ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ተፃፈ -አምረን(አሙ) እስኪ ርእስ ስጡልኝ… ከአዲሱ ታሪክ የተቀነጨበ ነው😘
ቢላ አንስቶ አዛዝጎ
ለሚከትፍ ስራው አርጎ
በደል ውሉ እዝነት ላጣ
ይቅር ማለት መራራቱ ከየት ይምጣ?!
ላላዘነ በቁም ቀብሮ
ላቆሰለ ልብን ሰብሮ
ላላረካው ድርብ ህመም
ምን ቆርጦኝ ምን ፈቅዶኝ አየሁትኝ ባንተ አይደረስ አትታመም…
ምን ቸርነት ምን ደግነት
ምን መራራት የምን እዝነት
በደል ያየው ላይፈርድብኝ
ቁስሌን የሚያውቅ ላያዝንብኝ
ላቆሰለኝ ላሳመመኝ
ምህረት ብነፍግ ማን ሊወቅሰኝ?!
ካላስገባው የኔ ጫማ
የከበደው የኔ ማማ
ለአስቃይ ለአስለቃሽ
ምህረት ብሎ ማነው ወቃሽ?!
እኮ ማን?!
ላልታዘበ የውስጥውስጡን
ላልቀመሰ ቁስል ቅጡን
ማለት ቢቀል ይቅር በሉ
ላልቆመበት ቢሆን ውሉ
ወቃሽ ናቂ ታማሚ ልብ
ሃኪም ያጣች ደካማ ቀልብ
ከሆነ አቅሟ መለመኑ
ለተበዳይ ዝም አይልም መናኑ!
ክፉ አትበሉኝ አላያችሁ
ስቃይ በደል ያልገባችሁ
አትፍረዱ ቀን ይፈርዳል
ወቃሽ ከንፈር ይወቀሳል!
አይደሉሁም አረመኔ
ለበደለኝ ብመኝ እኔ
ፍርዱን ከላይ ከጠየቅኩኝ
በሚፈርደው አትውቀሱኝ
ከአዛኝ አዛኝ ባለእዝነቱ
ይሁን ካለ በሂክመቱ
ከፈረደ በጥበቡ
እውነት አለኝ ነው ሂሳቡ!!
ይቀጥላል እስኪ እችላለሁ እንዴ☺️🥰
አሰላሙ አለይኩም ያጀማአ አላችሁ😍🥰
ኡሚ ሞሪንጋ🌿
የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን እየሰጠ ያለውና ለብዙ የጤና እንከኖች መፍትሔ ከመሆኑም በላይ ለጠንካራ እና ለስላሳ ፀጉር፣ለተስተካከለ የሰውነት ቅርፅ፣ እንዲሁም ለአጥንት ጥንካሬ እና በመገጣጠሚያ ላይ ለሚደርሱ ኢንፌክሽን እና እብጠቶች ለመከላከል በውስጡ ካልሺየም እና ፎስፈረስ የተባሉ ማእድናትን አምቆ የያዘውን፣ ለአስም ፣ለካንሰር እንዲሁም ከ50በላይ ለሚሆኑ በጤና ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመመከት አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለውን የሞሪንጋ ሻይ ዱቄት በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ዘንድ ያግኙ… ዋጋችን እጅጉን የተመጣጠነና ኪስ የማይጎዳ ከመሆኑም በላይ በብዛት መረከብ ለሚፈልጉ ደንበኞች ሰፋ ያለ discount እናደርጋለን።
ጥራቱን የጠበቀ የሞሪንጋ ሻይ ከፈለጉ፦ "ኡሚ"ሞሪንጋ ብለው በነዚህ አማራጮች ያግኙን👇
🤳0951051310
0987073746
0799110410
0703652703
ዱአሽን አላህ ሲቀበል ሙልት አድርጎ ነው። ባልሽ ባለፈው ህይወቱ ምናልባት አቶጂው ይሆን ይሆናል። አላህ ሲያዝን አበጀልሽ። ታውቂያለሽ ለራሴ እስክሰስት እወድሻለሁ😘 ፍቅር እስኪያንስብኝ ባጣሽ ምሞት እስኪመስለኝ" በደስታ ተቃቅፈን ቆየን። "ለምን የባለፈውን ጨዋታ እኔ እና አንተ አንሞክረውም…?" አለቺኝ። ለሰከንዶች የተለየ ነገር ነበር ያሰብኩት። አይኖቼን አንዴ ወደግራ አንዴ ወደሷ ሳይ "ባክህ እነ ማቲ ጋር የተጫወትነው እህ truth or Dare" ልስቅ አቃጣኝ እና ዋጥ አደረግኩት። "እሺ አልኳት እየተስተካከልኩ። "የላ በተራ ተራ እናድርገው ጀምር…" አለቺኝ።
"እሺ ምረጪ…"
"እውነት…"
"መቼ ነው እኔን በተለየ መንገድ ያየሺኝ…?" አይኖቿን በሁለት እጆቿ ይዛ ማውራት ጀመረች ።
"ያኔ ላብራቶሪ ክፍል ውስጥ ሳታስበው ትክ ብለክ ስታየኝ…"
"እሺ ግለጪ የኔ ልዩ…" እጆቿን ከአይኖቿ ላይ አንስቼ ሳምኳቸው።
"በል ምረጥ…"
"እውነት ነዋ…!"
"እሺ ከእኔ በፊት እንደዚህ እቅፍ ያደረግካት ሴት አለች…?" ውርር አደረገኝ ምን ልበላት? አይ ብዬ ልዋሽ ወይስ አው ብዬ ላስከፋት? ግራ ገባኝ ወዲያው "እህ… አለች እህቴም እኮ ሴት ናት" ብዬ አስቀየስኩ። ግን እኮ አቅፌያለው። አስታግፊሩላህ! ጌታዬንስ ምን ብዬ አስቀይሰዋለው እያወቀ ሲጠይቀኝ?! ኢግፊርሊ ያረብ!
"ሀ ሀ! the ማስቀየስ ይሁን እሺ የኔ ተራ ነው dare…" የፈለግኩትን ማዘዝ እንደምችል ሲሰማኝ ደስ አለኝ። "ግጠሚልኝ…" አልኳት። አይኖቿን ፍጥጥ አድርጋ ከሳቀች በኋላ
"ፀሀይ ጠዋት ወጥታ ቀንን ታደምቃለች
ማታ ደግሞ ጠልቃ ታጨላልማለች፣
ምኞቴን ታዝበክ ኢፍሩን ካልከው የኔ…
ጀሊል በራህመትህ በሞት እንኳን ቢሆን አትለየው ከጎኔ!"
ይህን ያክል እወደዳለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ውድድ ውድድድድድ… ፍቅር ፍቅርቅርቅርቅር… ራህመት! ዝም ብዬ ሳያት
"ኢፍሩዬ ያንተ ተራ ነው ላዝክ ነው!" አለቺኝ። ፈገግ እያልኩላት "ታዛዥ ነኝ…" አልኩ።
"አሁን… " አለች አሰብ እንደማድረግ ብላ "አሁን… ኒቃቤን ፈተክ ጉንጬን ትስመኛለክ!" አይኖቿን ቁልጭልጭ አደረገች። ልቤ መምታት ጀመረ።ማፈር አይቻልም፡ ደግሞ አላይሽም ብሎ ነገር አለ እንዴ? ኒቃቧን መፍታት ጀመርኩ። አይን አይኔን ታየኛለች። ፈትቼው አየኋት! በህይወት ዘመኔ እንዲህ የደነገጥኩበት ቀን አልነበረም። እንዴ ራህመት ማለት…? ግራ ገባኝ! ጭንቅ አለኝ ቅዠትም መሰለኝ። ፍንክንክ ትላለች! ምን ማለት ነው?! ብድግ ብዬ ተነሳው! አንቺ… አንቺ ሃያት ነሽ?! ሀዩ አልገባኝም?! ……
#ክፍል_8 ይቀጥላል ግን promissed ከ70ላይክ በኋላ እንደምንም ሙሉልኝ share Like Comment 🥰🥰
🥀ኢፍራዝ
ፀሀፊ-አምረን አብድልሃኪም(አሙ)
ወደኮሌጁ እየመጣ መንገድ ላይ መንገድ ላይ ተገጣጠምን። አቅፌ ጀርባውን ደበደብኩት። ለባህሩ እኮ መናገር አይጠበቅብኝም።"እንኳን ደስ አለህ ኢፍራዜ! ኒካሁን በቅርብ " አለኝ ኮስተር ለማለት እየሞከረ። ፈገግ ብዬ "ኢንሻአላህ" አልኩት። ሁኔታዬ በፍቅር ተስተካከለ።መቼም ላገኘው በማልችለው ደስታ ተዋጥኩ።ስለራህመት ልቤ እርግጠኛ ሆኗል። አንድ የከበደኝ ነገር ግን የራህመት አይኖች ፍፁም በሚባል ደረጃ ከሀዩ ማለቴ ከሀውለት ጋር መመሳሰላቸው ነበር።ከራህማዬ ጋር ድጋሚ ሳናወራ 1ሳምንት ተቆጠረ። እንዲሁ ነገሩ ተደባብሶ እንዳያልፍ በሚል ድጋሚ በጠዋት መጥቼ ጠበቅኳት። እንደልማዷ በጊዜ ነበር የመጣችው ዛሬ ግን ፈርታኛለች። ፍርሃቷ ደስ ሚል ንዝረት ያሰማኛል።እርስበርስ ከመሳሳቅ ውጪ ማውራት እራሱ ፈርተናል። እንደምንም መጥታ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ዝም አለች። "ራህማዬ… " የማንንም ስም በዚህ መንሰፍሰፍ ጠርቼ አላውቅም። የሀዩንም ጭምር! "ወዬ… " አለች። ቀና ብላ ስታየኝ ልላት የነበረው ጠፋብኝ። ከብዙ መመሰጥ በኋላ "ኢፍሩዬ ቶሎ ኒካህ እሰርልኝ"አለች። ዛሬ በዚች ቅፅበት ሚደረግ ቢሆን ኖሮ አስር ጊዜ አግብቻት ነበር። "መቼ… " አልኳት። "እሱ ባንተ ምርጫ አይሻልም ግን በቅርቡ ቢሆን ጥሩ ይመስለኛል" እራሴን ታዘብኩት ወዲያው ሽማግሌ መላክ ነበረብኝ። ልጅት እኮ የተከበረች ናት እንዴት ነው በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምጥላት! "እሺ በቅርቡ ቃል እገባለሁ ራህመቴ…" ፍንድቅ ስትል ልቤ ይመታላታል። ምን አይነት ፍቅር ነው ግን እኔ ላይ ሚወድቀው? ቀይስ ይህን ያክል ለይላን ይወዳት ነበር…? ሮሚዮስ ቢሆን ከእኔ የበለጠ አፍቃሪ ከነበር እንዴት ነበር ያፈቀረው…? በራህመት ክንፍ አልኩ በዚያው ሳምንት ጁምአ አያቷ ቤት ሽምግልና ላኩ። ከአጎቴ ጋር ሰላም ብንፈጥርም ትንሽ ቁርጥማት ነገር ስላጋጠመው ሊሄድልኝ አልቻለም በምትኩ ባህሩ ሰሊሜ ፉአዴ እና የአጎቴ ጓደኞች ሰብሰብ ብለው ሄዱ። ኒካህ መፈቀዱን ባህሩ ደውሎ ቢነግረኝም ራህመትን ሚድርልኝ ወሊይ ጠፋ! አባቷን ከስም ባለፈ የማታውቀው ራህመት ወንድምም ቢሆን የላትም! ራህመት መርዋን የአባቷ ስም ከአጎቴ ስም ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ እሱን እንደ አባት ሆኖ እንዲድራት አስፈቀደቺኝ እኔም ደስ ብሎኝ ለአጎቴ ነገርኩት። የአጎቴ ሁኔታ ሁሉን አስረስቶ ሆዴን አባባው! "ልጄስ ማንን ይሁን ምትጠይቀው…" ጉንጮቹ በውሃ ታጠቡ እንደምንም አፅናንቼ ተስማምቶ ራህመትን አጎቴ ዳረልኝ ያው ሸሪአ ፍርድ ቤት። እኔ እና ራህመት ኒካህ አሰርን። ብዙ ነገሮች ላይ ሀያእዋ ላቅ ያለ ነበር። ፊቷን ከሰርጋችን በፊት እንደምታሳየኝ ቃል ገባቺልኝ። ላቅፋት እንኳን የዛን ቀን አልፈቀደችም። ሁለት ቀን ክላስ ቀጥተን አንድ ቦታ ወሰደቺኝ። ደስ የሚል ሬስቶራንት ቦታ ያስያዘው ማን እንደሆነ እንድትገምቱ ለናንተው ተውኩት ያው በኋላ ካላመለጠኝ ሃሃ… ብቻ ቀኑን ስንዝናና ውለን ማታ ወደክፍላችን ገባን። ከሰርግ በፊት ምንም እንደማይፈጠርና ፊቷን ብቻ ላይ ተስማማን። ከዚያ በፊት ግን ትንሽ ልናወራ ተስማማን። "ሁቢዬ… " አለች ኒካሀችን ድፍረቷን ሙልት አድርጎላት። "ወዬ…" አልኳት። "ግን እንዴት ልትመርጠኝ ቻልክ ያውም ሳታየኝ…?" የኔም ጥያቄ ነው። ስለመልኳ አይደለም። ስለሀብቷም አላውቅም። ዝና እና ክብሯም አይደለም ራህመትን ነው ያፈቀርኳት። ይሄ እውነተኛ ፍቅር ነው።
ዝርዝር አድርጌ ነገርኳት። እሷም ፍንድቅ እያለች እቅፌ ውስጥ ገባች። ራህመትን ሳቅፋት ኢላሂ እስከዛሬ ያቀፍኳቸው ሴቶች ዘገነኑኝ። ሙቅ እቅፍ! ሀላሌ😘 ሳልጠይቅ ኒቃቧን መፍታት ጀመርኩ ታዘዘችልኝ። ወዲያው ግን እሰረው እሰረው ሚል ስሜት ተሰምኝ። "ምነው…?" አለቺኝ። "ራህመቴ ውስጤ ይሄን ሀሴት ሊያጣው እንደሚችል ተሰማኝ ይቆይ እስኪ አልይሽ…" ሳቅ ብላ "አስቀያሚ ትሆናለች ብለክ ነው…" አባባሏ እጇን አደራረጓ ምናምን ሳቅበሳቅ አደረገኝ። "ማን ያውቃል…" አልኳት። አንድ ሸክ የለኝም ቆንጂዬ ስለመሆኗ የፈራሁት ምን እንደሆነ ለራሴም ግልፅ አይደለም። "መልካሞቹ ለመልካሞቹ ከተባለ ቆንጆዎቹም ለቆንጆዎቹ ሚለው እኛ ቤት ውሏል ውድ ባለቤቴ" ጉሮሮ ድረስ ቅዝቅዝ የሚያደርገውን ሳቋ ረጨችው። "ልብላሽ… እንዴ ቆይ በአላህ" ከልቤ ነበር ያልኳት። ድመትም እኮ የፍቅሯን ልጇን ትበላለች። ለራህመት ፍቅር ሚባለው ሀል አንሶብኝ ዋጥ አድርጋት ይለኛል። "ም…ን?!"አይኖቿን አሰፋፍታ "እራሴ ዋጥ እንዳላደርግክ…" እንዲው ስንፈታተል ሰአቱ ከምሽቱ አራት ሰአት ሆነ። "እንተኛ… ወይስ ታመሻለሽ" እንቆይ ብትለኝ ደስ ይለኛል እሷም አላሳፈረቺኝም። ስላሳለፈችው ህይወት በጠቅላላው ትነግረኝ ጀመር። እንዲህ ተረከችልኝ…
የተወለድኩት እዚው አዲስ አበባ ነው። አባቴን በመልክ አላውቀውም። እናቴ እንደነገረቺኝ በጣም የተበላሸ ፀባይ የነበረው እና ይቅምም እንደነበር ነው። በኢባዳም ላይ አይኖርም። ከኡሚ ጋር ብዙ ሰላም አልነበሩም። ገና ህፃን እያለሁ ኡሚ ለአያቴ ሰጥታኝ አምስት አመት ሲሞላኝ እሷም ወደውጭ ወጣች። እኔም ከአያቴ ጋር መኖሬን ቀጠልኩ።በህይወት ቆይታዬ ብዙ ተምሬያለሁ። ስራ ሰርቼም አውቃለሁ ከፅዳት እስከ መስተንግዶ። ገንዘብ ይህን ያክል ቸግሮኝ ሳይሆን እራሴን በብዙ ቦታዎች አስቀምጬው ማየት ስለምፈልግ። የሰውን ባህሪ ትረዳበታለህ። ብዙ የፍቅር ጥያቄዎችም ደርሰውኝ ያውቃሉ። ሁሉንም በቀና መንገድ አላያቸውም ነበር። ግን ሲከፋኝ ማወራለት ሳጣ ምናምን አንድ ሰው አብሮኝ ቢሆን እል ነበር። የሆነ ሰው ሲተናኮላቸው "እ… ሀቢቢ" ብለው አፍንጫውን ሲያሰብሩት አንጀቴ እየራሰ ለኔ እራሴ አለው ስል ደጋፊ ቢኖረኝ ተመኝቼ አውቃለሁ። ሁቢዬ ጓደኞቼ በሙሉ relationship ውስጥ ሲገቡ የእኔን ጠያቂዎች ፊት መንሳት ልማዴ ነበር። ምክንያቱም ደስታቸው በዛ ሰው ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው። ያሰው ሲያስከፋቸው ተስፋ ይቆርጣሉ። በሱ ደስታ ብቻ እና ብቻ ደስተኛ መሆኑን አልወደድኩትም። በዚያ ላይ haram Relationship ነው።" ጠቀስ እያደረገቺኝ። ተመስጬ ስሰማት ነበር። ፈገግ ብዬ እንድትቀጥል ጠየቅኳት። እሷም ቀጠለችና አወራቺኝ። "ሃቢቢ ሳፈቅር የመጀመሪያዬ ነህ ብዬ አልዋሽክም ሰው ሲኖረኝ ያፈቀርኩት አብሮኝ ሲሆን ግን የመጀመሪያዬ ነህ። ሰው ማጣት ከባድ ነው። ስልኬ ሳትጠራ ሳምንታት ሲያልፉ ይከፋል። ሰው ወረተኛ ነው ወላሂ በትንሽ ነገር ተቀይሞ መቀየስ ይቀናዋል። አብሮ ስለታቀደ ነገር ግድ የለውም። ስላሳለፍነው ጊዜም ግድ የለውም ስለሱ መደበር እና መከፋት ብቻ ጓደኝነት ወዳጅነት እኮ ብድር አይደለም። ሁሌም ፈላጊ መሆን ውርደት አይደለም እኮ አይደል? ምንፈልገው ሰው ከልቡ እየፈለገን ስላልሆነለት ይሆናል ማይፈልገን የሚመስለን። ወላሂ ብቸኝነትን ቀምሼዋለው ሰውን ላለማስከፋት በሰዎች ዘንድ ለመወደድ ተሟሙቼያለው። ግን ሰው ሰውነቱን አይለቅም! ሁቢ ሲከፋኝ ሰው ማውራት ከልቤ እፈልጋለሁ። ግን ሰው ይታዘባል ይቀየማል ይሰለቻል! በመጨረሻም በሰው ተስፋ ቆረጥኩ።ማንም ሊረዳኝ እንደማይችል ሲገባኝ ማስረዳት አቆምኩ። ኦፍ! ሁቢዬ ከባድ ነው ብቻ… አልሃምዱሊላህ ግን ወደማያሳፍረው ተጠጋው ወደማይጥለው፣ ወደ ማይቀየመው፣ ወደማይታዘበው፣ ሳትደክም ወደሚረዳው! እሱ ጋር ምቾት ሳገኝ ስለሱ መኖር ጀመርኩ። የልቤን ሰው ምርጥዬን ሃላሌንም አንተን አደረገልኝ…" በፍቅር አስተያየት ስታየኝ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። እቅፍ አደረግኳት በርግጥ አላህ ስላንቺ አበጀኝ አልኩ በውስጤ! "ራህመቴ
[👒የልጅነት ጊዜ ጨዋታ
እስከምን ጊዜም የማይጠፋ❤️
ጨርሱት አላቹ ቤተሰብ ዛሬ አንድ ለየት ያለ ቻናል ይዘን መተናል ቻናሉ ልጅነታችንን የሚያስታውሱ ማንኛውም ነገሮች የሚለቀቁበት ነው እና ቶሎ ተቀላቀሉ❤️🔥
join የሚለውን በመንካት ተቀላቀሉ
👇👇👇👇](https://t.me/addlist/3agyuIn4l7IxYTg0)
በኒቃባቸው ምከንያት ከትምህርት ገበታ ታግደው የነበሩ ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታ እንድመልሱ ከስምምነት መድረሱን የአዲስአበባ መጅሊስ ገለፀ!
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰሞኑን በከተማችን በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በመዋቅሮቻችን አማካኝነት በየደረጃው ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱ ገልጿል።
በትላንትናው እለት ጥቅምት 20/2016 የከፍተኛ ምክር ቤታችን ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣የአ/አ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
በዚሁም መሰረት ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለና ዘላቂ መፍትሔ የሚያሻው ከመሆኑ አንጻር የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል መጅሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ዘላቂ እልባት የሚያመጣ የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል።
ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል።
ከፍተኛ ምክር ቤታችን ቀሪውን ስራ በትኩረት የሚያከናውን ሲሆን በውይይቱ የተካፈሉ የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በሙሉ ችግሩን ለመፍታት ላሳዩትን ተነሳሽነት በከተማዋ ሙስሊም ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲል የአዲስ አዲስ አበባ መጅሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባስተላለፈው መልክት አስተዋቋል።
ኒቃብ በመልበሳቸው ምክንያት ወደ ትምህርት እንዳይገቡ የተከለከሉ ተማሪዎች ኒቃባቸውን እንደለበሱ እንዲማሩ ተፈቅዷል። ሆኖም ጉዳዩ ዘላቂና ቋሚ መፍትሄ ይፈልጋል‼
ነገ ሐሙስ ነዉ የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ🤞
መልካም ለይል አህባቢ 🙌
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ما هي أعظم نعمة أنعم الله تعالى عليكم فى حياتكم وفرحتم به فرحا شديدا
በ ህይወታቹ ውስጥ አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የዋለላቹ በጣም ደስተኛ የሆናቹበት ትልቁ ኒዕማ ምንድን ነው ?
سلام على من اتبع الهدى🫀🫳
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago