ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
"የክርስቶስ ቤዛነት ይህ ነው፦ እርሱ ስለተሸከማቸው ዘግናኝ ሕማሞች እና ኃጢኣቶች እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ይናገራል። ኃጢኣት የማያውቀውን እርሱን እግዚአብሔር አብ ስለእኛ ሲል 'ኃጢኣት እንዲሆን' አደረገው። አመንዝራው፣ ስድ ሆኖ የሚበድለው፣ ቆሻሻ በሆኑ ተግባራት አረንቋ ውስጥ የሚዛቅጠው እና ኃፍረት አልባ በሆኑ ተግባራት የሚበላሸው ሁሉ ከክርስቶስ ሲሸሽ ድምጹ በኋላው ይከተለዋል። ይኸውም 'የተወደድህ ልጅ ሆይ፥ ና! ኃጢኣቶችህ ከእኔ ጋር ናቸው፤' እያለ የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ደም ነው! ገና የሠራሃቸው ዕለት ነው በምልዓት የተሸከምኳቸው። ካሣውን ከፍያለሁ፦ ሐፍረት ተጭኖብኛል፤ ተገርፌያለሁ፤ ደቅቄያለሁ፤ ተሰቅያለሁ፤ እንዲሁም መርገምን ተሸክሜያለሁ። ለአንተ የይቅርታ እና የንጽሕና ተግባራትን እንዲሁም ይገባኛል የምትልበትን ጸጋ አዘጋጅቼልሃለሁ። ና! ለአንተ መከራ የተቀበልኩትን ያህል በአንተ ደስ ይለኝ ዘንድ ና! የመዳንን ዘውድ እደፋልህ ዘንድ፣ ፍቅሬን እና መንፈስ ቅዱስን በአንተ ላይ አፈስስ ዘንድ፣ እንዲህ አድርጌ ወደ አባቴ አቀርብህ ዘንድ ና! አንተ ከበጎቼ ሁሉ እጅግ ውዱ ነህ፤ እኔ ደሜን እስከመክፈል ደርሼ ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥቼሃለሁና።"
የክርስቶስ ስሞች፣ ገጽ 135-36።
ይህን ምሥጢር የሆነ መሐፍ እንድታነቡት ግብዣችን ነው።
በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
“ኃጢአቷን የቀበረችው ማርያም” መጽሐፍ በድጋሚ ታተመ
-በመ/ር ሥሙር አላምረው የተዘጋጀው “ኃጢአቷን የቀበረችው ማርያም” የተሰኘ መጽሐፍ ጌታን ሽቶ ስለቀቡት ማርያም ኀጥእት ብዙ ኃጢአቷን ቀብራ ብዙ ጸጋ ስላገኘችውና ማርያም እኀተ አልዓዛር ልዩነት ያስረዳል፡፡ መምህሩ “ከዚኽ በኋላ ጌታችንን ሽቱ የቀቡት ሴቶች እንዴት ሥስት ናቸው ተባለ የጋራ የቤት ሥራ ይኾነናል እንጅ አንዲት ሴት ብቻ ቀባችው ብለን የጨለማ ገልማጭ አንኾንም” ይሉናል፡፡
የመጽሐፉ አላማዎች
1) በእኅተ አልአዛር ማርያም ስም ማርያም ኃጥእት ተሠውራ እንዳትቀር ማድረግ
2)ስለ ባለሽቱ ሴቶች የግብጽ ቤ/ንና ሌሎች ተቋማት ምን አይነት ትምህርት እንዳላቸው ማሳየት
3)የተለያዩ የሊቃውንት ትርጓሜ ስለ ኃጢአተኛዋ ማርያም ምን እንደሚሉ ማስረዳት
4) የማርያም ኀጥእትን ገድል መሠረት በማድረግ የንስሐ ለቅሶዋን፣ ያጋጠማትን ፈተና እንዲሁም ገድሉ ያሉበትን የስምና የታሪክ ቅደም ተከተል ዝንፈትን መጠቆም፡፡
5)መጽሐፈ ስንክሳር የካቲት 6 የእኅተ አልዓዛር መታሰቢያ እንዳልሆነና የማርያም ዘሀገረ ናይን መታሰቢያ እንደሆነ ማስረዳት
-የደራሲያን መጻሕፍት በመግዛትና በማንበብ እናበረታታ እንደግፍ፡፡
መጽሐፉን ቅዳሜ በግዮን መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
“ቃልኪዳን በነገረ ድኅነት” (በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ)
ቆየት ካሉ ነገር ግን እንደ መጽሐፉ ብስለት ብዙዎች እጅ ካልገቡ፣ በጥልቅ ትንታኔ ከተዘጋጁ መጻሕፍት አንዱ የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ “ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት” በሚል ርእስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ ያነበቡ አንባቢያን ትልቅ መንፈሳዊ መረዳትን ስለሚጠይቀው ስለ ቃል ኪዳንና ነገረ ድኀነት በቂ ግንዛቤ አግኝተውበት እምነታቸውን በማጽናት ከክርስቶስና ከቅዱሳን ጋር ተጣብቀው በምድር ሰማያውያንን መላእክትን መስለው ተዋሕዶዊ አኗኗርን ገንዘብ አድርገው ተመላልሰውበታል፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳን ከአምላካቸው ጋር ያደረጉትን ቃልኪዳንና በተሰጣቸው ቃል ኪዳን እኛ እንዴት መጠቀም እንዳለብን የሚተነትን ብቻ ሳይሆን፣ ነገረ ድኅነትን ተተርሰው ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ፣ ተግባራዊ ምልልሳችን በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ያለውን ፋይዳ፣ ስለንስሐና ሒደቶቹም በቂ ግንዛቤ እንዲኖረን ያበቃናል፡፡ መጽሐፉ በሰባት ምዕራፎች የተከፈለና በ188 ገጾች ተሰንዶ ለአንባቢያን በሚመች መልኩ የተዘጋጀ ግሩም መጽሐፍ ነው፡፡ ገዝታችሁ አንብቡት ትጠቀሙበታላችሁ፡፡
የተወሰነ ቅጅዎች ስላሉን በግዮን መጻሐፍት መደብር ታገኙታላችሁ።
ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን አምጣ የወለደችው የመምህረ ወንጌል የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ የተወሰኑ የመጽሐፍ
ቅጂዎች ስላሉን ማግኝት ትችላላችሁ።
በግዮን መጽሐፍ መደብር ደርዛቸውን የጠበቁ ነባርና አዳዲስ መጽሐፍቶችን ያገኛሉ። ለበለጠ መረጃ
በ0913083816/0931144330
"የክርስቶስ ቤዛነት ይህ ነው፦ እርሱ ስለተሸከማቸው ዘግናኝ ሕማሞች እና ኃጢኣቶች እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ይናገራል። ኃጢኣት የማያውቀውን እርሱን እግዚአብሔር አብ ስለእኛ ሲል 'ኃጢኣት እንዲሆን' አደረገው። አመንዝራው፣ ስድ ሆኖ የሚበድለው፣ ቆሻሻ በሆኑ ተግባራት አረንቋ ውስጥ የሚዛቅጠው እና ኃፍረት አልባ በሆኑ ተግባራት የሚበላሸው ሁሉ ከክርስቶስ ሲሸሽ ድምጹ በኋላው ይከተለዋል። ይኸውም 'የተወደድህ ልጅ ሆይ፥ ና! ኃጢኣቶችህ ከእኔ ጋር ናቸው፤' እያለ የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ደም ነው! ገና የሠራሃቸው ዕለት ነው በምልዓት የተሸከምኳቸው። ካሣውን ከፍያለሁ፦ ሐፍረት ተጭኖብኛል፤ ተገርፌያለሁ፤ ደቅቄያለሁ፤ ተሰቅያለሁ፤ እንዲሁም መርገምን ተሸክሜያለሁ። ለአንተ የይቅርታ እና የንጽሕና ተግባራትን እንዲሁም ይገባኛል የምትልበትን ጸጋ አዘጋጅቼልሃለሁ። ና! ለአንተ መከራ የተቀበልኩትን ያህል በአንተ ደስ ይለኝ ዘንድ ና! የመዳንን ዘውድ እደፋልህ ዘንድ፣ ፍቅሬን እና መንፈስ ቅዱስን በአንተ ላይ አፈስስ ዘንድ፣ እንዲህ አድርጌ ወደ አባቴ አቀርብህ ዘንድ ና! አንተ ከበጎቼ ሁሉ እጅግ ውዱ ነህ፤ እኔ ደሜን እስከመክፈል ደርሼ ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥቼሃለሁና።"
የክርስቶስ ስሞች፣ ገጽ 135-36።
የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ
ነገ ቅዳሜ በግዮን መጻሕፍት ታገኙታላችሁ።
ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ሕንፃ ቤተ መቅደስ እድሳት የሚውል።
በግዮን መጻሕፍት መደብር ነባር እና አዳዲስ መጽሐፍቶችን ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኛሉ።
እጻጻፋም እንደ ዮሐንሰ ስብከት ፊት ለፊት ነው፡፡ አለማወቅን ሲገስጽ እንደ ዮሐንስ ሰብከት ምሳሩን እያሳየ ነው ድንቁርና ጨለማን ሊያርቅም ዮሐንሰን ችቦ አድርጎ እያሰራ ነው። ከኃጢኦት አረገቋ ሲያጥብም በዮሐንስ የጥምቀትና የትምህርት ባሕር እየዘፈቀ ነው፡፡ ዮሐንሰን መውደድ ማን መውደድ መሆኑ ግልጽ ነው።ከእርሱ መጀከሮም በማን ለመጨረስ መሆኑ የታወቀ ነው ።በእርሱ መደነቅም በእርሱ ጌታ በክርስቶስ ቀርቶ በዮሐንስም ለመደመም እንኳ አቅመ ቢሰ መሆናችንን ለማሳየት መሆኑም የተገለጠ ነው ጌታ ስለዮሐንሰ እርሱ እውነት መስክሮአል እንዳለ ይህ መጽሐፍም፡- ቤተ ክርስቲያን ስለዮሓንስ የያዘችውን እውነት ግልጽ አድርጎ ያወጣ አዘጋጁን አባታችንም የእውነት መሰክር የሚያሰኝ ነው። እንዲያውም ቅዱስ ያሬድ ስለቅዱስ ዮሐንስ ውነቱ አነነ ኣብል በእንተ የተስሰ እና ከርስ እው እግዚኡ እእመረ፣ በዕለት ጥሉ አንደረት ነፍሱ ዲበ ምድር እንዳለው ስለዚህ መጽሐፍ ጠቀሜታ እኔም ብዙ ላለመናገር ብመርጥ መልካም ሳይሆን አይቀርም። በርግጥ መጽሐፉ አባታችንም የቅዱስ ያሬድ ልጅ መሆናቸውን የሚመሰከር ንዜኑ ንዜኑ የሚል መጽሐፍ መሆኑን ላለመመስከር ልላቀቅ አልችልም። ጌታን የሚያገኝ ዮሐንስ ቀድሞ ያስፈልገዋልና : አባታችንም ቀድመው ዮሐንሰ ይዘው ሰለመጡ የጌታን ነገር ሊያስከትሉ ነው ብዬ እንድገምት ማድረጉንም ልደብቅ እልችልም፡፡ እንግዲያውስ አንደ እነርሱ እመጣጥ ከስድስት ወር ልዩነት ሳያሰበልጡ ቶሎ ይዘውልን ይምጡ እያልኩ መማጸኔን ማሳወቅ ከፉ እልመሰለኝም።
ዲያቆን ብርሃኑ አድማሰ
ምስጢር ከሚፈስበት፣ከሚቀዳበት ከጉባኤ ቤት የተሰጠ የምስጢር መአድን አቅርብንላችኋል። "ከመዝ ነአምን" በመምህር የኔታ ገብረ መድኀን እንየው የተበረከተ። የጉባኤ ቤት ምስጢር የፈሰሰበት መጽሐፍ ነው።
መጽሐፍን እኛ ዘንድ በግዮን መጽሐፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኙታል።ገቢው ሙሉ ለሙሉ ለምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት የሚውል ነው። አንድም ከበረከቱ እንሳተፍ አንድም ምስጢሩን ከየኔታ እንቅዳ።
አድራሻ:-መ/ገ/ጽ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን
ለበለጠ መረጃ 0913083816 /0931144330
የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ ቅዳሜ ለሁሉም መጽሐፍ መደብሮች ትሰራጫለች።
የሽፋን ዋጋ 400ብር
ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ሕንፃ ቤተ መቅደስ እድሳት የሚውል።
ቅዳሜ በግዮን መጻሕፍት ያገኙታል።