✝️የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፎቶግራፍ 📸✝️

Description
🙏እግዚአብሔር ነግሠ ስብሐቲሁ ለብሰ
መዝ፦፺፪፥፩✝️
''እግዚአብሔር ነገሰ ምስጋናን ሁሉ ለበሰ''



✝️ይሄ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
✝️ መዝሙሮች
✝️ መንፈሳዊ ትምህርቶችና
✝️ መንፈሳዊ ፎቶግራፍ
የሚለቀቅበት ቻናል ነው #Share #share #share እያደረጋችሁ🙏
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 months, 3 weeks ago
***✝️*** ነገረ ድኅነት ***✝️***

✝️ ነገረ ድኅነት ✝️

✝️ ክፍል አንድ ✝️

✝️ ድኅነት ✝️

በመጽሐፍ ቅዱስ መዳን ተብለው የተገለጹ የተለያዩ ነገሮችን እናገኛለን። ከእነዚህም ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል። ኖኅና ቤተሰቦቹ በመርከብ አማካይነት ከጥፋት ውኃ መዳናቸው፥ እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ነጻ መውጣታቸው እና በባሕር መካከል በደረቅ መሸጋገራቸውና ሲከተሏቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው እጅ መዳናቸው፥ ንዕማን ሶርያዊ ከነበረበት ለምጽ በዮርዳኖስ ውኃ ታጥቦ መዳኑ፥ እስራኤላውያን በንጉሡ በሕዝቅያስ ዘመን ከሰናክሬም እጅ በተአምራት መዳናቸው፥ ሆኖም እነዚህ ሁሉ መዳኖች (ድኅነቶች) ለጊዜው ድኅነቱ የተደረገላቸውን ሰዎች ያስደሰቱና ከመከራ ያዳኑ ነገሮች ቢሆኑም ሁሉም ጊዜያዊና ድኅነታቸው በሥጋና በዚህ ዓለም የተወሰነ ነበር። ይህም ማለት የሰውን ልጅ መሠረታዊ ችግር ያልፈታ፥ ሰውን ከተፈረደበት የሞት ፍርድ ያላዳነ፥ በሰው ልጅ የተጎሳቆለ ሕይወት ላይ ይህ ነው የሚባል መሠረታዊና ተጨባጭ ለውጥ ያላመጣ ነበር። ነገር ግን እነዚያ የማዳን ድርጊቶች እግዚአብሔር በልጁ ሰው መሆንና መገለጥ በጊዜው ጊዜ ይፈጽመው ዘንድ ያለውን አማናዊ ድኅነት በጥላነት (በምሳሌነት) የሚያመለክቱ የተስፋ ጭላንጭሎች ነበሩ።

✝️ ድኅነት ማለት ምን ማለት ነው? ✝️

ድኅነት ስንል በኃጢአት ምክንያት የወደቀውና የጎሰቆለው የሰው ልጅ ከደረሰበት ድቀትና ሞት ሙሉ በሙሉ ነፃ መውጣቱንና አጥቶት የነበረውን ጸጋ ማግኘቱን፥ መጀመሪያ ከመበደሉ በፊት ወደ ነበረበት ሁኔታ (ከዚያም ወደ በለጠ ደረጃ) መመለሱን ማለታችን ነው። የመዳን ትምህርት (ነገረ ድኅነት) የቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረትና የመዓዝን ድንጋይ ነው። ማንኛውም አስተምህሮና ሐሳብ የሚመዘነውና የሚለካው በነገረ ድኅነት መሠረት ነው። ከነገረ ድኅነት ጋር የሚጋጭና የሚቃረን ትምህርት ሁሉ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የአንድ ትምህርት ወይም አስተሳሰብ ይዘትና አካሄድ ሲተነተን የሰውን መዳን ከንቱ ወደሚያደርግና “የሰው ልጅ አልዳነም” ወደሚል አቅጣጫ የሚወስድ ከሆነ የተለየና የተወገዘ ነው። ስለሆነም ከሐዋርያት ጀምሮ ከዚያ በኋላ የተነሡ ቅዱሳን ሊቃውንት የመናፍቃንን አስተሳሰብና ትምህርት ሲመዝኑና ከንቱነቱንና ስህተትነቱን ሲያጋልጡ የኖሩት በነገረ ድኅነት ማንጠሪያነትና መመዘኛነት እያጣሩና እየመዘኑ ነበር። “የሰው ልጅ ዳነ” ስንል በአጠቃላይ የሚከተሉትን ያካትታል።

✝️ 1. ተፈርዶበት የነበረው የሞት ፍርድ ተወገደለት፥ ተነሥቶት (ተወስዶበት) የነበረው ሕይወት ተመለሰለት ማለታችን ነው፤ ✝️

የሰው ልጅ “በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ” ተብሎ አስቀድሞ ተነግሮት የነበረው የሞት ማስጠንቀቂያ በገቢር ተፈጽሞበት፥ በሰውነቱ ላይ ሞት ነግሦበት የሞት ተገዢ ሆኖ ነበር። ዘፍ. 2:17 በሕይወተ ሥጋ እያለም ኑሮው በጽላሎተ ሞት (በሞት ጥላ ሥር) ውስጥ የወደቀና በሞት በፍርሃት የታጠረ፥ ሲሞትም ነፍሱ በጻዕር ተለይታ ሥጋው ወደ መቃብር ነፍሱ ወደሲዖል በመውረድ በጭንቅና በመከራ ይኖር ነበር። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የሚስማማውን የእኛን ሥጋ በመዋሓድ ሞታችንን ሞቶ በሞቱ ሞትን አጠፋልን፥ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን፥ ሞትን በትንሣኤ ለወጠልን፥ የመቃብርን ይዞ የማስቀረትና ሰውነታችንን የማፍረስና የመለወጥ ኃይል ድል በማድረግ በመቃብር ተይዞ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አጠፋልን።

✝️ ክፍል ሁለት ይቀጥላል... ✝️

https://t.me/OrthodoxPhotographs

3 months, 1 week ago
✝️የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፎቶግራፍ 📸✝️
3 months, 1 week ago

እንኳን ለቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል (በዓለ ዕረፈት) አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡  በዚህች በመስከረም 29 ቀን አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት እና የእርሷ ማኅበርተኞች ድል አድራጊዎች 27 ሰማዕታት በሰማዕትነት ያረፉባት ዕለት ነች፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸውን ይክፈለን፡፡ እነዚህም ቅዱሳን፤
1ኛ. #አርሴማ#ቅድስት_ወሰማዕት_ኃያል_ተጋዳሊት_
2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን
3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ
4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር
5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ
6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ
7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ
8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ
9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ
10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ
11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ
12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ
13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ
14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው
15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ
16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ
17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ
18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን
19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ
20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ
21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ
22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ
23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ
24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም
25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው
26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ
27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ
28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡

ሰላም ለፀዐተ ነፍስኪ በጊዜ ኃለፈ ሰይፍ፤
መንገለ ክሣድኪ ድኑን ለአምሳለ መሥዋዕት ውኩፍ፡፡
እስእለኪ አርሴማ በከናፍር ወአፍ፤
ረድኤትኪ ትሩፍ በላዕሌየ ያንጸፈጽፍ፤
እስመ አርአየኒ ዘንተ ሞትኪ ትሩፍ፡፡

ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤
ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡
ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤
ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤
በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡
/የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

4 months, 2 weeks ago

በደብረ ሊባኖስ ውስጥ የቆየችው ቅድስት እናት ተጋድሎዋን የፈጸመችው ግን ጣና ሐይቅ ውስጥ ነው:: በተለይ ለ፳፪ [22] ዓመታት ሐይቁ ውስጥ አካሏ አልቆ: አሣ በሰውነቷ ውስጥ እስከሚያልፍ ድረስ ተጋድላለች:: በቀኝና በግራ ፲፪ [12] ጦሮችን ተክላም ጸልያለች::

ብዙ ኃጥአንን አማልዳ: ፲፪ [12] ክንፎችን አብቅላ: ከፍ ከፍ ብላለች:: ከርሕራሔዋ ብዛት የተነሳ ሰይጣንን እንኩዋ ለማስታረቅ ሞክራለች:: ጌታም ከሲዖል ነፍሳትን እንድታወጣ ፈቅዶላታል:: ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ያረፈችው በዚህ ዕለት ሲሆን አጽሟ ዛሬ በራሷ ገዳም [ጣና ዳር] ይገኛል::

[ † ?  ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ  ? † ]

ቅዱስ ቶማስ "መርዓስ" በምትባል ሃገር የፈለቀ የንጋት ኮከብ: ጻድቅ: ገዳማዊ: ዻዻስ: ሐዋርያ: ሰማዕትና ሊቅ ነው:: የዚህን ቅዱስ ተጋድሎ እንደ እኔ ያለው ሰው አይቻለውም:: የእርሱ ሕይወት ክርስትና ምን እንደ ሆነ ያሳያል::

- " ቅዱስ ቶማስ " ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ
- ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ
- መርዓስ በምትባል ሃገር ዽዽስና ተሹሞ በእረኝነት ያገለገለ
- በሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስትና የመለሰ
- በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው::

ጨካኞቹ ቅዱሱን ለ፳፪ [22] ዓመታት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለ ነበር ፪ [2] እግሮቹ: ፪ [2] እጆቹ: ፪ [2] ጀሮዎቹ: ፪ [2] አፍንጫዎቹ: ፪ [2] ዐይኖቹ: ሁሉ አልነበሩም:: ነገር ግን እንዲህም ሆኖ አልሞተም ነበር::

በመጨረሻም በዘመነ መናፍቃን አርዮስን ካወገዙት ፫፻፲፰ [318]ቱ ሊቃውንት እንዳንዱ ተቆጥሯል:: ቅዱስ ቶማስ ዽዽስና በተሾመ በ፵ [40] ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የጻድቃንን: የሰማዕታትን: የሐዋርያትንና ሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል::

† የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች †

፩. ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
፪. ፍስሐ ፅዮን
፫. ሐዲስ ሐዋርያ
፬. መምሕረ ትሩፋት
፭. ካህነ ሠማይ
፮. ምድራዊ መልዐክ
፯. እለ ስድስቱ ክነፊሁ [ባለ ስድስት ክንፍ]
፰. ጻድቅ ገዳማዊ
፱. ትሩፈ ምግባር
፲. ሰማዕት
፲፩. የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
፲፪. ፀሐይ ዘበፀጋ
፲፫. የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
፲፬. ብእሴ እግዚአብሔር [የእግዚአብሔር ሰው]
፲፭. መናኒ
፲፮. ኤዺስ ቆዾስ [እጨጌ]

† እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:: †

አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ ምልጃ ክብራቸውን ያድለን:: በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን::

?

[  † ነሐሴ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [ መምሕረ ትሩፋት ]
፪. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ [ ጻድቅት ]
፫. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፬. አበው አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ

[  †  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
፪. ቅዱስ አጋቢጦስ [ ጻድቅ ኤዺስቆዾስ ]
፫. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፬. "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ ሱራፌል ]
፭. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም

† " ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል::" † [ማቴ.፲፥፵] (10:40)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

†              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
?                   ?                    ?

4 months, 2 weeks ago

? 

[  † እንኩዋን ለታላላቁ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት : ቅድስት ክርስቶስ ሠምራና ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

[ †  ? ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ  ? † ]

† ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይን ናቸው:: ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዐይኗን መጠንቆል ነው::

ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ: እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል: እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ: እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው: እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ: እንደ ባሕታውያን ግኁስ: እንደ መላዕክትም ባለ ክንፍ አባት ነበሩ:: ለዚሕ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይኔ የምትላቸው::

? ቅዱስ ተክለ-ሃይማኖት  ሐዋርያዊ  ?

[   ልደት   ]

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ:  ጸጋ-ዘአብ  ካህኑና  እግዚእ-ኃረያ  ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ : በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው  ቅዱስ ሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት : እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ [ከአረማዊ ጋብቻ] አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት ፳፬, በ፲፪፻፮ (፲፩፻፺፮) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ ፳፬, በ፲፪፻፯ (፲፩፻፺፯) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

[   ዕድገት  ]

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ብሉያት: ሐዲሳትን] ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ  አባ ጌርሎስ  ተቀብለዋል::

[   መጠራት    ]

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ ፦

"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት [ተክለ ሥላሴ] ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

[    አገልግሎት    ]

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ [ጽላልሽ] አካባቢ ብቻ በ፲ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ  ኢትዮዽያ  ፪ መልክ ነበራት::

፩.ዮዲት [ጉዲት] በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::

፪.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት  ሐዲስ ሐዋርያ  አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን [ጠንቁዋዮችን] አጥፍተዋል::

[   ገዳማዊ ሕይወት    ]

