ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
#ተከታታይ_ልቦለድ_ታሪክ
.
.
.
#ትንሽ_ስለ..!
ክፍል - ፲፫
.
.
("ምን አልባት ከቆየ ፍቅር ነው።
ምን አልባት ካለቀ የፍቅር ታሪክ ነው፣
እና ምን አልባት ጭራሹን ካልጀመረ ደግሞ ግጥም ነው።")
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የቤተ እምነት ስፍራዎች ለነብስ እና ለአዕምሮ እረፍትን ለልብ ሰላምን ይሰጣሉ።
"ጌታዬ ሆይ ይህ አለም ላንተ ያለኝን ፍቅር ሊሻማኝ በሬ ቁሟል፤ ወደ ቤቴ እንዲዘልቅ አትፍቀድለት! የቤተሰቦቼን ልብ አራርተህ ሃሳቤን እንዲረዱ አድርግ..በተለይ አባቴ በኔ እንዲከፋ አልሻምና የሱን ልብ አደራ..! አይ ይህ ዓለም ያቀረበልሽን ተቀበይ ካልክ ግን..እንደ ፍቃድህ ይሁን!!"
ብላ ሃሳቧን ለፈጠራት ሰንዝራ ዛፍ ስር ቁጭ አለች። ዓይኖቿ ያቀረሩትን እንባ ቢፈስ ደራሽ ወንዝ ሊመስል ይችላል..
. . .
አለምነህ ወደ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቤ ከዘለቀ በኋላ ጸሎቱን ማድረስ፣ ምኞቱን ማሰማት ጀመረ.. ምኞቱና ጸሎቱም እንዲህ ይል ነበር..
'እማውቀው ይመስለኛል!'
ምኑን?
'ጸሎትና ምኞቱን'
እውነት?
'አዎ!..ይመስለኛል..አዕምሮዬ ላይ ያቃጭላል..ለምን እንደሆነ እንጃ! የት እንደመጣም አላውቅም!!'
ግድ የለም ረጋ በልና ንገረኝ እስኪ..?
'እሽ.. እ.. ሰ ማ ዕ ቱ..'
በል አይዞህ..
"ሰ ማ ዕ ቱ አባቴ.. እባክህ የመኖር ብርታትን ስጠኝ! ከህያውነቴ ላይ ህይወትን ዝራ.. መንፈሴንም አነቃቃው.. ልቤንም በተስፋ ሙላው.. በዚህ ዓለም ለመኖር እሚገፋኝ ብርቱ ምክኒያት ፍጠርልኝ.. በራሴ ታሪክ ዋና ገፀባህሪ ባልሆንኳን ጥሩ ረዳት ተዋናይ አድርገኝ!.. ማስተዋልና ጥበብን ስጠኝ.. እናቴን እድሜና ጤና ሰተህ አቆይልኝ.. ሐገራችንን ባርክ..አሜን።" እንዲህ ብየ ጸለይኩ.. ማለቴ ጸለየ.. እራሴን አመመኝ.. ወደ ቤት ልሂድ በቃ!!!
ቆይ እንጂ..
'አይ ልክ ያልሆነ ነገር አለ!'
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሎዛ ቀኑ ለመምሸት ሲያስገመግም አይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ከቤተክርስቲያኑ ወጣችና ወደ ቤቷ ጠደፍ ስትል ድንገት እንደርሷ እሚጣደፈው አለምነህ ጋር ተጋጨች እና "ይቅርታ" ብላው ሳታስበው ፈገግ አለችና መንገዷን ቀጠለች.. አለምነህ በበኩሉ ፈገግ በማለቷ አፉ ተለጉሞ ምንም ሳይል ስትሄድ ቆሞ አያትና ለራሱ "በምሽት እሚታይ ፈገግታ! ወይ ግሩም!" አለ.. አዳሩንም እስኪገርመው ድረስ ፈገግታዋን እያሰበ ነጋ..
በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከቤተክርስቲያን መልስ ከማያውቃት ልጅ ጋር የተጋጩበት ቦታ ላይ ቆም አለና ድጋሚ ትጋጨው ይመስል ጠበቀ..
በራሱ ተገረመ.. "ምን ሁነህ ነው እዚህ የቆምክ? ኧረ ተንቀሳቀስ ባክህ ሰው ይስቅብሐል!" አለው ጭንቅላቱ..
አለምነህም እንደማፈር አንገቱን ደፍቶ እርምጃ ሲጅምር.. ከየት መጣች ሳትባል ሎዛ አሁንም ተጋጨችው.. አሁን ግን አለምነህ ባላወቀው ሐይል ተገፍቶ.. 'እያየሽ አትሄጅም?' አላት..(ማለት የፈለገው እንዳልሆነ ግልፅ ነው)
'በጣም ይቅርታ..!' አለችውና ፈገግ ሳትል ወደ መንገዷ ዞረች..
አለምነህ አሁንም ሳያስበው.. 'ትናንትም'ኮ እዚሁ ቦታ ላይ ተጋጭተሽኛል?' አላት..
ሎዛም ባለመገረም 'እውነት! ..ይቅርታ..ወንድም ስለቸኮልኩ ነው።' አለችው..
አይ ሁለቴማ ይቅርታ የለም! ባይሆን ፈገግ በይ!! ሊላት አስቦ ተወው እና.. እሽ..ብሏት ፊቱን ዞረ.. እርሷም ሳታመነታ ሄደች.. "ኧረ አለምነህ ነጋ! ምን ነካህ? ሆ!" አለ ለራሱ..
ባይሆን አሁን በደንብ አይቷታል.. እርሷም ድጋሚ ብታየው ታውቀዋለች..
.
.
.
..ይቀጥላል..
✍️Aman😑 YTZ
@amanytz
join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @amanytz
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
.
.
እንደምን አላቹህ ቤተሰቦች?
"ቀጠሮ ደረሰ
እየገሰገሰ.." እንዲል የቡሄ ጨፋሪ፤ ዛሬ ልቦለዱን እምንቀጥልበት ቀን ነበር ሁኖም በቀጠሮዬ ሰዓት አልተገኘሁም። ይህም ማለት እኔ Pure ሐበሻ ነኝ😇 + Lazy😖.. So ክፍል አሰራ ሁለት ላይ እንዳቆመ ከዚያ ቀጥሎ ያለው እንኳን እዚህ አዕምሮየ ላይም አልተፃፈም🤷♂️ እና ያው እንደ ሁልጊዜው🙄 ይቅርታ!🙏
ሰሞኑን Depressed ሳልሆን አልቀርም፤ እና ያው ታገሱ ለማለት ነው ይሄ ሁሉ..ታገሱሱሱ🙂🙏
'እስከ መቼ???☹️' ( እሚል አይጠፋም!🙄)
እስከ..ትንሽ🤏😊
.
.
.
✍️ Aman😑 YTZ
@amanytz
.
.
#ለጊዜ_ጌታ_የተፃፈ_ደብዳቤ!
.
.
ፈጣሪዬ ሆይ በሰማያት የምትኖር..
ብዙ መንገድ መተናል፣
ብዙ ትዝታዎችን ቋጥረናል፣
ብዙ ተስፋዎችን ሰንቀናል፣
ብዙ ሰዎችን አቅርበናል፣
ልብ ለልብ ተሳስረናል፣
መኖር አስከፊ ገፅ ቢኖረውም!
ለመሰንበት ጓጉተናል፣
ገና መኖርን ናፍቀናል፣
አዲስ ትዝታዎችን መመስረት አስበናል፣
በጥልቅ ፍቅር ወድቀናል፣
አብሮ ማርጀትን ተመኝተናል፣
ሞትን አርቀህ ትንሽ ጊዜ ስጠን ብለናል፣
እባክህ ጌታ ሆይ..
ቅጣት ያልካት ምድር አቅፋ አኑራኛለች፣
ስረግጣት ቢመራት ልትውጠኝ 'ጠብቃለች..!
እማይቻልህ የለ
ሁሉ በጅህ አይደለ!
በቃ ጊዜን አቁመው ቀናተም ይዘግዩ፣
የሰው እድሜ ይርዘም የወጣትነቱ፤
ኧረ ባክህ ጌታ ያላየነው አለ..
አታሳልፍብን ትንፋሽህን አትንሳን
ከመምጣታችን በፊት መቆየት እንሻለን..
ወይ ደግሞ ሁሉም ይቅር! ሁሉም ባንዴ ይጥፋ፣
የቀደመው ሞቶ! ቀሪው ከሚከፋ!
ወይ ሁሉም ባንድ ይሁን..!!
.
.
.
✍️Aman😑 YTZ
@amanytz
join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @amanytz
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
#~~የመስመር_ዳኛ~~ #፩
.
.
ለእግዜር ያልተዘረጋ እጅ.. ለሰው ልጅ ቢዘረጉት ከማሳፈር በቀር በረከት የለውም!!
.
.
..መኪናው ውስጥ ተደላድሎ እንደተቀመጠ ለመኪና ማቆያ ጠባቂው ወጣት በመኪናው መስኮት በኩል ሶስት የአስር ብር ኖታዎቸን አውለበለበለት.. ጠባቂውም ገስገስ ብሎ በመቅረብ እጥፍ ዘርጋ ልምጥምጥ እያለ በፈገግታ እያመሰገነ ተቀበለ፤..
ታዲያ ይሄኔ አዳፋ የለበሰች፣ አይኗ የደፈረሰ፣ መልኳ የጠወለገ፣.. ህፃን ያዘለች እንስት ወደ ባለ መኪናው በልመና እጇን ዘረጋች..ባለ መኪናው ግን ዝም ብሎ መስኮቱን ዘግቶ መኪናውን አንቀሳቀሰ..
"እንደዘጋህባት! ፈጣሪ ስትለምነው ይዝጋብህ!" አይባል ነገር።
የእንስቷ መልክ ሃዘን አላስነበበም.."ከተገኘ ጥሩ ካልሆነም ምንም አይደል!" እንደማለት..
እጆቿ መፍተልን፣ መስፋትን፣ ማስጌጥን.. ተነጥለው ከሰው ደጅ መጥናት ብርቱ ልማዳቸው እንዳደረጉ ያስታውቃል። በይሉንታ በአዕምሮዋ ሳታንሰላስል እጇ ለልመና ይፈጥናል። እጥፍ ዝርጋ ይላል። ይቺ እንስት ግን ለፈጠራት አምላክ ይህን ያህል ደጅ ፀንታ ይሆን?
ፈጣሪዋስ እንዲህ ሲያያት ምን ይላል!?
አንዱን አዝላ ሶስት እግር ተከል ልጆቿን እያስከተለች የጠወለገው መልኳ እንደ ሻማ መክብብ ባይፈካም፤ ባደፈው አይኗ የዛሬን ወጋገን ባታይበትም፤ የነገን ጀንበሮች አቅፋ ታድራለች።
.
.
.
ነሐሴ 03/2016 ዓ.ም
✍️Aman? YTZ
@amanytz
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @amanytz
✍✍✍✍✍✍
.
.
#ያንድ_ምሽት_ሀሳብ
ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤
ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤
የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥
የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤
ለካ ሰው ቢማር፥
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ::
✍በእውቀቱ ስዩም
(from= FB page= የመጽሐፍ ዓለም-Book Shelf)
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @amanytz
✍✍✍✍✍✍
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቤተሰቦች እንደምን አላቹህ??
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"Long Time No See?" እንዲል ፈረንጅ? በኢንተርኔት መገዘት ምክኒያት ጠፍተን ከርመናል እና ያው አሁንም ኢተርኔት ተፈቶ ሳይሆን ባንዱ ሆቴል Wifi ተጎልቸ ነው፤ እና በዚሁ ሳልፍ ሰላምታ ለማስተላለፍ እና በተግስት ቻናሉን ላለቀቃቹህ ቤተሰቦች ምስጋና ላቀርብ ነው!? እዚህ ላይ አንዳንድ አንባቢ? "እና Wifi ካለህ እስከዛሬ ምን ይዘጋሃል እማትፅፍ!!" ይል ይሆናል! ያለማስተባበያ መልሴ እሚሆነው Pure ስንፍና ብቻ ነው!!?♂️ እና ለዚያም ይቅርታ!????
መጨረሻ ሳስታውስ ቻናሉ 2K በላይ አባላት ነበሩት አሁን ወደ 1.7K ዝቅ ብሏል ግን ቢሆንም ብዙ አልከፋኝም ያለውን ይባርክ ነው።? እና ለናንተ 1.7K ግን ምስጋናየን አቀርባለሁ??? እንግዲህ በቻልኩት መጠን በሳምንት አንዴም ቢሆን የሆነች ነገር ለማጋራት እሞክራለሁ!! ማንኛውም አይነት ስነ-ጽሑፍ ያላቹህና ማጋራት እምተፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ ምክኒያቱም የቻናሉ አላማ ያ ነውና!!!
በመጨረሻም መልካም ቆይታ
ኢተርኔት እስኪፈታ
እኔ ሸገር ለመሄድ እስኪያበቃኝ
ወይ ሸገርን ማምጫ እስክናገኝ
በትግስት ጠብቁ
ከቤተሰብነት ሳትለቁ???
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
.
.
#ገጣሚ_አታፍቅሪ
ገጣሚ
ከሴት መተኛት ምንም
ስሜት አይሰጠው ለእርሱ
ከቃል ነው እንጂ
ከሴት ፍቅር አይዘው እርሱ
ስለዚህ
አፈቀርኩሽ ወደድኩሽ
ብሎ ቢያወራልሽ
ከሺህ ቃላት ወስዶ
እንድ ቃል ቢነግርሽ
እንዳትሰሚው እርሱን
እንዳታደንቂ ቃላት አጠቃቀሙን
ምክንያቱም
ላንቺ ቃል እምነት ነው
ላንቺ ቃል ፍቅር ነው
ላንቺ ቃል ተስፋ ነው
ግን
ቃል ለእርሱ ቀላል ነው
በቃ ዝም ብሎ
ፊደል መመስረት ነው
.
.
✍ገጣሚ ስንታየው ታገሰ
join and share
@Yelbedrset
@Yelbedrset
✍✍✍✍✍✍
inbox me @aman116
✍✍✍✍✍✍
ከዕለታት በአንዱ ቀን በምሰራበት የህክምና ማዕከል እድሜው ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ውስጥ የሆነ ያደፈ የወታደር መለዮ የለበሰ በክንራች የሚራመድ ረዘም ያለ ሰው ተራኛ ሁኖ ፊት ለፊቴ ካለው ወንበር ተሰይሟል
ስለመጣበት የህክምና ጉዳይ የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች ከጨረሰኩ በኃላ በመሀል....
እድሜህ ስንት ነው ብሎ ጠየቀኝ ?
እኔም ግራ እየተጋባሁ በመንተባተብ እድሜን ነገርኩት
ይገርማል ! ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ የህክምና ባለሙያ ወይም ህግ ማጥናት ነበር ዓላማዬ ብሎ መሬቱን በክራንች መታ መታ አድርጎ ያው የእናት ሀገር ጥሪ ሆኖ ህልሜን ጥዬ ጠብመንጃ ጨበጥኩ ወንድሜ
ብሎ በአይኑ የሞላውን እምባ በመዳፉ ጠራርጎ ንግግሩን ቀጠለ︎ :
ምን መሰለህ ወንድሜ ! ህልም የሌላት ሀገር የልጆቿን ህልም ትነጥቃለች ፤ ህልማችንን ነጥቀው ህልማቸውን አለበሱን። እንኳን ለቤተሰብና ለሐገር ልተርፍ ለራሴም አልሆንኩ ።
አቤት ያ ትንታግ ወጣት እንዴት ያሳዝን ነበር መሰለህ ወንድሜ ! ሲለኝ ድምፁ ውስጥ ቁጭትና ተስፋ መቁረጥ ተደብቆ ነበር ፤ ጎርናናው ድምፅ በችግር ግርማው ተነጥቆ ፣ መልከመልካም መልኩ በፀሐይ በውርጭ ከስሎ ላየው ልብን የሚሰረስር ሃዘን ጨምድዶ ይይዛል ።
ሰውየው ግን ቀጠለ ፦ ማንም ይሁን ማን ብሶቱን የሚተነፍስበት እህ ብሎ የሚያዳምጠው ጀሮ ይፈለጋል
አንዴ እኔን አንዴ ግድግዳውን እያየ በረጅሙ ተንፍሶ ....
“ ከሃዘን የከፋ ሃዘን አካል መጉደል እንዳይመስልህ
ሞትም ቢሆን ለሀገር የሚበረከት ትልቅ ስጦታ ነው።
ከሁሉ የከፋው ሃዘን ለሀገርህ የከፈልከው ውለታ ፣ የሰዋኸውን ወጣትነት በዜሮ አባዝቶ ለግለሰቦች ስልጣንና ለተራ ፓለቲካ ጨዋታ የተከፈለ መስዋዕትነት መሆኑን ስታይ ነው ።
አንድ ሀገር ሀገርነቷ የሚቀጥለው ወጣቱን ትውልድ በተለያየ የትምህርት መስክና ዘርፍ አስተምራ ሀገሩንና ወገኑን የሚጠቅምና የሚያገለግል ማድረግ ስትችል ብቻ ነው። ካለፈው ጦርነት ምን አተረፍን ብዙ ሞት፣ ብዙ አካል መጉደል ፣የብዙ ወጣት ምኞትና ዓላማ መሰናከል፣
ህፃናት ያለ ቤተሰብ መቅረትና ወላጆች ያለጧሪ መቅረት
ብዙ ብዙ ነገር አተሪፍን ፤ ይህ አልበቃ ብሎ ሌላ ጦርነት መች ነው ከዚህ አዙሪት የሚወጡት ብሎ ለአመታት ያመቀውን እንባ እንደዥረት ያወርደው ጀመር።
የማደርገው ግራ ገብቶኝ ፈዝዜ አየዋለሁ ።አንዳንዴ ከማፅናናት በላይ የሆኑ ሃዘኖች አሉ “በአይዞህ” የማይጠገኑ ስብራቶች አሉ.....ጠንክረህ ስራ ተስፋችን ነህ ብሎኝ ፊቱን አዙሮ በክራንች ነጠር ነጠር እያለ ከክፍሉ ለቆ ወጣ።
ክፍሉየን ለቆ ከወጣ ጀምሮ ስለሰውዬው እያሰብኩኝ
የሰውየውን ሁኔታ ለሰው ሳልናገር ተኛሁ።
እንቅልፌ ግን ሰውየውን ተከትሎ ወጦ ሄዶ ነበር። እኩለሌሊት ሲሆን ውስጤ የገባውን የማያባራ ሃዘን በግጥም ለመተንፈስ ተነሳሁና መፃፍ ጀመርኩ.....
በሃገሬ ሰማይ ስር
በሃገሬ ሰማይ ስር
በሃገሬ ሰማይ ስር........
ከዚህ በላይ መፃፍ አልቻልኩም !!
ልክክ የሌለው ደስታና ጫፍ የሌለው ስቃይ የሚገለጠው በዝምታ ነው።
ላልተፃፉ ሃዘኖቻችን
ላልተፃፉ ደስታዎቻችን
ፅዋችንን እናንሳ !
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana