ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 1 day ago
Last updated 2 weeks, 3 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
የማትረግፍ አበባ የማትጠወልግ
ዘውትር 'ምታብብ
መዓዛ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ናት
መድኃኒተ ሕዝብ
...
የሲና ሐመልማል እሳት የተስማማት
መቃጠልን 'ማታውቅ የመለኮት ሌማት
የእርሷ ድንግልና ዘላለማዊ ነው
የማትረግፍ ሲላት ያሬድን አየነው
...
ተቀጥፋ የቆየች የአቤሜሌክ ቅጠል
66 ዓመት ደርቃ ሳትቃጠል
መስጠት ያላቆመች የልምላሜዋን ጠል
ፍሬዋ ክርስቶስ አበባ ናት ድንግል
...
ከአሮን በትር ላይ አብባ የተገኘች
የደረቀን ዓለም ማለምለም ታውቃለች
አባ ጊዮርጊስም አላት ፈርከሊሳ
እንደ አንበሳ ኃጢአቱን ድል እንድትነሳ
...
የምታሳሳ እናት ውብ ናት እንደ አበባ
በምልጃዋ ያመነ ስንቱ ገነት ገባ
አባ ጽጌ ድንግል ማበቧን ያወቀው
ማኅሌቷን ታጥቆ ተመስጦ ነጠቀው
...
በጽጌ ማኅሌት ንዒ ንዒ እያልን
እኛም ከሊቁ ጋር ልንጠራት ሌት አለን
አበባ ነፍሳችን ጠውልጋ እንዳትረግፍ
የምልጃዋ ጥላ በእኛ ላይ ይረፍ።
ዜማ:- ቀሲስ ግርማ አዳነ
ግጥም:- ዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን
በልቅሶና በጩኸት የወርቅና የብር መፈተን የሆነ መፈተንሽ እንደ ምን ያለ ፍጹም ድንቅ ነገር ነው? ... የፈጣሪ የኢየሱስ እናት ሆይ! ቀን በፀሐይ ሐሩር፣ ሌሊትም ፍጹም ምሳሌ በሌለው ውርጭ ልምላሜያዊ ሰውነትሽ እንደ ምን ጠወለገ?... 'ከመ ዘእሳት ዘሐቅል ሕሊናየ ውእየ' ... እመቤቴ ማርያም ሆይ! ሀገርን የሚጠብቁ ሰዎች 'የእኔንና የተወደደ ልጄን ልብስ ገፈፉ' በማለት በተናገርሽው ነገርሽ ሕሊናዬ እንደ በረሓ እሳት ተቃጠለ..... እንደ ውኃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቴ ሁሉም ተበተነ፤ ኃይሌም እንደ ገል ልምላሜን ዐጥቶ ደረቀ፤ ምላሴም በጉረሮዬ ውስጥ ዱረቀ"
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
"ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ትእምርተ መስቀል የከበረ ነው።
እግዚአብሔር ምሳሌው የሆነ ትእምርተ መስቀል ከሁሉ አስቀድሞ ተፈጠረ። በሱ አምሳል አዳምን ፈጠረው።
ለመላእክትም የመስቀል ምልክት አክሊል አላቸው። እንደ መብረቅ ያለ ዘውድም አላቸው። የመስቀል አምሳል በትርም አላቸው። ፊታቸውንም በመስቀል ምልክት ይሸፍናሉ። የመስቀል ማዕዘን አራት እንደ ሆነ የመንበሩም ጎኖቹ አራት ናቸው።
ይህ መስቀል የሄኖስ የሽቱ እንጨቱ ነው። የአብርሃም የወይራ እንጨቱ፣ የይስሐቅ የነጭ ሐረጉ፣ የያዕቆብ የዕጣኑ እንጨት ነው።
ይህ መስቀል የሙሴ የሃይማኖት በትሩ ነው። ይህ መስቀል ክንድን በኤፍሬምና በምናሴ ራስ ላይ በማስተላለፍ የጥላ ምልክት ነው።
ይህ መስቀል የኤርምያስ የሎሚ በትሩ ነው። የኢሳይያስ የስሙ መታሰቢያ ነው።
ይህ መስቀል በሰሎሞን ያለ የእንኮይ እንጨት ነው። ከእንኮይ አነሳሁህ፤ በዚያም የወለደች እናትህ ታመመች ብላ ይህች ሙሽራ ስለ ሙሽራዋ ብዙ ተናግራለችና። ስለ መስቀሉም ከጥላው በታች መቀመጥን ወደድሁ አለች...."
ድርሳነ መድኃኔ ዓለም ዘቀዳሚት
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በዓል አደረሳችሁ!
ለቅርብ ወዳጅ ለመንገር የሚቸኩሉት ዓይነት ነገር ነው። የዛሬ ወር አካባቢ የአቃቂ መድኃኔዓለም ሰንበት ትምህርት ቤት የሐዊረ ሕይወት ዓይነት መርሐ ግብር አዘጋጅቶ በዚያ መርሐ ግብር ላይ ከመምህራን ጋር ተጋብዤ ተሳትፌ ነበር። (ይሄ መርሐ ግብር በራሱ ሊነገርለት የሚገባ ነው) በዚያው ዕለት የቅድስት ጣማፍ ሄራኒ (ኡምና /እናት/ ኢሪን) ሁለተኛው መጽሐፍ ይመረቅ ነበር። ቀድሜ በያዝኩት መርሐ ግብር ምክንያት ባለ መገኘቴ ለተርጓሚዋ ለአዜብ በርሔ ገልጬ ውሎዬን ከአቃቂ ምእመናን ጋር አደረግሁ። አብረውኝ የነበሩት ቀሲስ ዶክተር መዝገቡም ባጋጣሚ ቀድመው ለመጽሐፍ ምርቃቱ ተይዘው እንደ ነበርና በዚህኛው መርሐ ግብር ምክንያት እንዳልተገኙ ነገሩኝ። ያኔ የመጽሐፍ ምርቃቱ ጉባኤ አሳሰበኝ።
የ"ሐዊረ ሕይወት" መርሐ ግብሩ ላይ የነበረኝ አገልግሎት ተፈጽሞ፣ የዚያኑ ዕለት ማታ ለነበረኝ የኢጃት ጉባኤ ወደ ደብረ ምሕረት ሚካኤል ሮጥኩ። ስደርስ ጥቂት ጊዜ ስለ ነበረኝ፣ ያሳሰበኝ የመጽሐፍ ምርቃት ጉባኤው እንዴት እንደ ሆነ ለማወቅ ወደ አዜብ ደወልኩ። የሰማሁት ታሪክ ግን እንዳይሆኑ አደረገኝ። በስልኩ በዚያኛው ጫፍ ያለችው አዜብ የመርሐ ግብሩን እጅግ በሚያስደስት ሁኔታ ማለፍ ገልጻልኝ፣ በዚሁ በከተማችን በአንዱ አጥቢያ ላይ ቅድስቲቱ እያደረገች ያለውን ተአምር፣ በተለይም ለአብነት ትምህርት ቤቱ መምህርና ደቀ መዛሙርት በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ምን እንደ ተከናወነ፣ ለጊዜያት ማን እንደ ሆነች ሳያውቅ በሌሊት እየመጣች ስለምትቀሰቅሰውና "ቀስቅሺኝ አላልክም? ተነሥ እንጂ!" ብላው ከክፍሉ ስለምትወጣው 'አንዲት የአረብ ሴት' ጉዳይ እና እስኪያውቃት ድረስ ስላለፈው የጭንቀት ጊዜ ስለ መሰከረው አገልጋይ ስትነግረኝ እኔ ባለሁበት "እንዳይሆኑ ሆኜ" ነበር። አተራረኳ ይሁን የቅድስቲቱ ነገር፣ ወይም የመገለጧ ዕፁብነት ብቻ "እንዲያ ያንሰፈሰፈኝ" ምን እንደ ሆነ አላውቅም። ድምጼ መቀየሩን እንዳታውቅ እየተጠነቀቅኩ ለአዜብ "አሁን የነገርሽኝን እባክሽ በአካል አግኝቼሽም ንገሪኝ!" አልኳት።
ብዙ ጊዜ አይገጥመኝም እንጂ አንድ መንፈሳዊ ኩነት ልቤን ነክቶት በውስጤ የሚፈጠረውን "መረበሽ /ነውጥ/ ማዕበል" እጅግ እወደዋለሁ። ሁለመናን የማተኮስ ፣ ጆሮ የመጋል፣ ደም በደም ሥር ውስጥ ሲፈስ የማወቅ የሚመስል ዓይነት ስሜት። ለጥቂት ደቂቃዎች ባለሁበት ብቻዬን ሆኜ አስብ የነበረው ይህንን "ማዕበል" ለየትኛው የልብ ወዳጅ ነግሬ አብረን ሔደን ያንን አጥቢያና ቅድስቲቱን እንደምንሳለም ነበር። እንዲሁ በአሳብ ስናወጥ የጉባኤው ሰዓት ደረሰና ወደ አገልግሎቴ ሥፍራ ገባሁ።
ይህንን በዚህ በሙባአ ሕማማት እንድናገር ያደረገኝ ትናንት ቅዳሜ: ቅድስቲቱን የተመለከተው ፊልም ተተርጉሞ መመረቁ ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ፊልሙ በማኅበረ ቅዱሳንም በቦሌ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤትም ተለፍቶበት ተተርጉሞ በተመሳሳይ ጊዜ ለእይታ ቀርቧል። የቅድስቲቱ ታሪክ ልብን የሚቆጣጠር ነውና፣ ከዓመታት በፊት ቅድስቲቱን ያስተዋወቀችን እኅታችን አዜብ የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅድመ ኅትመት እንዳየው ስትሰጠኝ፣ ከዓመታት በፊት ለነበረው የመጽሐፉ ምርቃት መጽሐፉን እንድዳስስ ስትጋብዘኝ (ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋሽ ታዬን ያገኘሁበት አጋጣሚ ነበር) ማኅበሩም ለምርቃቱ አገልግሎት ሲጋብዘኝ፣ የቦሌ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞቼም (እንዴት እንዳኮራችሁኝኮ!) መተርጎማቸውን ሲነግሩኝና እንዳስተዋውቅ ሲያዙኝ፣ ቅድስቲቱ በሕይወታቸው የጎበኘቻቸው ወንድሞቻችን የሕይወት ልምድም ሲነገረኝ ደስታ ውስጤን ተቆጣጥሮት ቅፅበቶቹን አልዘነጋቸውም።
በሁለት ክፍል የተሰናዳውንና የቅድስት ሄራኒን ሕይወት የሚያሳየውን ፊልም በቦሌ ሚካኤል በኩልም በማኅበሩ በኩልም ታገኙታላችሁ። ለዚህ ጽሑፍ አንባብያን ሁለቱም አካላት ማስፈንጠሪያዎቹን በአስተያየት መስጫው እንደሚያስቀምጡልን ተስፋ አደርጋለሁ።
እኔም ከዓመታት በፊት ለተጻፈው የመጀመሪያው ክፍል መጽሐፍ የጻፍኩትን ማስተዋወቂያ አስተያየት አስቀምጣለሁ።
የቅድስት ሄራኒ (እናት ኢሪን) እና የቅዱስ ቤተሰቧ በረከት ይደርብን! አሜን!
ዲያቆን ሕሊና በለጠ
ፌስቡክ ፔጅ:- https://www.facebook.com/hilinabeletezehohitebirhan?mibextid=ZbWKwL
ኢንስታግራም:- https://www.instagram.com/hilinabelete?igsh=MXEwNDhuODI4azA4Nw==
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 1 day ago
Last updated 2 weeks, 3 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago