን ድል አድርገናል። ሞት ማለት በዳቢሎስና በአዳም ስርዓት ውስጥ መያዝ ማለት ነው። አሁን ግን እኛ ህያዋን ሆነናል ማለት ከእነዚህ ሁሉ ስርዓቶችና ከስጋችን ሐሳብና ፍቃድ ወጥተን አሸንፈናል(ሮሜ 6:7-11)።
ይህንን አካል ግን የሞት ስርዓት፣ የሞት ባህል፣ ሞት የሚያደርገው አካላዊ ሆነ መንፈሳዊ ነገር አይገዛውም። ምክንያቱም ትንሳኤን አግኝቷል። ስለዚህ ትንሳኤ ማለት ከዚህ በኋላ የአዳምና የሰይጣን ስርአት የአመፃ ልጆች መንግስት አይገዛኝም ማለት ነው። ጳውሎስ በኤፌሶን 1:10 ላይ ስለ እግዚአብሄር አንዱ መንፈሳዊ እቅድ ሲናገር ሁሉንም አለም በላይ ያሉትን ሁሉ ከክርስቶስ እግር ስር ማስገዛት ነው። ስሜት ቢሆን፣ ፍቃድ ቢሆን፣ በአየሩ ላይ ያለው አለቃ ቢሆን፣ የዚህ የዓለም ኑሮ ቢሆን፣ መበስበስ ቢሆን፣ መጥፋት እና መሞት ቢሆን፣ ይህንን ሁሉ ለክርስቶስ ማስገዛት ነው።
እኛ ከክርስቶስ ጋር ከተነሳን ሞት አይገዛንም። በየለቱ የሚከታተለን የሚገዳደረን ሃጥያት አይገዛንም። እንደ እግዚአብሄር ቃል ያልሆነ ስርዓት፣ ባህል፣ ወግ፣ አስተሳሰብ፣ ስሜት፣ ፈቃድ አዳም የፈበረካቸውና የሰው ልጅ ሊኖርበት የሚታገልበት የትኛውም ነገር አይገዛንም። ጸጋ ማለት ድናችዃል ከእግዚአብሔር ይቅርታን ተቀብለናል ማለት ብቻ አይደለም፤ ሰዎች ራሳቸው ከገነቡት፤ ዲያቢሎስ ከሚገዛው መንግስት በክርስቶስ መስዋዕትነት ነፃ ወጥተዋል ማለት ነው።
3. ከክርስቶስ ጋር በቀኙ ተቀመጠን
በቀኝ መቀመጥ ማለት ስልጣንን ማግኘት ማለት ነው። የክርስትና ትልቁ መገለጥ ትንሳኤው ነው። የእግዚብሔርን የሀይሉ ችሎት፣ ታላቅነቱን የምናየው በክርስቶስ ትንሳኤ በኩል ነው። ከሙታን ሲያስነሳው ብቻም ሳይሆን አስነስቶ ከአለቆች ከስልጣናት ከሀይላት ሊመጣ ካለው ገና ወደፊት ሊሰየሙ የሚችሉ ስሞች በላይ የሆነን ስም ሰጥቶት በቀኙ ሲያስቀምጠው ነው።
ለመሆኑ ጌታችን አየሱስ ክርስቶስ ቀድሞ ክብር አልነበረውም ነበር? ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ 28 ላይ ስልጣን በሰማይና በምድር ተሰጠኛ አለ። ታዲያ እንደ አምላክነቱ ስልጣን ቀድሞ አልነረውም? ስልጣን በሰማይና በምድር ተሰጠኝ ሲል የተሰጠው ስልጣን መሲሃዊ ስልጣን ነው። በዚህ ስልጣን የሰውን ልጆች ለማዳን እስከመስቀል ሞት ድረስ ሄዷል። ልጆቹን ለማዳን ስቃይ ውስጥ አልፏል። አሁን ግን በመስቀል ላይ ያንን ዋጋ ከፍሎ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ነገር፤ የሰው ልጆች ከቸግራቸው ለማውጣት የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ በአብ ቀኝ ተቀምጧል።
በክርስቶስ ኢየሱስ የተሰራውን አስገራሚውን ስልጣን መረዳት የህይወት አቅጣጫን ይቀይራል። ሐዋሪያው ጳውሎስ ከተገዢነት አለም ገዢ ወደምትሆኑበት አለም ገብታችኋል ነው የሚለን። እግዚአብሔርን መውደድ ማለት አመፃን መጥላት ማለት ነው። እግዚአብሔር በዚህች አለም ላይ ስልጣን ሰጥቶናል። በኃጢአት ላይ፣ በአመፅ ላይ የምናሸንፍበት አለም ሰጥቶናል። (ኤፌ 6:11)
4.አዲስ ፍጥረት አድርጎናል(ኤፌ 2:10)።
እግዚአብሔር በአዳም በኩል የመጀመሪያውን ፍጥረትን ፈጥሯል። አሁን ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ አዲስ ፍጥረት ፈጥሯል። ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ተሠርተናል ማለት ነው። ወደ መኖር መምጣት ብቻ ሳይሆን እንደ አዲስ ተቀርፀናል።
እግዚአብሔር ለራሱ ክብር መኖር እንድንችል፤ የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን መልክ እንድንመስል አስቦ አሰማምሮ በክርስቶስ ኢየሱስ ፈጠረን። የተፈጠርነው ለመልካም ስራ ነው። ይህ መልካም ስራ የሙታን ስራ ተቃራኒ ነው። የዚህ መልካም ስራ አለቃው ክርስቶስ ነው።
Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa
የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ጥር 18 /2017 ዓ.ም
2. የመንፈስ አለቃ አለ(ኤፌ 2-2)
ይህ አለቃ እርሱም ዲያቢሎስ ነው። በዚህ ዓለም ውስጥ የመንፈስ አለቃ በአየሩ ላ፣ በሰው ልብ ውስጥም አለ። አለም ባዶና ቀላል ነገር አይደለም። መንፈሳዊ አለቃ አለው። የአዳም መንግስት ብጥብጥና ችግር ያለበት የጨለማ ህይወት ነው።
ይህ የመንፈስ አለቃ በማይታዘዙ ሰዎች ላይ ይሰራል። እነርሱም የአዳም መንግስት ልጆች ናቸው። በአዳም መንግስት ውስጥ ያሉ እግዚአብሔር የለሽ የሆኑ ሰዎች ብቻቸውን አይደሉም። የክፉ መንፈስ አለ።
3.የስጋችንና የልቦናችን ፍላጎት
ልቦና ማለት አዕምሮ አስተሳሰብ ማለት ነው። አዳም ይህንን ዓለም ሲያቋቁም የራሱን አስተሳሰብ እና አመለካከት መስርቷል። አምላክ አዞትና ፈልጎ የፈጠረው ዓለም ሳይሆን በሰው ልጅ ፈቃድ የተመሰረተ ዕርኩሰት የሞላበት የሃጥያት አለም ነው። ስለዚህ ጳውሎስ ሲናገር የታሰርን ነን ይላል።
አዳም ተስፋን ሊሰጠን ይችላል። ይህንን አደርጋለሁ ብሎ ህግን ያወጣል፤ ነገር ግን መፍትሄው ራሱ መልሶ ያጠፋናል። እንከን የሌለበትን ስራ የሚሰራው እና መፍትሔን የሚሰጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
2. የቁጣ ልጆች ነበርን
ከዚህ ቁጣ ማን ያወጣናል? በኤፌሶን 2:4-5 ላይ "ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና" ይላል።
አዳም ሞትን፣ አሮጌ መንግስትን ሰጠን። ስንወለድ በአዳም ከተማ፣ ስርዓት፣ ባህል ውስጥ ነው የምንወለደው። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ህይወትን ሰጠን። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደሚገዛው አዲስ ህይወት፣ መንግስት ገባን(ሮሜ 6፤ ቆላ 1:13-14)።
ማጠቃለያ
ይህንን የክርስቶስ ህይወት ተቀብለናል? ወይስ አሁንም በራሳችን መንግስት ስር እየኖርን ነው የምንገኘው? በአዳም ህይወት እና ስርዐት ውስጥ መልፋት ምንም ትርፍ የለውም። በአዳም ስርዓት ውስጥ እንደገና ምንወድቅበትን ህይወት አይደለም እግዚአብሄር የሰጠን። የማይጠፋ፣ የማይበሰብስ፣ አዲስ ስርዓት ነው የተሰጠን። ይህም ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ሆኖ የሚኖርበት መንግስት ነው።
እንደማንኛውም በአለም ውስጥ እንዳለ ሰው ልንኖር እንችላለን፤ ነገር ግን የሚገዛን ክርስቶስ ነው። ራሳችንን፤ ቤተሰባችን፣ ትዳራችንን፣ ለዕርሱ እያስገዛን ልንኖር ይገባል። የራሳችንን ኑሮ በራሳችን ለመኖር አንጣር በጸጋው ድነናል። ወደ እግዚአብሔር መንግስት ፈልሰናል። በነጻ የህይወት ተቀብለናል። ይህ ሁሉ በአንዱ መታዘዝ ሆኖልናል።
Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa
የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ጥር 11 /2017 ዓ.ም
በፀጋ ድናችኋል።
በዶክተር እንዳለ ሰብስቤ
በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ጥር 11/2017 ዓ.ም እሁድ ጥዋት በሁለት ፈረቃ የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም
በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት ዶክተር እንዳለ ሰብስቤ ኤፌሶን 2፡1-10 ላይ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቃል መሰረት በማድረግ "በፀጋ ድናችኋል " በሚል ርዕስ ቀጥለው በቀረቡት ነጥቦች ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።
የኤፌሶን መጽሐፍ ፀሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ መጽሐፍ ለአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የተጻፈ ሳይሆን ለኤፌሶን ሰዎች ደግሞም በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ምዕመናን ሁሉ የተፃፈ ነው። ምእመን የሚለው ቃል በእምነታቸው የፀኑ፤ ለእግዚአብሔር የታመኑ፤ እንዲሁም የታመኑ የክርስቶስ ደቀ መዝሙሮች ወይም ተከታዮች ማለት ነው።
በዚህ መፅሐፍ የመጀመሪያዋቹ ምዕራፍ ላይ መለኮታዊና መሰረታዊ ጥልቅ የሆኑ የክርስቶስን ስራ እና ይህንን ያመኑ ሰዎች በማመናቸው ምክንያት ያገኙትን ህይወት የሚያስረዳ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከአይሁድና ከአህዛብ አንድ አዲስ ሰውን እንዴት እንደፈጠረ የሚያብራራ መልእክት ነው። ቀጣዮቹ ምዕራፎች ደግሞ ስለ አገልግሎትና በዕለት ተዕለት ሂወታችን እንዴት መኖር እንደሚገባን የሚያሳዩ ናቸው።
ሐዋሪያው ጳውሎስ በምዕራፍ 1 በሰማያዊ ስፍራ ተባርካችዋል ይለናል። የተባረክንበትን በረከት በመንፈስ ቅዱስ በመታተማችንን፣ በኛ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ባለቤትነት ከነገረን በሁዋላ ግን አንድ ነገር ይጎድላችኋል ይለናል። እሱም የጥበብና የእውቀት መንፈስ ነው፤ ስለዚህም እንድታገኙት እጸልይላቸዋለሁ ይላል።
ክርስቲያኖች ምንም እንኳን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው ቢታተሙም የእውቀት ክፍተት ሊፈጠር ወይም ሊኖር እንደሚችል ይህ ክፍል ያሳየናል። ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስላመነ የጥበብ እና የዕውቀትን መንፈስ ወዲያዉኑ ይቀበላል ማለት አይደለም። በቅስፈት ቢቀበል ኖሮ ጳውሎስ እጸልይላችኋለሁ አይልም ነበ፤ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያንም አያሳስባትም ነበር፤ ስለዚህ አንድ ክፍተት አለ ማለት ነው፤ እርሱም የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ ነው(ኤፌ 1:17-19)።
ክርስትያኖች ይህ በህይወታችሁ ሲሆን የሃይሉን ታላቅነት እና የዕርስቱን ባለጠግነት ታውቃላችሁ። እነዚህን ሁለት ነገሮች ስታውቁ ክርስትናን መኖር ትጀምራላችሁ። እነዚህን ነገሮች እንድታውቁ የሚያደርገው የክርስቶስ ድል ነሺነትና የበላይ መሪነት ነው።
የቤተክርስቲያን ሙላት የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? ምን ችግር ነበረ? ለምንድነው እንደገና ክርስቶስ ያስፈለገው? ለምንድነው በጸጋ መዳን ያስፈልገው? ስንል ጳውሎስ እንደገና ወደ ምዕራፍ ሁለት ይመልሰናል። ከሰው ልጅ አቅም በላይ የሆነ ከፍተኛ ችግር ነበር፤ እርሱም በደል እና ሀጥያት ነው።
የሰው ልጆች በራሳቸው ኃይል ጥበብ ችሎታ እና እውቀት ሊፈቱት ማይችሉት የኃጢአት መአት ውስጥ ገብተው ወድቀዋል። ከዚህ ውድቀት ሊያወጣቸው የሚችል ማንም የለም። በዚህም በኤፌሶን መልዕክት የሰው ልጅ በራሱ ኃይልና ችሎታ ከዚህ መዓት መውጣት እንደማይችል ያስረዳል። ይህንን ካልተረዳን የድህነትን ጥልቅ ዋጋ ልንረዳ አንችልም።
ሐዋሪያው ጳውሎስ መጀመሪያ የችግራቸውን ምንጭ እና ጥልቀት ያሳያቸዋል። በኤፌሶን ምዕራፍ 2:1:10 የተፃፈው መልዕክት ጳውሎስ በሮሜ ምዕራፍ 1-16 የፃፈውን ጨምቆ ያስረዳበት ክፍል ነው ተብሎ ይታሰባል።
ሰለዚህ እኛም ችግራችንን እስቲ እንመልከት። ምን ችግር ነበረብን? ከምን ውስጥ ወጣን? ከኛ ምን አይነት ሕይወት ይጠበቃል? ምን አይነት ችግሮች ነበሩብን
1.ሞት ነው
“በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው” (ኤፌሶን 2፥1-2)። የሞተ ሰው እንዴት ይመላለሳል? ብዙዎችችን እንደምናስበው ሞት የሚለው ትርጉም በድን፣ ምላሽ የማይሰጥ፣ ሙት እንደማለት ነው። እዚህ ክፍል ላይ ግን የሞተ ሰው የሚመላለስ የሚንቀሳቀስ ነው ይለናል። መመላለስ ማለት መኖር ማለት ነው።
ሞት የሚለውን ጽንሰ ሀሳብን እራሱ እግዚአብሔር ነው ያስተዋወቀው። ለአዳም መልካም እና ክፉውን የምታስታወቀውን ዛፍ ከበላህ ትሞታለህ ያለው ራሱ እግዚአብሔር ነው። አዳም ፍሬዋን በበላ በዛው ሰዓት አልሞተም። እንደውም ከእግዚአብሔር ጋር ለምን በላህ? እንዴት በላህ? ማን ነው ያበላህ? እየተባባሉ ይነጋገሩ ነበር። ከዚያም የአዳም ህይወት ይቀጥላል። ከኤደን ገነት ይባረራል፤ ይወልዳል፤ ይበዛል፤ ህዝብ ይሆናል፤ እንዲህ እያለ ህይወቱ ይቀጥላል፤ ስለዚህ ይህ ሞት በዛው ቅጽበት የሚሆን አይደለም ማለት ነው። ይህ ሞት በእግዚአብሔር ላይ ያመፀ፤ ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀ፤ ተፃራሪ የሆነ ማለት ነው።
በዘፍጥረት ምዕራ3 ላይ እግዚአብሔር "አሁን አዳም ክፉንና መልካሙን ለማወቅ ከኛ እንደ አንዱ ሆኗል" ነው ያለው። መልካምና ክፉን እያወቀ የሚኖር እግዚአብሔር የለሽ፤ እግዚአብሔር የማይገዛው፤ እግዚአብሔር የማይቆጣጠረው የህይወት ስርዓት ያለው ሕይወት ሞት ነው። ሞት ማለት ከእግዚአብሔር ተፃራሪ የሆነ የህይወት ዘይቤ ነው።
በበደላችሁና በሃጥያታችሁ ሞታችኋል ማለት ከእግዚአብሔር የተለየ እራስ ገዝ የሆነ መንግስት መስረታችኋል ማለት ነው። ስለዚህ ሞት ከአንድ የህይወት ስርዓት ወደ ሌላ የህይወት ስርአት መሸጋገሪያ መንገድ ነው ማለት ነው። አዳም የእግዚአብሔርን ፍቃድ እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት ይኖርበት ከነበረበት ገነት ከምትባለው መንፈሳዊ ግዛት ፍጹም ሰላም ቅዱስናና ጽድቅ ከነበረበት ቦታ ወጥቶ ራሱ ወደ ሚያስተዳድረው ዓለም እና ስርአት ሲገባ ወደ ሞት ገባ ተባለ። ስለዚህ ሞት ስርዓት ነው፤ አገዛዝና መንግስት ነው፣ ሞት ከእግዚአብሔር ተለይቶ መኖር ነው።
ሮሜ ምእራፍ 5:12 ጀምሮ እስከ ምእራፍ ስምንት ድረስ ጳውሎስ የሚያብራራው ይህንን ነው። ሞት ነገሰ ገዢ ሆነ በአንዱ አለመታዘዝ ሞት ነገሰ... ስለዚህ ሞት በድንነት የሚሆን ሳይሆን የህይወት ስርዓት ለውጥ ነው። ስለዚህ አንዱ ችግራችን ከእግዚአብሔር የተለየ አምላክ የለሽ ስርአት ውስጥ መግባታችን ነው። በደል የሚለው ቃል በግሪኩ መንሸራተት ማለት ነው ከአንድ ህይወት መንገድ ዘወር ማለት መውደቅ(ፈንገል) ማለት ነው።
ጳውሎስ በዚህ ሞት በሚባለው አለም ውስጥ ሶስት ነገሮችን ያሳየናል
1.በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ
በእዚህ ሞት በሚባል ዓለም ውስጥ አዳም(የሰው ልጅ ) የራሱን መንግስት ማቋቋም የጀመረው እግዚአብሔር ከኤደን ገነት ካስወጣዉ በኋላ ነው። በእግዚአብሔር የማይተዳደር፤ ራሱን የቻለ፤ እግዚአብሔር የማያስፈልገው፤ በሃጥያትና ትዕቢተኝነት የተሞላ መንግስት ፈጠረ፤ አቋቋመ።
ይህንን ከእግዚአብሔር የተለየ ኑሮና ዓለም የጀመረው እና የመሰረተው እራሱ አዳም ነው፤ ጳውሎስ በእነዚህ ተመላለሳችሁባቸው ይላል፤ እነሱም ሃጥያት፤ በደልና እንቢተኝነት ናቸው፤ እነዚህ የአዳም መንግስት መርሆች ናቸው።
ኑሮ የሚለው ቃል አኗኗር ስርአት ማለት ነው። ይህንን ኑሮ የሰራው እግዚአብሔር አይደለም፤ አዳም ነው። የራሱን መንግስት መሰረተ፤ የራሱን ኑሮ አበጀ፤ ይህም አገዛዝ እስከ አሁን ድረስ አለ ከዚህ አገዛዝ ውስጥ ብዙ ክፉና ብዙ መልካም ነገሮችን የሰው ልጅ ፈጥሯል (ሮሜ 5)።
ይህ ተስፋ በክብሩ እና በጸጋው ጉልበት በሚያስገርም ሁኔታ የዚህ አለም ነገሮች ከነ ከንቱ ምኞታቸው እንዲደበዝዙብን ያደርግና የጌታችንን ዳግም መመለስን ግን አጉልቶ በማሳየት ጌታችን እስኪመለስ ድረስ እርሱን ተስፋ ከሚያደርጉ ቅዱሳን ጋር እንድንተያይ፣ እንድንሰበሰብ፣ እንድንተናነጽ እና እንድንጽናና ያደርገናል (1ኛተሰ.5፤1-23)።
ከዘለአለም ሞት ያዳነን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ወደዚህ ምድር ሲመጣ በዓለሙ ላይ ከሚመጣ ቁጣ ደግሞ የሚያድነን እርሱ እንደሆነ በማወቅና በመረዳት በእግዚአብሔር ላይ ባለን እምነት ደግሞ እምነታችን በመልካሙ ስራ ሲገለጥ ለ እግዚአብሔር ባለን ፍቅር ላልዳኑ ሰዎች ምሳሌ በመሆንና የጌታችንን የአዳኛችንን ዳግመኛ መመለስ ተስፋ በማድረግ እሰከመጨረሻ በመፅናት የምንቆምበትን ጸጋና ሀይል እግዚአብሔር ያብዛልን ፡፡
አሜን!!!
Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa
የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ጥር 4 /2017 ዓ.ም
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago