ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Description
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።

ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን።

YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8
Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

8 months, 2 weeks ago
8 months, 2 weeks ago

15/07/16 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።

ምስባክ፦ መዝ ፷፰፥፱
እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዐኒ
ትእይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ

ትርጉም
የቤትህ ቅናት በልቶኛልና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና
ስውነቴን በጾም አደከምኋት

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፪፥፲፪ - ፍጻሜ
ቅዳሴ፦  ዘእግዚእነ

? @ortodoxmezmur ?
? @ortodoxmezmur ?
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

8 months, 2 weeks ago
8 months, 3 weeks ago

የምንጠብቀው መልስ ከላይ እንደሆነ ተነጋግረን ከጨረስን በኋላ ወደ ታች ድጋሚ መጠየቁ ስለምን ይሆን??? ምንስ አገኘን???

8 months, 3 weeks ago

ርግብና ዋኔን

ርግብና ዋኔን
አብረዉ ዘመቱና ዋኔን
ርግብ ደህና ገባች >> /2/
ዋኔን ገደሉና >> /2/

በዘርና ጎሳ ዋኔን
ሠዉ ሁሉ ተከፍሎ >>
ሰይፍንም ጨበጠ >>
ልቦናዉ ቂም አዝሎ>>
ሰላምን የሚያወርድ >>
እንድ የሚያረገንን >>
እባክህን አምላክ >>
ሙሴን አድለን >>
ሠላምህን አብዛ ምድሪቷን አሳርፍ
የቅዱሳን አምላክ በጭንቃችን ድርስ /2/

በወገን ላይ ወገን ዋኔን
ይብቃ መነሳቱ >>
ይስፈን በምድር ላይ >>
የእግዚአብሔር መንግስቱ >>
ጦራችን ይሰቀል >>
እንያዝ በገና >>
ሠላምን እናዚም >>
በፍቅር እንፅና >>
ምድሪቷን አሳርፍ ሰላምህም ይብዛ
በአንድነት አኑረን የአለሙ ቤዛ /2/

የመርገም ጨርቅ ሆነ ዋኔን
ፅድቃችን በሙሉ >>
አንተን ያልበደለ >>
ማነዉ በዘመኑ>>
አማነዉ በማታ >>
ቀን ያከበርነዉን >>
የኛ ስራ ሆኗል >>
መክሰስ የበቃው >>
ፍቅር ባትሆን ኖሮ ባያቅትህ መጥላት
አይታይም ነበር የሰዉ ልጅ በህይወት

ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሳሙኤል
? @ortodoxmezmur ?
? @ortodoxmezmur ?
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

8 months, 3 weeks ago

ዐብይ ጾም ለምን የንሰሐ መዝሙር ብቻ ሆነ?

? ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ድምፀ
??በዐብይ ጾም ለምን ከበሮ አይመታም
??በዐብይ ጾም ለምን ፅናፅል አንጠቀመም
??በዐብይ ፆም መብላት የሌለብን ምግቦች በየአመቱ ጥያቄ እሚያስነሳው ???? ዓሳን አለመብላት

? @ortodoxmezmur ?
? @ortodoxmezmur ?
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

10 months, 3 weeks ago

​​​​✞ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" እና "ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ሥሉስ_ቅዱስ

ምሥጢራት በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::

+እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::

+ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::

+ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::

+እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ያውቃል::

በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን : በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

በዓለ ሥላሴ በዚህ ቀን የሚከበረው ስለ 2 ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን 2ኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር

ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

+ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

+ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

+መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

+ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

+ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት

ልክ የዛሬ 324 ዓመት: አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት: (በ1684 ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

+ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

+ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
? @ortodoxmezmur ?
? @ortodoxmezmur ?
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

[​​](https://telegra.ph/file/2194e662d5b5b2ca466cd.jpg)[​​](https://telegra.ph/file/cf4b48ebe16563a505f8a.jpg)✞ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" እና "ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
10 months, 3 weeks ago
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
10 months, 3 weeks ago
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
11 months ago

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የጥምቀት መዝሙር ጥናት እንጀምራለን። ሁላችሁም ሼር በማድረግ ወንድም እህቶቻችንን ወደ ዝማሬ ዳዊት እንጋብዝ።

https://t.me/+SoivjLkD4oUfYh7H
https://t.me/+SoivjLkD4oUfYh7H

Telegram

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . #ዝማሬ\_ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit\_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ **የጥምቀት መዝሙር** ጥናት እንጀምራለን። ሁላችሁም ሼር በማድረግ ወንድም እህቶቻችንን ወደ ዝማሬ ዳዊት እንጋብዝ።
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago