እንቆጳግዮን ✞

Description
@Ethiopiansecret
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 years, 6 months ago

ኢትዮጲያ ግን እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር እምትዘረጋበት ቀን እጅግ ቀርቧል:: አሁን የጦር ዛቻ እያየንበት ያለው መዘዘኛው አባይንም በተመለከተ በአንድ በኩል እንደሚያጋድለን በትንቢቱ :~
" አባይ ደፈረሰ ጣናንም ያ'ሙታል:
እንዳትከተሉት ሙት ይዞ ይሞታል" ብለው: ሼህ ሁሴን ተናግረውለታል::

ወደፊት ምን እየተካሄደ እንዳለ እንኳን እንደዚህ ሀሳብ እምንለዋወጥበት እድል እማይኖርበት ግዜ ይመጣል::ዛሬ የተጋራነው ሀሳብ በመጭው ግዜ ትዝታ ይሆናል :: የብሔርና የሃይማኖት ጦርነት የተነሳ ግዜ ያኔ ሁሉ እንዳልነበር ይሆናል:: ከዚህ እሚያድነን አንድ እና አንድ መፍትሄ አሁንም ዛሬ ላይ ሆነን ተግተን እምናረገው ፀሎት እና የእግዚያብሔር ምህረት እንጂ የታጠቅነው የጦር መሳሪያ አይደለም::

አባ ዘወንጌል ስለ አንበጣውም ሆነ ስለጦርነቱ ተናግረውት ያለፉትን ከዚህ ትንቢት ጋር እሚጋራውን ብዙ ነጥቦች አስታውሱ::

ይህን ፖስት ያረኩት የቅርብ ሩቁን ነገን እያሰብክና/እያሰብሽ ጭንቀት ውስጥ ገብተህ/ሽ መኖር እንድታቆም/ሚ አይደለም::ይልቁንም ግዜው እየጠበበ እየጠበበ እንደሄደ አስተውለን ቦታው
ላይ ሲደርስ የተዘጋጀ ልብ እንዲኖረን :ግዜው
እንደ ወጥመድ ድንገተኛ እንዳይሆንብን መጭውን አውቀን ህፀፃችንን እያረምን ራሳችንን እያስተካከልን በፀሎት ከመፃኢው መከራ አትርፎ ለትንሳኤዋ ዘመን እንዲያበቃን እየተማፀንን ኑሮዋችንን እንድንቀጥል ነው::

ምክንያቱም የኛ አይን መጨፈን እሚሆነውን ከመካሄድ አያስቆመውም : ጆሮዋችንን መድፈን እሚነገረውን ከመነገር አይከለክለውም::ይልቁንም አውቀነው መፀለያችን ነገሩን እንደነነዌ ያረግልናል ሊያስቀርልን ይችላል::"

እግዚአብሔር የኢትዮጲያችንን መከራ ያሳጥርልን :ከመፃዒው ጥፋትም ያድንልን!
መድሃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም እስከዘላለም ያው ነው:: መንገድም እውነትም ህይወትም መድሃኒትም እርሱ ነው!!! ወደርሱ እንመለስ ።

3 years, 6 months ago

አስፈሪው የኢትዮጲያ ቀን!!!
ትንቢተ ኢትዮጲያ!

ራሺያ በምስራቅ :ጀርመን እና ጣሊያን በሰሜን : የአረብ ጦርም ሁሉ ወደ ኢትዮጲያ
ይገባል: ምድሯን ባዶ ያረጋል!

ቅዱስ መፅሃፉ ደግሞ ይህን ይላል :~
"እናንተ ኢትዮጲያውያን ደግሞ በሰይፌ ትገደላላችሁ::እርሱም በሰሜን ላይ እጁን ይዘረጋል::..."
ትንቢተ ሶፎኒያስ 2(12)

ምን ያህሎቻችን እንዳስተዋልን ባላውቅም
በ2017 ላይ RT ኒውስ :~
**አፍሪካውያን የውጪ ጦር ሰራዊት ወደ አሃጉራቸው ያስገቡ ግዜ ትልቅ ተሸናፊዎች ይሆናሉ! ብሎ የዘገበው በወቅቱ ቀልቤን የያዘውን ዘገባ አሁን ላስታውሳችሁ ግድ አለኝ::ይህ ለሚገባው ትልቅ ማንቂያ ደውል ነው::

እሚያስፈራው መስዋዕትነት ቢጠይቅም
በትንቢቱ ላይ ስለ ወያኔ :~
የአስመራ ጦርነት ሲጀመር ወያኔ
ይሞታል ተብሎ የተፃፈለት በርግጠኝነት
በኢትዮጲያ ጦርመደምሰሱ የማይቀረው ዛሬ ላይ ያለው የህወሓት ሰራዊት ሳይሆን: ሊፈፀም እየተቃረበ ያለው ትንቢት ላይ የተፃፈው ጥምር የውጪ ጦር በሰላም ማስከበር ስም ወደፊት መግባት እና በቅርብ የሚሆነው የኢትዮጲያ ትንሳኤው ቅድመ መከራ ነው::

ይህ የወያኔ እና የኢትዮጲያ ጦርነት ጥቅምት እንደሚጀምር የተናገረው የሼህ ሁሴን ትንቢት እንደተባለው አሁን ከህወሀት ጋር የተጀመረው ጦርነት ጥቅምት መሆኑ ስናይ ትንቢቱ ዝንፍ አለማለቱን ልብ ያለው ልብ እንዲል ከዚህ ቀደም ፖስት አድርጌው ነበር::

በብልፅግና ወንጌል የሰከሩ በየቸርቹ የፈሉ 2013 የሰላም ግዜ ነው እያሉ እግዚአብሔር ያላላቸውን በስሙ እየዋሹ ከአባታቸው ከዳቢሎስ የሆነ ሆነብሽ ሆነልህ እያሉ ዛሬም ድረስ እማያስተውለውን መንጋ አሜን እያስባሉ እሚነዱ የሀሰት ትንቢት ሲነዙ የነበሩ የመንደር ውርጋጦች አንድም ትንቢታቸው በስህተት ሲፈፀም አላየንም: ይልቁንም ይሄኛው ቃል በቃል ሲሆን እያየነው ነው::

ቅዱስ መፅሃፉም ትንቢትን አትናቁ ሁሉን ፈትኑ
እንዳለ ማሰብ ግድ ይለናል::በክርስቶስ ያላመነው ቀያፋም የተናገረው ትንቢት መፈፀሙን አንዘንጋው::ቀጣዩ ምጥ በቅርቡ ወደፊት ወያኔ በእባባዊ ፍኖቱ ዘርቶት የሄደው የጎጠኝነት መርዝ የብሄር ፖለቲካ :ለሁሉም ግዜ አለውና በጊዜው ሲገነፍል :

ለማናችንም የማይጠቅመው አሁን ላይ ቆሞ ለመራመድ ድክድክ እያለ የታዘብነው የእርስ በእርስ በዘር የመባላታችን ነገር ለይቶለት የጀመረ እለት የሚሆነው ሀገራዊ መዳከምና ለውጪ ጥንተ ጠላቶቻችን ለነጮቹ: ለአረቦቹ (ለግብፅም )ይሁን ወይ ድርቡሽ: ወይ ለአሸባሪው አልሻባብ እና አይሲስ ይሁን ለሌላ የሚያደርገው በር መክፈት ነው::

ልክ በትንቢቱ ላይ እንደተፃፈው ሁሉ:~
ይህ ሰበብ በርግጠኝነት አሸባሪነትን ለመደምሰስ ሰላም ለማስከበር በሚል ሰበብ ኢትዮጲያ ውስጥ እነ ራሺያ : አረብ ኢምሬትስ ጀርመን እና ጣሊያን እንዲገቡ እና ሀያላኑ ሀገራት እስካሁን በሶሪያ:የመን:አፍጋኒስታን: ሊቢያ እና ሌሎችም ላይ ሀገር ሲያፈርሱ ምድራዊ ገሀነብ ሲፈጥሩ እንዳየነው የራሳቸውን ሀገር ላለመጉዳት በሰው ሀገር እየገቡ የጡንቻቸውን ልክ የሚያሳዩበትን መንገድ ይከፈታል::ለዚህም RT news
የነጮቹን አላማ ፍንጭ ቀድሞ ነግሮናል:
ማገናዘብ የኛ የአፍሪቃውያኑ ፋንታ ነው::

የትንቢቱን እውነተኝነት የምትጠራጠሩ
እስኪ ራሺያ እስከዛሬ ያላረገችውን ከቅርብ ግዜ ወዲህ አሁን ላይ የጦር ሰፈርዋን ለማቋቋም ከሱዳን በቅርቡ የተስማማችው ለምን ይመስላችሁዋል?
ይህ ትንቢት መፈፀሚያው ባይደርስ ነው?
አሜሪካና ቻይና ዱባይስ/አረብ ኢምሬትስ/ በምፅዋ: በጅቡቲ እና በበርበራ /ሱማሌ ወደብ ዙሪያ ከ3 በላይ የጦር ሰፈር እየገነቡ የከበቡን ለምን ይመስላችሁዋል?

በኢትዮጲያ ውስጥስ አይተነው በማናቀው ሁኔታ ተከባብሮና ተዋዶ ሲኖር የነበረው ወንድማማች ህዝብ ተጨካክኖ በማይካድራ በጉሊሶ በመተከል ወዘተ ሲቀራደድ የባእዳኖቹ በተለይም የግብፅ ስውር እጅ እገዛ ባንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሌለበት ይመስላችሁዋል?

ይህንን የሚሊተሪ ቤዝ/ጦር ሰፈር ከቦን ስናይ እንዴት ነው አይተን እማናውቀው አይነት አደጋ ከፊታችን እንደተጋረጠ እማይሸተን::ከታች ፖስት የተደረጉትን ዜናና ምስሎች አስተውሏቸው::ከዚህ ቀደም ፖስት ካደረኩት የትንቢቱ ክፍል በዚ ትንቢት ተፅፎ እስካሁን በእድሜያችን ያየነው ስለ ቻይና: ስለ ወያኔ : ስለአስመራ : ስለወልቃይት ...ወዘተ አሁን ድረስ የተፃፈው መፈፀሙን እስካየን ድረስ ቀጣዩም እንደሚፈፀም ጥርጥር የለውም::

ይህ ደግሞ በትንቢቱ እንደተፃፈው ኢትዮጲያን ከሶሪያ ያልተናነሰ ቀውስ ውስጥ ከቶ ይገድላታል:ብዙ ልጆቿ ጥለዋት ይሰደዳሉ: ብዙ ደም ይፈሳልም::ይህ ሁሉ ግን እሚሆነው :ዛሬ ላይ ያለው መንግስት የፈጠረው ችግር ስለሆነ አይደለም::ዛሬ ላይ ባለው የዶ/ር አብይ መንግስትም ቆይታ ላይ ላይሆንም ሊሆንም ይችላል::ብቻ ወደፊት ማንም እቺን አገር ቢመራ ሊሆን ያለው ከመሆን ስለማይቀር ነው::

ምክንያቱም በክርስትና እምነትም/በፍካሬ ኢየሱስ/ ሆነ በእስልምና ይፈፀም ዘንድ የተባለለት :ከአምላኳ ጉያ ርቃ እማታቀው ኢትዮጲያ ዛሬ ስለፋነነች ለዚህም የእግዚአብሔር የቁጣው ሰአት ስለደረሰ :~በክፋት በጭካኔ
በመከዳዳት: በገንዘብ ወዳድነት :በአስማት በሌዝቢያን እና በጌይነት: እየተዘፈቀ በሁሉ ቅጥ አጥቶ ከፈሪሀ እግዚአብሔር እየተለየና