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ፫ ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ፲፪ ዓመታት: በአቡነ  ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ፯ ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ፯ ዓመታት: በአጠቃላይ ለ፳፮ ዓመታት አገልግለዋል::

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ  ዞረሬ  ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ፳፪ ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም ፮ ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ፯ ዓመታት ጸልየዋል::

[  ስድስት ክንፍ    ]

ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ  እሥራኤል  የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት  አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-

¤ በቤተ መቅደስ ብስራቱን
¤ በቤተ ልሔም ልደቱን
¤ በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤ በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤ በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው  ቀራንዮ  ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ  እመቤታችን ድንግል ማርያም  ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::

በዚያም :-

¤ የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤ ፮ ክንፍ አብቅለው
¤ የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ ከ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
¤ ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤ "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

[   ተአምራት    ]

የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::

† ሙት አንስተዋል ፥ ድውያንን ፈውሰዋል ፥ አጋንንትን አሳደዋል ፥ እሳትን ጨብጠዋል ፥ በክንፍ በረዋል ፥ ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

[   ዕረፍት    ]

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ፺፱ ዓመት: ከ፰ ወር: ከ፩ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬, በ፲፫፻፮ (፲፪፻፺፮) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: ፲ ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

ይህች ዕለት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ናት፡፡

[ † ?  ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  ? † ]

እጅግ የከበረችና የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እናመሰግናታለን:: እርሷ በሁሉ ጐዳና ፍጹምነትን ያሳየች ኢትዮዽያዊት እናት ናት:: ገና ከልጅነት የነበራት የትሕትናና የመታዘዝ ሕይወት እጅግ ልዩ ነበር:: እናታችን ቅድስናን ያገኘችው ገና በትዳር ውስጥ እያለች ነው::

ከተባረከ ትዳሯ ፲፪ [ 12 ] ልጆችን አፍርታ: ምጽዋትን የዕለት ተግባሯ አድርጋ ኑራለች:: በዚህ ደግነቷም ሙት እስከ ማንሳት ደርሳለች:: አብያተ ክርስቲያናትን አንጻ አንድ ልጇን [ዳግማዊ ቂርቆስን] አዝላ ምናኔ ወጥታልች::

4 months, 3 weeks ago

?

[ † እንኳን ለቅዱሳን አበው አባ መቃርስ: ቅዱስ አብርሃም እና ቅዱስ ፊንሐስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

[ † ? ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ? † ]

† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [መቃሬ] "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ ከ፹ ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ በግብፅ ትልቁን ገዳም [አስቄጥስን] የመሠረተ ከ፶ ሺህ በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::

በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ፪ ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነንጉሳቸው አጥምቀዋል::

በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ [ስም አጠራሩ ይክበርና] እመቤታችንን ቅዱሳን ሐዋርያትን አዕላፍ መላእክትን በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን ማርቆስን ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

ታላቁ ቅዱስ መቃርስና መቃርዮስ ከ፪ ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት በዚችው ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ፶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::

ይህች ዕለት ለአባታችን መቃሬ በዓለ ፍልሠቱ ናት:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ታላቁ ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ [የሳስዊር] ሰዎች ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ ያደገባት ወላጆቹ [አብርሃምና ሣራ] የኖሩባት ቦታ ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::

በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት አደረጉት::

ወደ ሳስዊርም ወስደው ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለመቶዎች ዓመታት ተቀመጠ:: በ፯ኛው መቶ ክ/ዘመን ግን ተንባላት [እስላሞች] መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::

በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት በነበረበት ዘመን ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ ሰውነታቸው ታወከ::

ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን" ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::

መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው:: በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::

ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት ከብዙ እንባ ጋር ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው በክብር አኑረውታል:: ይህ የተደረገው በዚህች ዕለት ነው::

[ † ? አባታችን ቅዱስ አብርሃም ? † ]

የሃይማኖት-የደግነት-የምጽዋት-የፍቅር አባት የሆነው አብርሃም ደጉ በዚህች ቀን ይታሠባል:: በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የአብርሃም አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::

በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ:: "አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ:: መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::

"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን እያለው የማያይ ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::

ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት ሔደዋል:: ከገበያ ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ አብርሃም እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው::

ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው:: ይህ የተደረገው ከ፪ ሺህ ዓመታት በፊት በዚህች ቀን ነው:: የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ የእግዚአብሔር ወዳጅ አባታችን አብርሃም በመጨረሻው በውሃ በነፋስ በእሳትና በፀሐይ ተመራምሮ ፈጣሪውን አግኝቷል::

[ † ? ቅዱስ ፊንሐስ ካህን ? † ]

ካህኑ ፊንሐስ የብሉይ ኪዳን ዘመን አገልጋይ ከነገደ ሌዊ የሊቀ ካህናቱ የአሮን የልጅ ልጅ ነው:: አባቱም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ነው:: ፊንሐስ እሥራኤል ከግብጽ ሲወጡ ሕጻን የነበረ ሲሆን አድጐ በመጀመሪያ ካህን አባቱ አልዓዛርና አያቱ አሮን ሲያርፉ ደግሞ ሊቀ ካህንነትን ተሹሟል::

አንድ ቀን በጠንቅ-ዋዩ በበለዓም ክፉ ምክር እሥራኤላውያን ከሞዐብ ሴቶች ጋር በኃጢአት በመሳተፋቸው እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበር:: ያጠፋቸው ዘንድም መቅሰፍት ተጀምሮ ሳለ ፊንሐስ ወንድና ሴት በደብተራ ኦሪቱ አንጻር የማይገባውን ሲሠሩ አያቸው::

ለፈጣሪው ቀንቶ በአንድ ጦር ሁለቱንም በአንድ ላይ ጥሏቸዋል:: ያን ጊዜ ጌታ "አስተንፈስካ ለነፍስየ" ብሎታል:: መቅሰፍቱም ተከልክሏል:: በዚህም ምክንያት ካህኑ ፊንሐስ የ፫ መቶ ዓመት ዕድሜ ተጨምሮለት እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል:: [ዘኁ.፳፭፥፯] , መዝ.፻፭፥፴]

ለአበው ቅዱሳን የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን:: ክብራቸውንም በእኛ ላይ ይሳልብን::

[ ነሐሴ ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል [፬ኛ ቀን]
፪. ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [ፍልሠቱ]
፫. አባታችን ቅዱስ አብርሃም [ጣዖቱን የሰበረበት]
፬. ቅዱስ ፊንሐስ ካህን [ወልደ አልዓዛር]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

"እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ::" [ዕብ.፮፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

†              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
?                   ?                    ?

4 months, 3 weeks ago

ያልፉልኛል ብዬ፣ ተማሪ ቀኖቼ
አስተማሪ ሆኜ ፣ ጀርባዬን ሰጥቼ
ሰሌዳው ላይ ፊቴን፣ ስቋጥር ስፈታ
ድንገት መንሾካሾክ ፣ ከጀርባ ሰምቼ፡ ዞር ስል ዝምታ...
«ማነው የሚያወራው? ወይስ ሁሉን ልምታ?»

ጥቂት ፀጥ አለና፡ ሹክሹክታው ቀጠለ 
በንዴት በግኜ፡ ዞር ስል አየሁት
«አንተ ነህ አይደለ? ...»
«የምትረብሸኝ?» ነደድኩኝ በቁጣ

«ና! ግጥም ና! ውጣ!»

(ጧ! )

ዘርጋ! ግጥም ዘርጋ!
በቀን`በር የኋሊት ፣ የታሰርኩኝ ፊጋ
ሳቢውን ጎትቼ ፣ ላሳልፍ ስፈጋ
ለምን ነው ጀርባዬ፡
ታሪክ እያነሳህ፡ የምትፈተፍተው?
ዞሬ ስሟገትህ ፡ የፊቴን እንድተው?
ኧረ ተው? ኧረ ተው... ?!

ያረድኩትን ፍስክ፡ ትናንት ቋጭቼ
ዛሬ ልፆም ብዬ፡ እህል ውሃ ትቼ
ማጣጣም ስጀምር፡ የረሀብን ጸጋ
አ'መህ ለመታወስ፡ ጥርስ የቀረህ ስጋ
'ካፍ አድረህ ለማግደፍ፡ ጥርስ የቀረህ ስጋ...!
ባደረ መጠዝጠዝ ፡
ባለፈ መነዝነዝ ፡ ዘርጋ ግጥም ዘርጋ...!
ዝቅ አርገው እጅህን፡ ወደኔ አታስጠጋ

(ጧ! ጧ! )

ያለፈን ለመጪው ፡ እንዳላስቆጥረው
የማላውቀውን ነው ፡ ልፅፍ የምጥረው
እድሜ ላንተ ግጥም፡ ልቅጣ ብዬ ቀረሁ!
ዝጋ ግጥም ዝጋ፣
ቆሽቴን አታጭሰው
ስትጮህ ስመታህ
ሲነደኝ ብደፋህ፡ ቤትህን ባፈርሰው
መመጠን የማይችል? ጀማሪ ሊለኝ ሰው?

ግጥም ተው! ግጥም ተው!
ሲቃህን ዋጥ አርገው
አፍንጫህን አብስ፡ እንባህን ጥረገው
ጥረግና ስማ...

ያልመጡ ቀናቴን፡ ላለፉት ልታማ
ጥበቃን በስንኝ፣ መቅረትን በዜማ
ለውሰህ ልትግተኝ፡ እረፍ አትታገል
ከአፈር ነው «እፍፍፍ» እንጂ ፣ አይወራም ከገል
ከሙት አትሟገት፡ ቀብረህ ተገላገል
ቀንጥሰው ሀረጉን፣ ስንኝህን ቀልጥም
እያልኩኝ ስዳረቅ...
ዞሬ ቀረሁ ባንተ፣ ዝጋ ዘርጋ ግጥም!

(ጧ! ጧ! ጧ! )

የፊቴ ጥቁር ነው፣ የጠፋ ሰሌዳ፡ ያልተደነገገ
ከሚሞቀኝ ትናንት፣ የማላውቀው ነገ
እፈጥራለሁ ብዬ፣ ሳወርድ ሳወጣ
በቃል ስታስቀረኝ፡ ሰይጣኔስ ቢመጣ?
በስሜት ስይዝህ
እጄ ላይ ብትሞትስ?
ውጣ ግጥም ውጣ!

(ጧ! ጧ ! ጧ! ጧ! )

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112

  • *
4 months, 3 weeks ago

መምሰል
°°°°°°°°

ከደጇ ቁሚያለሁ
በረከት ለማግኘት ከ'ናቴ ፍልሰታ፣
ማረጓን ያመነ
ይኸው ያሰማል መዝሙርና እልልታ።
"ማርያም አረገች አረገች"

ቀና ብዬ አየሁ የሰማዩን ከፈን፣
ለጠርጣራው ልብሽ ማሳረፊያ 'ሚሆን፥
ከሰጠችሽ ብዬ እንደ ቶማስ ሰበን።

አየሽ ሞኝነቴን
ከፍቅሬ የተነሳ ላንቺ ምህረት ስሻ፣
ከስንት ዘመን በፊት
ያረገች እናቴን
እንዳ'ዲስ ሳሳርግ በምናቤ ዋሻ።

ግን መጥተሽ ይሆን?

ህጻናት በክብር
ስጋ እና ደሙን ቀምሰው ሲመለሱ፣
ቆርበሽ ከሆን ብዬ
እስክትወጭ አያለሁ ከቤተ መቅደሱ።

አየሽ የዋህነቴን
በሴት ግዳጅ ታስረሽ
መግባት እንደማትችይ እያወ'ኩ ጠንቅቄ፣
ትኖሪያለሽ ብዬ
በከንቱ ሳማትር በፍቅርሽ ታንቄ።

ግን መጥተሽ ይሆን?

እልፍ ሆኖ ሳለ
እምነት የተቀባ ነጠላ ያጣፋ፣
ቅጽሩን ሙሉ ብቃኝ
አንችን የሚመስል አንድ ውብ ሴት ጠፋ።

ተመልከች እብደቴን
ተስፋዬ ተሟጦ
ለስግደት ስደፋ ከ'ናቴ ስዕል ፊት፣
ወለል ብሎ ታየኝ ያንቺ መሳይ ውብ ፊት፤
ይኸው ተገፈፈ
ማጣት ያሳወረው
የዓይኔ ላይ ጉድፍ ልክ እንደ ቅርፊት።

ቁጭ እሷን!!
ቁጭ አንችን!!

ሰዓሊ ለነ ቅድስት!!

ለማን ነው የሰገድኩት?

ግን አንቺ ነሽ?

አንቺም አር'ገሻል እንደ እመቤቴ?

አበድኩ መሰለኝ
የማይሆን ጥያቄ ወጣ ካ'ንደበቴ።

JOIN US???

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112

...............

5 months ago
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana