ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

Description
ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

3 weeks, 4 days ago
3 weeks, 4 days ago

አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው!

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች "ዐሊመሏህ" عَلِمَ اللَّه የሚለው ቃል ወስደው "አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነውን? ብለው ይጠይቃሉ፦
2፥235 አሏህ እናንተ በእርግጥ የምታስታውሷቸው መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ
2፥187 አሏህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَخْتَانُونَ أَنفُسَكُمْ

"አል ማዲ" الْمَاضِي ማለት "አላፊ"Past" ማለት ሲሆን "ዐሊመ" عَلِمَ አላፊ ግሥ ነው፥ አሏህ ቀድሞ ማወቁ ችግሩ ምንድን ነው? "አሏህ ዐወቀ" ማለት ጥንቱንም ማወቁን ያሳያል እንጂ በዐማርኛ "ዐወቀ" ማለት ያላወቀውን ዐወቀ ማለት አይደለም። ተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር ከባይብል በንጽጽር እንመልከት! "የደ ኤሎሂም" יֵּ֖דַע אֱלֹהִֽים ማለት በአላፊ ግሥ "አምላክ አወቀ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 2፥25 አምላክ የእስራኤልን ልጆች አየ፥ አምላክ በእነርሱ ያለውን ነገር "አወቀ"። וירא אלהים את בני ישראל וידע אלהים׃

"የደ" יֵּ֖דַע ማለት "አወቀ" ማለት ሲሆን አላፊ ግሥ ነው፥ "አምላክ ቀድሞ ማወቁ ችግሩ ምንድን ነው? "አምላክ ዐወቀ" ማለት ጥንቱንም ማወቁን ያሳያል እንጂ በዐማርኛ "ዐወቀ" ማለት ያላወቀውን ዐወቀ ማለት አይደለም" ካላችሁ ይበል የሚያስብ ነው፥ እንግዲያውስ የቁርኣኑን አናቅጽ በዚህ መልክ እና ልክ ተረዱት! በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

3 weeks, 5 days ago

ያ ጀመዓህ አሠላሙ ዐለይኩም

የኡሥታዛችን አቡ ሀይደር "ቀዷ ወል ቀደር" የሚለው መጽሐፉ ሰውዲ 550 ፍሬ አለ። የምትፈልጉ ልጀች እኅት ፎዚያን 009660507751537 አግኛት!
ሌሎቻችን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።

3 months ago

የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 16ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://t.me/Jemutimenhajselfi34
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

3 months ago

እዚህ አንቀጽ "በ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲያ" διά ሲሆን "በኩል" ማለት ነው፥ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ለአብ በክርስቶስ በኩል መሆንን ያሳያል። ይህንን ከተረዳን ዘንድ ኢየሱስ መንበርከኪያ መሣሪያ"Instrument" እንጂ የሚንበረከኩለት ማንነት እና ምንነት አይደለም፥ "ፊልጵስዩስ 2፥10 ላይ መንበርከክ ለኢየሱስ እንደሆነ ያሳያል" የሚለው ሙግት ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ሙግት ነው። “በ” አስመላኪ ሲሆን “ለ” ደግሞ ተመላኪ ነው፥ “በ” የሚለውን “ለ” ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ “በ”-ጽዮን” የሚለውን “ለ”-ጽዮን” ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦
መዝሙር 65፥1 አቤቱ “በ”-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון

ዋናው ነጥብ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክ ለኢየሱስ ስም ሳይሆን በኢየሱስ ስም ለፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አስመላኪ እንጂ ተመላኪ አይደለም፥ ለፈጣሪው ተንበርክኮ የሚያመልክ አካል ተመልሶ ተመላኪ አይሆንም። ኢየሱስ እራሱ በጉልበቱ ተንበርክኮ እና በፊቱ ተደፍቶ ወደ ፈጣሪ ይጸልይ ነበር፦
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀ እና ሲጸልይ። καὶ προελθὼν μικρὸν ἔπεσεν ἐπὶ πρόσωπον αὐτοῦ προσευχόμενος
ሉቃስ 22፥41 ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ "ተንበርክኮም" ጸለየ። καὶ αὐτὸς ἀπεσπάσθη ἀπ’ αὐτῶν ὡσεὶ λίθου βολήν, καὶ θεὶς τὰ γόνατα προσηύχετο