ከፈጣሪ መንገድ እያፈነገጠ ሃዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቲዮስ በፃፈው 2ተኛ መልእክት 3ተኛ ምእራፍ ላይ የተዘረዘረውን የሃጥያት አይነት ሙሉ ለሙሉ እያሟላ
የሄደው እና የከፋው የኛ ዘመን ትውልድ ላይ ቅጣቱ ሊሆንበት ይህ ትንቢት ሊፈፀም ግድ ስለሆነ ነው::
ምናልባትም በምህረቱ ቢያስበን ሁላችንም ራሳችንን ልንመረምር እና ከፈጣሪ ልንታረቅ ግድ ይለናል::

ለቁጣ የታዘዙት ባእዳን ከላይ በጦራቸው እየደቆሱ ከታች ሀብቷን በሰበቡ ሊቦቡጡ ለጡትዋ እንደ መዥገር ሊሆኑ ልጆችዋን በጦርነትና ስደት ሊጨርሱ ከፈጣሪም የተሰጣቸው ግዜ ያልቅና ኢትዮጲያ ተመልሳ እንደምታገግም ከዛ በሁዋላ እንደምትባረክም እንዲሁ በሌላ ቦታ ተፅፎላታል:: ስለ አጥፊዎችዋ መግቢያ ግን በትንቢቱ ይህ ተነግሯል :~

በምስራቅ ኢትዮጲያ በሀረርጌ በኩል የሚገባው የራሺያ ጦር እንደሆነ
በሰሜን የሚመጣው ብዙም ሳይቆይ የሚመለሰው የጀርመንና ጣልያን ጦር::
**ሌላው ደሞ አረብ ኢምሬትን ጨምሮ የያዘ የ7 አረብ ሀገራት ጥምር 1 ጦር ወደ ኢትዮጲያ ይገባል::

ምእራባዊያኑ ሲቪል ዋር እያሉ በየሚዲያዎቻቸው እየለፈፉ የጦር ነጋሪት እሚጎስሙብን ዛሬ ላይ መንግስት ነገሩን
ተቆጣጥሮ ማረጋጋት ቢችል ራሱ : ነጮቹ ግን
መተራመሳችንን አጥብቀው የሚሹት ነገር በመሆኑ በዛም በዚህም ብለው ነገሩን ወደፊትም ቢሆን ከመፈጠር ወደሁዋላ አይሉም::

ኢትዮጲያ ሞታ እምትነሳበት እየመጣ ያለው ግዜ ከባድ ይሆናል::ሀያላኑ ሀገራት ሶሪያን ግራና ቀኝ አቅማቸውን ሲፈታተሹ ዱቄት አድርግዋት እንደሄዱ ኢትዮጲያንም ቀጣይዋ ሶርያ ከማረግ ወደ ሁዋላ አይሉም::
ይህን ክፉ ጊዜ እሚያሳጥረውም ይትረፍ ያለውንም የሚያተርፈው የእግዚያብሔር ምህረት እና ፀሎታችን ብቻ ነው::ይህን እውነታ መዋጥ የማንፈልግ ካለን መጭውን ሁላችን አብረን የምናየው በመሆኑ አይይሳስብም::

3 years, 6 months ago

ሰኔ ፴ ልደቱ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

?በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር፤ ሚስቱም ኤልሣቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ እርሷም የመውለጇ ዘመን አልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም በእግዚአብሔር የታመኑ ጻድቃን ነበሩ፡፡ 

?ከዕለታት በአንድ ቀንም ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት በገባበት ሰዓት በዕጣን መሠውያው በቀኝ በኩል የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ታየው፤  እንዲህም አለው ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቷልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል፡፡›› (ሉቃ.፩፥፲፫-፳)

?ከዚህም በኋላ ሚስቱ ኤልሣቤጥ ፀነሰች፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት በማሕፀኗ ውስጥ ሳለ ሕፃኑ ለእግዚአብሔር ልጅ ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩)

?ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ መውለዷን የሰሙ ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም ደስ ተሰኙ፤ ልጁንም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ሊገረዙት መጡ፤ ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ወደዱ፤ ነገር ግን እናቱ ዮሐንስ ተብሎ መጠራት እንዳለበት ተናገረች፡፡ ሆኖም ግን ከዘመዶቿ መካከል ስሙ ዮሐንስ የሚባል ባለመኖሩ አባቱ እንዲወስን ካህኑ ዘካርያስን በጠየቁት ጊዜ መናገር የተሣነው ዲዳ ነበርና ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ሲጽፍ ሁሉም ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜም የዘካርያስ አንደበት ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡

?ካህኑ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ በመላበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ትንቢት መናገር ጀመረ፤  ‹‹ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፡፡ ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ፤ ቸርነቱን  ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ፤ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ያስብ ዘንድ፤ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ ያለ ፍርሃት፥ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ በዘመናችን ሁሉ እንድናመልከው ይሰጠን ዘንድ፤ አንተም ሕፃን፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱንም ትጠርግ ዘንድ በፊቱ ትሄዳለህና፡፡ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኃኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ፤ ከአርያም በጎበኘን በአምላካችን በይቅርታውና በቸርነቱ፤ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻቸውንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ፡፡›› ሉቃ.፩፥፷፰-፸፱
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት እና ተራዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!

3 years, 6 months ago
"እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ …

"እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም" ማቴ. 11÷11

እንኳን አደረሳችሁ!

3 years, 6 months ago

+++ ምን ብዬ ልጸልይ? +++

በግሪክ ሀገር ሁለት ሴት ልጆቹን ያሉት አንድ አባት ነበር። በአንድ ዓመት ብቻ የሚበላለጡትን እነዚህን ሕጻናት እንደ አባትም እንደ እናትም ሆኖ ተንከባክቦ ማሳደግ የዚህ ሰው ዋነኛ ሥራው ነበር። ስለዚህ ወጥቶ በገባ ቁጥር ልጆቹን የሚያስደስት ነገር እየገዛ ፣ የሚጠይቁትን እያሟላ በድሎት ያኖራቸው ነበር። የራሱን ሕይወት ወደ ጎን ትቶ ለልጆቹ መኖሩ ያለ ዋጋ አልቀረም። ሁለቱም ልጆቹ በጤንነት አድገው ዕድሜያቸው ለጋብቻ ደረሰ።

አባት የለፋባቸው ልጆቹን ከመዳሩ በፊት ብዙ መሰብ ነበረበት። አስተዋይ ነበርና ብዙ ሽማግሌ ቢላክበትም ልጆቹን ለመሥጠት የወሰነው ግን በጥንቃቄ ነበር። ስለዚህ ልጆቹ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እንዳይቸገሩ በማሰብ የተለያየና የማይነጥፍ መተዳደሪያ ላላቸው ወንዶች ባል እንዲሆኑ ለማድረግ ወሰነ።

እንዲህ ሲልም ያወጣና ያወርድ ጀመር :
"ሰዎች ሁልጊዜም ምግብ ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ ገበሬ መቼም ቢሆን እህል ገዢ አያጣም። እንዲሁም ሰዎች ውኃ ለመቅዳት ምግብ ለመሥራት ሸክላ ስለሚፈልጉ ሸክላ ሠሪም ገበያ አያጣም። ስለዚህ ልጆቼን የምሠጠው ለሸክላ ሠሪና ለገበሬ ነው" አለ። እንዳለውም አንዲቷ ልጁ የገበሬ ሚስት ሌላኛዋ ደግሞ የሸክላ ሠሪ ሚስት እንዲሆኑ ሠጣቸው።

ከብዙ ጊዜ በኋላ በአንድ ሰንበት ይህ ሽማግሌ ዛሬስ ልጆቼን ልጠይቅ ብሎ ተነሣ። በመጀመሪያ ወደ ገበሬው ሚስት ሔዶ ሲጫወት አረፈደ።
ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል ልጁ እንዲህ አለችው :

"አባዬ እስካሁን ኑሮአችን ሰላም ነበር። አሁን ግን ችግር ላይ ነን። ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም ጨርሶ አልዘነበም። በዚሁ ከቀጠለ የዘራነው አይበቅልም ፣ ተክሎቻችንም ይደርቃሉ። አባዬ አደራ! በሚመጣው ወር ከባድ ዝናም እንዲጥል ወደ ፈጣሪ ጸልይልን!"
አባት አደራውን ተቀብሎ ተሰናብቶ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ለመሔድ ጉዞውን ጀመረ።

ከሰዓት በኋላ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ሲደርስ ከሸክላ ሠሪው ባሏ ጋር በአክብሮት ተቀብለው አስተናገዱት። ከጠዋቱ የበለጠ ደስተኛ ሆኖም አሳለፈ። መሰናበቻው ላይ ግን ልጁ ተነሥታ እንዲህ አለችው:

"አባዬ ለአንተ ለጸሎተኛው አባቴና ለጠንካራው ባለቤቴ ምስጋና ይሁንና ኑሮአችን እስካሁን ጥሩ ነው። እንደምታውቀው ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም አልዘነመም። በዚህም ደስተኞች ነን። አሁን የምለምንህ አንድ ነገር ብቻ ነው። በሜዳ ላይ ተደርድሮ እንደምታየው እጅግ ብዙ ሸክላዎች እየሠራን ነው። በሚመጣው ወር ዝናም ካልዘነመና ደረቅ ከሆነ የሠራናቸው ዕቃዎች ሁሉ ደርቀው ለገበያ ይደርሱልናል። ስለዚህ በሚመጣው ወር ዝናም እንዳይጥል ወደ ፈጣሪህ ጸልይልን"

አባት ተሰናብቶ ሲወጣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ
"ፈጣሪዬ ሆይ አንዲቱ እንዳይዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ሌላዋ እንዲዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ምን ብዬ ልጸልይ?" አለ።

ይህ አረጋዊ የእኛን ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቢያስቀድስ ኖሮ ግን እንዲህ አይጨነቅም ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ የሚያነበው ምእመናን በግንባራቸው ተደፍተው የሚሰሙት "በእንተ ቅድሳት" የሚባል ጸሎት ላይ የዚህን ሽማግሌ ልብ የሚያረጋጋ ስለ ዝናም የሚጸለይ አንቀጽ አለ። እንዲህ ይላል:

"በሚሻበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ ስለ ዝናም እንማልዳለን"

"በሚሻበት" የሚለው ቃል ላይ "ሻ" ጠብቃ ትነበባለች። "በሚፈለግበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ" (ኀበ ዘይትፈቀድ መካን) ማለት ነው። ቀሳውስቱም ስለ ዝናማት በሚጸልዩት መስተብቁዕ ላይ "ወደ ሚሻበት ቦታ ዝናሙን ይልክ ዘንድ" (ከመ ዝናሞ ይፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) "ወደሚሻበት ቦታ ዝናሞችህን ላክ"(ዝናማቲከ ፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) ይላሉ።

ዝናም እንደ ገበሬው ቤት የሚፈለግበት ቦታ እንዳለ ሁሉ እንደ ሸክላ ሠሪው ቤት ደግሞ የማይፈለግበት ቦታ አለና ቤተ ክርስቲያን ከፈጣሪዋ ዝናም ከመለመን አልፋ የሚያዘንምበትን ቦታም እየጠቆመች ትጸልያለች።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

3 years, 6 months ago
እንቆጳግዮን ✞
3 years, 7 months ago

ለኃጢአት ቀጠሮ
"ኢየሱስ ሠርግ ቢጠሩት በቃና ዘገሊላ ውሀውን ጠጅ አድርጎ አጠጣ በሰው ሠርግ እንደዚህ የሆነ በራሱ ሠርግ እንዴት ይሆን? የእግዚአብሔርን ልጅ ሠርግ አይቼ፣ ከድግሱም በልቼ ጠጥቼ ከዚያ ወዲያ በሞትኩ" ይላሉ አለቃ ዘነበ በመጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ፤ አብዛኞቻችን ከሠርጉ በመግባት ከማዕዱ መካፈልን ችላ እንላለን ለዚህም እንደምክንያት የምናቀርበው “ዛሬ ከምሥጢራት ብካፈል፣ በዚህ ሕይወት ብኖር፣ ነገ ደግሞ በዚያ ኃጢአት ብወድቅስ”፣ “ነገ ላይ እንዲያ ባደርግስ” የሚል ነው፣ በተቻለ መጠን አውቆ ከማጥፋት ራስን መገደብ ይገባል እንጂ “ነገ ስለማጠፋ ዛሬ በቅድስና መኖርን አልሻም” እንዴት እንላለን? ወትሮም መድኃኒት የሚያስፈልገው እኮ ለበሽተኛ እንጂ ጤነኛማ ጤነኛ ነው።
?ደግሞስ ብቻችንን እየኳተንን መች ተወን እንኳን ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረታዊ ህልውና ውስጥ የሚያስገባንን ማህተም ይዘን፤ ለዚያ አይደል ባለ ቅኔው መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ
"ስጋህን በልቼ ደምህን ጠጥቼ ሲኦል ብታወርደኝ
አብረን እንወርዳለን እኔ ምን ጨነቀኝ!" ሲሉ የተቀኙት
?ሰው ወደ ብርሃን በቀረበ ቁጥር ነው ብርሃን ያገኛል፤ ወደ እሳት በቀረበ ቁጥር ነው ሙቀት ያገኛል፣ ወደ ቅድስናም በቀረበ ቁጥር እንደዚሁ ቅዱስ መሆንን ያገኛል ፣ከእርሱ ርቆ ቅድስናን መመኘት ግን ከባድ ነው፣ ስለዚህ 'እኔ ራሴን አስተካክዬ ጥሩ ስሆን እመጣለሁ' አንበል ምክንያቱም እርሱ እንዲህ ይለናል' ራስህን ጥሩ አድርገህ ወደእኔ ከምትመጣ ወደ እኔ ናና ጥሩ አደርግሃለሁ!' ስለዚህ ለኃጢአት ቀጠሮ መስጠት ይብቃን፣ ኑ ወደ መድኃኒት እንቅረብ!

3 years, 7 months ago
እንቆጳግዮን ✞
4 years, 1 month ago

➢ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ጾሙን ያልጀመራችሁ ህዝበ ክርሰቲያን በሙሉ አሁንም ጊዜው አልረፈደም...

4 years, 1 month ago

➢ በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን እንደሚከተለው ተገልጿል

◎ ጾም፡- ከትርጉሙ እንደተረዳነው ከእህል ከውኃ ከመከልከሉ ጋር ከክፉ ነገር ከኃጢአት መራቅ ስለሆነ ጾማችን ከክፉ ነገር በመራቅ፣ በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ነቢዩ ኢሳይያስ “በምትጾምበት ጊዜ እንጀራህን ለተራበ ብትቆርስ ብርሃንህ እንደንጋት ይበራል የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል ትጮሀለህ እርሱም እነሆ ይላል”/ኢሳ.58፡6-9/ ባለው መሠረት በጾም ጊዜ የጧት ቁርሳችን ለድሆች ከተሰጠ ሰማያዊ ዋጋ እናገኛለን፡፡

ስለዚህ ጾማችን ከምጽዋት ጋር መሆን አለበት፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ምጽዋት አይለያዩምና እነዚህን ገንዘብ እናድርግ። በረከተ ሥጋ፣ በረከተ ነፍስ እንድናገኝ ጾማችን በቅንነትና በንጹሕ ልብ ይሁን ጾማችን ከምጽዋት ጋር ይሁን፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ቅዱሳን በአማላጅነታቸው ይርዱን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Ethiopiansecret ??❤️

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana