ኢማን መልቲሚዲያ

Description
<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)


https://telega.io/c/sineislam
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month, 2 weeks ago

❤️የኛ ነብይ ﷺ
ዝምታቸው ብዙ ሳቃቸው ትንሽ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ በህፃናት ጎን ሲያልፉ ሰላም ይሏቸው ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ለሰው ልጆች ለእንስሳት ሳይቀር ያዝኑ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ሰዎችን አክባሪና ተናናሽ ኩራት የሚባል ነገር አያውቁም ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ይቅር ባይና ይቅር ማለትን የሚወዱ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ የቅርቧ አለም ብልጭልጭ ይልቅ የመጨረሻውን አለም የሚናፍቁ
ዛሂድ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ጌታቸውን አመስጋኝ ሰዎችንም አመስጋኝ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ሷላትን የልቤ እርጋታ እያሉ ለጌታቸው ባጣምም ይሰግዱ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ በፈተናዎች እና በችግሮች ላይ ታጋሽ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ውሸትን በጣም ይጠሉ የነበሩ «ታመኙ-እውነተኛ» ነበሩ።

❤️የኛ ነብይﷺ ስድብንም ሆነ እርግማንን ይጠሉ ነበር።

የኔ ዉድ ነብይ ፤ ሩሔም፣ ገንዘቤም እናቴም፣ አባቴም ለአንቱ ፊዳ ይሁኑሎት..
ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም።

@sineislam
@sineislam

1 month, 2 weeks ago

ተወዳጁ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በተምር ቁራጭ ቢሆንም እንኳን እሳትን ተጠንቀቁ።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
:
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ሶደቃ ሰውየውን ከአላህ ቅጣት ይታደጋል። ወንጀሉና ኃጢኣቱ ጥፋት ሲፈርድበት። ሶደቃ ይመጣና ከቅጣት ያድነዋል። ከጥፋት ያላቀዋል።»
#በተምር ቁራጭም ቢሆን ነፍሳችሁን ከእሳት ጠብቁ!…

@sineislam

1 month, 2 weeks ago

መቼ ነው እውነተኛ ሙስሊሞች የምንሆነው?

መቼ ነው አላህ በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው?

መቼ ነው አሏህ ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው?

መቼ ነው አሏህ እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው?

መቼ ነው ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው?

መቼ ነው እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?

መቼ ነው ሀዲስና ቁርአን ስንሰማ የምንደነግጠው?

መቼ ነው ለመልካም ስራ ሰበብ የምንሆነው?

መቼ ነው በሰላታችን የምንጠቀመው?

መቼ ነው ዱአችን ተሰሚነት የሚያገኝው?

መቼ ነው ዲናችንን የምንረዳው?

መቼ ነው ውሎና አዳራችን በሱና የሚሆነው?

መቼ ነው ሙሉ በሙሉ በአሏህ ላይ የምንመካው?

መቼ ነው የዱንያን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?

መቼ ነው ቤታችን ውስጥ ያለው  የተበላሸ ሂዎት የሚስተካከለው?

መቼ ነው ቤታችን ውስጥ ቁርአንና ሀዲስ የሚቀራው የሚወራው?

መቼ ነው ውሽት እምናቆመው?

መቼ ነው የአሏህን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው?

መቼ ነው እኔ እኔ ማለት ትተን ውንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው?

መቼ ነው ለሰዎች ከአላህ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው?

መቼ ነው በኛ ዘመን በዲናችን የበላይነት ምናገኝው?

መቼ ነው የኢስላም ዘቦች የምንሆነው?

መቼ ነው ኢስላምን የምናስተዋውቀው?

መቼ ነው ለድሃ እምናዝነው?.

መቼ ነው ትዳራችን ስላም ሚያገኝው?

መቼ ነው የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበት ለትዳር የምንቻኮለው?

መቼ ነው ዱአቶቻችን ለገጠሩ የሚጨነቁት?

መቼ ነው ከሀሜት; ስውን ከመበድል; ክማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው?

መቼ ነው ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው?

መቼ ነው ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው?

መቼ ነው ለአሏህ ብለን እምንዋደደው?

መቼ ነው አሏህ በወሰነልን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?

መቼ ነው የሌሊት ሰላትንና ዚክርን የምንላመደው?

መቼ ነው የበድለንን ይቅር የመንለው?

መቼ ነው ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው?

መቼ ነው ከሞት ቡኃላ ላለው ሂወት ስንቅ እምናዘጋጀው?

መቼ ነው ኡለማዎቻችንን እምናከብረው?

መቼ ነው ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው?

መቼ ነው ባወቅነው የምንሰራው?

መቼ ነው የ ምንሞትበትን ቀንም ይሁን ስፍራ እንደማናውቅ ተገንዝበን በተጠንቀቅ የምንቆመው?

መቼ እረ መቼ ነው ኢስላምን የምንኖረው?

መቼ ነው ለእነዚህ ተግባራዊ መልስ የምንመልሰው?

አሏህ ያግራልን

አሚን

አቡ ፋሩቅ

@sineislam
@sineislam

3 months, 3 weeks ago

**1. በጣም ብዙ የምትናገር ከሆነ ፤ ትዋሻለህ።

  1. በጣም ብዙ የምታስብ ከሆነ ፤ ድብርት ውስጥ ትገባለህ።

  2. በጣም ብዙ የምታለቅስ ከሆነ ፤ የአይን እይታህን ታጣዋለህ።

  3. በጣም ብዙ የምታፈቅር ከሆነ ፤ ማንነትህ ይጠፋል።

  4. በጣም ብዙ ስለሰዎች የምታስብ ከሆነ ፤ ዋጋህን ሰዎች እያጡት ይመጣሉ።

  5. በጣም ብዙ የምትጫወት ከሆነ ፤ አብዛኛውን ጊዜ ማንም ከቁምነገር አይቆጥርህም።

  6. በጣም ብዙ የምታምን ከሆነ ፤ በሰዎች ትካዳለህ።

  7. በጣም ብዙ የምትሰራ ከሆነ ፤ በውጥረት ትሞታለህ።

  8. በጣም ብዙ የምትመገብ ከሆነ ፤ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ውስጥ ትገባለህ።

  9. በጣም ብዙ እንቅልፍ የምትተኛ ከሆነ ፤ ስራ ፈት ትሆናለህ።

  10. በጣም ብዙ ገንዘብ የምታባክን ከሆነ ፤ የወደፊት ነገር ምንም አይኖርህም።

  11. በጣም ብዙ ሜክፕ የምትጠቀም ከሆነ ፤ የአንተን ውበት እያጣኋው ትመጣለህ።

  12. በጣም ብዙ ነገር የምትመለከት ከሆነ ፤ ትኩረትህን እያጣኸው ትመጣለህ ።

  13. በጣም ብዙ ስለ ህይወት የምታስብና የምታሳድድ ከሆነ ፣ ሁሉንም ነገርህን ታጣለህ።

  14. በጣም ብዙ ነገር የምትጠብቅ ከሆነ ፤ በጣም ትከፋለህ። በጣም ብዙ አትሁን ምክንያቱም ያ በጣም ብዙ ነገር ብዙ ይጎዳሀልና።**@sineislam@sineislam

3 months, 3 weeks ago

**20 ምርጥ መልዕክቶች

1. ነገሮች ሲጠኑባችሁ ወደ ሱጁድና ዱዓእ ፍጠኑ እንጂ ብሶትና ለቅሶ አታብዙ፡፡

2. ሁሉም ነገር ይሄዳል፤ ሲሄድ ግን አይመለስም፡፡ ዱዓእ ሲቀር፡፡ ዱዓእ ተስፋን፣ በረከትን፣ ሲሳይን፣ ድልን፣ ስጦታን ይዞ ይመለሳል፡፡

3. በምድር ላይ አንድም ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ለወላጆቹ መልካም የመዋል ታሪክ ያለው ቢሆን እንጂ፡፡

4. የሰው ልጅ ሆኖ ከሀሳብ ነፃ የሆነ የለም፡፡ ሆኖም ግን ያለበት ሀገር ዱንያ መሆኗን እያስታወሰ ፈገግ የሚል ብዙ ሰው አለ፡፡

5. ምርጦቹ ጓደኞችህ ዱንያ የሳቀችልህ ቀን አይደናገጡም፡፡ በዞረችብህ ጊዜም አይደሰቱብህም፡፡

6. ግርማ ሞገስን ከሚያጎናጽፉ ነገሮች መካከል ብዙ አለማውራት፤ የፊትን ዉበት ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል ፈገግታን ማብዛት ይገኙበታል፡፡

7. የሰው ልጅ ባያምንበትም እንኳ የሚናገርን ሰው ሀሳብ ቢያዳምጥ የሚማረው ነገር ይኖራል፡፡

8. ልጅህን ቁርኣንን አስተምረው፤ ቁርኣን ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል፡፡

9. ትላልቅ ሰዎችን አክብሩ፤ ዘመናቸው ባልሆነ ዘመን ውስጥ እየኖሩ ነውና፡፡

10. ሁሉንም ሰው ለማስወደድና ለማርካት አትፍጨርጨር፡፡ በዚህ ጉዳይ ነቢያትም እንኳን አልተሳካላቸውምና፡፡

11. ዉስጥህን ህመም እየተሰማህ ፈገግ የምትል ከሆነ የጥንካሬህ ማሳያ ነው፡፡

12. የሰው ልጅ የሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነው፡፡ ፀሐይ እሳት ጭምር አላት ነገርግን ብርሃን ትሠጣለች፤ ፍጥረተ ዓለሙን በብርሃን ትሞላለች፡፡

13. በእናቱ እግር ሥር አገልጋይ ሆኖ የኖረ በሰዎች አናት ላይ ንጉስ ሆኖ ይኖራል፡፡

14. ብዙ በመናገር የማይታወቅ ሰው መናገር ሲጀምር ትኩረት ይስባል፡፡

15. ባመለጠችህ አንዲት ኮከብ አትከፋ፡፡ ሰማይ በከዋክብት የተሞላች ናት፡፡ እሷን ከረሳህ ምናልባት ጨረቃ ትወጣልህ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡

16. ከአላህ (ሱ.ወ.) መልካም ነገር እንጂ አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ወደ ቀናው መንገድ መራን፣ ጤና ሰጠን፣ ዕድሜ ሰጠን፣ ቤተሰብ ሰጠን፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰጠን፡፡

17. ልንረሳቸው ብንፈልግ እንኳን ዉስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ኃጢአቶችን ይዘን እየዞርን ነው፡፡

18. የሐዘን ባቡር ፉርጎው ቢበዛም ቢረዝምም የመጨረሻ ፌርማታው ደስታ ስለመሆኑ  አንጠራጠር፡፡

19. ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አንዳንድ  ደግሞ ዕድሜ ነው፡፡ ዕድሜህ ሊሆን የሚችልን ዕድል በቀላሉ አታሳልፍ፡፡

20. የተጃጃለ ሰው ሁኔታው እንደ በራሪ አዕዋፍ ነው፡፡ ከፍ ባለ ቁጥር ሰውን አሳንሶ ይመለከታል፡፡**@sineislam@sineislam

3 months, 3 weeks ago

**ሁለት ወጣቶች ከበረሃው አቅጣጫ አንድን ሰው አንጠልጥለው ለዳኝነት ዑመር ሸንጎ ፊት አቆሙት።

"ምንድን ነው?" አለ ዑመር ግራ ተጋብቶ
"የሙእሚኖች መሪ ሆይ ይህ ሰው አባታችንን ገሎብናል ተገቢው ቅጣት ይፈፀምልን" አሉ
ዑመር ወደ ሰውየው ዞሮ "እውነት አባታቸውን ገድለሀልን?" ሲል ጠየቀው።

"አዎ" አለ።
"ለምን ገደልከው?!"

"ግመሉን እየነዳ አጥሬን ዘልቆ ገባ ከግቢዬ ውጣ ብለው አልሰማም አልወጣም አለኝ። ለማባረር ትንሽዬ ድንጋይ አንስቼ ብወረውር አናቱ መሐል ላይ አርፎ በዛው ምክንያት ሞተ" አለ። በዚህ ጊዜ ዑመር ውሳኔ አስተላለፈ። ቂሳስ ነውና እንዲገደል ወሰነ።

ሰውዬው ፈቃድ ጠይቆ መናገር ጀመረ
"የሙእሚን መሪ ሆይ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረው ጌታ እለምንሀለው ሚስቴና ልጆቼን በምድረ በዳው በረሀ ብቻቸውን ትቻቸዋለሁ ተሰናብቻቸው እንድመለስ ፍቀድልኝ። ከአላህ በታች እኔ እንጂ ማንም ዘመድ የላቸውም" አለ
"ወደ ቤተሰብህ ሄደህ እስክትመለስ ተያዥ ዋስህ ማነው?"

"የማውቀውም የሚያውቀኝም ማንም የለም" አለ ዓይኖቹን እያስለመለመ

ስሙንም፣ ቤቱንም፣ ጎሣውንም የሚያውቅ የለምና ሁሉም ሰው ዝም ጭጭ አለ። ሰውየው ቢቀር የሞት ውሳኔው ተያዡ ላይ ተፈፃሚ ስለሚሆን አንገትን በሰይፍ ለሚያስቀነጥስ ዋስትና ማን ይድፈር?!

ልጆቹ በረሃብ እየሞቱ ይግደለው ወይስ ያለ ተያዥ ይልቀቀው የሚያደርገው ጠፍቶት ግራ በመጋባት አንገቱን አቀረቀረ። አባታቸው ወደተገደለባቸው ልጆች ዞሮ አውፍ ይሉት ዘንድ ቢጠይቅ በፍፁም አባታችንን የገደለ መገደል አለበት ብለውት ይባስ ተጨነቀ።

"እናንተ ሰዎች ሆይ!" በማለት የተሰበሰበውን ህዝብ ተጣራ "ለዚህ ሰው ዋስ የሚሆነው ማነው?" አለ ከፍ ባለ ድምፁ።  አቡ ዘር አል-ጊፋሪ ተነሳና "የሙእሚን መሪ ሆይ! እኔ ተያዥ ዋስ እሆነዋለሁ" አለ

"ገዳይ ነው ባይመለስ የሞት ፍርድ ውሳኔው ተፈፃሚነቱ ባንተ ላይ እንደሚረጋገጥ ታውቃለህ አይደል?!" አለ ዑመር
"አዎ አውቃለሁ"

"እንዴት ለማታውቀው ሰው ዋስ ለመሆን ደፈርክ"

"የአማኝነት ገፅታዊ ምልክቶችን ከፊቱ ላይ አነበብኩ በአላህም ፈቃድ ተመልሶ ይመጣል ኢንሻ አላህ"

ዑመርም "አቡ ዘር ሆይ ከሦስት ቀን በላይ ከዘገየ እንደማልተውህ እወቅ" እያለ ሰውየውን ወደቤተሰቡ እንዲሄድ ፈቀደ። ልጆቹንና ቤተሰቡን እንዲሰናበት ከዛም የቅጣቱ ውሳኔ ተግባራዊ ይደረግበት ዘንድ የሶስት ቀን ጊዜ ገደብ ተሰጠው።

ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ አቅንቶ ባለቤቱን አተኩሮ አያያት ቁም ነገር ያለው ወሬ እያወራችው ቢሆንም እሱ ግን ቀልቡ ተሰርቋል። ንፋሱ ሐዘኑን ሊያባብስ በስሱ የሚነፍስ አቀጣጣይ ማራገቢያ ይመስላል ሽው ሽው ይላል።
"የት ሄድክ" አለችው  ሽምጥ የጋለበውን ቀልቡን አይታ። ከሐሳቡ ሳይንደረደር ወርዶ በእንባ እየታጀበ የገጠመውን ሁሉ በዝርዝር ነገራት።

ዕንባዋ ኩልል ብሎ እየፈሰሰ  "ፀሐይ ንዳዷን ስትለቅ ውላ መጥለቂያዋ ሲቃረብ ውበትን፣ መስከንንና ደብዘዝ ብሎ መጉላትን ታሳያለች ጠዋት ልንሞቃት ወጥተን እናንጋጣለን ቀትር ሲቃረብ እናማራለን አብሽር አላህ የተሻለ አለው" ብላ አፅናንታ በእቅፏ አስተኛችው።

ከሦስት ቀናት በኋላ ዑመር ቀጠሮውን አልዘነጋም። የአስር ሰላት እንደተሰገደ ከመዲና መስጂድ ሚንበር ላይ ሆኖ  አስሰላቱል ጃሚዓ ሲል ተጣሪው ተጣራ። ሰው ሁሉ ወደሜዳው ወጥቶ ተሰበሰበ። አባታቸው የተገደለባቸው ሁለቱ ልጆች በቦታቸው ተሰየሙ። አቡ ዘርም ከፊት ለፊት ተቀመጠ።

"ሰውየው የታል?!" አለ ዑመር ወደ አቡዘር ፊቱን አቅጣጭቶ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ።
  "አላውቅም" አለ አቡዘር።

ሰሐቦች በተፈጠረው ነገር ደንግጠዋል።  ክስተቱን የሚያይ ሁሉ ከንፈሩን ይመጣል። አንዳንዱ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። እውነት ነው አቡ ዘር ዑመር ዘንድ ተወዳጅ ቢሆንም የአላህ ህግ ግን ከሁሉም ነገር በላይ ነው።

ፀሐይ ያለወትሮዋ እንደምትጠልቅ ነገር ወደ መግቢያዋ በፍጥነት ቁልቁል በመንደርደር ላይ ሳለች አንድ ሰው እየጋለበ ወደስብስቡ ገሰገሰ "አላሁ አክበር" የሚሉ ድምፆች ከወዲህ ወዲያ እየተሰሙ አካባቢው በተክቢራ ተናጠ።
"መኖርያህንም አድራሻህንም አናውቅም ነበር እንዴት መጣህ?!" አሉት ዑመር።

"በአላህ እምላለሁ የፈጠረኝን ጌታ በእጅጉ እፈራለሁ ሙስሊሞች የገቡትን ቃል መሙላት አቆሙ ታማኝነታቸው ተረሳ እንዳይባል ሰዓቴን ሳላዛንፍ ሚስትና ልጆቼን ለአላህ ትቼ ይኸው ልገድል መጥቻለሁ" አለ ሳግ እየተናነቀው።
"አንተስ እንዴት ዋስ ሆንከው" አሉ ዑመር ወደ አቡ ዘር ዞረው ከዓይናቸው ላይ ዕንባቸውን እየጠረጉ።  "መልካም ሰዎች ከሙስሊሞች ጠፍተዋል እንዳይባል ሰግቼ" አለ አቡዘር።
ወደ ሁለቱ ወጣቶች "እናንተስ ምን ትላላችሁ?" ብሎ ጥያቄውን ሲሰነዝር

ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ያ አሚሩል ሙዕሚኒን "ይቅር ብለነዋል እኛስ ብንሆን አውፍና ይቅርታ ከሙስሊሞች ዘንድ ጠፋ መባልን እንዴት አንስጋ?!" አሉ። ዑመር ፂሙ እስኪርስ እያነባ አካባቢውን ለቆ ወደ ቤቱ አቀና።

ታማኝነት የሙስሊሞች መገለጫ መሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ**@sineislam@sineislam

6 months, 3 weeks ago

ሰሉ አለ ነቢ አላሁመ ሰሊ  ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድﷺ
اللهم صل وسلم على نبينا محمدﷺ
اللهم صل وسلم على نبينا محمدﷺ
?መልካም  ጁምዓ?

6 months, 3 weeks ago
6 months, 3 weeks ago
6 months, 3 weeks ago

??"13ቱ" የጥሩ ሚስት መገለጫዎች

① የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች

②ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች

③ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች

④ቤትና ንብረቱን እንዲሁም ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች

⑤እሱ የማይፈልገውን ሰው አትጠጋም አታስጠጋምም

⑥ ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም
ከቤትም አትወጣም

⑦ የባሏንና የቤቷን ሚስጥር
በሚገባ ትጠብቃለች

⑧ ባሏን በመልካም ነገር ላይ ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣ ሲረሳ ታስታውሳለች

⑨ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች

①∅ ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥ እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም

①①በሚያደርግላት ነገር በሙሉ
ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች

①② ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤት አትገነባም!

①③ አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች አበቃ የጥሩ ባልን መገለጫ በቅርብ ቀን ይጠብቁን ኢንሻአላህ "ሁላችንም አላህ ሳሊሖች ያድርገን።

@sineislam
@sineislam

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago