🕊[ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ]🕊

Description
ይሄ የኔ የጐሥዓ ቻናል ነው።በዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ቁም-ነገር ያስጨብጣሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ጽሑፋትን አቀርባለሁ።ወዳጄ ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለህ።ወዳጆች ሆይ ቴሌግራማችንን ለመልካም ነገር እንጠቀምበት።

Comment▹ @Gosa_Dave1229
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 weeks, 5 days ago

📌ደስስስስስስ ብሎኛልና ደስስስስስስ ይበላችሁ❗️ ⚜️መዝገበ ሕይወት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ይላል፦ ✍️"እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል"ይላል። 📚ሉቃ፦15፥7 🧭ስማችንን ሳትገልጽ ደስታህን በፈለከው መግለጽ ትችላለህ ያሉኝ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ፣ ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ ቻናል ከተከፈተ ጀምሮ በውስጥ መስመር…

3 weeks, 5 days ago

📌ደስስስስስስ ብሎኛልና ደስስስስስስ ይበላችሁ❗️

⚜️መዝገበ ሕይወት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ይላል፦
✍️"እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል"ይላል።
📚ሉቃ፦15፥7

🧭ስማችንን ሳትገልጽ ደስታህን በፈለከው መግለጽ ትችላለህ ያሉኝ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ፣ ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ ቻናል ከተከፈተ ጀምሮ በውስጥ መስመር ተከታታይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ትምህርት በሚገባ ተምረው፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን በሚገባ አውቀውና ተረድተው በዛሬዋ ዕለት በዕለተ አርብ እነሆ ምስክረነታቸውን ሰጥተው ተጠምቀው ወደ ቀደመችው ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረት ተመልሷልና ደስስስስስ ይበላችሁ።

⚜️ይማሩ የነበሩት ትምህርት የሚከተሉ ነበሩ፦

1ኛ፦መሠረተ ሃይማኖት
●ምስጢረ ሥላሴ
●ምስጢረ ሥጋዌ
●ምስጢረ ጥምቀት
●ምስጢረ ቁርባን
●ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን

2ኛ፦ነገረ ክርስቶስ (ትምህርተ ድኅነት)
●ነገረ ድኅነት በመጽሐፍ ቅዱስ እና
●ነገረ ድኅነት በሊቃውንት

3ኛ፦ነገረ ማርያም
●ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን
●ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን
●ነገረ ማርያም በሊቃውንት

4ኛ፦ነገረ ቅዱሳን
●ነገረ ቅዱሳን በብሉይ ኪዳን
●ነገረ ቅዱሳን በሐዲስ ኪዳን
●ነገረ ቅዱሳን በሊቃውንት አንድበት

5ኛ፦የቤተ ክርስቲያን ታሪክ
●ዓለም አቀፍ ጉባኤያት

🧭እነዚህን ትምህርቶች ስከታተሉ ቆይተው የንስሐ አባት በመያዝ የንስሐ አባታቸው ፈቅደውላቸው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት በጥምቀት በማግኘት ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በረት ተመልሷልና እንኳን ደስስስስስ ያላችሁ።

🧭ወንድሞቼ እና እኅቶቼ እንኳን ደስ ያላችሁ።የናፈቃችሁትን የክርስቶስ ኢየሱስን ቅዱስ ሥጋውን በመብላት ክቡር ደሙንም በመጠጣት ፍቅሩን ማጣጣም ጀምራችኋልና።

🧭ወንድሞቼና እኅቶቼ መንገዳችሁ ረጅም እና በፈተና የታጀበ ነውና እንድትፈጽሙት በተሰጣችሁ የመዳን ጸጋ 30፣ 60፣ 100 ፍሬ እንድታፈሩ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ወተክለ ሃይማኖት ይርዳችሁ።የቀድሞ ሕይወታችሁን እና የነበራችሁን የአገልግሎት ጊዜ ትታችሁ እንደመምጣታችሁ ስሜታዊ ሊያደርጓችሁ የሚነቅፏችሁን ባልሰማ በማለፍ በዝምታ ቅጧቸው።

◈ዝምታችሁ ከንግግራችሁ በላይ ያማቸዋልና።
◈ብሽሽቅ እና መናናቁ አያስተምርም።
◈ይልቁንም የሚነቅፏችሁን የሚሰድቡዓችሁን መርቁ፣
◈እንደተሳሳታችሁ የሚነግሩዓችሁን እውነት ሊያስተምሩዓችሁ ወይም ሊማሩ ሳይሆን ለክርክር ነውና ዝም በሏቸው።

✍️**አሁን ትንሽ ትዕግሥት አድርጋችሁ
በትምህርተ ሃይማኖት በርትታችሁ
በሚያምረው ግሩም አንድበታችሁ
እግዚአብሔርን በዝማሬ እያመሰገናችሁ
በፍቅር እንድታገለግሉ ፈጣሪ ይርዳችሁ።
ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለያችሁ
ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ይጋርዳችሁ
መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ።

✍️[ጐሥዓ (ዳዊት) {ኃ/ሚካኤል}]**

3 weeks, 5 days ago
***📌*****መልእክት ለኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ ቻናል ቤተሰብ**!

📌መልእክት ለኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ ቻናል ቤተሰብ!

⚜️ወዳጆቼ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ የተለያዩ ትምህርቶችን በዚህ በእኔ ቻናል ላይ፦
●ትምህርት የሚሰጡ፣
●ቁም-ነገር የሚያስጨብጡ፣
●የሚመክሩ፣
●የሚገስጹ
●በአጠቃላይ ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ እንዲኖረን እና አዕምሮዓችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲሰፋ እየሰራ ያለ ቻናል እንደ ሆነ ብዙዎቻችሁ በውስጥ መስመር አጋርታችሁኛል።

⚜️አክብራችሁኝ ስለምትከታተሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ በቻናለረ ስም ሁላችሁንም ከልብ አመሰግናለሁ።

⚜️ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ ቻናል አሁን 1,170 Subscribers ያሉት ሲሆን ከዚህ በላይ ደግሞ በዚተን ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮዓችን እንዲሰፋ የእናንተ ትብብር ያስፈልገኛል።

⚜️ቻናሉን ለወንድም እኅቶቻችሁ Share በማድረግ አብረን ይሄንን ቻናል በፍቅር እና በኦርቶዶክሳዊ አዕምሯዊ ጥበብ እናሳድገው።

┈‒‒‒‒┈┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈‒‒‒‒‒┈┈
©**ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ {ኦር.አዕ.በጐ.}
┈┈┈‒‒‒‒┈••●●●●◉❖◉●●●●••┈┈‒‒‒‒‒┈

❖Join & Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
💚 @Be_Gosa1224 💚
💛 @Be_Gosa1224 💛
@Be_Gosa1224 ** http://t.me/Be_Gosa1224

3 weeks, 5 days ago

📌የሰው ልጅ የአትክልት ስፍራው ወዴት የሰሆን?

🧭ወዳጄ የሰው ልጅ የአትክልት ስፍራው ወዴት ነው ትለኝ እንደሆነ አዕምሮው፣ ልቡ፣ ሰውነቱ እና ነፍሱ ነው እልሃለሁ።እያንዳንዱ ቀን ተዓምር ነው፤ያልተመረመረ በረከት ነው ፤በሕይወት እና በጤና እንዳለን እናውቃለን።ጨለማው ተገፎ ራስን በብርሃን ማጥመቅ ሌላ የአዲስ ሕይወት ጅምር ነው።ከሀብት በላይ በጤና፣በሰላም እና በፍቅር አዲስ ቀን ማዬት ጸጋና እና በረከት ነው።

🧭ወዳጆቼ ይህን ለማመስገን ምክንያት ካልሆነን ስህተቱ የራሳችን ነው።በብዙዎች ዘንድ ዛሬ የተናቀ እና ችላ የተባለ ሰው ነገ የመሪነትን ደረጃ ይይዛል፤ትናንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙ የተከበረ ሰው ዛሬ ተንኮታኩቶ ተስፋ ቢስ ይሆናል።አለኝ ብለህ አትኩራራ፤አጣሁም ብለህ አትዘን።በፈጣሪህ ታምነህ ጠብቅ።

🧭ወዳጄ ቢራቢሮዎችን በማሳደድ ጊዜህን አታባክን፤የአትክልት ቦታህን አስተካክል፥ቢራቢሮዎቹ በፈለጉ ሰዐት ወደ አንተ ይመጣሉ።የአትክልት ስፍራህን ሁሌም ለማስዋብ ትጋ ያኔ ዝንቦች ሸሽተው ንቦች እና ቢራቢሮዎች ወዳንተ ይመጣሉ።ጥሩ ቦታህን ያላዳነቀች ወይም ውበቷን ያልተረዳች ቢራቢሮ ወደ አንተ ለመቅረብ በእውነቱ ይደክማታል፤ትሸሻለችም።የቆሻሻ የአትክልት ስፍራ ወይም ጥሩ ያልሆነ ቦታ የትንኞች፣የቢንቢዎች እና የዝንቦች መሰብሰቢያ ከመሆን ውጭ ቢራቢሮወች እና ንቦች በፍጹም ወደ አትክልት ስፍራህ ሊቀርቡ አይችሉም።

🧭ወዳጄ አንድ ሰው ሊያደርገው የሚችለው ትልቁ ኢንቨስትመንት በራሱ ላይ መስራት፣ቅንነትን መላበስ፣ትሁት እና ጥሩ አሳቢ መሆን፣እንደሚደርስበት ደረጃ ልክ ከራስ ባለፈ ሌሎችን ማክበርን አለመርሳት፣ለሌሎች መሰናክል ሳይሆኑ በራሱ ላይ መስራት አለበት።የሰው ልጅ የአትክልት ስፍራው አዕምሮው፣ልቡ፣ሰውነቱ እና ነፍሱ ናቸው።እነዚህን ማለምለም ፣መንከባከብ እና መጠበቅ አለበት።በማንኛውም መንገድ ራሱን ማረም ፣ማዘጋጀት እና ዲሲፕሊን ሆኖ መቆዬት አለበት።በቀኑ መገባደጃ በራስ ዝግጁ እና በራስ መተማመን ሲኖር ለነፍሷ የሚገባትን ቦታ ፍለጋ ቢራቢሮ አንተን መከተል እና መቅረብ ትጀምራለች።በሁሉም ሰው ለመወደድ መጣር ራስን ያሳጣል።ሁሉንም ሰው ትቶ ቅድሚያ ራስን ፈልጎ ማግኘት እውነተኛ ደስታ እና የልብ ሰላምን ይሰጣል::

🧭ወዳጄ ጠንካራ ሰው ማለት በሰውነቱ የደረጀ፣ባለ ትልልቅ ጡንቻ ፣ጉልበታም እና ተዋጊ ሰው አይደለም።ጠንካራ ሰው ማለት በደረሰበት መከራ፣ሀዘን፣ችግር ጉስቁልና የልብ ስብራት ተቋቁሞ አለም ከረገጠችው በኋላ ሕይወቱን ለማስቀጠል ድጋሜ በደግነት የሚነሳ እና ምንም ቢያጋጥመው የኃይል ሚዛኑ የማይናወጥ፣ከመልካም ስብዕናው የማይሸሽ እና ዋጋውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤በፍቅር የሚያምን፣ሩህሩህ እና ደግ ፣የራሱን እና የሌሎችንም ክብር የሚጠብቅ ማለት ነው።

🙏እግዚአብሔር ማስተዋልን፣ ጥበብን፣ እውቀትን ከፍቅር ጋር ይሰጠን ዘንድ ጸልዩ!!!!!🙏

3 weeks, 6 days ago
***📌***[**ሰንበትን በሰንበት ትምህርት ቤት**](https://t.me/Be_Gosa1224)***❗️***

📌ሰንበትን በሰንበት ትምህርት ቤት❗️

⚜️እነሆ የና/ደ/አ/አ/ተ/ ሃይማኖት ቤ/ክ ፈ/አ/ሰ/ት/ቤት "ሰንበትን በሰንበት ትምህርት ቤት" በሚል ርዕስ ልዩ መርሐ-ግብር ስለ አዘጋጀ እርስዎም በዕለቱ ተገኝተው ከመርሐ-ግብሩ ቁም-ነገር እና ትምህርት እንዲቀስሙ ተጋብዘዋል።

⚜️ፍቅርን ፣ኅብረትን ሁሉን ያስተማረችን፤ ቤተ ክርስቲያናችንን እንድናውቅና እንድንወድ ኮትኩታ ያሳደገችን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ናት።የሰንበት ትምህርት ቤትን ውለታ ለመግለጽ ቃላት የለኝም።ቃላት የሚገልጸው አይደለም።

⚜️የሰንበት ትምህርት ቤትን ውለታ የሚያውቀው በውስጧ ያደገ እና የተጠቀመበት ነው።የሙዝን እና የብርቱኳንን ጣዕም የሚያውቀው የቀመሰ እንደሆነ ሁሉ የሰንበት ትምህርት ቤትም ጣዕሟን የሚያውቀው የቀመሰ ብቻ ነው አራት ነጥብ

📌የመርሐ-ግብሩ ቀን እና ሰዓት መች ነው?

ታኅሳስ 13
በዕለተ እሑድ
ከቀኑ 8:00-11:00 ድረስ

📔"ሰንበትን በሰንበት ትምህርት ቤት ትላለች ፈለገ አሚን"

✍️ፈለገ አሚን ሰንበት ትምህርት ቤት!!!!

3 weeks, 6 days ago

📌አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ ቻናል❗️ 📌ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❗️ ⚜️ክፍል ስድስት [፮] @Be_Gosa1224 🔰አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር።ቢቱ፦ ✍️“በምጽአት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም” የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር።ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ…

3 weeks, 6 days ago
***📌***[**ወዳጄ አትቸኩል ተረጋጋ**](http://t.me/Be_Gosa1224)***❗️***

📌ወዳጄ አትቸኩል ተረጋጋ❗️

●ወዳጄ ከዚህ በታች የተጻፉትን (የተዘረዘሩትን) ከማድረግህ በፊት ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ቆም ብለህ አስባቸው።ግን አትቸኩል።

ቸኩለህ ቃል አትግባ
ቸኩለህ አታፍቅር
ቸኩለህ አትመን
ቸኩለህ አትገምት
ቸኩለህ አትወስን
ቸኩለህ አውቀዋለሁ አትበል።

●ወዳጄ ረጋ በል።ይሄውልህ ወዳጄ ረጋ ስትል….✍️

●የረጋ ፍቅሩ ይጣፍጣል
●የረጋ እምነቱ ይጠነክራል፣
●የረጋ ግምቱ ልክ ይሆናል፣
●የረጋ ውሳኔው እንከን አልባ ይሆናል።

●ወዳጄ ስትረጋጋ ብዙ ነገር ታተርፋለህ እንጂ አትከስርም።ስለዚህ ተረጋጋ።

🕊️ስትረጋጋ አፍህን ከስድብ ትጠብቃለህ
🕊️ስትረጋጋ አንደበትህን ከቁጣ ትጠብቃለህ
🕊️ስትረጋጋ እጅህን ከመሰንዘር ትቆጠባለህ
🕊️ስትረጋጋ ስሜትህን ትቆጣጠራለህ
🕊️ስትረጋጋ አስበህ መወሰን ትችላለህ።

ስትረጋጋ ከሁሉም በላይ ከአላስፈላጊ ጸጸት ትድናለህ!

🙏ወዳጆቼ ሆይ እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይሰጠን ዘንድ ጸልዩ!!!!!🙏

*✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ።
👇*👇👇👇
@Gosa_Dave1229
@Gosa_Dave1229
@Gosa_Dave1229 ◈** http://t.me/Be_Gosa1224

3 weeks, 6 days ago
***📌*****የማይበድል ባርያ፤ የማይምር ጌታ የለም*****❗️***

📌የማይበድል ባርያ፤ የማይምር ጌታ የለም❗️

●እብሉይ የተባለ በግ ጠባቂ ነበር ከኃጢአትት ስራ የቀረው የለም። ያመነዝራል፣ ይሰርቃል ይገድላል በዚህም የሰይጣንን ሥራ እየፈጸመ ፵(40) ዓመት ኖረ።

●በአንዲት ዕለትም ከቀኑ እኩሌታ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ እርጉዝ ሴትን አየ ሰይጣንም በልቡ ክፉ ሃሳብን ጨመረበት እንዲህም አለ ሆዷን ሰንጥቄ ህጻኑ እንዴት እንደሚተኛ ማየት አለብኝ ብሎ ጸጉሯንም ጎትቶ ከመሬት ጣላት ሆዷንም በቢላ ሰንጥቆ ልጁንም እናቱንም ገደላቸው።

●በግ አርቢውም የሰራውንም ኃጢአት ተመልክቶ እጅግ አዘነ የማይበድል ባርያ የማይምር ጌታ የለም ብሎ አምርሮም እያለቀሰ ወደ በረሀ ሄዶ ፵(40) ዓመት ስለበደሉ አለቀሰ አጋንንትም ተገልጸው ከአንተ ዲያቢሎስ አባታችን ይሻላል እያሉ ያፌዙበት ነበር።እሱ ግን በተጋድሎ በረታ።

●የእግአብሔር መልአክም ተገልጾ ስለ ሴቲቱ ደም ጌታ ይቅር ብሎሃል ስለ ልጁ ግን ይቅር አላለህም አለው አባ እብሉይም ተጨማሪ ፵(40) ዓመት ተጋደለ ጌታም ይቅር አለው።
📖ስንክሳር የካቲት ፭

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር ይቅር ባይ መሐሪ አምላክ ነው እንደ ቸርነቱ ነው እንጅ እንደኛ በደልማ በጠፋን ነበር።ስለዚህ ንስሐ ከመግባት አንቦዝን።

✍️አስተያየት ለመስጠት፣ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ጥቆማ ለመስጠት፣ በቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት የእናንተ አሳብ ካለ በዚህ ላኩልኝ።
👇*👇*👇👇
@Gosa_Dave1229
@Gosa_Dave1229
@Gosa_Dave1229 ◈** http://t.me/Be_Gosa1224

4 weeks ago

📌አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ ቻናል❗️ 📌ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❗️ ⚜️ክፍል አምስት [፭] @Be_Gosa1224 🔰ከዚህ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ዋናው ትኩረቱ በድርሰቱ ላይ ሆነ።ወደ ጳጳሱ ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ዘንድ በመሄድ የቅዳሴ ድርሰት ለመድረስ እንዲፈቀድለት ከጠየቀ በኋላ የቅዳሴ ድርሰት ማዘጋጀቱን ገድሉ ይገልጣል።ይህም የኢትዮጵያ ቅዳሴያት ደራሲያቸው…

4 weeks ago

📌አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ በጐሥዓ ቻናል❗️ 📌ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❗️ ⚜️ክፍል አምስት [፭] @Be_Gosa1224 🔰ከዚህ በኋላ የአባ ጊዮርጊስ ዋናው ትኩረቱ በድርሰቱ ላይ ሆነ።ወደ ጳጳሱ ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ዘንድ በመሄድ የቅዳሴ ድርሰት ለመድረስ እንዲፈቀድለት ከጠየቀ በኋላ የቅዳሴ ድርሰት ማዘጋጀቱን ገድሉ ይገልጣል።ይህም የኢትዮጵያ ቅዳሴያት ደራሲያቸው…

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana