Sophia Ahmed [ Judi ]

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 2 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month ago

Last updated 2 months ago

4 months, 1 week ago

ስለ አላህ አስባለሁ ......

እንዲሁ እንደሚያኖረኝ … እኔ ላይ ቂም አልባ እንደሆነው። በጥፋቴ መቅጣቱን ሳይሆን ይቅርታውን እንደሚያስቀድምልኝ! ነውሬን የመደበቁ ልክ ወስን አልባነቱን! " አንተ አይብን ደባቂ ነህ! " ደብቅልኝ!

ስለ አላህ አስባለሁ ስለ እዝነቱ......

ስለሚያሳየኝ የልኮች ሁሉ ከፍታ … ስለሚጠቁመኝ መልካም ነገሮች። ስለ አላህ ስለ እዝነቱ ፤ ከጭካኔው በእጥፍ ስለራቀው። የመኖሬም፤ ነገ ጀነትን የመሻቴም ቁልፍ ስለሆነው ስለ እዝነቱ አስባለሁ። " ከእዝነትህ አታጉድልብኝ! "

ስለ አላህ ስለ ውዴታው አስባለሁ.....

ስለሰጠኝ ሰፊ ኒዕማ ከኔ ስላለመጠበቁ። ስለ እንክብካቤው … በሶላቱ እንደሚያነፃኝ፣ በፆሙ እንደሚያድሰኝ ፣ በሶደቃው እንደሚያቆመኝ ፣ በዱዐዬ እንደሚጠግነኝ። ስለ ሁሉም ስለኔ ስላለው ስለውዴታው አስባለሁ። " ከውዴታህ አታርቀኝ!

አልሃምዱሊላህ!

@Sophia_Ahmed1
@Sophia_Ahmed1

4 months, 1 week ago

የልብ ወግ #3፡ " ያለፈ ታሪክ.... "

"ስልችት ብሎኛል!"

"ምኑ?"

"የሚመረጥ የለውም... መኖር አሰልችቶኛል?"

"ጓዝ አበዛሽ እንዴ?"

"የምን ጓዝ?"

"ተጥሎ መረሳት የነበረበትን ያለፈ ታሪክ ዛሬም ያለ እና የሚኖር እስኪመስልሽ ተሸክመሻል?"

"እንዴ? ... ወዴት ይጣላል? የኔ እኮ ነው። የኖርኩት። ማንነቴ የተገነባበት ነው። ወደ የት ነው የምጥለው? አያስፈልገኝም ልጣለው ብልስ ግማሽ አያስቀረኝም?"

"ወጣት ነሽ አይደል? ህፃን እያለሽ የነበሩሽን የምትወጃቸውን እና በምርጫሽ የተገዙልሽ የነበሩ የምትምነሰነሽባቸው ልብሶችሽን ፤ ያለ ምርጫሽ የተገዙልሽ የነበሩ የለበስሻቸውን ሁሉ አሁንም ትለብሻቸዋለሽ?"

"አይሆኑኝም እኮ ልኬ አይደሉም እንዴት እለብሳቸዋለሁ? በየጊዜው እየተካካሁ አስወግጃቸዋለሁ"

"ያለፈ ታሪክም እኮ እንደዛ ነው ለዛሬው አንቺነትሽ ያዋጣው ነገር ይኖራል እንጂ ለዛሬው አንቺነትሽ ግን ላይበቃሽ ይችላል። ልክ እንደልብሶችሽ በጊዜ ሂደት ወደሚሆንሽ እየተቀየረ በአዲስ መተካት ይኖርበታል!"

"የማይጠቅመኝን ያለፈ ነገር ማስወገድ ከመሰላቸት የሚያድነኝ ከሆነ በደስታ አደርገዋለሁ! ቀላል ይመስልሻል ግን?"

"ለአመታት በወጉ ያልተያዘን ቤት በደቂቃዎች ውስጥ ማሳመር ቀላል ነው?"

"እንዴት ቀላል ይሆናል?"

" ይሄም ቀላል አይደለም። ለመሞከር መነሳት ግን በግማሽ መንገዱን ይጠርገዋል!"

"በጉጉት መኖር ምን እንደሚመስል ማወቅ እና መኖር እፈልጋለሁ።"

"እንዲሆንልሽ ምኞቴ ነው።"
©muna_Abduselam

@Sophia_Ahmed1
@Sophia_Ahmed1

5 months ago

"ለምንድነው ለሰውም ለምንም ነገር ግድ የሌለሽ?"

ከማንም በላይ ግድ ኖሮኝ ያውቅ ነበር።

"ታዲያ ምን ቀየረሽ?"

አልተቀየርኩም መቆጠብ ነው የጀመርኩት።

"አልገባኝም!"

በርምጃቸው ልክ መራመድ፤ በሁኔታቸው ልክ መሆን፤ አለመግፋትም አለመሳብም፤ አለ አይደል የሚሆነውን መመልከትና በልኩ መልስ መስጠት? ልክ እንደዛ ማለቴ ነው።

"ይቻላል?"

በትግል አዎ። አንዳንዴ ያቅተኛል እንደረደራለሁ። አንዳንዴ ደግሞ አልንቀሳቀስም። ስራ የበዛብኝ ይመስለኛል።

"ደስ አይልም አይደል?"

ደስ ይላል ደስም አይልም። የውስጥን ማንነት ያስክዳል። አጥብቀው ማቀፍ እየፈለጉ በቀዝቃዛ ስሜት እጅን ብቻ እንደመዘርጋት ነው። የሚያሳምም ጥፊ መሰንዘር እየፈለጉ ከውስጥ ጋር ታግሎ ስስ የማይሞቅም የማይበርድም ፈገግታ ፈገግ እንደማለት ነው።

"ታዲያ ለምን በራስሽ ልክ አትሆኚም? ግድ እንዳይሰጥሽ መሆንን ለምን ትለማመጃለሽ?"

ፍራቻ ነዋ!

"የምን ፍራቻ?"

የልብ ስብራት ፍራቻ። እንዳይጠገኑ ሆኖ ተሰባብሮ ማለቅን ፍራቻ።

"ምን ይሻላል?"

እኔእንጃ ... ግን የሆነ መንገድ ቢኖር እመኛለሁ። የማይጠነቀቁበት... የማይሰጉበት... ግድ የለሽ መሆንን ምርጫ ከማድረግ የሚዳንበት።

"ባደረገው!"

እምምም...
©Muna_Abduselam

@Sophia_Ahmed1
@Sophia_Ahmed1

5 months, 4 weeks ago
Sophia Ahmed [ Judi ]
5 months, 4 weeks ago
Sophia Ahmed [ Judi ]
5 months, 4 weeks ago
Sophia Ahmed [ Judi ]
5 months, 4 weeks ago
Sophia Ahmed [ Judi ]
5 months, 4 weeks ago
Sophia Ahmed [ Judi ]
5 months, 4 weeks ago
Sophia Ahmed [ Judi ]
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 weeks, 2 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month ago

Last updated 2 months ago