Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Hilina Belete

Description
Deacon Hilina Belete is a servant of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church.
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 5 days, 4 hours ago

Last updated 3 weeks, 1 day ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks ago

ክፍል አንድ ብዙዎች ጋር ደርሷል። ክፍል ሁለትም እነሆ። ይህን የዩቲዩብ ቻናል ቢወዳጁ እንደሚጠቀሙ በፍጹም አልጠራጠርም።

https://youtu.be/GGIivFJGgDQ?si=X4n_FN0YuZfvE0y-

YouTube

በሕማማት የሚከለከሉና የሚፈቀዱ ነገሮች ። | zehohitebirhan media official | #podcast #newvideo #orthdox #eotc

#ዘኆኅተ\_ብርሃን #ቦሌ\_ማርያም #Zehohitebirhan #Bole\_Mariam #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ቤተ\_ክርስቲያን #Orthodox #Tewahedo #Church #eotc #podcast #newvideo #ምክር #መንፈሳዊ\_ሕይወት #ዲያቆን\_ሕሊና\_በለጠ #ሕማማት #eotc Instagram - https://www.instagram.com/zehohitebirhan\_official/ Facebook - https://…

3 weeks, 1 day ago

ለቅርብ ወዳጅ ለመንገር የሚቸኩሉት ዓይነት ነገር ነው። የዛሬ ወር አካባቢ የአቃቂ መድኃኔዓለም ሰንበት ትምህርት ቤት የሐዊረ ሕይወት ዓይነት መርሐ ግብር አዘጋጅቶ በዚያ መርሐ ግብር ላይ ከመምህራን ጋር ተጋብዤ ተሳትፌ ነበር። (ይሄ መርሐ ግብር በራሱ ሊነገርለት የሚገባ ነው) በዚያው ዕለት የቅድስት ጣማፍ ሄራኒ (ኡምና /እናት/ ኢሪን) ሁለተኛው መጽሐፍ ይመረቅ ነበር። ቀድሜ በያዝኩት መርሐ ግብር ምክንያት ባለ መገኘቴ ለተርጓሚዋ ለአዜብ በርሔ ገልጬ ውሎዬን ከአቃቂ ምእመናን ጋር አደረግሁ። አብረውኝ የነበሩት ቀሲስ ዶክተር መዝገቡም ባጋጣሚ ቀድመው ለመጽሐፍ ምርቃቱ ተይዘው እንደ ነበርና በዚህኛው መርሐ ግብር ምክንያት እንዳልተገኙ ነገሩኝ። ያኔ የመጽሐፍ ምርቃቱ ጉባኤ አሳሰበኝ።

የ"ሐዊረ ሕይወት" መርሐ ግብሩ ላይ የነበረኝ አገልግሎት ተፈጽሞ፣ የዚያኑ ዕለት ማታ ለነበረኝ የኢጃት ጉባኤ ወደ ደብረ ምሕረት ሚካኤል ሮጥኩ። ስደርስ ጥቂት ጊዜ ስለ ነበረኝ፣ ያሳሰበኝ የመጽሐፍ ምርቃት ጉባኤው እንዴት እንደ ሆነ ለማወቅ ወደ አዜብ ደወልኩ። የሰማሁት ታሪክ ግን እንዳይሆኑ አደረገኝ። በስልኩ በዚያኛው ጫፍ ያለችው አዜብ የመርሐ ግብሩን እጅግ በሚያስደስት ሁኔታ ማለፍ ገልጻልኝ፣ በዚሁ በከተማችን በአንዱ አጥቢያ ላይ ቅድስቲቱ እያደረገች ያለውን ተአምር፣ በተለይም ለአብነት ትምህርት ቤቱ መምህርና ደቀ መዛሙርት በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ምን እንደ ተከናወነ፣ ለጊዜያት ማን እንደ ሆነች ሳያውቅ በሌሊት እየመጣች ስለምትቀሰቅሰውና "ቀስቅሺኝ አላልክም? ተነሥ እንጂ!" ብላው ከክፍሉ ስለምትወጣው 'አንዲት የአረብ ሴት' ጉዳይ እና እስኪያውቃት ድረስ ስላለፈው የጭንቀት ጊዜ ስለ መሰከረው አገልጋይ ስትነግረኝ እኔ ባለሁበት "እንዳይሆኑ ሆኜ" ነበር። አተራረኳ ይሁን የቅድስቲቱ ነገር፣ ወይም የመገለጧ ዕፁብነት ብቻ "እንዲያ ያንሰፈሰፈኝ" ምን እንደ ሆነ አላውቅም። ድምጼ መቀየሩን እንዳታውቅ እየተጠነቀቅኩ ለአዜብ "አሁን የነገርሽኝን እባክሽ በአካል አግኝቼሽም ንገሪኝ!" አልኳት።

ብዙ ጊዜ አይገጥመኝም እንጂ አንድ መንፈሳዊ ኩነት ልቤን ነክቶት በውስጤ የሚፈጠረውን "መረበሽ /ነውጥ/ ማዕበል" እጅግ እወደዋለሁ። ሁለመናን የማተኮስ ፣ ጆሮ የመጋል፣ ደም በደም ሥር ውስጥ ሲፈስ የማወቅ የሚመስል ዓይነት ስሜት። ለጥቂት ደቂቃዎች ባለሁበት ብቻዬን ሆኜ አስብ የነበረው ይህንን "ማዕበል" ለየትኛው የልብ ወዳጅ ነግሬ አብረን ሔደን ያንን አጥቢያና ቅድስቲቱን እንደምንሳለም ነበር። እንዲሁ በአሳብ ስናወጥ የጉባኤው ሰዓት ደረሰና ወደ አገልግሎቴ ሥፍራ ገባሁ።

ይህንን በዚህ በሙባአ ሕማማት እንድናገር ያደረገኝ ትናንት ቅዳሜ: ቅድስቲቱን የተመለከተው ፊልም ተተርጉሞ መመረቁ ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ፊልሙ በማኅበረ ቅዱሳንም በቦሌ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤትም ተለፍቶበት ተተርጉሞ በተመሳሳይ ጊዜ ለእይታ ቀርቧል። የቅድስቲቱ ታሪክ ልብን የሚቆጣጠር ነውና፣ ከዓመታት በፊት ቅድስቲቱን ያስተዋወቀችን እኅታችን አዜብ የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅድመ ኅትመት እንዳየው ስትሰጠኝ፣ ከዓመታት በፊት ለነበረው የመጽሐፉ ምርቃት መጽሐፉን እንድዳስስ ስትጋብዘኝ (ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋሽ ታዬን ያገኘሁበት አጋጣሚ ነበር) ማኅበሩም ለምርቃቱ አገልግሎት ሲጋብዘኝ፣ የቦሌ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞቼም (እንዴት እንዳኮራችሁኝኮ!) መተርጎማቸውን ሲነግሩኝና እንዳስተዋውቅ ሲያዙኝ፣ ቅድስቲቱ በሕይወታቸው የጎበኘቻቸው ወንድሞቻችን የሕይወት ልምድም ሲነገረኝ ደስታ ውስጤን ተቆጣጥሮት ቅፅበቶቹን አልዘነጋቸውም።

በሁለት ክፍል የተሰናዳውንና የቅድስት ሄራኒን ሕይወት የሚያሳየውን ፊልም በቦሌ ሚካኤል በኩልም በማኅበሩ በኩልም ታገኙታላችሁ። ለዚህ ጽሑፍ አንባብያን ሁለቱም አካላት ማስፈንጠሪያዎቹን በአስተያየት መስጫው እንደሚያስቀምጡልን ተስፋ አደርጋለሁ።

እኔም ከዓመታት በፊት ለተጻፈው የመጀመሪያው ክፍል መጽሐፍ የጻፍኩትን ማስተዋወቂያ አስተያየት አስቀምጣለሁ።

የቅድስት ሄራኒ (እናት ኢሪን) እና የቅዱስ ቤተሰቧ በረከት ይደርብን! አሜን!

ዲያቆን ሕሊና በለጠ
ፌስቡክ ፔጅ:- https://www.facebook.com/hilinabeletezehohitebirhan?mibextid=ZbWKwL
ኢንስታግራም:- https://www.instagram.com/hilinabelete?igsh=MXEwNDhuODI4azA4Nw==

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

3 weeks, 1 day ago
Hilina Belete
3 weeks, 1 day ago
Hilina Belete
3 weeks, 3 days ago

ይህችን ዝግጅት ጊዜ ወስዳችሁ ብትመለከቱ፣ የዩቲዩብ ቻናሉንም ብትወዳጁ እንደምትጠቀሙ አልጠራጠርም።

https://youtu.be/oeBg42VwjNM?si=CH6HhhE7helotEuu

YouTube

ሕማማት እና ሥርዓቱ| Zehohitebirhan media official | " መድኃኒታችን እስከምን ታመመ" #podast #orthdox #newvideo

#ዘኆኅተ\_ብርሃን #ቦሌ\_ማርያም #Zehohitebirhan #Bole\_Mariam #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ቤተ\_ክርስቲያን #Orthodox #Tewahedo #Church #eotc #podcast #newvideo #ምክር #መንፈሳዊ\_ሕይወት #ዲያቆን\_ሕሊና\_በለጠ #ሕማማት #EOTCMK Instagram - https://www.instagram.com/zehohitebirhan\_official/ Facebook - https:/…

3 weeks, 5 days ago
Hilina Belete
2 months, 3 weeks ago
"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ …

"ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን፡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ" ሮሜ 8÷35-39።

3 months ago
፨፨፨(የየካቲት 12) የሰማዕታት ሐውልት፨፨፨

፨፨፨(የየካቲት 12) የሰማዕታት ሐውልት፨፨፨

፨መታሰቢያነቱ - ፋሽስት ጣሊያን በወገኖቻችን ላይ ላደረሰው መከራና በግፍ በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ለተጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን

፨የሐውልቱ ቀራጮች - አጉበቲን ሲች አንቶንና ከርሰኔች ፋራን የተባሉ የዩጎዝላቪያ ዜጎች ናቸው፡፡

፨ሐውልቱ የቆመበት ቦታ ዲያሜትር - 26 ሜትር

፨የሐውልቱ ቁመት - 28 ሜትር

፨መገኛ ሥፍራ - 6 ኪሎ

(ምንጭ ፡- ኅብረ ኢትዮጵያ ፣ ቴዎድሮስ በየነ)

3 months, 1 week ago

የተወደደው ሐዋርያ

“…ድንግልን በስጦታነት የተቀበለው ፣ ተቀብሎም ወደ ቤቱ የወሰዳት ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ ነው፡፡ ዮሐንስ ጌታ የሚወደው እርሱም ጌታን የሚወድ ሐዋርያ ነው፡፡ ከሌሎቹም ሐዋርያት ይልቅ ለጌታ ፍቅሩ የጸና ስለ ነበር ፣ ጌታም እርሱን ይወደው ስለ ነበር ፍቁረ እግዚእ - የጌታ ወዳጅ ተባለ፡፡ ለዚህም ነው … “የሚወደውን ደቀ መዝሙሩን” ተብሎ የተነገረለት፡፡ ታዲያ ጌታ ለምን እመቤታችንን ለዮሐንስ ሰጠ? ለምን የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ለሰጠውና ብፁዕ ነህ ብሎ ላመሰገነው ለጴጥሮስ አልሰጠውም? (ማቴ.16፡17-19)፡፡ እርሱስ ቢሆን ጌታን መውደዱን “እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” ብሎ የሚመሰክር አይደለምን? (ዮሐ.21፡15-17)፡፡ ቅዱስ ሥጋውን ከመስቀል አውርደው ለገነዙት ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስስ ለምን አልሰጣቸውም? ለሌሎቹ ሐዋርያትስ ለምን አልሰጣቸውም? ድንግልን ይወስዷት ዘንድ ቤት የላቸውምን? አይደለም፡፡…

“…ዮሐንስ የሚሰጠውን ስጦታ ለመጠበቅ ከሌሎቹ ሐዋርያት ይልቅ ብቁ ስለነበርም ድንግልን ለመቀበል በመስቀሉ ሥር እንዲገኝ እግዚአብሔር ፈቀደ፡፡ ሐዋርያት በጌታ መከራ ሞት ጊዜ አይሁድን ፈርተው እንደ ሸሹ ከዮሐንስ በቀር በእመቤታችን ሞትም ጊዜ አይሁድን ፈርተው ከጌቴሴማኒ የሚሸሹ ናቸውና ድንግልን እንደ ፍቁረ እግዚእ ለመቀበል አልቻሉም፡፡ ራሱን የሰጣቸውን ጌታ በቀራንዮ ጥለውት እንደ ሔዱ ሁሉ ከመስቀሉ ሥር የምትሰጣቸውን እመቤታችንንም በጌቴሴማኒ ጥለው የሚሔዱ ናቸውና በቀራንዮም በጌቴሴማኒም ለሚጸና ለዮሐንስ ተሰጠች፡፡…

“…በርግጥ በዮሐንስ በኩል ድንግል ለተጠቀሱትም ላልተጠቀሱትም ለሁሉም ተሰጥታለች፡፡ ነገር ግን በዮሐንስ በኩል እንዲሆን ዮሐንስን የመረጠበት የተለየ ምክንያት አለው፡፡ ከማይመረመረው ከመለኮታዊው ምክንያቱ ባሻገር ዮሐንስን ከላይ እንደገለፅነው ይወደው ነበር፡፡ እመቤታችንን በስጦታነት ለመቀበል በጌታ መወደድ ያስፈልጋል፡፡ ማርያም ማርያም ለማለት በክርስቶስ መወደድ ያሻል፡፡ ድንግል ታማልዳለች ብሎ ምልጃዋን ለመቀበል በመድኃኔዓለም መወደድ ግድ ነው፡፡ ስሟ ሲጠራ ፊታቸው የሚጠቁር ሰዎች ምንም እንኳን እርሱ እንደሰው ቢወዳቸውም በተሳሳተ መንገድ ውስጥ ናቸውና እንደ ዮሐንስ ስላልተወደዱ ድንግልን ለመቀበል ብቁ አይደሉም፡፡ ጴጥሮስ እንዳለው ቆይተው “እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” የሚሉ እንኳን ቢሆኑ መከራ ሞቱ በጾም ሲታሰብ ፣ ሕማማቱ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ሲዘከርና ቤተ ክርስቲያን ስሟ ሲጠራ ጴጥሮስ “የምትሉትን ሰው አላውቀውም” ብሎ ገና ዶሮ ሳይጮህ ነገር በሚጸናባት ቁጥር ሦስት ጊዜ እንደ ካደ እነርሱም “የምትሉትን ሃይማኖት አናውቅም ፣ የምትሉትን ጾምና ሥርዐት አናውቅም” ብለው በጽናት ክደዋልና መስቀሉ ሥር ተገኝተው “እነኋት እናትህ” ሊባሉ አልቻሉም፡፡ (ማር.14፡71)፡፡…

“…ጌታ በመስቀል ላይ እመቤታችንን ለዮሐንስ ከመስጠቱ በፊት ዮሐንስን ለእመቤታችን ሰጥቶ ነበር፡፡ አንድ ሰው ድንግልን ለመቀበል አስቀድሞ ራሱ ለድንግል መሰጠት አለበት፡፡ ለውዳሴዋ ፣ ለብፅዕትነቷ ፣ ለንጽህናዋ ፣ ለድንግልናዋ ፣ ለቅድስናዋ መጀመሪያ ራሱን መስጠትና ማስገዛት ይኖርበታል፡፡ ዮሐንስን መምሰል ያስፈልገዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድርሳነ ማርያም ማንን ለድንግል እንደሚሰጥ ሲገልፅ የሚከተለውን ብሏል፤

“በኢየሩሳሌም ትነግሺ ዘንድ ነይ፡፡ መታሰቢያሽን የሚያደርግ በቃሉ የማይዋሽ ፣ መጽሐፍሽን የጻፈ ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ፡፡ ለአንቺም ይሆን ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡”

“…አንድ ሰው ራሱ ለእርሷ ለመሰጠት ሲበቃ ከዚያ በኋላ እርሷን ለመቀበል የሚችል ዕደ-ልቡና ይኖረዋል፡፡…

“…ድንግልን ለመቀበል መሰጠት ያስፈልጋል፤ እመቤታችንን ለመቀበል ሞት በመጣ ጊዜ ከክር ይልቅ አንገትን የምታስቀድም በ”እንኩ” ባይ ፍቅር ፣ በቅዱስ ጥብዐትና በሰማያዊ ተስፋ የሠለጠነች የክርስትና እምነትን መሰነቅ ግድ ነው፡፡ ድንግልን ለመቀበል ቤትን ማዘጋጀት ሳይሆን እንደ ዮሐንስ የተወደደች ሃይማኖትን ይዞ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ ድንግል በዮሐንስ በኩል ለሁሉ እንደ ተሰጠች በተወደደች ሃይማኖት በኩል እንጂ በሌላ በምንም በኩል አትሰጥም፡፡ …”

“…ከዚህ በተጨማሪም ጌታ የሚወዳት እናቱን በመስቀል ላይ ሳለ ነፍሱን ከሥጋው በፈቃዱ ከመለየቱ በፊት ሊያያት እንደወደደ እመቤታችንም በሞቷ ጊዜ ነፍሷ ከሥጋዋ ከመለየቱ በፊት ልጇ በመስቀሉ ሥር ልጅሽ ይሁን ብሎ የሰጣትን ውድ የመንፈስ ልጇን ፣ ስጦታዋን - ዮሐንስን ልታየው ወዳ ነበር፡፡ እንዲህ ብላም ጸለየች፤

“‘በሰማይ የምትኖር ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ጸሎቴን ልመናዬን ስማኝ፣ ታናሹ ዮሐንስንም ላክልኝ፣ አይቼው እደሰት ዘንድ እወዳለሁና፤ ዳግመኛም ወንድሞችህ ሐዋርያትን ሁሉ ላክልኝ፤ በሰጠኸኝ ጸጋም አምናለሁ፤ እንደምትሰማኝ በአንተ ዘንድ የፈለግሁትን ሁሉ እንደምትሰጠኝ አምናለሁ’ እያለች ጸለየች፡፡”

የመሰጠት ሕይወት ፣ ከገጽ 71-92 ድረስ ከሚገኘው በጥቂቱ የተወሰደ

5 months ago
ሀገሬ በሶ ናት!

ሀገሬ በሶ ናት!
፨፨፨
ሀገሬ በሶ ናት

ክንዱ የፈረጠመው በሰፊው መዳፉ፣
በውኃ አርሶ ሊጎርሳት በአፉ፣
እጥፍ ዘርጋ አ'ርጎ ጨብጦ 'ሚይዛት፣
እንደ ይበሉባው ቅርጿን እሚያበጃት፣

ሀገሬ በሶ ናት።

ቢበላ 'ማይጠግበው ክፉ ራብ ያለበት፣
በዘጋባት ኮዳ ከፍ ዝቅ አድርጎ የሚበጠብጣት፣
በጥብጦ በጥብጦ #ባንድ_አፍ 'ሚጨልጣት፣

ሀገሬ በሶ ናት።

መበጥበጥ ያቃተው፣
መጨበጥ ያልቻለው፣
ብናኙ እንዳይቀረው፣
ጤዛ አርከፍክፎ የሚያንፈረፍራት፣
ለውሶ ለውሶ
ለውሶ አበስብሶ
እጁን ማንኪያ አልብሶ ቅሞ የሚያስቅማት፣

ሀገሬ በሶ ናት።

ሥልጡን ገበሬዎች ገብስ አ'ርገው የዘሯት፣
ጠይም ባለሙያ ቆልታ የፈተገቻት፣
ወገቧን ሸብ አ'ርጋ በመጅ የፈጨቻት፣
ርቀው ለሚጓዙ ስንቅ የሚቋጥሯት፣
ሀገሬ ኢትዮጵያ ስንዱ በሶ ናት።

መበላቷ አይደለም በንዴት ሚያፋጅ፣
ለጩኮ ተሠርታ መበጥበጧ እንጅ።

ይ'ቺን ጥዑም በሶ ካለ የሰነቃት፣
እነ አባ ጨብጥ
እነ አባ በጥብጥ
እነ አባ ጨልጥ
ጨብጠው በጥብጠው ጨልጠው ሳይፈጇት፣
በቅቤ አርሶ ቶሎ ጩኮ ያድርጋት።

መንገዴ እጅግ ሩቅ በሶ ደግሞ ስንቄ፣
ነጣቂ ሳይመጣ መጓዜ ነው ርቄ፣

ሳይነቃ ጨባጩ፣
ሳያየኝ በጥባጩ፣
በከረጢት ይዣት ልሩጥ እንጂ በ'ግሬ፣
ሀገሬስ በሶ ናት በሶ ናት ሀገሬ።

(ከስድስት ዓመታት በፊት ለጥፈሃታል ብሎ FB ቢያስታውሰኝ መልሼ ለጠፍኳት)

©ዘሕሊና

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 5 days, 4 hours ago

Last updated 3 weeks, 1 day ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 1 month, 3 weeks ago