Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

Description
ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

hace 1 mes

ዘካህ ለሠለምቴዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው።
“ማል” مَال ማለት “ሀብት” ማለት ሲሆን የማል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አምዋል” أَمْوَال ነው፥ ከተቀማጭ ሀብት ላይ ወይም ከትርፍ ላይ የሚሰጠው ዘካህ “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال ይባላል። በነቢያችን”ﷺ” ሸሪዓህ ግን ዘካቱል ማል ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

“ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏

“ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው።

ዘካቱል ማል ከቤት ለተባረሩ ሠለምቴዎች መቋቋሚያ መስጠት ከፈለጋችሁ እና ዘካቱል ፊጥር ለመሣኪን ሠለምቴዎች ማስፈጠሪያ መስጠት ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች ያሉትን አድሚናት አናግሩ፦
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

hace 1 mes

ወደ ዲኑል ኢሥላም ስንመጣ "ዐቅመ ጋብቻ" ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ፦ የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦
4፥6 የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ

"ኢዛ"  إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ ግሥ ሲሆን ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት "ጋብቻን እስከደረሱ" ድረስ በማለት ይናገራል። እዚህ አንቀጽ ላይ  "ጋብቻን እስከደረሱ" ለሚለው የገባው ቃል "በለጉ" بَلَغُوا ሲሆን "ለጋብቻ በሰሉ" ማለት ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት እራሱ "ለጋብቻ በሰለ" ማለት ሲሆን "በለገት" بَلَغَت ማለት ደግሞ "ለጋብቻ በሰለች" ማለት ነው። "ባሊግ" بَٰلِغ ማለት እራሱ "ዐቅመ ጋብቻ"Puberty" ማለት ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6 "ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ" የሚለውን ሙጃሂድ፦ "ለዐቅመ ጋብቻ ነው" ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ "ለዐቅመ ጋብቻ" ለጋዎች "ኢሕቲላም" ሲኖራቸው ነው" ብለዋል። አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"።
( حتى إذا بلغوا النكاح ) قال مجاهد : يعني : الحلم . قال الجمهور من العلماء : البلوغ في الغلام تارة يكون بالحلم ، وهو أن يرى في منامه ما ينزل به الماء الدافق الذي يكون منه الولد . وقد روى أبو داود في سننه عن أمير المؤمنين علي بن أبي طالب ، رضي الله عنه ، قال : حفظت من رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا يتم بعد احتلام
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"።  قَالَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ حَفِظْتُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يُتْمَ بَعْدَ احْتِلاَمٍ

"ዐቅመ ጋብቻ" አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። አንድ ለጋ ሕጻን ለዐቅመ አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦
24፥59 ከእናንተም ሕፃናቶቹ "ዐቅመ አዳምን" በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ

አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ"  إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ ግሥ የዐቅመ ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ ጋብቻ ለማመልከት "ዐቅመ አዳም" ለሚለው ቃል "በለገ" بَلَغَ  የሚል የግሥ መደብ ይጠቀማል። አንዲት እንስት ለዐቅመ ሐዋህ ደረሰች የሚባለው አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት ደግሞ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ሲጀምር ነው። ይህ የምታመነጨው ፈሳሽ "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ሲባል ትርጉሙ "ከረቤዛዊ ፈሳሽ"Vaginal lubrication" ነው፥ ይህ ፈሳሽ ከጨቅላነት ወደ ዐቅመ ሐዋህ የምትሸጋገርበት አካላዊ ሽግግር"physical transition" ምልክት ነው።
ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ በማድረግ እናታችን ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ለነቢያችን"ﷺ" የተዳረችው በስድስት ዓመቷ ሲሆን ለዐቅመ ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ለሦስት ዓመት ከተጠበቀ በኃላ በዘጠኝ ዓመቷ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቤት ገብታለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 82
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቡኝ የስድስት ዓመት እንስት ነበርኩኝ፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ስሆን ወደ ቤቱ ገባሁኝ"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ تَزَوَّجَنِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ وَبَنَى بِي وَأَنَا بِنْتُ تِسْعِ سِنِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 69
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቧ የስድስት ዓመት ነበረች፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ሲሆናት ደረሱባት"። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم تَزَوَّجَهَا وَهْىَ بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ

በስድስት ዓመቷ ተድራ ሦስት ዓመት የመቆየቷ ጉዳይ ለዐቅመ ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ነው፥ "በስድስት ዓመቷ ተድራ በዘጠኝ ዓመቷ ለምን ተራከበች" ብለህ እርር እና ምርር የምትል ከሆነ እንግዲያውስ ይስሐቅ ርብቃን በሦስት ዓመቷ ማግባቱን እና በስድስት ዓመቷ ተራክቦ ማድረጉን ስትሰማ ልትንጨረጨር እና ልትንተከተክ ይገባክ ነበር። የምጣዱ እያለ የዕንቅቡ ተንጣጣ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ወይም ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት ይሉካል እንደዚህ ነው። በነገራችን ላይ ጥንታዊ ዘመን"classical age" ላይ የነበሩትን ባህል፣ ወግ፣ ልማድ፣ ትውፊት በድኅረ ዘመናዊ ዘመን"postmodern age" ባህል፣ ወግ፣ ልማድ፣ ትውፊት መመዘን ከሥነ አመክንዮ አንጻር ታሪካዊ ሕፀፅ"historical fallacy" ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

hace 1 mes

የርብቃ ጋብቻ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥6 የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ

እንደ ዘፍጥረት ዘገባ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ እንደነበር ተዘግቧል። በዚያን ይስሐቅ የሠላሳ ስድስት ዓመት ልጅ እንደነበር በታርገም ዮናታን ተዘግቧል፦
ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 22፥1 ይስሐቅም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "እነሆ፥ ዛሬ የሠላሳ ስድስት ዓመት ልጅ ነኝ"። ויען יצחק: "הנה אני בן שלושים ושש שנה היום".

ምሁራን ይስሐቅ በሞርያ ተራራ ሠላሳ ስድስት ዓመት ከመንፈቅ ስላለፈ ሠላሳ ሰባት ዓመቱ እንደነበር ይዘግባሉ፦
ራሺ ዘፍጥረት 25፥20 "አብርሃም ከሞሪያ ተራራ በመጣ ጊዜ ርብቃ መወለዱን ሰምቷልና፥ በዚያ ጊዜ ይስሐቅ የሠላሳ ሰባት ዓመት ልጅ ነበር። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ሣራ ስለሞተች። שֶׁהֲרֵי כְּשֶׁבָּא אַבְרָהָם מֵהַר הַמּוֹרִיָּה נִתְבַּשֵּׂר שֶׁנּוֹלְדָה רִבְקָה, וְיִצְחָק הָיָה בֶּן ל"ז שָׁנָה, שֶׁהֲרֵי בּוֹ בַּפֶּרֶק מֵתָה שָׂרָה, וּמִשֶּׁנּוֹלַד יִצְחָק עַד הָעֲקֵדָה שֶׁמֵּתָה שָׂרָה, ל"ז שָׁנָה הָיוּ

"ይህም ከሆነ በኋላ" ማለትም "ይስሐቅ ሊሠዋ ከሆነ በኃላ" ለአብርሃም ሚልካ ለወንድሙ ለናኮር ልጆችን ወለደች፦
ዘፍጥረት 22፥20 ይህም ከሆነ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወንድምህ ለናኮር ልጆችን ወለደች።

ሚልካ የናኮር ሚስት ስትሆን የአብርሃም ወንድም ናኮር ዑፅ፣ ቡዝ፣ ቀሙኤል፣ ኮዛት፥ ሐዞ፣ ፊልዳሥ፣ የድላፍ፣ እና ባቱኤል የሚባሉ ስምንት ልጆችን ወለደች፦
ዘፍጥረት 22፥21-22 እነርሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወንድሙ ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥ ኮዛት፥ ሐዞ፥ ፊልዳሥ፥ የድላፍ፥ ባቱኤል ናቸው።

ባቱኤል የናኮር የመጨረሻ ልጅ ሲሆን ባቱኤል ደግሞ ርብቃን ወለደ፦
ዘፍጥረት 22፥23 ባቱኤልም ርብቃን ወለደ።

በትንሹ ይስሐቅ ርብቃን በሠላሳ ሰባት ዓመት ይበልጣታል፥ ይስሐቅ አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፦
ዘፍጥረት 25፥20 ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ።

ይስሐቅ ርብቃን ሲያገባት የሦስትት ዓመት ልጅ ነበረች፥ ምክንያቱም 40-37=3 ይሆናልና። ከጋብቻ በኃላ ይስሐቅ ከርብቃ ጋር በተራክቦ ለመራከብ የነበረው የጊዜ ክፍተት ሦስት ዓመት እንደነበር በራሺ ዘፍጥረት ላይ እንዲህ ተዘግቧል፦
ራሺ ዘፍጥረት 25፥20 "ለጋብቻ ብቁ እስክትሆን ድረስ ሦስት ዓመት ጠበቀ፥ ከዚያም ደረሰባት። הִמְתִּין לָהּ עַד שֶׁתְּהֵא רְאוּיָה לְבִיאָה ג' שָׁנִים וּנְשָׂאָהּ:

ስለዚህ የሦስት ዓመት ልጅ ለአርባ ዓመት ሰው መዳር በጥንት ጊዜ የተለመደ ጉዳይ መሆኑ ይህ ታሪክ ጉልኅ ማሳያ ነው። እንደ ታሪኩማ ይስሐቅ በተራክቦ ሲራከባት ርብቃ መካን ነበረችና ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ አምላክ ጸለየ፥ አምላክም ስለተለመነው ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች፦
ዘፍጥረት 25፥21 ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ ያህዌህ ጸለየ፥ መካን ነበረችና ያህዌህም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች።

hace 3 meses

"ኤሎሂም" በሚል ትምህርት ተለቋል። "ኤሎሂም" ማለት ትርጉሙ "አማልክት" ማለት ሲሆን ፈጣሪ “ኤሎሂም” ሲባል ምን ማለት ነው? "አማልክት" የተባሉት ሥላሴ ከሆኑ ሥላሴ አማልክት ናቸው? እነዚህ የመሳሰሉ እሳቦት ዳሰሳ አድርገናልና ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/DYDqQqemDFk?si=qYY0t9HgIv-F0cvi

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!

hace 3 meses

"በቀኝ እጁ" እና "በግራ እጁ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! የእርሱን እጆች ትርጉም በመስጠት ሳናራቁጥ እና ከፍጡራን እጆች ጋር ሳናነጻጽር እርሱ በነገረን መሠረት እንቀበላለን። ወደ ባይብሉ ስንገባ ያህዌህ አምላክ ሰውን ከምድር አፈር ያበጀው በእጆቹ ነው፦
መዝሙር 119፥73 "እጆችህ" ሠሩኝ አበጃጁኝም። יָדֶ֣יךָ עָ֭שׂוּנִי וַֽיְכֹונְנ֑וּנִי
ዘፍጥረት 2፥7 ያህዌህ አምላክ ሰውን ከምድር አፈር "አበጀው"። וַיִּיצֶר֩ יְהוָ֨ה אֱלֹהִ֜ים אֶת־הָֽאָדָ֗ם עָפָר֙ מִן־הָ֣אֲדָמָ֔ה

"እጆች" የሚለው ቃል "እጅ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ጭቃ" ማለት "የውኃ እና የአፈር ቅልቅል ነው። ፈጣሪ ሰውን ከጭቃ በእጁ ለውሶ ሠራው፦
ኢዮብ 10፥8 እጅህ ለወሰችኝ ሠራችኝም። יָדֶ֣יךָ עִ֭צְּבוּנִי וַֽיַּעֲשׂ֑וּנִי
ኢዮብ 33፥6 እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ። מֵ֝חֹ֗מֶר קֹרַ֥צְתִּי גַם־אָֽנִי׃

ፈጣሪ ሰውን ከጭቃ በእጆቹ ካበጀ እና ከሠራ እጆቹ ቀኝ እና ግራ ናቸው፥ ምክንያቱም ፈጣሪ ቀኝ እና ግራ ካለው ቀኝ እና ግራ እጆች አሉት፦
1ኛ ነገሥት 22፥19 ሚክያስም አለ፦ እንግዲህ የያህዌህን ቃል ስማ! ያህዌህ በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ "በቀኙ" እና "በግራው" ቆመው አየሁ። וַיֹּ֕אמֶר לָכֵ֖ן שְׁמַ֣ע דְּבַר־יְהוָ֑ה רָאִ֤יתִי אֶת־יְהוָה֙ יֹשֵׁ֣ב עַל־כִּסְאֹ֔ו וְכָל־צְבָ֤א הַשָּׁמַ֙יִם֙ עֹמֵ֣ד עָלָ֔יו מִימִינֹ֖ו וּמִשְּׂמֹאלֹֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀኝ" ለሚለው የገባው ቃል "የሚን" יָמִין ሲሆን "ግራ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ሸሙል" שְׂמֹאול ነው። "ሠለስቱ ምዕት" ማለት በ 325 ድኅረ ልደት በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት ናቸው፥ እነርሱም "ፈጣሪ እጅ አለው" ሲባል የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም" ብለዋል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 30
“ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በከበሩ መጻሕፍት የተጻፈ ሁሉ የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም”።

እርማችሁን አውጡ! ሠለስቱ ምዕት ፈጣሪ እጅ እንዳለው እንቅጩን ፍርጥ አርገው ተናግረዋል። ለእግዚአብሔር እጆች እንዳሉት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ተናግሯል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 62
“እግዚአብሔር እጆች እና ክንድ፣ ጥፍር እንዳለው ዕወቁ”።

ስለዚህ "አሏህ እጆች አሉት" ሲባል በደምሳሳው የምትተቹ ሰዎች መጽሐፋችሁ ላይ ያህዌህ እጆች እንዳሉት ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን? የመነቸከ ሙግት ከምትሟገቱ ይልቅ የፋፋና የዳበረ እንዲሁ የላመና የጣመ ሙግት ለማደራጀት እና ለማዋቀር መሞከር አይሻላችሁምን? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

hace 3 meses

የአሏህ እጆች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥75 አሏህም «ኢብሊሥ ሆይ! "በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

አምላካችን አሏህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል የራሱ ባሕርያት አሉት፥ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም፦
42፥11 የሚመስለው ምንም "ነገር" የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስል" مِثْل በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው "ከ" كَ የሚል መስተዋድድ "በጭራሽ" ማለት ነው፥ "ነገር" በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉም ፍጡራን የሚካተቱ ሲሆኑ ከፍጡራን መካከል እርሱን የሚመስል ብጤ በጭራሽ የለም። እዚሁ አንቀጽ ላይ አሏህ "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ተገልጿል፥ ሰውም "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ሌላ አንቀጽ ላይ ተገልጿል፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

የአሏህ መስማት እና ማየት ከፍጡራን ጋር እንደማይመሳሰል እና እንደማይነጻጸር ሁሉ የፈጣሪ ባሕርዮት ከፍጡራን ጋር አይመሳሰለም አይነጻጸርም። ይህንን መረዳት ይዘን ቁርኣን ላይ አምላካችን አሏህ እጆች እንዳሉት ይናገራል፦
38፥75 አሏህም «ኢብሊሥ ሆይ! "በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

"ሁለት እጆች" ለሚለው የገባው "የደይየ" ِيَدَىَّ ሲሆን ሙሰና"dual" እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላካችን አሏህ ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰሉ እጆች አሉት፥ የእርሱ እጆች ፍጥረታዊ ሳይሆኑ መለኮታዊ እንዲሁ ሰዋዊ ሳይሆኑ አምላካዊ ናቸው። የአሏህ እጆች ቀኝ ናቸው፦
ሚስካቱል መሷሒብ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 30
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ አል ዓሲ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ፍትኸኞች አሏህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር ረሕማን በስ ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፥ "ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው"። وَعَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: إِنَّ الْمُقْسِطِينَ عِنْدَ اللَّهِ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ عَنْ يَمِينِ الرَّحْمَنِ وَكِلْتَا يَدَيْهِ يمينٌ

"የሚን" يَمِين ማለት "ጠንካራ" "አውንታዊ" "ሙሉነት" በሚል ትርጉም ይመጣል፥ "ሸማል" شِّمَال ማለት "ደካማ" "አሉታዊ" "ጎዶሎነት" በሚል ትርጉም ይመጣል። በዐማርኛችን "በቀኝ አውለኝ" እና "ግራ ያጋባል" በሚል ዐውድ ቀኝ እና ግራ አውንታዊ እና አሉታዊ ነገር ለማመልከት ይመጣሉ፥ እሩቅ ስንሄድ "left" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "ደካማ"weak" ማለት ነው። ስለዚህ "የአሏህ እጆች ቀኝ ናቸው" ማለት "ጠንካራ፣ አውንታዊ፣ ሙሉ ናቸው" ማለት ነው እንጂ አሏህ ቀኝ እና ግራ የሆኑ እጆች አሉት፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 52 ሐዲስ 7
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ዐዘ ወጀል በፍርዱ ቀን ሰማያትን ይይዛል፥ ከዚያም በቀኝ እጁ ያረግና፦ "እኔ ንጉሡ ነኝ፥ ትዕቢተኞች የት አሉ? ኩሩዎች የት አሉ?" ይላል፥ ከዚያም ምድርን በግራ እጁ አድርጎ፦ "ትዕቢተኞች የት አሉ? ኩሩዎች የት አሉ?" ይላል። عَبْدُ اللَّهِ بْنُ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَطْوِي اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ السَّمَوَاتِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ثُمَّ يَأْخُذُهُنَّ بِيَدِهِ الْيُمْنَى ثُمَّ يَقُولُ أَنَا الْمَلِكُ أَيْنَ الْجَبَّارُونَ أَيْنَ الْمُتَكَبِّرُونَ ثُمَّ يَطْوِي الأَرَضِينَ بِشِمَالِهِ ثُمَّ يَقُولُ أَنَا الْمَلِكُ أَيْنَ الْجَبَّارُونَ أَيْنَ الْمُتَكَبِّرُونَ ‏"‏ ‏.‏

hace 3 meses, 1 semana

"ሥሉስ አምላክ" በሚል ትምህርት ተለቋል። “ሥሉስ” ማለት “ሥስት”three" ማለት ሲሆን "ሥሉስ አምላክ" ማለት "ሦስት አምላክ" ማለት ነው። ሥላሴአውያን "አምላክ ሦስት ነው" ብለው በትውፊታቸው ማስቀመጣቸው ዳሰናል። ትምህርቱን በጥሞና እና በቅጡ ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/iZuSQVwoI3A?si=8wQKlLznMBEH-fOd

ሌሎቻችሁ ሼር አርጉት!

hace 3 meses, 1 semana

ትራይፎም አምላክ እና መልአክ የተለያዩ ምንነቶች እንደሆነ ሲነግረው ዮስጦስም የሰማይ ነገርን ሁሉ ትቶ በትንሽ የምድር ክፍል የሚመጣው ሌላው አምላክ ኢየሱስ እንጂ የሁሉም ነገር ፈጣሪ እና አባት የተባለው አንድ አምላክ አብ እንዳይደለ ነግሮታል፦
"አንተ እንዳልከው "ሁለቱ መልአክ እና አምላክ ነበሩ" ቢሆን በጣም ትንሽ ዕውቀት ያለው ሰው ካልሆነ በቀር፦"የሁሉም ነገር ፈጣሪ እና አባት የሰማይ ነገርን ሁሉ ትቶ በትንሽ የምድር ክፍል ላይ ታየ" ብሎ ለማስረገጥ አይደፈርም"።
Dialogue with Trypho (Justin Martyr) Chapter 60.

ዮስጦስ የጂፒተር ልጆች ለሚባሉት ለግሪካውያን የአምላክ በኵር የሆነው ቃል ያለ ተራክቦ መገኘት "እናንተ የጂፒተር ልጆችን ከምታምኑባቸው ጋር ተመሳሳይን እንጂ የተለያየ ነገር አላመጣንም" በማለት ዓይኑን አፍጦ እና ጥርሱን አግጦ ትምህርቱ ከአረማውያን ጋር እንደሚመሳሰል ተናግሯል፦
"እንዲሁ የአምላክ በኵር የሆነው ቃል ያለ ተራክቦ መገኘት እና መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቀለ፣ ሞተ፣ ተነሳ እና ወደ ሰማይ ዐረገ ስንል እናንተ የጂፒተር ልጆችን ከምታምኑባቸው ጋር ተመሳሳይን እንጂ የተለያየ ነገር አላመጣንም"።
The First Apology (St. Justin Martyr) chapter 21

እንግዲህ ሐዋርያት "አንድ አምላክ አብ ነው" ብለው ስላስተማሩ "አሐዳውያን"unitarian" የነበሩ ሲሆን ከሐዋርያት ቀጥለው የመጡት አበው የሄሌናዊውን ዐረማዊነት በመቀየጥ ከአንዱ አምላክ ከአብ ሌላ ኢየሱስን ሁለተኛ እና ሌላ አምላክ በማድረጋቸው "ክልዔታውያን"Binitarian" ነበሩ። የክርስትና ታሪክ ምሁር ኤድዋርድ ጊቦን "History of christianity" በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለ ክርስትና ዐረማዊነት"paganism" እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦
"አረማዊነት በክርስትና ድል ቢነሳም ክርስትናም በዚያው መጠን በአረማዊነት ተበክሏል"።
History of christianity (Edward Gibbon) page XVI(16)

ከዚህ ሁሉ ውዝግብ በኃላ አምላካችን አሏህ ቁርኣንን በነቢያች"ﷺ" ላይ እነዚያን "ፈጣሪ ልጅ ወልዷል" ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው፦
18፥4 እነዚያንም «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

"ፈጣሪ ልጅ ወልዷል" የሚለው ይህ የዐረማዊ ትምህርት ዓለም ላይ ያለውን ሁለት ቢልዮን ክርስቲያን የሚያወዛግብ ስለሆነ ቁርኣን ይህንን ለማስጠንቀቅ መውረዱ ተገቢ ነው። አሏህ አንድ ነው፥ አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው፦
114፥1 በል «እርሱ አሏህ አንድ ነው»፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥2 «አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው»፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

እርሱ የሁሉ መጠጊያ ከሆነ ጊዜን እና ቦታን ያካበበ ፈጣሪ በጊዜ እና በቦታ ውስጥ ገብቶ እና ተወልዶ በአጭር ቁመት እና በጠባብ ደረት አይወሰንም፥ በእርሱ ባሕርይ መውለድ እና መወለድ ስለሌለ አልወለደም አልተወለደምም፦
112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

"ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ቢጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ ከሌለው ምንም ልጅን አልወለደም፥ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፦
23፥91 አሏህ ምንም ልጅን አልወለደም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ

ከእርሱ ጋር ሌላ ወይም ሁለተኛ አምላክ ቢኖር ኖሮ በመካከላቸው መለያየት ኖሮ ከፊሉ በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር፥ አሏህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፦
23፥91 ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር፡፡ አሏህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! እኛንም በተውሒድ ጸንተው ከሚሞቱ ሙሥሊም ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

hace 3 meses, 1 semana

ሁለተኛ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥91 አሏህ ምንም ልጅን አልወለደም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ

"ክርስትና" የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የሰየመው አግናጢዮስ ዘአንጾኪያያ በ 110 ድኅረ-ልደት ነው። ክርስትና በአውሮፓ የተሸመነበት ድርና ማግ እንደሆነ ሁሉ የተዋረደበት ማቅ፣ የተገነዘበት በፍታ፣ የተከፈነበት ግምዣ ነው፥ ክርስትና የየአውሮፓ ግሪክ ወሮም"Graeco-Roman" ፍልስፍና እና የኢየሱስ ትምህርት ቅይጥ ነው። የክርስትና ታሪክ ምሁር አዶልፍ ሃርናክ "Outlines of the History of Dogma" በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ክርስትና ሥሩን በሄሌናውነት"hellenism" አፈር ውስጥ እንዴት እንደሰደደ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦
"ክርስትና ሥሩን በሄሌናዊነት አፈር ውስጥ ሰደደ፥ በዚህም ምክንያት ለአብዛኞቹ ክርስቲያኖች ምሥጢር ሆነ"።
Outlines of the History of Dogma(Adolf Harnack) Page 194

በሄለናዊ ግሪክ ሥነ-ተረት"hellenistic Greek mythology" ስለ አማልክት ያላቸው እሳቦት "ዙስ" Ζεύς የሄርሜስ አባት ሲሆን ማዕረጉ "ሆ ቴዎስ ሆ ፓትሮስ" Ο Θεός ο Πατρὸς ነው፥ "ሆ ቴዎስ ሆ ፓትሮስ" ማለት "አምላክ አባት"God the father" ማለት ነው።
"ሄርሜስ" Ἑρμῆς ደግሞ የዙስ ልጅ ሲሆን በሰማይ እና በምድር መካከል ያለ መካከለኛ "መልእክተኛ" ነው። ይህ መልእክተኛው ልጅ ማዕረጉ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ነው፥ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" ማለት "አምላክ ልጅ"God the son" ማለት ነው። አረማውያን አምላኪዎች በሊቃኦንያ ከተማ "አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል" በማለት በርናባስንም "ዙስ" ጳውሎስ "ሄርሜስ" አሉዋቸው፥ የድያ ካህን እና ሕዝቡ መሥዋዕት ሊሠውላቸው ወደዱ፦
የሐዋርያት ሥራ 14፥12 በርናባስንም "ዙስ" አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ "ሄርሜስ" አሉት። ἐκάλουν τε τὸν Βαρνάβαν Δία, τὸν δὲ Παῦλον Ἑρμῆν, ἐπειδὴ αὐτὸς ἦν ὁ ἡγούμενος τοῦ λόγου.

ዙስ በንግግር ሳይናገር ከእርሱ ተልእኮ የሚናገር መልእክተኛ ሄርሜስን እንደሚልክ በተመሳሳይ የማይናገረውን በርናባስን "ዙስ" የሚናገረውን ጳውሎስን "ሄርሜስ" የማለታቸው ምክንያት ይህ ነው፥ "ዙስ" Ζεύς በሮማውያን "ጁፒተር" ሲባል "ሄርሜስ" Ἑρμῆς ደግሞ በሮማውያን "ሜርኩርይ" ይባላል።
ከ 20 ቅድመ ልደት እስከ 50 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ፊሎስ ዘእስክንድርያ የግሪክን ፍልስፍና ከአይሁድ ትምህርት ጋር የሚቀይጥ አይሁዳዊ ፈላስፋ እና መካከለኛ አፍላጦናዊነትን"middle platonism" የሚያቀነቅን የነበረ ሲሆን ስለ ሎጎስ እንዲህ ይላል፦
"ሎጎስ የአምላክ የበኵር ልጅ እና የአምላክ መልአክ ነው"። Frederick Copleston, A History of Philosophy, Volume 1, Continuum, (2003), pp. 458–462.

"ዲዩቴሮ ቴዎስ" δεύτερο Θεός ማለት "ሁለተኛ አምላክ" ማለት ሲሆን ይህ ሄለናዊ ፊሎስ ሎጎስን "ሁለተኛ አምላክ ነው" ብሎ ያስተምር ነበር፦
"በአምላክ የተነገረው ይህ የንግግር ዓረፍተ ነገር በጣም ተገቢ እና ምንም ውሸት የሌለበት ነበር፥ ሟች የሆነ ነገር የአጽናፈ ዓለም ታላቁ አባት በሆነው ምሳሌ ሊፈጠር አይችልምና። ነገር ግን(የተፈጠረው) የታላቁ ኑባሬ ቃል በሆነው "በሁለተኛው አምላክ" ምሳሌ በኃላ ነው"።
Philo: Questions and Answers on Genesis, Chapter 2 Number 62

"ሁለተኛው አምላክ" የሚለው ይሰመርበት! የእስክንድሪያው አርጌንስ ደግሞ ኢየሱስን "ሁለተኛ አምላክ" ብሎ ያስተምር ነበር፦
"ቢሆንም እኛ "ሁለተኛ አምላክ" ብለን ልንጠራው እንችላለን፥ "ሁለተኛ አምላክ" በሚለው ቃል ስንጠራው ሌሎችን በጎነቶችን የማካተት ችሎታ ካለው በጎነት በቀር ምንም ማለት እንዳልሆነ ይወቁ። Origen Against(Contra) Celsum, Book 5 chapter 39

"ሁለተኛው አምላክ" የሚለው ይሰመርበት! "ሄቴሮ ቴዎስ" ἕτερο Θεός ማለት "ሌላ አምላክ" ማለት ሲሆን ዮስጦስ ሰማዕቱ ትራይፎ ለሚባለው አይሁዳዊ ጓደኛው ኢየሱስን "ሌላ አምላክ" ብሎታል፦
"መጻሕፍትን ስለ ተረዳችሁ ላሳምናችሁ እሞክራለሁ፥ እኔ ከምለው ነገር አለ እና አለ ከተባለው፣ ለሁሉን ነገር ፈጣሪ የሚገዛ "ሌላ አምላክ" እና ጌታ አለ። እርሱም መልአክም ተብሎም ተጠርቷል"። Justin Martyr, Dialogue with Trypho, chapter 56

"ሌላ አምላክ" የተባለው ኢየሱስ "ለሁሉን ነገር ፈጣሪ" ለተባለው ለአብ ይገዛል፥ ዮስጦስ ይህንን ሌላ አምላክ መልአክ ተብሎ የተጠራ እና ለሙሴ የተናገረው አምላክ ብሎ የጠራው ከሁሉ ነገር ፈጣሪ ከሆነው ማንነት ለይቶታል፦
የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ እና የያዕቆብም አምላክ የነበረው ለሙሴ የተናገረው አምላክ የሁሉ ነገር ፈጣሪ አይደለም"።
Dialogue with Trypho (Justin Martyr) Chapter 60.

hace 5 meses, 1 semana

እኛ ሙሥሊሞች ክርስቲያኖችን፦ ኢየሱስ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ ስጡን ስንላቸው እነርሱ፦ "ኢየሱስ አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" ብሏል ብለው ይመልሳሉ፥ እውን "አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ" የሚለው ማን ነው? ኢየሱስ ወይስ የኢየሱስ አምላክ? ያድምጡና ያስደምጡ፦ https://youtu.be/U0JrbUdiW2Y?si=zh10yRilGdpxDPgb

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas