ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 days, 23 hours ago
Last updated 4 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 2 days ago
በትግራይ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀመሯል።
በክልሉ በተሳለጠ የትምህርት ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 26,156 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል።
ክልል አቀፍ ፈተናው በ451 ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል።
የተማሪዎቹ የፈተና ውጤት በአምስት ቀናት ውስጥ እንደሚገለፅና ወደ 9ኛ ክፍል የሚያልፉ ተማሪዎች በቀጥታ የ9ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።
ታደሰ ረጋሳ (ዶ/ር) ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ህዳር 30/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል።
ለታ ተስፋዬ (ዶ/ር) የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመማር ለተመደቡ አዲስ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።
ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የመግቢያ ቀናት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።
በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመደበኛ የማስተርስ ፕሮግራም በ General Public Health እና በ Reproductive Health የትምህርት መስኮች ለመማር ከጤና ቢሮ የተላካችሁና የመግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።
ሦስት የደቡብ ክልል እና የሲዳማ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ከክልል የጤና ሳይንስ ኮሌጆች የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው በሚማሩ መምህራን ላይ ሕገወጥ ተግባር እየተፈተመባቸው መሆኑ ተሰማ።
ዩኒቨርሲቲዎቹ መምህራኑን ከትምህርት ገበታቸው ማገድ፣ በገንዘብ መደራደር እና መምህራኑ ትምህርታቸውን የጨረሱበትን ማስረጃ ባለመስጠት ሕገወጥ ድርጊት ላይ መሰማራታቸው ለሕ/ተ/ም/ቤት በቀረበ ጥቆማ ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለጸው ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባ፣ የጤና ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ከምክር ቤት አባላት ለቀረባለቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
አዳነ አደቶ (ዶ/ር) የተባሉ የምክር ቤት አባል ለጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባቀረቡበት ጥያቄ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከክልል ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የትምህርት ዕድል አግኝተው የሚማሩ መምህራን ላይ ሕገወጥ ተግባር እየተፈተመባቸው ነው ብለዋል፡፡
ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከክልል ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው የሚማሩ መምህራንን ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ ማድረግ፣ በገንዘብ መደራደር እና ሌሎች ሕገወጥ ተግባሮች ላይ መሰማራታቸውን አስረድተዋል፡፡
ድርጊቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሆኑም በላይ የመንግሥትን ሥራ አደናቃፊ መሆኑን በማመን የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጉዳዩን እንዲያጣራ የም/ቤቱ አባል ጠይቀዋል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ ዓለሙ ታምሶ እስካሁን በዩኒቨርሲቲው ይህንን ዓይነት ድርጊት ስለመኖሩ መረጃ የለኝም ብለዋል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈፅሙ አካላት ካሉና ለፓርላማው የቀረበው ጥቆማ ተጨባጭ ከሆነ፤ ዩኒቨርሲቲው ድርጊቱን በፈፀሙ ግለሰቦች ላይ በፍጥነት ዕርምጃ እንደሚወስድ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
"በተለይ ይህንን ዓይነት ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ሕገወጥ መሆናቸው ታምኖበት ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል" ያሉት ኃላፊው፤ አንድ መምህር ትምህርቱን በአግባቡ ከጨረሰ በኋላ የትምህርት ማስረጃ የማያገኝበት ምክንያት የለም ብለዋል፡፡
ሪፖርተር ከፓርላማ አባል የቀረበውን ጥያቄ መሠረት አድርጎ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችን በስልክ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካ መቅረቱን ጠቁሟል፡፡ #ሪፖርተር
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 days, 23 hours ago
Last updated 4 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 2 days ago