ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month ago
Last updated 3 weeks, 6 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month, 2 weeks ago
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል‼️
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ " የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ " ሲል አሳስቧል።
የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?
*➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር
➡️ የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።*@Esat_tv1
@Esat_tv1
የመንግስት ሠራተኞች ጥናቱ በሚኒስትሮች ምክር-ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት በድጋሚ እንዲታይ ተጠየቀ‼️
አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ እንደጠበቅነዉ አይደለም ያሉ የተለያዩ የመንግስት ስራተኞች ጥናቱ በሚኒስትሮች ምክር-ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት በድጋሚ መታየት እንዳለበት መናገራቸውን ካፒታል ዘግቧል።
ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ከማፅደቁ አስቀድሞ ሰራተኞችን ማወያየት እንዳለበት እና በድጋሚ መታየት እንደሚኖርበት ተጠይቋል ያለው ካፒታል ያነጋገራቸው ሠራተኞች እንደገለፁት የደመወዝ ማሻሻያው አሁን ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ እንደተባለውም ከግምት ያላስገባና እንደጠበቁት እንዳልሆነ አስረድተዋል።
''ስለደመወዝ ማሻሻያው ጠ/ሚኒስትሩ በተናገሩበት ሰዓት እጅግ በጣም ጠብቄ ነበር ነገር ግን አሁን ከዛ የተለየ ነገር ነው የሆነው'' ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህር ነግረውኛል ብሏል።
የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከመኖሪያ ቤት ኪራይ ጀምሮ ከምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን ጨምሮ የዋጋው ንረቱ በእጥፍ እንደጨመረ ሠራተኞቹ ለካፒታል ያቀረቡት ቅሬታ ያመላክታል።
ይህ እንኳን ተፈፃሚ ይሁን ከተባለ የስራ ግብር እንዲቀነስ መደረግ አለበት በማለት ተናግረዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን በሚመለከት ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት " በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ “በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም” ብለዋል።
በአዲሱ እርከን ከተካተቱት የመንግስት ሰራተኞች ዉስጥ የጤና ባለሞያዎች ይገኙበታል። ካፒታል ያነጋገራቸዉ እነዚህ ባለሞያዎች እንደሚሉት " ቀድሞ የመሰለን ጭማሪዉ በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺህ ብር የሚያህል ገንዘብ ቢሆንም በተቃራኒው የሆነዉ ግን ያሳዝናል ። አሁን ላይ ከ 1500 ብር በታች ነዉ የተጨመረዉ ይህ ደግሞ ተመልሶ በስራ ግብር የሚቀነስ መሆኑ የተደረገዉ ጭማሪ ሳይሆን ተስፋ ብቻ ነዉ በማለት ቅሬታዎች አቅርበዋል።
የደሞዝ ጭማሪ መኖሩን መንግስት መናገሩን ተከትሎ በማግስቱ የሁሉም ነገር ዋጋ በሁለት እጥፍ ጨምሯል። በዚህም ሰራተኛዉም ሆነ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ምንም የተሰጣቸዉ ነገር ሳይኖርና ጭማሪ እጃቸዉ ሳይገባ የኑሮ ዉድነቱ ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉም ሁኔታዉን በምሬት ገልፀዉታል።
ከቀናት በኃላ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀዉ ረቂቅ ጥናቱ ላይ እንደተገለፀዉ ዝቅተኛው ደረጃ የመነሻ ደመወዝ በመንግስት መሥሪያ ቤቶች አሁን በሥራ ላይ ካለው ብር 1,100 የመነሻ ወደ 4760 ወይም 332.73% የተደረገ ሲሆን ፤
ከፍተኛው ደረጃ የመነሻ ደመወዝ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የፕሮፌሰር የሥራ መደብ ካረፈበት የመነሻ ደመወዝ ብር 20,468 ሲሆን ይህ ተደርጎል የተባለዉ ጭማሪ በ5% በመቶ ወይም 1023 ብር እንደሆነ ካፒታል በረቂቅ አዋጁ ተመልክቷል ።
ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለዉሳኔ የቀረበዉ እና በገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካኝነት ጥናት ተደርጎበታል የተባለው ይህ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክርቤት በቀን 28 /12/ 2016 ዓ.ም. ነዉ በመቅረብ ለማወቅ የተቻለው።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month ago
Last updated 3 weeks, 6 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month, 2 weeks ago