ʜᴀɴᴀɴ ɪsʟᴀᴍɪᴄ ᴘᴏsᴛ

Description
ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲ ብለዋል
"ዱኒያ አላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ
ምታክል ቦታ ቢኖረው ኖሮ
በአላህ የካዱ ሰዎች
አንድ ጉንጭ ውሀ አይጎነጭም ነበር::"

?ቲርሚዚ ዘግበውታል: 2320
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months ago

Last updated 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 2 weeks ago

5 months ago

==========❨  )========
        ..........ፍርሀት? .........
?ፀሀፊ:- semi nas   
==========❨ )=========

===========⨳ ⨳========
@hanan_islamic የተዘጋጀ
===========⨳ ⨳========

========+ +====
#ክፍል_ አስር
          =======+ +=====

<< ምዕላዴ አደራ ወደ አላህ ተመለስ ለኔም ለራስህም ዱዓ አርግ እኔም ይቺን አለም ልገላገላት አንድ ቀን ነው የቀራኝ ይሄን ደብዳቤ እንዳነበብክ መቃብሬ ጋር መጥተክ ዘይረኝ
ደሞ አደረ በጭራሽ ትምህርትን አታቋርጥ ክላስ ገብተህ እንደማታውቅ ነግረውኛል ይሄ ሁሉ በኔ ምክኛት እንደሆነ አውቃለሁ ለዚም በጣም ይቅርታ አርግልኝ ተምረህ የምርቃትህ ቀን መጥተህ ንገረኝ።
"የኔ ውድ ዛሬ ሳላይህ አንድ ወር ሆነኝ እኮ በጣም ነው የናፈቅከኝ እኔም ወደ አላህ ከተመለስኩ አንድ ወር ሆነኝ ሰላት ውስጥ ቁርኣን ውስጥ ያለው መረጋጋት አጠይቀኝ ታስታውሳለህ ስንጋባ በአንድ ወር ነው ቁርኣን ማዛፍዝሽ ብለህኝ ነበር ምዕላዴ ይሀው ካቆሙኩበት ጀምሬ ዛሬ ሳላሳውን ቁርኣን ሀፈዝኩ ደስ አለክ አይደል ረምላ ቀና ብላ አየችው እንደ ቅድሙ የሀዘን ለቅሶ አልነበረም ፈገግ ብሎ ነበር የደስታ ሚያነባው የምስጋና ስጁድ አደረገ ረምላ ለሷ ያለውን ጥልቅ መውደድ አስተውላ ፈገግ አለች
"እና ደሞ አላህ ተውበቴን እንዲቀበለኝ ዱዓ አርግልኝ አንተም ለጌታህ ፍፁም ታዛዥ ሁን አደራ አደራ
ካንተዋ ኸውሰር>>
ወረቀቱን እያጣጠፈች ቀና ብላ አየችው እሱ ግን ጭንቅላቱን እግሩ ላይ ደፍቶ የኔ ኸውሰር ይቅር ብዬ ሻለሁ ይቅር በይኝ ቀና ብሎ ወረቀቱን ተቀብሏት ወደ ደረቱ አስጠጋው
ፖስታ ውስጥ ቀለበት ነበረ ረምላ አይታው ደበቀችው
ምዕላድ መለወጥ አለብህ ለሷም ለእናትህም ለአባትህም ለእህትህም ስትል ያንን ወደ አላህ መመለስ ከራሷ መመለስ የበለጠ ትፈልጓለች የራሷ ሳይሆን ያንተን ንፅህና ትፈልጋለች ምዕላድ ፖስታውን የሰጠችህን ልጅ ካወካት ነገ ሄደን እናወራታለን ወደ ሀገርህም ሄደህ አባትህንም እናትህንም አፉታ ትጠይቃለህ ምዕላድ አዲስ ቀን ሰንቀህ ተነስ እናት እህትሀ ያፈቀርካት እኔ እያደመጥኩክ ያለውት እንኳን ሴት ነን በቃ ውስጥ ያለውን ጥላቻ አውጣው
"ረምላ የማታውቂው ነገር አለ ያልነገርኩሽ
"ከዚ ውጭ ምን ይኖራል ስትል አሰበች እና አሁን ትነግረኛለህ ወይስ ሌላ ቀን
"ነገ ልጅቷን አግኝተን ከመጣን በኋላ እነግርሻለሁ
"እሺ ተነስ አስር መስጂድ እንሰግዳለን ተነስ ጃኪት ላምጣልህ ብላ ተነሳች።
"ጃኪቱን አቀብላው ተነስቶ ለበሰ ክፍት ጫማ ሰጥታው እሱ ከፊት እሷ ከኋላ ሆነው ከቤት ወጡ።

#######
"ኑር ከጫካው ማዶ ያለው ቡና ቤት መመላለስ ከጀመረ ሰነባበተ በትንሹም ከልጅቷ ጋር ተግባብተዋል
"ከአንድ ጥግ ቆሞ ልጅቷን ያወራታል እናቷ እየተከታተለቻት ስለነበር ብዙም ለማውራት አልተመቻትም አንዴ እናቷን አንዴ ደሞ ኑርን እያየች ታወራለች ኑር ነገሩ ስለገባው ተመልሶ እንደሚመጣ ነግሯት ተሰናብቷት ወጣ። እናቷም ኮስተር ብላ ጠራቻት አንቺ ሚልኮ ነይ ወዲ እንከፍ አለቻት
ሚልኮ የናቷ ሁኔታ ግራ አጋብቷት ወደ እናቷ ፈጠን ብላ ሄደች "አዮ "ምን አረኩ አለቻት መሬት መሬት እያየች እናቷ ቆጣ ብላ
"ምን እራስሽን ታስገምቺያለሽ አትረጋጊም
"እንዴ አዮ እራስሽ አደል እንዴ ብረት መዝግያ ነው አይንሽን ክፈቺ ያልሽኝ
"ጉድ ፈላ እና ያልኩሽ እንደሆነስ በየ ቦታው ገልፍጭ አልኩሽ እንዴ ደሞ አንቺ ነሽ ትላለች እንዴ በይ ቀጥይ ወደ ኩሽና ግቢ አለቻት እየገላመጠቻት
"ሚልኮ በናቷ ሁኔታ እየሳቀች ገባች ኑርን ወደዋለች ግን መስነቃት አልፈለገችም።

ኑር ጫካው ውስጥ ትንሽዬ መኖሪያ አለው ከጫካው ያደነውን እየጠበሰ እሳት አጠገብ ቁጭ ብሎ ከጠበሰው እየበላ ቤተሰቡን ልጅነቱን መስታወስ ጀመረ
"ኑር የሼኽ ዩሱፍ አራተኛ ልጅ ነው የቤቱ የመጨረሻ ልጅ ከመሆኑ በጣም ተወዳጅ ነው ምንም ቢፈልግ ይደረግለታል ኑር በልጅነቱ ወደ መድረሳ ሂድ ሲባል እምቢ እያለ የዱሪዬነት መንገድ ጀመረ ከናቱ መቀነት አንድ ብር ማንሳት ጀመረ እያለ እያለ አስራዎቹን ሲጠጋ አንድ ጥጃ አውጥቶ ሸጠ ከዛን ግዜ ጀምሮ ጠንከር ጠንከር ያሉ ነገሮችን ማንሳት ጀመረ
ያን እለት አባቱ ቀልቡ ተነካ ረገሙት እርግማናቸው ምንም ያልመሰለው ኑር ቤት ጥሎ ጠፋ
ኑር ወጣቶቹን አደራጅቶ የሌብነት ቡድን አቋቋማ በሱ መሪነት ሰፈርን አዛ አደረጉ በዛመንደር የሚኖሩ ሰዎች ለንብረቶቻቸው መስጋት ከጀመሩ ሰነባበቱ።
አንድ ዕለት የአባቱን ንብረት ለመዝረፍ እቅድ ነደፉ ከዛ ተከፋፍለው ወደ አባቱ ቤት በሱ መሪነት አመሩ
"ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ ሰፈሩን አቆራርጠው ወደ ተወለደበት ቤት ደረሱ ኑር ከቤታቸው ጀርባ ያለውን የከብቶችን ማደሪያ ቀስ አርጎ ከፍቶ ገብቶ እንዳለ ከብቶችን እየነዳ ወጣ ጓደኞቹ ኳላ ኳላ እየተከተሉት ወደ ተከራዩት መንደር ደረሱ። ሲነጋ የሰረቋቸውን ከብቶች እንዳለ ሸጧቸው ከዛ ለ ኑር አብዛኛውን ገንዘብ ሰጠው ለራሳቸው የቀረውን ተከፋፈሉ
"ጧት ከሼኽ ዩሱፍ ቤት ጩሀት ተሰማ የመንደሩ ሰው ሁሉ ወጣ ሼኽ ዩሱፍ ልጃቸው እንዳጠቃቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ቁጭ ብለው ማልቀስ ጀመሩ የመንደሩ ሰዎች ""ድሮም ቃልቻ ልጅ አዮጣለትም"" እያሉ መንሾካሾክ ጀመሩ
አላህ ለልጁ ቀልብ እንዲሰጠው ዱዓ አረጉ እናቱ
ሼክ ዩሱፍ ግን ልጄ አይደለም አሉ የባትና የልጅ ጋመድ ያኔ ተበጠሰ
"ኑር ከትዝታው መለስ እያለ አባቴ የት ይሁን አለ የእናቱ ናፍቆት አላስችል አለው ስለማንም አያገባኝም እናቴ አንቺ ግን ኑሪልኝ አለ ወደ መተኛው እየሄደ።

ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል.....

ከ 100 like? ቡኃላ

@hanan_islam
@hanan_islam

5 months ago

?"ቆይ አንቺ ልጅ ሁልጊዜ ፈገግ
ማለትሽ ምንድን ነው?"

" እስኪ ሚስጥሩን ገምት"

?"ግምት አልችልም
ግን ማወቅ እፈልጋለሁ"

"እኔ ሳዝን የሚከፉ ወዳጆች አሉኝ
ለእነርሱ ስል እበረታለሁ"

?"አስቀናሽኝ
ጥንካሬሽን ሳላደንቅልሽ
ማለፍ አልፈልግም"

"ሁሌም ለራስ ተብሎ ብቻ አይኖርም
ለኛም ብለው ለሚኖሩም ሰዎች
ተብሎም ይኖራል?"

የማይታበስ እንባ
kamil wenji

@hanan_islam

5 months ago

በአንድ ገጠራማ አካባቢ ገበሬወች ተሰብስበው ዝናብ እንዲዘንብ(صلاة الاستسقاء)  እንስገድ ተባባሉ አንድ ሰው ብቻ ግን ጥላ ይዞ ወጣ?

~ይህ ተወኩል ይባላል

AT✍️

@hanan_islam
@hanan_islam

5 months, 1 week ago

አስላሙ አሌይኩም ኢስላሚክ ቻናል ብቻ
Wave መጀመረችን ይተወቀል የኔ ዌብ የጠዋት ዌቤር ነኝ ለሱቢ ስናሳ አንድ ዲስክ ብቻ ነው የምሰረው የቀረውን ሰዓት ቻናሎችን ለመቀጠጣር እጠቀማለሁ እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ ብቻ ነው የምቆየው ከዛ በኋላ የረሴን ዲስክ አጥፍቼ እወጣለሁ ኑ ኢስላሚክ ቻናል በለ ቤቶችን ብቻ
1k
2k
3k
4k
5k
10k+ ማስገባት የምትፈልጉ 
Dm me
**

ኑ እኔ ጋር በአብሮነት #እንደግ የኔ ሳይሆን የኛ የሚል አስተሳሰብ ይኑረን?❤️

? In-box @waver_boy_433 ?
? In-box @waver_boy_433 ?**

5 months, 1 week ago
  1. ወንድ ልጅ ትዳር መፈለጉን እንዴት ማወቅ ይቻላል??
  2. ሴት ልጅንስ የትዳር ጥያቄ እንድትቀበል እንዴት ማድረግ ይቻላል?

በእርጋታ ያንብቡት። አስገራሚ መልሶችን ከታች ይዘን ቀርበናል

5 months, 1 week ago

ልዩ ፍጡር.... ?**

ደግ መልካም የኔ ጥሩ ሰው
ለሃዘኔ አይንሽ ሚያለቅሰው

ሲከፋኝም ሆነ ስደሰት እኔ
ከኔ ጋር ሆነሽ ቆመሽ ከጎኔ

መከራ ችግር ፊትና ሲበዛ
አይለኘኝም ያንቺ እገዛ

የኔ ጓደኛ ዘላቂ ፍቅሬ
አንቺ ነሽ ሌኔ ልዩ ፍጡሬ

ሂባ

5 months, 2 weeks ago

ካጋጠመኝ

ከእለታት በአንዱ ቀን ከጓደኞቼ መሃል አንዷ እንዲህ የሚል ጥያቄን አቀረበችልኝ " ሶፊ ግን ሳንቀራረብ በፊት ለኔ ያለሽ አመለካከት እንዴት ነበር? "
ጥያቄዋን ስሰማ ከሁለት አመት በፊት በሀሳብ ወደ ኋላ መለስ ብዬ እሷን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁበት ቀን አስታወስኩት... ከክላሳችን ፊት ለፊት የጆሮ ማዳመጫዎቼን ሰክቼ ለብቻዬ ቁጭ ብዬ ሳለሁ ድንገት ቀና ስል ከክፍላችን በር ፊት ለፊት ቆማ ስልኳን ስትነካካ ተመለከትኳት.... ቀጠን ብላ ረዘም ያለች ቡናማ ቀለም ያላት መልከ መልካም ቆንጂያ ልጅ ናት ከነገሯ ሁሉ ደግሞ መልኳ ይበልጥ ሳበኝ ምክኒያቱም ሳላገኛት 8 አመት ያስቆጠርኩትን የእናቴን መልክ አስታወሰኝ በጣም ወደድኳት ቀን በቀን ሳያት ደግሞ ይበልጥ ደስ እያለችኝ እና ፍቅሯ እየጨመረብኝ መጣ በመጨረሻም በአንድ አጋጣሚ ተዋወኳትና በጊዜ ሂደት ጓደኛዬ ሆነች።

ከሀሳብ መልስ ... በፈገግታ ተሞልቼ ለጥያቄዋ መልስ መስጠት ጀመርኩ
" በጣም እወድሽ ነበር ወላሂ "
" አዎዎዎዎ... የኔ ልዩ የዋህ እኮ ነሽ " ብላ በረጅሙ ተነፈሰችና ንግግሯን ቀጠለች " ሶፊ የሆነ ነገር ልንገርሽ አትቀየሚኝም? " አለች
" ለምን እቀየምሻለሁ አልቀየምሽም ንገሪኝ ምንድነው እሱ? "
" እንዲ ሳልቀርብሽ በፊት በጣም እጠላሽ ነበርኮ "
" ወይኔ በረቢ እየቀለድኩ ነው በይኝ "
" ወላህ ሶፊ አፉ በይኝ በጣም ታስጠይኝ ነበር " አሳቀችኝ ምክኒያቱም እንዲህ ከሚሉኝ ሰዎች መሃል አንዷ ናት እንጂ የመጀመሪያዋ አልነበረችም
" በነገራችን ላይ እንዲህ ማለትሽ አልገረመኝም ምክኒያቱም ብዙ ሰዎች ናቸው ሳይቀርቡኝ በፊት ለኔ ያላቸው አስታየትና ከቀረቡኝ በኋላ ያላቸው አመለካካት በጣም ልዩነት እንዳለው የነገሩኝ.... ቆይ ግን የሌላዎቹን እርሺው እና አንቺስ ለምን ጠላሽኝ በአላህ? " አልኳት በፈገግታ እንደተሞላው
" እኔንጃ ሶፊ... ግን በቃ እንዲሁ ሳይሽ ትደብሪኛለሽ ፣ የሆንሽ ጢባራም ክፉ ሴት ነው የምትመስዪኝ "
" አላሁአክበር ያንቺስ ባሰ ሉላዬ ... ሰው እንዴት ከመሬት ተነስቶ ሰውን ይህን ያህል ደረጃ ይጠላል? "
" እኔ ምን አውቄ ሶፊ ግን በአላህ አፉ በይኝ አሁን እውነታው ይፋ ሆኖልኛል ፈፅሞ እንዳሰብኩሽ አይነት ሰው አይደለሽም " ብላ ከእቅፌ ገባች
" እና ምን አይነት ሰው ነኝ? " ብዬ ፈገግ እያልኩ እኔም አቀፍኳት
ፈገግታዬ ተጋብቶባት ፈገግ እያለች ከእቅፌ ወታ አይን አይኔን እያየች ማውራት ጀመረች
" የዋህ ፣ ሩሩህ ፣ ደግ.... ቃላት የማይገልፅሽ ጥሩ ሰው ነሽ የኔ ልዩ ጓደኛ አላህ አንቺን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ ወላህ "
" ለኔም አላህ አንቺን የመሰለች እናቴን መሳይ መልከ መልካም ጓደኛ ስለሰጠኝ እጅግ በጣም ደግሜ ደጋግሜ አመሰግነዋለሁ የኔ እብድ " ብዬ መልሼ ከእቅፌ አስገባኋት።

አንድ አንዴ ለአይን እንኳን ምንጠላቸው ሰዎች ባላሰብነው ሁኔታና መንገድ የኛ የቅርብ ሰው ይሆናሉ።
ሰዎችን አይተን ብቻ ስለጠላናቸው አላህ ከነሱ አያርቀንም ፣ ስለወደድናቸው ብቻም ወደነርሱ አያቀርበንም ሁሉም ነገር እርሱ ያለው እና የፈቀደው ብቻ ነው የሚሆነው።
እና እኛም በቻልነው አቅም ሰዎችን ከላይ የሚታየውን ገፅታቸውን አይተን ብቻ መውደድ ወይም ደግሞ መጥላት የለብንም ምክኒያቱም ከውስጥ ያለውን ማንነታቸውን ከአንድ አላህ እና ከቀረባቸው ሰው በቀር ማንም አያውቀውም እና በቅጡ ሳናውቃቸው የነሱን ማንነት መለካት ሚዛናዊ አይደለም
‼️
ታዲያ እንጠንቀቅ ነገሮችን ማወቅ ባለብን ልክ ሳናውቅ ይህ ጥሩ ነው ይህ ደግሞ መጥፎ ነው ብለን መፍረድን እናቁም
‼️**

ሂባ**

5 months, 2 weeks ago

ዛሬ ያለ ወትሮዬ በጧት ተነስቼ ወደ ስራቦታ እየሄድኩ ነበር
መንገድ ላይ አንዲት በ ሀያዎቹ መጀመሪያ የምትገኝ እንስት ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ነበር
እኔም ስልኬ ውስጥ የሰኣድ አልጋምዲን ውብ ድምፅ እያደመጥኩ ዝም ብያት አለፍኩ ትንሽ ራቅ እንዳልኩ ግን አላስቻለኝም ተመለስኩ

"እናት ምን ሁነሽ ነው አልኳት ከወገቤ ጎንበስ ብዬ
"ምንም ምንም ምንም አልሆንኩም
"ታዳ ለምን እንዲ ታለቅሻለሽ
"ብርሃኔ ጨልሞ
"እኔም ነገሩ ግራ አጋብቶኝ ቁጥጥ ብዬ ምን ማለት ነው አልኳት
"ብርሃኔ ጨለመ ብርሃኔ ጨለመ ብርሃንሽ ጨልሞ ያውቃል አለችኝ
"ግልፅ ስላሎነልኝ አይ አልጨለመም
"ስሜቴን አትረጂኝም ታዳ ለምን ጠየቅሽኝ አለችኝ
"ነግረሽኝ እንድረዳሽ
" ልንገርሽ ምድር ለወንዶች ታደላለች በጣም ታደላለች አላህ እኩል አደል የፈጠረን ታዳ እነሱ እኛ ላይ ለምን የበላይ ይሆናሉ ለማን ነው ምከሳቸው ለማን ነው የውስጤንስ ለማን ልናገር እእእ ንገሪኝ እያለች መንሰቅሰቅ ጀመረች
"ብያንስ የሆንሽውን ንገሪኝ ልርዳሽ
"እሺ ብላ የውስጧን መናገር ጀመረች
እእእ ማታ አባቴን በጠና አሞት ማስታገሻ ልገዛለት ወጣው እ ኧ ከዛ ገዝቼ ስመለስ አራት ጎረምሳ ዱሪዬዎች ደ..ፈ መጨረስ አቃታት እልህ እየተናነቃት አለቀሰች
"ነገሩ ግልፅ ሆነልኝ እና ከዛስ እሺ ሀኪም ቤት ሄድሽ አልኳት ለቅሷ ተጋብቶብኝ
"ሚሰማኝን አጣው ሚረዳኝን አባቴ ደሜን ሲያይ እዛው ፀጥ አለ
እናቴም በድንጋጤ ወደቀች
ወንድሜ አባቴን ገደልሽብኝ ብሎ ከቤት አባረረኝ
"በጣም ደነገጥኩ አፈጠጥኩባት
"ተይ አንቺም ልወቅሽኝ ነው አለችኝ እጇ እየተንቀጠቀጠ
"አይ አይ በጭራሽ አንቺን ሳይሆን እነዛን በስሜታቸው የተራመዱትን ነው ምወቅስ አንቺ እኮ ንፁ ነሽ ምን አደረክሽ እእ ቃል እገባልሻለሁ አንቺም ፍትህን እነሱም የስራቸውን ውጤት ያገኛሉ እምባሽን አብሽ አልኳት በእልህ
"የተኛው ለሴቶች የሚፈርደው ፍትህ ንገሪኝ ፍትህ አለ እንዴ እእእ ንገሪኝ የት ነው ያለው
"የኔ ውድ እህት አዎ አለ ያውም ምድርን ሁሉ የሚያዳርስ ፍትህ ፍትህ
"አንቺ ቀልድ ላይ ነው ያለሽው ብላ ጥላኝ ጭንቅላቷን ይዛ ሄደች
ከፊቴ እስክትሰወር ድረስ አየዋት

ሰሚ ያጣ ጩሀት
አልኩት ግን ቆይ እውነት ፍትህ የለም ነው ወይስ በፍትህ ሚፈርዱ ሰዎች የሉም???????????

ዳኛዋ ነኝ

5 months, 2 weeks ago

ወዳጆቼ ሞት ሲመጣ አይጠብቅም። ከነገ ጀምሮ ተውበት አደርጋለሁ ፥ ለቁርአን ቲላዋ ፕሮግራም አወጣለሁ ፥ ኪታብም መቅራት አለብኝ ፥ ሰላት በስነ ስርዓቱ እጀምራለሁ ፥ ሀራም አላዳምጥም ፥ አልመለከትም... ወዘት እንላለን። ከዛ ነገ ያልነው ቀን ይመጣል። ነገር ግን ካሰብናቸው ነገራቶች አንዱንም አንጀምርም። ከምኞታችን ርዝመት የተነሳ ሞትን ሩቅ አድርገን ማሰብ ጀምረናል።

በነገራችን ላይ ከደቂቃ በፊት የሞቱ ሰዎችም እንደኛ ያስቡ ነበረ። ሰዎች ሆይ ወደአላህ ተቻኮሉ ምክንያቱም የአንድ ሰዓት ጊዜ ህይወታችሁን በሙሉ ሊያወድም ይችላልና። ሱናቢህ የሚባል አንድ ታቢዒይ ከየመን ተነስተው ወደ መዲና ይጓዛሉ ልክ እዛ ሲደርሱ የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ማግኘት ፈለጉ። ነገር ግን የአላህ መልዕክተኛ ወደ አኺራ ከተሸጋገሩ አምስት ለሊቶች አልፈዋል ተባሉ። አስቡት አምስት ለሊት በማርፈዳቸው ብቻ ሶሀባ መሆን አልቻሉም። የአላህን መልዕክተኛ ገፅታቸዉን መመልከት ተከለከሉ። ለለውጥ ቀጠሮ አትያዙ አሁኑኑ ጀምሩ!!!

ስመክርህ/ሽ ካንተ/ቺ እኔ የተሻልኩ ነኝ ማለት አይደለም። ነገር ግን የምልህ/ሽ በጎ እመኝልኃለሁ/ሻለሁ ነው።

[የማይታበስ አንባ]

@hanan_islam

5 months, 2 weeks ago

ይቺ ዱንያማ?
ሁሌም ላትሞላ?
ችግርና ጭንቅ?
ደስታና ታድላ?
ሲፈራረቁ?
ተራ በተራ?
ዛሬ ብሆን ነጌ?
ላይቀር መከራ?

@hanan_islam

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months ago

Last updated 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 2 weeks ago