ሸብረክ እና ብርክክ ብሎ ለፈጣሪው ሡጁድ የሚወርድ ኢየሱስ እራሱ አምላኪ መሆኑን ይህ ጥቅስ ጉልኅ ማሳያ ነው፥ እንደው ለኢየሱስ ቢንበረከኩለት እንኳን መንበርከክ በእስራኤል ባህል አክብሮትን ለማሳየት ይመጣል፦
2ኛ ነገሥት 1፥13 በኤልያስ ፊት በጒልበቱ "ተንበረከከ"። וַיִּכְרַ֥ע עַל־ בִּרְכָּ֣יו לְנֶ֣גֶד אֵלִיָּ֗הוּ

"ዪክራ" כְרַ֥ע የሚለው የግሥ መደብ "ካራ" כָּרַע ለሚለው አሁናዊ ግሥ ነው፥ ታዲያ አምሳ አለቃው ለኤልያስ በጒልበቱ ስለተንበረከከ ኤልያስን እያመለከው ነበርን? እረ በፍጹም። ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የምድረ በዳ ዘላኖች እንደሚንበረከኩለት ተናግሯል፦
መዝሙር 72፥9 የምድረ በዳ ዘላኖች በፊቱ ይንበረከካሉ። לְ֭פָנָיו יִכְרְע֣וּ צִיִּ֑ים

"ጺዪ" צִיִּי ማለት "የምድረ በዳ ዘላን" ማለት ሲሆን የጺዪ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ጺዪም" צִיִּ֑ים ነው፥ ይህም ቃል የበረሃ ሰውን ወይም የዱር አውሬን ለማመልከት ይመጣል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ይንበረከካሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ይክራዩ" יִכְרְע֣וּ ሲሆን "ካራ" כָּרַע ማለትም "ተንበረከከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ነው፥ ስለዚህ መንበርከክ በራሱ አምልኮ አይደለም። ዋናው ነጥባችን "ፊልጵስዩስ 2፥10 ላይ በሰማይ እና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም የሚንበረከኩት ለአብ እንደሆነ የሚናገር ክፍል ነው" የሚል ሰፊ ሙግት ነው፥ በእርግጥ ለእኛ ለሙሥሊሞች የጳውሎስ ንግግር መረጃ"Information" እንጂ ማስረጃ"Evidence" አይደለም። የአምላካችን የአሏህ ንግግር ማስረጃችን ሲሆን ኢየሱስ የመልእክቱ ጭብጥ «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» የሚል እንደነበር አሏህ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ፍጡር ከማምልከ ነጻ ወጥታችሁ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

3 months ago

መንበርከክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ፈጣሪ በመጀመሪያ መደብ "ጕልበት ሁሉ “ለ”-እኔ ይንበረከካል" በማለት ይናገራል፦
ኢሳይያስ 45፥23 ጕልበት ሁሉ “ለ”-እኔ ይንበረከካል። כִּי־לִי֙ תִּכְרַ֣ע כָּל־בֶּ֔רֶךְ

"ሊ" לִי֙ ማለት "ለእኔ" ማለት ሲሆን "እኔ" በሚል ተውላጠ ስም መነሻ ላይ ያለው "ለ" የሚል መስተዋድድ መንበርከክ ለእርሱ እንደሆነ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ "ለ" ቀጥታ የሚንበረከኩለት ማንነት እና ምንነት ነው፦
ሮሜ 14፥11 "ጉልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል"። ὅτι ἐμοὶ κάμψει πᾶν γόνυ, 

"ኩርዮስ" Κύριος ከቀኝ ወደ ግራ የሚነበቡት ቴትራግራማቶን ስለሚያመለክት እና ከኢሳይያስ 45፥23 ላይ ስለተጠቀሰ "ዮድ ሔ ቫቭ ሔ" יְהוָה֮ የተባለውን አብን አመላካች ነው፦
ኤፌሶን 3፥15 ስለዚህ ምክንያት በሰማይ እና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ። ἐξ οὗ πᾶσα πατριὰ ἐν οὐρανοῖς καὶ ἐπὶ γῆς ὀνομάζεται,

"ከአብ ፊት እንበረከካለሁ" የሚለውን አስምረህ በሰማይ እና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለአብ የሚንበረከከው "በ"-ኢየሱስ ስም እንደሆነ ጳውሎስ ተናግሯል፦
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይ እና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ነው። ἵνα ἐν τῷ ὀνόματι Ἰησοῦ πᾶν γόνυ κάμψῃ ἐπουρανίων καὶ ἐπιγείων καὶ καταχθονίων,

እዚህ አንቀጽ "በ" ለሚለው መስተዋድድ የገባው ቃል "ኤን" ἐν ሲሆን "በኩል" ማለት ነው፥ "ዲይ" δἰ ወይም "ዲያ" διά ከሚል ቃል ጋር ተለዋዋጭ ነው። "ኤን ቱ ኦኖማቲ የሱ" ἐν τῷ ὀνόματι Ἰησοῦ ማለት "በኢየሱስ ስም" ማለት ስለሆነ የተለያዩ ዕትማት በትክክሉ "በኢየሱስ ስም"in the name of Jesus" በማለት አስቀምጠዋል፦
1. American Standard Version
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
2. Aramaic Bible in Plain English
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
3. English Revised Version
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
4. Literal Standard Version
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
5. Young's Literal Translation
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"

ብዙ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች "በኢየሱስ ስም" የሚለው "ለኢየሱስ ስም" በማለት እያጠናገሩ ስለሆነ ትኩረት ሰቶ ማንበብ ያሻል፦
ኤፌሶን 5፥20 ሁልጊዜ ስለ ሁሉ "በ"-ጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን እና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ። εὐχαριστοῦντες πάντοτε ὑπὲρ πάντων ἐν ὀνόματι τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ τῷ Θεῷ καὶ Πατρί,

አሁንም "በ" ለሚለው መስተዋድድ የገባው ቃል "ኤን" ἐν ሲሆን "በኩል" ማለት ነው፥ ጳውሎስ "አምላካችንን እና አባታችንን" ያለው አብን በኢየሱስ ስም ስለማመስገን ብዙ ቦታ ይናገራል፦
ሮሜ 1፥8 አምላኬን “በ”-ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ። εὐχαριστῶ τῷ Θεῷ μου διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ 
ሮሜ 7፥25 “በ”-ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን “ለ”-እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።χάρις τῷ Θεῷ διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν. 
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። μόνῳ σοφῷ Θεῷ, διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ᾧ ἡ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.

ሦስቱም አናቅጽ ላይ "በ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲያ" διά ሲሆን ምስጋናው "አምላኬ" ለሚለው ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር አብ ነው፦
ቆላስይስ 3፥17 እግዚአብሔር አብን “በ”-እርሱ እያመሰገናችሁ። εὐχαριστοῦντες τῷ Θεῷ Πατρὶ δι’ αὐτοῦ.
ዕብራውያን 13፥15 እንግዲህ ዘወትር “ለ”-እግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ “በ”-እርሱ እናቅርብለት። δι’ αὐτοῦ οὖν ἀναφέρωμεν θυσίαν αἰνέσεως διὰ παντὸς τῷ Θεῷ, τοῦτ’ ἔστιν καρπὸν χειλέων ὁμολογούντων τῷ ὀνόματι αὐτοῦ.

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "በ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲይ" δἰ ሲሆን ምስጋናው “ለ”-እግዚአብሔር አብ" ነው፥ "ለ" መስተዋድዱ የሚጠጋው ብቻውን ለሆነ አምላክ እና መድኃኒት ነው፦
ይሁዳ 1፥25 ብቻውን "ለ"-ሆነ አምላክ እና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ "በ"-ጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን! አሜን። μόνῳ Θεῷ Σωτῆρι ἡμῶν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν δόξα μεγαλωσύνη κράτος καὶ ἐξουσία πρὸ παντὸς τοῦ αἰῶνος καὶ νῦν καὶ εἰς πάντας τοὺς αἰῶνας· ἀμήν.

3 months, 1 week ago

ትንቅንቅ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

40፥41 «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ማለት "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብሎ ለእርሱ ብቻ መገዛት ነው፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِين

እዚህ አንቀጽ ላይ “ታዘዙ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ሲሆን “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፥ “አሥሊሙ” የሚለው ቃል “ሙሥሊም” مُسْلِم ለሚለው ቃል ትእዛዛዊ ግሥ ነው። ሙሥሊም ወደ አሏህ በመጥራት ቃሉ ያማረ ነው፦
41፥33 ወደ አሏህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ፦ «እኔ ከሙሥሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ሙሥሊም ሰዎችን የሚጠራው ወደ መዳን ነው፥ ሰዎች ከእሳት እንዲያመልጡ ነው። ሙሽሪክ ደግሞ ወደ እሳት ነው የሚጠራው፦
40፥41 «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

ሙሽሪክ ጥሪው በአልምህ ለማስካድ እና በእርሱም ዕውቀት የሌለንን ነገር በእርሱ እንዳጋራ እንድናጋራ ነው፥ ሙሥሊም ግን ወደ አሸናፊው መሓሪው አሏህ ነው፦
40፥42 «በአሏህ ልክድ እና በእርሱም ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ፡፡ እኔም ወደ አሸናፊው መሓሪው አሏህ እጠራችኋለሁ፡፡ تَدْعُونَنِي لِأَكْفُرَ بِاللَّهِ وَأُشْرِكَ بِهِ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ وَأَنَا أَدْعُوكُمْ إِلَى الْعَزِيزِ الْغَفَّارِ

እንግዲህ በሙሥሊም እና በሙሽሪክ መካከል ያለው ትንቅንቅ ይህ ነው፥ ወደ አሏህ መጣራት ይህ መንገዳችን ነው። ከአጋሪዎች አይደለንም፥ ይህም ቀጥተኛ  መንገድ ነው። ሌሎች የጥመት መንገዶችንም አትከተል፥ ከቀጥተኛው መንገድ እኛን ለመለየት ነው ጥሪው፦
12፥108 «ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአሏህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡፡ قُلْ هَـٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
6፥153 «ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ፡፡» وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

አምላካችን አሏህ ይህንን እውነተኛ የተውሒድ መንገድ አመጣልን፥ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች እውነቱን ጠይዎች ናቸዉ፦
43፥78 እውነተኛውን መንገድ በእርግጥ አመጣንላችሁ፡፡ ግን አብዛኞቻችሁ እውነቱን ጠይዎች ናችሁ፡፡ لَقَدْ جِئْنَاكُم بِالْحَقِّ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَكُمْ لِلْحَقِّ كَارِهُونَ

ሙስሊም ወደ አንድ አምላክ መንገድ  ሲጣራ መጣራት ያለበት “ስሙር ሙግት”valid argument”  ተጠቅሞ ነው፤ ይህ ሙግት በእማኝነትና በአስረጂነት ጠቅሶና አጣቅሶ መሟገት ነው፤ በትክክለኛው የአስተላለፍ ስልትና አወቃቀር ስለተዋቀረ የራሱ የሆነ መንደርደሪ፣ የሙግት ነጥብ”premise” እና መደምደሚያ ያለው ነው፤ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ማስረጃ በአጽንኦትና በአንክሮት ለማዳመጥ ጥልና ጥንፍፍ ያለ መረዳት ነው፤ ይህን ሙግት አምላካችን አላህ መልካም ክርክር ይለዋል፤ ይህ ዘዴ ርቱዕ አካሄድ”optimistic approach” ነው፦
16፥125 ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”። ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

“ሙሽሪክ” مُشْرِك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በአንድ አምላክ ላይ ሌሎች ማንነቶችንና ምንነቶችን "አጋሪ" ማለት ነው፥ ድርጊቱ  “ሺርክ” شِرْك ማለትም  “ማጋራት” ይባላል፤ በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ።    
ይህ ትንቅንቅ ይቀጥላል፤ ሙሽሪክ፦
1ኛ  ሦስት ማንነቶችን ማለትም ሥላሴን እንድናመልክ ይጠሩናል፥ ግን መመለክ ያለበት አንድ ማንነት ብቻ ነው።
2ኛ  ሰው እንድናመልክ ይጠሩናል፤ ኢየሱስ ሰውነቱ ይመለካል፥ በሰውነቱ ፍጡር ነው ይላሉና።
3ኛ ፍጡራንን እንድናመልክ ይጠሩናል፥ ፍጡራንን በሌሉበት ወደ እነርሱ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመን፣ መጸለይ፣ ስለት መሳል፣ መስዋዕት ማቅረብ፣ ስማቸውን መጥራት የአምልኮ ክፍል ነው፤ ሁሉን የሚሰማ፣ የሚያይ፣ የሚያውቅ አንድ መለኮት ብቻ ሆኖ ሳለ ወደ መላእክትና ቅዱሳን ይህንን ማድረግ ሺርክ ነው።
4ኛ. ለተቀረጸ ምስል እንድንሰግድ ይጠሩናል፤ ለተቀረጸ ምስል አትስገድ ተብሎ ነገር ግን በተቃራኒው ከእንጨት፣ ከብር፣ ከወርቅ፣ ከብረት፣ ከድንጋይ ለተቀረጹ መስቀል፣ ስዕል እና ሃውልት ይሰግዳሉ። ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? እሳት መግባት አልፈልግም፦
40፥41 «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

3 months, 2 weeks ago

መልአክ ይመለካልን?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን ከማምለክ አይኮሩም። ያወድሱታልም፥ ለእርሱ ይሰግዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ

ሰዎች የማይሉትን እና የማያምኑትን እንደሚሉ እና እንደሚያምኑ አርጎ ሙግትን አዋቅሮ እና አደራጅቶ መሞገት ቁልመማዊ ሕፀፅ"strawman fallacy" ነው፥ አንድ ሰው ሰዎች የማይሉትን እና የማያምኑትን እንደሚሉ እና እንደሚያምኑ አርጎ ቁልመማዊ ሕፀፅ ማፀፅ የአጠይቆትን እሳቤ በቅጡ ያልተረዳ ሰው ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "እንዚራ ስብሐት" በሚል መድብሉ "የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ" "የአምልኮ መሥዋዕትን ለአንቺ አቀርብልሻለሁ" በማለት በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማርያምን እንደሚያመልክ ይናገራል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 12 ቁጥር 98 "ለአንቺም የምስጋና እጅ መንሻን አቀርባለሁ፣ በመፍራት እገዛልሻለሁ፣ በመስገድም እጅ እነሣሻለሁ። "የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ"።
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 13 ቁጥር 113
"ማርያም ሆይ! ያማረ ፍጹም ምስጋና አቀርብልሻለሁ። የሚጣፍጥ "የአምልኮ መሥዋዕትን ለአንቺ አቀርብልሻለሁ"።

"ለአንቺ" የሚለው ይሰመርበት! ለዚህ ጥያቄ መልስ ቀጥታ መመለስ ያቃተው ዲያቆን ዘማርያም(ቴዲ) "በባይብልም እኮ መልአክ እንደሚመለክ ይናገራል፥ ያ ትርጉም ከገባችሁ ይህንን መረዳት ቀላል ነው" በማለት ተቃራኒ አጸፋ ከመስጠት ይልቅ ከትካች አጸፋ በመስጠት አግባባዊ ሕፀፅ"Relevance fallacy" ሲያፅፅ ነበር። አንዱ ቀዳዳን ለመድፈን ሌላው ሲቦተረፍ የታየበትን ጥቅስ እንመልከት፦
የሐዋርያት ሥራ 27፥23 የእርሱ የምሆን እና ደግሞ የማመልከው የአምላክ መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና። παρέστη γάρ μοι ταύτῃ τῇ νυκτὶ τοῦ Θεοῦ, οὗ εἰμι, ᾧ καὶ λατρεύω, ἄγγελος

"ላትሬኦ" λατρεύω ማለት "አምልኮ" ማለት ሲሆን "የማመልከው" የሚለው የሚጠጋው "አምላክ" ወደሚለው እንጂ "መልአክ" ወደሚለው አይደለም፥ ይህ ሰው እንግሊዝኛ፣ ግዕዝ እና ግሪክ ቢያንስ እንዲያጠና ምከሩት! "የአስቀሪዬ የኡሥታዝ ልጅ ሰላም አለኝ" ብል "የአስቀሪዬ" የሚለው የሚጠጋው "ኡሥታዝ" ወደሚለው እንጂ "ልጅ" ወደሚለው አይደለም። አንድ ተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር እስቲ እንመልከት፦
ራእይ 6፥9 የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። εἶδον ὑποκάτω τοῦ θυσιαστηρίου τὰς ψυχὰς τῶν ἐσφαγμένων

ሰው እንጂ ነፍስ እንደማይታረድ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን "የታረዱትን" የሚለው የሚጠጋው "ሰዎች" ወደሚለው እንጂ "ነፍሳት" ወደሚለው አይደለም። "የ" የሚል አገናዛቢ ዘርፍ ያለበት "ሰዎች" የሚለው ቃል ባለቤትን ስለሚያሳይ "የታረዱትን" የሚለው የሚጠጋው "ሰዎች" ወደሚለው እንደሆነ ሁሉ "የ" የሚል አገናዛቢ ዘርፍ ያለበት "አምላክ" የሚለው ቃል ባለቤትን ስለሚያሳይ "የማመልከው" የሚለው የሚጠጋው "አምላክ" ወደሚለው ነው፥ ጳውሎስ የማመልከው የሚለው አምላክን እንጂ መልአክን በፍጹም አይደለም፦
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥3 ሌሊት እና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን አምላክን አመሰግናለሁ። Χάριν ἔχω τῷ Θεῷ, ᾧ λατρεύω ἀπὸ προγόνων ἐν καθαρᾷ συνειδήσει, ὡς ἀδιάλειπτον ἔχω τὴν περὶ σοῦ μνείαν ἐν ταῖς δεήσεσίν μου νυκτὸς καὶ ἡμέρας,

"የማመልከውን አምላክን" የሚለው ኃይለ ቃል የሚመለከው አምላክ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። "እንደ አባቶቼ አድርጌ" የሚለው ቃል ከጥንት ጀምሮ አባቶች ሲያመልኩት የነበረው መልአክን ሳይሆን አምላክን ነው፥ የኦርቶዶክስን አምልኮተ ማርያም ስህተት ለመሸፈን ባይብል ውስጥ ገብቶ መደበቅ አግባብ አይደለም።

ይህንን መጣጥፍ መልስ ለመስጠት የተነሳሁበት ዓላማ ኦርቶዶክሳውያን "እኛ ማርያምን አናመልክም፥ ቁርኣን ቁልመማዊ ሕፀፅ ሐፅፆአል" ብለው ለከሰሱት የሐሰት ክስ ምላሽ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "እንዚራ ስብሐት" መድብል ላይ አንብበን ያቀረብነው እኛ ሙሥሊሞች ነን፥ ይህንን ሙግት ፕሮቴስታንቱ ከእኛ ተቀብለው ሲያራግቡ ዲያቆን ዘማርያም መልስ ብሎ የመለሰው ገለባ መልስ እኛ ስለሚመለከት ብቻ ነው እንጂ በሰው ጉዳይ ለመፈትፈት አይደለም።

አሳብ መሞገት የሚበረታታ ጉዳይ ነው፥ በአሳብ ሉዓላዊነት፣ ልዕልና፣ ገዢነት እና ዘውግ የሚያምን ሰው ረብጣ የሆነ አሳብ ሲመጣለት በተሻለ አሳብ ማረቅ እና ማሳለጥ እንጂ እርር እና ምርር ብሎ መንጨርጨር እና መንተክተክ አግባብ አይደለም።

ከአንዱ አምላክ በቀር ለአንዳች ነገር የአምልኮ መሥዋዕት መሠዋት በገሃነም ሊያስጠፋ የሚችል ወንጀል ነውና ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፈርታችሁ ከዚህ ድርጊት ተቆጠቡ፦
ዘጸአት 22፥20 ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።
ማቴዎስ 10፥28 ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።

ከአምልኮተ ማርያም ወጥታችሁ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

3 months, 2 weeks ago

ሦስት ፀሐይ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ

አምላካችን አሏህ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነው፥ ለእርሱ ሞክሼ የለውም፦
19፥65 እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና አምልከው! እርሱን በአምልኮቱ ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا

አሏህ ከፍጥረት የሚመስለው ምንም ነገር የለም፥ ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፦
42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

"ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ቢጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ የለውም። በዲኑል ኢሥላም ለአሏህ አምሳያዎችን ማድረግ ሺርክ ነው፦
16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ

ነገር ግን በቤተክርስቲያን አበው አምላክን በፀሐይ ይመስሉታል፥ ፀሐይን ለአምላክ ሦስትነት ይጠቀሙበታል። "የፀሐይ ክበቡ አብ፣ ብርሃኑ ወልድ፣ ሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ" በማለት ይናገራሉ፥ ይህ የአምላክን ሦስትነት ያሳያልን?
፨ ሲጀመር ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አብ ካልሆኑ ብርሃን እና ሙቀት ግን ከክበቡ ከመውጣታቸው በፊት እራሱ ክበቡ ናቸው።
፨ ሲቀጥል ከክበቡ የሚወጡት ሦስት ናቸው፥ እነርሱም ብርሃን፣ ሙቀት፣ ጨረር ናቸው፥ ከክበቡ ጋር አራት ይሆናሉ።
፨ ሢሰልስ ለወልድ ምሳሌ የተሰጠው ብርሃን ከነበረ "ብርሃናት" የብርሃን ብዙ ቁጥር ነው፥ አንዱ ብርሃን አብ ሁለቱ ብርሃናትን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በጥቅሉ ሦስት ብርሃናት ናቸው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 10 ቁጥር 6
"ዕውቀትን የሚገልጹ ብርሃናት ናቸው"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 10 ቁጥር 12
"አብ ብርሃን ነው፣ ከአብ የተወለደ ቃሉ ወልድ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፣ እንዲሁ ከአብ የሠረፀ መንፈስ ቅዱስም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው"።

፨ ሲያረብብ ፀሐይ አንድ አካል(Body) እንጂ ሦስት አካል አይደለችም፥ ክበብ፣ ብርሃን፣ ሙቀት፣ ጨረር የፀሐይ ክፍሎች እንጂ ማንነት(Person) አይደሉም። እንደ ሥላሴ ትምህርት ሦስቱ አካላት ማንነት እንጂ ክፍሎች"Particles" አይደሉም፥ ፀሐይ አንድ ስትሆን ሥላሴ ግን ሦስት ፀሐይ፣ ሦስት የብርሃን አዕማድ፣ ሦስት የእሳት ባሕርይ ናቸው፦
"ሦስት ፀሐይ" ብለው አስቀምጠዋል፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 21
"ሦስት ፀሐይ አንድ ብርሃን ነው"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 21
"ሦስት የብርሃን አዕማድ በመጠን ግን አንድ ነው"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 17
"ሦስት የእሳት ባሕርይ ነገር ግን አንድ ብርሃን ነው"።

አንዱን አምላክ በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? ይህ እኮ ነውር ነው፦
ኢሳይያስ 40፥18 እንግዲህ አምላክን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?
ኢሳይያስ 46፥5 በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?

ፈጣሪ፦ "በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ? እያለ እናንተ በፀሐይ፣ በውኃ፣ በእንቁላል፣ በሻማ፣ በባሕር እንዴት ትመስሉታላችሁ? አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

6 months, 1 week ago

አምላካችን አሏህ በዒሣ ቀዳማይ ተከታዮች ልቦች ውሰጥ መለዘብን እና እዝነትን አድርጎ ሳለ የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ምንኩስና ፈጠሩ፥ ነገር ግን አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስናን በእነርሱ ላይ አልደነገገም። ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ሲሆኑ ጥቂት አሓዳውያን በቁርኣን ላመኑት ምንዳቸውን ሰጣቸው፦
57፥27 ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፥ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ فَـَٔاتَيْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌۭ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ

እነዛ ጥቂት አሓዳውያን ቁርኣን በወረደበት ጊዛ በቁርኣን አምነዋል፥ ቁርኣን በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በቁርኣን አምነናል፡፡ ቁርኣን ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ "እኛ ከቁርኣን በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ "በእርሱ ያምናሉ"፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ "እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

"እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን" የሚለው ይሰመርበት! "ሙሥሊም” مُسْلِم ማለት "አንዱን አምላክ በብቸኝነት አምላኪ፣ ተገዢ፣ ታዛዥ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ሙሥሊሞች" ለሚል የገባው ቃል "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው። ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የመጣው ወሕይ ጭብጡ እና አንኳር መልእክቱ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" የሚል ነው፦
6፥19 «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
21፤108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين እንደሆነ ልብ አድርግ! "አንድ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል “ዋሒድ” وَٰحِد ነው፥ "አሏህ አንድ ነው" ብሎ የሚያምን አማኝ “ሙዋሒድ” مُوَٰحِد ሲባል የአንድ አምላክ አስተምህሮቱ ደግሞ "ተውሒድ" تَوْحِيد ይባላል። ከእነርሱም ብዙዎቹ ከቀጥተኛው መንገድ ከተውሒድ ወጥተው በሥላሴ በማመን የተሳሳቱ ናቸው፥ ቅሉ ግን ጥቂት ያልተሳሳቱ የኢየሱስ ተከታዮች ነበሩ፦
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ "አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው"። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ሙዋሒዲን የሄዱበትን መንገድ "ምራን" ብለን እንቀራለን። ታዲያ ሞናርኪያውያን በታሪክ ውስጥ ምን ሆኑ? አሁን ላይ የት አሉ? ኢንሻላህ ይቀጥላል.....

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago