ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
በአዲስ አበባ 12ተኛ ክፍል ተፈትነው ያለፉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተ
የሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለተፈተኑ 39 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱን ገለጸ።
ከተሸለሙ ተማሪዎች ውስጥም 9ኙ ቀጥታ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተዘዋወሩ ሲሆን የተቀሩት 30 ተማሪዎች በሪሚድያል ውጤታቸውን አሻሽለው ወደ ዩንቨርስቲ እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል።
የአዲስአበባ የሴቶች ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወሮ ገነት ቅጣው " የአሁኑ አመት ካባለፈው አመት የተማሪዎች ውጤት መሻሻል እንደታየና ተማሪዎቹም ያለባቸውን ጉዳት ተቋቁመው ይህን ውጤት በማስመዝገባቸው ሊበረታቱ ይገባል
እንዲሁም ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሽልማት መርሐግብራችንንም አካሂደናል" ብለዋል።
በዕለቱም አካል ጉዳተኛ የሆኑ የዮንቪርሲቲ ተማሪ የነበሩ ሰዎች በመገኘት ለተማሪዎቹ ግንዛቤ ማስጨበጥና ከህይወት ልምዳቸውም በማካፈል አካልጉዳተኝነታቸው ከምንም እንደማያግዳቸው መግለጻቸውን አሳውቀዋል ።
በ2016 በአካል ጉዳተኞችና በአይነስውራን የተሰሙ አበይት ክስተቶች
የሰው ልጅ በተለያዩ የህይወት ውጣውረድ ሲያልፍ ኑሮው አሰልቺ እንዳይሆንበት ጊዜን በሴኮንድ፣ በደቂቃ፣ በሰኣት፣ በእለታት፣ በሳምንት፣ በወራትና በአመታት እየከፋፈለ በጊዜ ምሕዋር ይጓዛል።
ባበጀው ጊዜና በወቅቶች ፍርርቆሽ ላይ በመመርኮዝ ግላዊና የወል በአላትን ይዘክራል፡ ያከብራል። እንዲያ እንዲህ እያለ ነባሩን ጊዜ “አሮጌ” ብሎ ሲሸኝ መጪውን ደግሞ በአዲስ መንፈስ ራሱን አድሶ ይቀበላል።
“አዲሱ አመት” ብለን የተቀበልነው 2016 አመት በተራው ደግሞ “አሮጌ” ተብሎ ላዲሱ 2017 አመት ተራውን ካስረከበ 16 ቀናት ተቆጠሩ። እነሆ ዛሬ መስከረም 16 2017 ነውና እንኳን ለመስቀል ደመራ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!
በ2016 በአካል ጉዳተኞችና በአይነስውራን ዙሪያ የተከሰቱ ሁነቶችን በወፍበረር እንደሚከተለው እንዳስስ።
የአዲስ አበባ የአካል ጉዳተኞች ማህበር ከወረዳ አንስቶ እስከማእከል ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አዳዲስ አመራሮችን ሾሟል.
ከሞላጎደል “ሰላማዊ ነው!” በተባለው ምርጫ በትምህርት ደረጃቸው የተሻሉና በድምጽ ብልጫ ያሸነፉ አዳዲስ አባላት ተመርጠዋል።
አዳዲስ የአይነስውራን ት/ቤቶች ተገነቡ.
በአዲስ አበባ በአቃቂቃሊቲ ክፍለከተማ በቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት አስተባባሪነት “ብርሀን የአይነስውራን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት” የተሰኘው ት/ቤቱ በግንቦት ተመርቆ 312 ተማሪዎችን ለመቀበል ክፍት ሆኗል።
በተጨማሪም በቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከተማ “ድጋፍና እንክብካቤ” ማእከል ልዩ የአይነስውራን አዳሪ ት/ቤት ገንብቶ በሚያዝያ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
የኢትዮጵያ አይነስውራን ብሄራዊ ማህበር የስነጽሁፍ ምሽት አዘጋጀ.
ከቅርብ አመታት ወዲህ “የመጀመሪያው ነው!” በተባለው የስነጽሑፍ ምሽት የማህበሩ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች የራሳቸውንና የሌሎች ደራሲያን ስራዎችን አቅርበዋል።
በማህበሩ ጽ/ቤት አዳራሽ በተካኼደው የስነጽሁፍ ምሽት የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆነው ደበበ ሰይፉ ተዘክሯል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የነበረችውና የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ስራአስኪያጅ የሆነችው የዝና ወርቁ የስነጽሁፍ ልምዷን ለታዳሚያን አካፍላለች።
"ከለቻ" መጽሐፍ ተመርቋል።
በአይነስውሩ ጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ "ከለቻ" በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ በጳጉሜ 3 2016 በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ተመርቋል።
"ከለቻ" መጽሐፍ በዘውግ በኩል ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ5 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በ96 ገፆች ተቀንብቦ በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
በዚህ መጽሐፍ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ፀሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን አጋርተዋል።
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን “አ.ሚ.ኮ” የሚሰራው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ በ2012 “እየሞኸረሩ መሀይም” የተሰኘ መጽሐፉን አሳትሞ ነበር።
በስፖርቱ ዘርፍ ያለውን ጉዳይ ስንዳስስ በፓሪስ ፓራል ኦለምፒክ ትእግስት ገዛኸኝ በ1500 ሜትር ከፊል/ጭላንጭል አይነስውራን ውድድር ወርቅ አግኝታለች። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በቶክዮ 2021 በተካኼደው የፓራል ኦለምፒክ በተመሳሳይ ርቀት አሸንፋለች።
ኢትዮጵያ በታሪኳ በ1500 ሜትር ከፊል/ጭላንጭል አይነስውራን ያገኘችው ወርቅ ሜዳሊያ ሁለት ሲሆን ሁለቱንም ወርቆች ያመጣችው ትእግስት ገዛኸኝ ናት።
በፓሪስ 2024 የፓራል ኦለምፒክ ያየሽ ጌቴ በ1500 ሜትር ሙሉበሙሉ አይነስውር “T11” በተደረገው ውድድር አራት ደቂቃ 27 ሴኮንድ 68 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች።
ያየሽ ጌቴ በጃፓን ኮቤ 2024 የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ውድድር በራሷ ተይዞ የነበረውን “አራት ደቂቃ 31 ሴኮንድ” የአለም ሪከርድ በአራት ሴኮንድ በማሻሻል የበላይ ሆናለች።
በሌላ በኩል በስድስት ኪሎ ጥር 18 2016 ከማርቆስ ቤተክርስትያን ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ሲሻገሩ ሶስት ሴት የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሶስቱም ተማሪዎች አዲስ ገቢዎች ነበሩ። የአንደኛዋ ተማሪ ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።
This is a file showing a step by step registration process.
Celebrate our phenomenal achievements of the past 9 months, a testament to our unwavering dedication and teamwork! Let's harness this momentum, unite once more, and reach even greater heights of success together.
Dear how are you. Nice to meet u. Please, if there is a student (Male or female) with minor or major types of disability & want to apply for MA scholarship at Gondar University, share this call. Thank you.
በዚ ፎቶ ላይ የምትመለከቷት ተማሪ አስቴር ፋንቱ ለመጨረሻ ጊዜ ማክሰኞ መጋቢት 10 ሲሆን የታየችው በጊቢ ውስጥም ሆነ ከጊቢ ውጭ ያያቹሃት እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።
Section 1
Phone no 0931629632
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana