ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
ንቁ ብርቱ ጀግና 90 ቀናት ሁለንተናዊ ለውጥ
ማስተር ሄኖክ 90 ቀናት(ብሬቭ) ሁለንተናዊ የለውጥ ማዕከል ላለፉት 10 አመታት በአካል ብቃት፣ ሥርዓተ ምግብ ፣በህይወት ክህሎት ፣በውፍረትና ከውፍረት ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች (ስኳር ፣ደምግፊት፣ ኮሌስትሮል) ለሚቸገሩ ዜጎች ሳይንሳዊ የሆኑ ስልጠናዎች በተለያዩ ማዕከላት እየሰጠ ይገኛል፡፡
በዚህም በርካቶች በአካልና በስነልቦና ብርቱ ሆነዋል፡፡ ከተለያዩ ህመሞች ማዳን ተችሏል ተብሏል ።
90 ቀናት ሁለንተናዊ የለውጥ ማዕከል መክፈል ለማይችሉ በአካል ብቃት፣ በስርዓተ ምግብ እና በህይወት ክህሎት በነፃ ያሰለጠናቸውን 8ኛ ዙር ሰልጣኞች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና የኪነጥበብ ባለሞያዎች በተገኙበት በወዳጅነት ፓርክ አስመርቋል ።
እንዲሁም ለ9ኛ ዙር አዲስ 2000 ተመዝጋቢዎች ልዩ የማስጀመሪያ እና የመቀበያ ዝግጅትንም ተካሂዷል ፡፡
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ከእስር ተለቀቁ
የደቡብ ኮሪያ ፍርድቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ላለመጠየቅ በመወሰኑ ዛሬ በሴኡል ከሚገኘው እስርቤት ተለቀዋል፡፡
ዮን በእ.አ.አ ታህሳስ 3 ቀን ባሳለፉትና ለአጭር ጊዜ በቆየው የማርሻል ህግ ምክንያት ከስራቸው እንደታገዱ የሚቆዩ ሲሆን በአመፅ የቀረበባቸው ክስም እንዳለ ይቆያል ተብሏል፡፡
የወንጀል ጉዳዩ በስልጣን ላይ በሚኖራቸው ቆይታ ዙርያ ክሚታየው የፍርድ ሂደት የተለየ ሲሆን በህገ-መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ወደ ሥራ ይመለሱ ወይም ከሥልጣናቸው ይነሱ በሚለው ጉዳይ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።
የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በሚከተሉት 7 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
ሀገራዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸው የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች የሚውሉ የቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ አፅድቋል::
መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
በምሽት የንግድ ቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ለማራዘም በወጣው ደንብ ዝርዝር ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
የተርሚናል አገልግሎት አሠራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አደረጃጀት እና አሠራርን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 166/2016 ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ለመተግበር የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል::
የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ‹ምቹ ዲጂታል ብድር› የተሰኘ ስርዓት በመተግበር ከ18.4 ቢሊየን በላይ ያለማስያዣ የዲጂታል ብድር መስጠቱን አስታወቀ፡፡
ባንኩ በፋይናንስ አቅርቦቱ" ለህብረት ሥራ ማህበራት ሲሰጥ የቆየውን ከማስያዣ ነጻ ብድር ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ዘርፍ በማስፋፋት በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን ‹ምቹ ዲጂታል ብድር› ሥራ ላይ በማዋል ከ18.4 ቢሊየን በላይ ያለማስያዣ ዲጂታል ብድር መስጥቱን አስታዉቋል፡፡
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደርቤ አስፋው ፤ የዲጂታል የብድር አገልግሎቱ ከ1.2 ሚሊያን በላይ ባለሂሳቦችን ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ይህም የስራ እድልን የፈጠረ፤ የአነስተኛ የንግድ ተቋማትን የአርጭር ጊዜ የፋይናንስ ችግር የቀረፈ ፤ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የተበደሩበት ፤በቤት ውስጥ የሚሰሩ ወጥተው ሰቅ ተከራይተው አገልግሎታቸውን ይበልጥ ተደራሽ ያደረጉበት፣ እንዳንዶች ደግሞ የነበረውን የቢዝነስ እንቅስቃሴያቸውን ይበልጥ በማቀላጠፍ ትርፋማ የሆኑበት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ባንኩ በሞባይል ዋሌት አገልግሎቱ ‹ኮፔይ ኢ ብር፤ ከ2.6 ትሪሊያን በላይ ግብይት በማከናወን ከግል ባንኮች አንደኛ ሲሆን ፤በኢትዮጵያ አገልግሎቱን ከሚሰጡ ተቋማት ድግሞ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛልም ብለዋል፡፡
‹ኮፔይ ኢ ብር› አሁን ላይ ከ14.5 ሚሊየን በላይ ደንበኞቹ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ትልቅ ፕላትፎርም ነው ያሉት።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደርቤ አስፋው ይህን የገለጹት፤በዛሬዉ እለት ባንኩ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ‹ፕሮጀክት 20 ለ 20ኛ ዓመት›በሚሊ መሪ ቃል በዋናዉ መስሪያ ቤቱ እያከበረ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡
የአርሶ አደሩን ማህበረሰብ ፤የህብረት ሥራ ማህበራትን በማስተባበር የተመሰረተው የአሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንከ፤ በወቅቱ ለገጠሩ ማህበረሰብ የፋይናንስ አቅርቦት እጦት ዓይነተኛ መፍትሄ በመሆን የባንክ ኢንዱስትሪዉን የተቀላቀለ ነዉ ተብሏል፡፡
በአገልግሎቱ ተደራሽነት የሀገሪቱን ከልሎች ከጫፍ እስከ ጫፍ በማዳረስ፣ መሰረተ ልማት ላልደረሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ አማራጭ ይዞ ስለመምጣቱም ተነግሯል፡፡
ልኡል ወልዴ
የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
የጨዋታ ቀን !
ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ያውንዴ በሚገኘው ኦሌምቤ ስታዲየም በካሜሩን እና ኢትዮጵያ መካከል ከምሽቱ 3፡00 ላይ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት ጨዋታውን በሚያደርግበት ኦሌምቤ ስታዲየም አከናውኗል።
ድል ለኢትዮጵያ
ጋዲሳ መገርሳ
የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago