ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 1 day ago
Last updated 1 week, 3 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 4 weeks ago
Our prophetic Sunday service highlights
የጥበባችን መጀመሪያ (ራስ) ኢየሱስ ነው።
ምሳሌ 1:7
ሮሽ/ራስ/Head
እግዚአብሔር ለራሱ ዓላማ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ያሳልፋል። አንዳንድ ጥያቄዎች ያለመመለሳቸው ምክንያትም ሊጥሉት የተገባ ግን ያልጣሉት ነገር ከእነርሱ ጋር ስላለ ነው። ጌታ ኢየሱስ ዐይነ ስውሩን ሰው ከከተማ አውጥቶ ከፈወሰው በኋላ ወደዚያ እንዳይመለስ የነገረው የቀድሞ አመለካከት፣ ያለፈን ታሪክ ሁሉ ነው።
ብረት ቀጥቃጭ ብረቱ የፈለገውን ቅርፅ እንዲይዝለት ከማድረጉ በፊት የሚያስገባው እሳት ውስጥ ነው። ብረቱ በእሳት ብዛት መልኩ ወደ ቀይነት ሲለወጥ ያን ጊዜ ብረት ቀጥቃጩ እንደወደደ አድርጎ ይሠራው ዘንድ ራሱን ሰጥቷል/ዝግጁ ሆኗል ማለት ነው።
እግዚአብሔር ነገሮችን ከመፈጸሙ በፊት ያዝ የሚያደርጋቸው ሰዎችን መባረክ ስለማይፈልግ ሳይሆን የሰዎች ባሕርይ ቀድሞ መስተካከል ስላለበት ነው።
በመንፈስ ዓለም ለማደግ እና አቅጣጫ ለመቀየር ቅባት ብቻ ሳይሆን ባሕርይ እጅግ ትልቅ ሚና አለው፤ እግዚአብሔር የሚቀባው እሱን ነውና። ሰዎች ለነገሮች ያላቸው አቀባበል ወሳኝ ነው። መላእክቱ ያወሩትን አብርሃም እና ሣራ እኩል ቢሰሙም እምነት በአብርሃም ዘንድ ነገሩ ዕውን ከመሆኑ በፊት ሲገለጥ፣ ሣራ ጋ ግን ካለፈ/ከተቀበለች በኋላ ነበር። አብርሃም የሚያውቀው «ይስሐቅ ቢሞት እንኳ እግዚአብሔር ያስነሳልኛል» የሚለውን ቢሆንም እግዚአብሔር ግን በስጦታው በኩል የኢየሱስን መንፈስ እንዲገናኘው ሊያደርግ ወዷል።
፨ አንድ ዓይነት መገለጥ ግን የተለያየ አቀባበል!
፨ ሣራ እስከ ማሳደግ፤ አብርሃም ግን እስከ መሠዋት!
እግዚአብሔር ለሰዎች የከበረን ነገር መስጠት ሲፈልግ ያዘገያቸዋል። በዚያ ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የባሕርይ ክፍሎችን የሚያስጥልበት ሥልጠና አለው። ከሙሴ ዘንድ ፍርሃት እንዲጠፋ ሲያለማምደው፣ ሳምሶንን በኤሽታኦል ሸለቆ ሲያነቃቃው (ሲያሠለጥነው) እንደነበር ማለት ነው።
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሔርን ሲጠጉት ዐውቀውና ተረድተው የጨረሱ ይመስላቸዋል፤ ሊያርሙት የሚቃጣቸውም አይጠፉም። እግዚአብሔር ግን የሚያደርገውን ያውቃል። ሁልጊዜም ትክክል ነው።
⛔️የማይቀርበት ልዩ ቀን⛔️
📍 እሁድ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ
የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ሀይል የምንቀበልበት ልዩ ትንቢታዊ ቀን!!!
በተለያዩ ጥያቄዎች ውስጥ ያላችሁ እና የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ምሪት እና በረከት የምትፈልጉ ሁሉ ተጋብዛችኋል!!!
እግዚአብሔር ዛሬም ይሰራል!!!
📍አድራሻ:- ሃያ ሁለት አደባባይ የመገናኛ ታክሲ መያዣ ጋር በሚገኘው ሰገን ህንፃ ስር
የእግዚአብሔር ድንቅ ተዓምራት / የብላቴናው የማይሰማ ጆሮ ተከፈተ
https://youtu.be/8JKi0BZCPr4
ስማቹ ማነው?
አምርራችሁ ያለቀሳችሁበት ጉዳይ አፍ ሆኖ ይናገርላችኋል
1ኛ ሳሙ 1:10-11
በኤፍሬም ሀገር ትኖር የነበረችው የሕልቃና ሚስት ሀና ባለመውለዷ ነቀፌታ ምክንያት ጣውንቷ ፍናና እጅግ ታስቆጣት እና ታበሳጫት ነበር።
ሀና፣ ምንም እንኳ ባለቤቷ ሕልቃና አብዝቶ ቢወዳትና ስጦታዎችን ቢሰጣትም የልቧን ሐዘን ሊሽርላት ግን አልቻለም ነበር።
የሀናን ታሪክ ስንመለከተው በአንድ ምዕራፍ ስለተጻፈ ቀላል ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የሀና ምሬት ብዙ ዓመታትን የዘለቀ ነበር።
ፍናና ብዙ ወንደችና ሴቶች ልጆች ወልዳ ባሳደገች ቁጥር ሀና ባለመውለዷ ምክንያት ስትነቀፍ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል።
ባሏ ሕልቃናም በዚህ ሁሉ ውስጥ ባለመውለዷ ምክንያት ከሚሰማት ሐዘን ለማጽናናት ይሞክር ነበር። ነገር ግን በሕይወታችን የምናነሳቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ሰውም ገንዘብም የሚመልሱት ላይሆን ይችላል። ያለንበትም ሁኔታ ምድረ በዳ ሆኖ የሚረዳን እግዚአብሔር እና እግዚአብሔር ብቻ ይሆናል። በዚህ ወቅት የውስጣችንን ጩኸት ብናወጣና ለማስረዳት ብንሞክር እንኳ የሚረዳን አናገኝም።
ይህን መልዕክት ለምታነቡና ባልተመለሱ ጥያቄዎች ምክንያት አምርራችሁ እያለቀሳችሁ ላላችሁ ሰዎች በዚህ ክፍል ካገኘሁት መረዳት አንጻር አንድ መልዕክት አለኝ። ‹አንገት የደፋችሁበት ነገር በኩራት አፍ ሆኖ ይናገርላችኋል።› !!
ሀና ለሕልቃና የሚገባውን እንዳልሰጠችው በተሰማት ጊዜ ባሏ ሕልቃና ከልጆች ይልቅ እኔ አልበልጥብሽም ወይ ቢላትም ይህ አባባሉ ግን መልስ ሊሆንላት አልቻለም። የቱንም ያህል በባሏ ዘንድ ብትወደድም እንዲህ ዓይነት ነገሮች በባሕል ውስጥ እንኳ በሰዎች ዕይታ እና ንግግር ነቀፌታን የሚያስከትል ነው።
በእግዚአብሔር ቤት ለራሳቸው እና ለልጆቻቸው መሥዋዕት ለማቅረብ ብዙዎች ሲሄዱ ሀና ግን መሄድ እንኳ እስኪከብዳት ትደርስ ነበር። ይህች ሴት ከነ ነቀፌታዋ በእግዚአብሔር ቤት በተመላለሰችባቸው ጊዜያት ሁሉ ግን «በእግዚአብሔር ቤት እየተመላለሰች፣ እየጸለየች እንዴት ነው ጥያቄዋ የማይመለስላት?» የሚል ነቀፌታ ነበረባት።
ወደ እግዚአብሔር ቤት በሄዳችሁ ቁጥር ጥያቄያችሁን የሚያውቁ ሰዎች ይህን ተመሳሳይ ጥያቄ በእናንተም ላይ እያነሱ ይሆናል።
ሀና ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ስትሄድ ልቧ ሁሌም ባዘነ ልብ ነበር። ምክንያቱም መሥዋዕት የምታቀርብለት ልጅ የላትም። ይህን ጥያቄ በተደጋጋሚ ለዓመታት ስትጠይቅ መልስ አላገኘችም ነበር።
እኛም በሕይወታችን ውስጥ የምንጠይቃቸው ብዙ ጥያቄዎች ይኖራሉ። አንዳንድ ጥያቄዎችን ደግሞ ካልተመለሱ በቀር በማንተውበት ደረጃ አምርረን እንጠይቃለን። የመጨረሻው ጊዜ ነው ብለን እርግጠኛ የምንሆንባቸው ጥያቄዎች ወደ ጫፍ ይደርሳሉ።
ሀናም በዚያ ሥፍራ ለአንዴና ለመጨረሻ ቆርጣ፣ ከልቧ አምርራ ስትለምን የምሬቷ ደረጃ ካህኑ ዔሊ እንኳ እሷን እንደ ሰካራም እስኪመለከታት አድርጎታል። ምክንያቱም በውስጧ የነበረው ለብዙ ዓምታት የተጠራቀመ ብሶት፣ ሐዘን እና ጩኸት ነው።
እግዚአብሔር ግን በጩኸቷ ውስጥ መልስን የሚሰጥበት የመጨረሻ ቀን ነበር። ሀናም ለዔሊ ልቧ ያዘነባት ሴት እንደሆነችና ንግግሯ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሆነ ስትገልጽለት እግዚአብሔር ልመናዋን እንዲቀበል ባርኮ ሸኛት። ካህኑ ዔሊ ነቢይ ነበር። ከነቢይ አፍ ቃል ሲወጣ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለች፤ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል፦ «ከዚያች ቀን ጀምራ ሀና አዝና አልታየችም።»
ምንድን ነው ያስመረራችሁ? ምንድን ነው ጥያቄያችሁ? ምንድን ነው ነቀፌታችሁ? እግዚአብሔር ነቀፌታችሁን፣ ጥያቄያችሁን፣ ያስመረራችሁን ጉዳይ መልስ አድርጎ ይሰጣችኋል።
ለሀና እግዚአብሔር ልመናዋን ሰምቶ ነቀፌታዋን አነሳላት፤ ጥያቄዋንም መለሰላት።
1ኛ ሳሙ 2 ላይ ልጇን ሳሙኤልን ለእግዚአብሔር ከሰጠች በኋላ አፏ ለምስጋና ተከፍቶ እግዚአብሔርን ስትባርክ እንመለከታለን።
እዚህ ጋር አንድ ነገር እንድናስተውል ያስፈልጋል!
ሀና ሳሙኤልን ከወለደች በኋላ ለሁሉም እየዞረች እግዚአብሔር ልጅ ሰጠኝ ልጅ ሰጠኝ አላለችም። ልጇን ለእግዚአብሔር ከሰጠች በኋላ በድፍረት «አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ» ስትል ተናገረች። የሀና ጩኸት ሳሙኤል እንዲወለድ ነበር።
፨ ሳሙኤል ደግሞ የአንድ ተራ ጩኸት መልስ አይደለም፤ ራሱ ድምፅ ሆኖ የተወለደ ነቢይ እንጂ!!
ሀና አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ ብላ እንድትናገር ያደረጋት መረዳት የወለደችው ልጅ 120 ግዛት ሙሉ ድምፁ የሚሰማ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የተናገረው ቃል የማይሻር፣ እሱ ተናገረ ማለት ንጉሥ ሳይቀር የሚንቀጠቀጥለት ነቢይ ስለሆነ ነው። ለሀና አፍ የሆነላት የራሷ አፍ ሳይሆን የወለደችው ልጅ ነው።
ስለሆነም ... ነቀፌታን በተቀበላችሁበት፣ በሰው ሁሉ ፊት አንገት በደፋችሁበት በዚያ ጥያቄ እግዚአብሔር በሰው ሁሉ ፊት ያንን ጥያቄ ድምፅ አድርጎ ለእናንተ የሚናገር የምሥራች አድርጎ እንዲመልስላችሁ ባረኳችሁ። የጥያቄ ውጤት ተራ መልስ ሳይሆን የሚያወራ፣ ትውልድ የሚናገረው መልስ እንዲሆንላችሁ ባርኬያችኋለሁ✋
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 1 day ago
Last updated 1 week, 3 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 4 weeks ago